Telegram Web
Forwarded from መዝሙር ዘዳዊት (አክሲማሮስ 21)
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ❤️ እንዲህ ያስተምረናል

+++ ለራስህ ነው +++

👉አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡

👉 ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡

👉ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡

👉 ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡

👉ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

👉ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡

👉 ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡

👉እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

https://www.tgoop.com/mezmur_Zedawitt
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+

+ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ
ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ
ክርስቲያን
ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ
ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል::

+አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች
ይሉናል::

+በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት
(የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ
የአብዛኞቹ
ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው
"ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን
አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ
ተፈጥሯል::

+እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን
እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ
የሚጨመርላቸው የለምና::

+ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት
አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3
ዓመታት
ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

+ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል::
በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት
ሰማዕትነትን ከተቀበሉ
በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል::

+ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው
ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት
እያነደዱ
ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው
ከርሱ ጋር አልተለየም::

+ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን:
ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን
ለረዥም
ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል::

❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖

+ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት
ወለተ ማርያም ትታሰባለች::

+ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ
ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት::
በንግስትነት
በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ
ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር::

+ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር
የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን
ቤተሰብ ወደ መልካም
ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች::

❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን::

❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ)
2.አባ ብሶይ ሰማዕት
3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ
4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት)

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን
4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5፡ አባ ዜና ማርቆስ
6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ

++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት
ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው
. . .
እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል
ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም
ምንም የለም::
ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ
አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ
ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Audio
ከእግዚአብሔር አባታችን ከጌታም ከኢየሱስ
ክርስቶስ ጸጋና ሰለም ለእናተ ይሁን።
"የትንሣኤው በረከት በሕይወታችን ውስጥ"
1/የመጀመሪያው በረከት፦አለመቻል አይኖርም
ሁሉም ነገር ይቻላል! የሚለው ነው። ሰዎች
በሥራ መስኮቻቸው ውስጥ የሚችሉትን ሁሉ
ያደርጋሉ። በእግዚአብሔር ፊት ሲቆሙ ግን
የሚሠሩት ሥራና ያለቸው እውቀት ሙሉ ለሙሉ
ሰለሚቆም ለመሥራት የሚሞክሩት ሙከራ ሁሉ ጥቅም አይኖረውም።
ይህ ከምተ በኋላ በመቃብር ውስጥ ለአራት
ቀናት የቆየው የአልአዛር እህቶች የማርያምና
የማርታ ስሜት ነበር ፡ስለ አልአዛር እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፦"የሞተውም እኅት ማርታ
ጌታ ሆይ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለቸው"ዮሐ 14:39።
መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሰው ከሞት ሲያስነሰው የማይችል ነገር እንደሌለ
እርግጠኞች ሆነዋል። ክርስቶስ አልአዛርን ካስነሣው በኋላ ይህ አልአዛር ተመልሶ ቢሞትም እስከ አሁን ድርስ አልተነሳም። ይህ
ይህን እንጂ መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በራሱ ትንሣኤ ሞትን ድል ነሥቶታል አስከ
ዘለዓለም ድረስ አጥፍቶታል። የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ዘላለማዊ ስለሆነ
ከዚህ ትንሣኤ ቦኋላ ሞት የለበትም።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የዚህን ትንሣኤ ኃይል ስለ ተመለከተ"ሞት ሆይ መውጊያህ የት
አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ? "
1ኛ ቆሮ 15:55 በማለት ተናግሯል።
በእርግጥም ሞት ስለ ተንኮታኮተ ማንኛውም
ነገር የሚችል ሆኗል። ሰዎች ያመኑት ሁሉን
ማድረግ የሚችለውን እግዚአብሔርን ሁሉን
ነገር ማድረግ የሚችል መሆኑን ብቻ ሳይሆን
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው
ሰዎችም በእርሱ ኃይል ሰጪነት ሁሉንም ነገር
ማድረግ እንደሚችሉ እንዲህ በማለት አስረግጦ ገልጧል፦"ኃይልን በሚሰጠኝ
በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። " ፊሊጵ 4:13
ከዚህ ቀደም ብሎ ሲናገረም"...እርሱን የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ...."ፊሊጵ 3:10
መጽሐፍቅዱስ ስለ አለመቻል በወጣው
መመሪያ ውስጥ እንዲህ የሚል ተጽፎ እናነባለን"...ለሚያምን ሁሉ ይቻላል... "ማር 9:23 በማለት ጌታ ተናግሯል። ስለዚህ የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ ካለ ቅ.ጳውሎስ
በትንሣኤው የተገኘ በረከት አንዱ ሁሉን መቻል
ነው። ይህንን ያደረግልን አምላካችን የተመሰገነ
ይሁን። መልካም ጊዜ ተባረኩ።
Forwarded from Bketa @¥
የቅዱስ-ያሬድ-ዜማ-ምልክቶች_2.pdf
1001.6 KB
Share የቅዱስ-ያሬድ-ዜማ-ምልክቶች_2.pdf
Forwarded from Bketa @¥
📌 22ቱ ስነ ፍጥረት

❖ ስነ ፍጥረት ማለት የሁለት ቃላት ጥምር ዉጤት ነው፤

ስነ ማለት 

❖ በግዕዝ ያማረ፣ የተወደደ ፣ የተስማማ ማለት ነው፤ 

ፍጥረት ማለት

❖ የተፈጠረ ማለት ነው፤

ስነ ፍጥረት ማለት 

❖ ያማረ ተፈጥሮ፣ የተወደደ ፍጥረት እንዲሁም እርስ በእርሱ የተስማማ ፍጥረት ማለት ነው። 

❖ በ6 ቀናት እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት በጠቅላላ ሲጠቃለሉ #22 ናቸው።

እሁድ

ስምንት መባላቸው ለምንድ ነው 

2ኛ ነፋስ

ሰኞ

❖ ሁለተኛ ቀን ምን ተፈጠረ 1 ነገር ተፈጠረ። 

❖ እሁድ የፈጠረውን ውኃ ለ2 ከፍሎ የላይኛውን ኃኖስ በተባለ ንፋስ እንዲረጋ አደረገውና ስሙንም "ጠፈር" አለው እኛ በተለምዶ ሰማይ የምንለው ሌላው ከመሬት በታች ያለውን ደግም "ውቅያኖስ" አለው።
📖መጽሐፈ ኩፋሌ 2፥9

ማክሰኞ 

❖ ሶስተኛ ቀን ምን ተፈጠረ 4 ነገሮችን ፈጠረ። 

❖ ያለዘር እፅዋትን ምድር አስገኘች እነሱም

3ኛ የሚበሉ ፍራፍሬ(ዘሮችን)

1ኛ ፀሀይ
2ኛ ጨረቃና
3ኛ ከዋክብት
📖መጽሐፈ ኩፋሌ 2፥13-14

ሐሙስ  

❖ አምስተኛ ቀን ምን ተፈጠረ 3 ነገሮችንፈጠረ

1ኛ በልብ የሚሳቡ በውሃ የሚኖረ አንበሪዎች
2ኛ በውሀ የሚንቀሳቀሱ አሶች
3ኛ የሚበሩት ወፎች
📖መጽሐፈ ኩፋሌ 2፥15-16

አርብ

❖ ስድስተኛ ቀን ምን ፈጠረ 4 ነገሮችን ፈጠረ
1ኛ እንስሳትን(የቤት)
2ኛ አራዊትን(የዱር)
3ኛ በደረታቸው የሚንፏቀቁ እና ሌሎችም በምድር የሚመላለሱ ፍጥረታት
📖መጽሐፈ ኩፋሌ 3፥1

❖ በሰባተኛው ቀን ግን ከሁሉ ስራዉ አረፈ። 

❖ ይህ ማለት ግን እሱ የሚደክም ሆኖ እረፍት አስፈልጎት ሳይሆን እኛ 6 ቀን ሰርተን በ7ተኛው ቀን (በሰንበት) እንድናርፍ አርአያ ሲሆነን ነው።
📖ኦሪ ዘፍ 1፥1-31
📖መጽሐፈ ኩፋሌ 3፥2

ስለዚህም ስነ ፍጥረት ሲጠቃለሉ 22 ናቸው።

📌 አዘጋጅ
® ዲ/ን ብሩክ 
Forwarded from Bketa @¥
🌟በእንተ ግእዝ🌟 

... ግእዝ ወ ግዕዝ

          🍀ግእዝ : ገአዘ (ግእዘ) ( መጀመሪያ, አንደኛ , ቀዳሚ ) ከሚለው ግስ የተገኘ ዘር ሲሆን አንድ ቅንጣት ያለው ቅጥያ የሌለው, የፊደል ስም ማለት ነው።

ቅጥያ የሌለው ስንልም የመጀመሪያዎቹ ፊደላት( ቅጥያ የሌላቸው ) ግእዝ ተብለው ስለሚጠሩ ነው። ለምሳሌ ሀ-ግእዝ: ለ: ግእዝ ወዘተ...።

          🍀 ግዕዝ : ገዐዘ (ግዕዘ) ( አዘነ, ተበሳጨ, ተቆጣ ) ከሚለው ግስ የተገኘ ዘር ሲሆን አመል, ጠባይ, መበሳጨት, ማዘን የሚለውን ይወክላል።

🍀 ልሳነ ግእዝ 26 መደበኛ ፊደላትና 4 ሕጹጻን (ጎደሎ) ፊደላትን ይይዛል።
( በአጠቃላይ (26*7)+(4*5) = 202 ፊደላት አሉት ማለት ነው)
      🍀መደበኛ ፊደላት  🍀ዝርዋን(ጎደሎ)                      
                                                         ፊደላት
ሀ: ሁ: ሂ:ሃ: .......            ኰ: ኲ: ኵ: ኳ: ኴ    
                                       ጐ: ጒ: ጕ: ጓ: ጔ     
                                       ኈ: ኊ:ኍ: ኋ: ኌ      
                                      ቈ: ቊ: ቍ: ቋ: ቌ    

🍀 ከ 26 ቱ መደበኛ ፊደላት መካከል 22ቱ አሌፋት የሚባሉ ሲሆን 4ቱ ደግሞ  
( ፐ, ፀ, ጰ እና ኀ ) ሗላ የተጨመሩ ፊደላት ናቸው።
Forwarded from Bketa @¥
መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ
በሶስት ክፍል ከፋፍለን እንማማራለን።
መዝሙር ምንድን ነው? የሚለውን መጠይቅ ለርዕሰ ነገራችን ሐተታዊ ፍሬ ነገር መነሻ በማድረግ መሠረታዊ ትምህርታችንን እንጀምራለን፡፡
መዝሙር የባሕርይ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የሚመሰገንበት፣ የሚቀደስበትና የሚለመንበት ዐቢይ የጸሎት ክፍል የሆነ ጣዕመ ዜማ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና ለአምላካችን ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነውና››ይለናል መዝሙረኛው ዳዊት መዝ. 146፥1 በተጨማሪ ኢሳ. 6፥1-5፣ መዝ. 65፥1-5 መመልከት ሰለ መዝሙር ምንነት ያስረዳል፡፡
መዝሙር ማለት ምን ማለት ነው? ያልን እንደ ሆነ መዝሙር ዘመረ አመሰገነ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም ምስጋና፣ ልመና ወይም መማፀን፣ ማስደሰት፣ መደሰት፣ ማዜም ማለት ነው፡፡ ከዚህም ሌላ እግዚአብሔርን በእጥፍ ድርብ ማመስገን ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን እልል እንበል . . . አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና›› ይለናል መዝ. 94፥1-3 ስለ ጠቅላላ ትርጉሙ መዝ. 116፥1-2፣ ኢሳ. 35፥1-6 /38፥9/ መዝ.149፥1-4፣ መዝ. 150፥1-7፣ መዝ. 80፥1-3፣ ማቴ. 26፥30፣ ማር. 14፥26፣ ቆላ. 3፥16፣ ራእ. 14፥1-5 ማቴ. 21፥9፣ ማር. 11፥9፣ ሉቃ. 19፥38 መመልከት ይጠቅማል፡፡ ከላይ እንዳልነው መዝሙር ሲባል ማዜም ማለት ነው፡፡ ዜማ ማለት ራሱ በቀጥታ ሲፈታ ጩኸት /ድምፅን ማሰማት/ ማለት ነው፡፡
ይሁን እንጂ ዜማ የምስጋና ብቻ ሳይሆን የሐዘን /የለቅሶ /የቀረርቶ /የሽለላ /የፉከራና የደስታ ስሜት መግለጫ ድምፅ ነው፡፡ ኢሳ. 6፥1-5 ማቴ. 26፥30
ከዚህ ላይ ግን ዜማ ባልን ጊዜ የምስጋና መዝሙር ድምፅ ሐሴት ማለታችን ነው፡፡ ለምን ቢሉ ዜማ ራሱን የቻለ ጥሬ ቃል ቢሆንም ዘመረ፣ አመሰገነ፣ አዜመ ካለው ቃል ጋር በጠባይና በግብር ይመሳሰላልና ነው፡፡
የመዝሙር ወይም የዜማ ጥቅሙ ምንድን ነው?
ሀ. መዝሙር ለመማሪያና ለማስተማሪያ መዝሙር እግዚአብሔርን በተመስጦ ለማመስገን
ለ. መዝሙር ወደ እግዚአብሔር ልባዊ ጸሎት ወይም ልመና ለማቅረብ
ሐ. መዝሙር ልብን ለማነፅና ነፍስን ለማስደሰት ማለትም መንፈስን ለማደስ ለምክርና ለተግሣፅ ደግሞም ለማፅናናትና ለመፅናት እጅግ አድርጎ ይጠቅማል፡፡
መዝሙር ወይም ዜማ፡- የተጀመረው በአራቱ ሰማያት ማለትም በሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ በኢዮር፣ በራማና በኤረር በእነዚህ ያሉ መላእክት እግዚአብሔር ፈጣሪያቸውን ያለ ዕረፍት ሲያመሰግኑት ነው፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፡፡ . . . አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጮኹ ነበር፡፡ የመድረኩም መሠረት ከጩዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ ቤቱም ጢስ ሞላበት፡፡›› ይላል ኢሳ. 6፥1-5፣ ራእ. 4፥4 ይህም በኪሩቤልና በሱራፌል ማለት በመላእክት የተጀመረው ጣዕመ ዜማ /መዝሙር/ በእነሱ አሰሚነት ለሰው ልጆች ታድሏል፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሥልጣነ እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ የባርነት አገዛዝ ነፃ ባወጣበት ጊዜ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ በደረቅ ምድር ሲያሻግራቸው ሙሴና ተከታዮቹ በተለይም እኅቱ ማርያምና ሙሴ እግዚአብሔርን በከበሮ ድምፅ እያጀቡ በጣዕመ ዜማ አመስግነዋል፡፡ መዝሙርም በይፋ መጀመሩ የታወቀው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ዘጸ. 15፥1-22 ደግሞም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ባየው ራአይ 14፥1-6 በምድር የተዋጁት 144 ሺህ ወገኖች ማንም ያልዘመረውንና ሊዘምረውም የማይቻለውን ጣዕሙ ልዩ የሆነ አዲስ መዝሙር በመድኃኒታችን ዙፋን ፊት በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል እንደዘመሩ ይገልፃል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዜማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘወትር ፈጣሪዋን የምታመሰግንበት ልዩ ዜማ /መዝሙር/ ከመላእክት የተገኘ ነው፡፡ ስለዚህ መዝሙራችን እስከ አሁን በዓለም ተወዳዳሪ አልተገኘለትም የተገኘውም በኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ነው፡፡
እኛም አሁን የምንዘምረው መዝሙር በቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያው ዜማም አርያም ይባላል፡፡ አርያም ማለትም ልዑል ከፍተኛ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን ዜማ አርያም ብሎ የሰየመው ከሰማይ ካሉ መላእክት ሰምቶ መዘመር ስለጀመረ ነው፡፡ ይህም ሲታወቅ ‹‹ቀዳሚ ዜማ ተሰምአ እም ሰማይ›› እያለ ይሄድ እንደነበር ሊቃውንት ይተርካሉ፡፡ ይህ ታላቅ ሊቅ በመንፈሳዊ ተመስጦ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ ከመላእክት ያገኘው ዜማ ዓይነቱ ሦስት ነው፡፡
እነዚህም
1ኛ. ግእዝ
2ኛ. ዕዝል
3ኛ. አራራይ ይባላሉ፡፡
እስከ አሁን በዓለም የማናቸውም ፍጥረት ዜማ ጣዕሙ ይለያይ እንጂ በእነዚህ የዜማ ዓይነቶች ብቻ የተጠቃለለ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ የዜማ ስልቶችም ምሳሌና ትርጉም አላቸው ይኸውም፡-
ግእዝ፡ - ርቱዕ ማለት ነው፡፡ አብን ርቱዕ ሎቱ ነአኰቶ ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን ማለት ነው፡፡
ዕዝል፡ - ጽኑዕ ማለት ነው፡፡ ወልድ ጽኑዕ መከራ ተቀብሎ አዳምን እንዳዳነው ለማጠየቅ ነው፡፡
አራራይ፡ - ጥዑም ማለት ነው፡፡ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን እንደተጎናጸፍን ለማስረዳት ነው፡፡
ይህም ቢሆን ታዲያ ተነጣጥለው አይቀሩም ግእዝ ከተሰኘው ዜማ ዕዝልና አራራይ ይወጣሉ፡፡ ይህም በአሐዱ አብ ዜማ ይታወቃል፡፡ ምሥጢረ ሥላሴም ከአብ እምቅድመ ዓለም ወልድ ለመወለዱ፣ መንፈስ ቅዱስ ለመስረጹ ምሳሌ ነው፡፡ ከዚህም ጋር የንባቡና የድምፁ ቃና አንድ መሆን የሥላሴን አንድነት ሲያስረዳ የዜማው ሦስት ዓይነት መሆን ደግሞ የሦስትነታቸው ምሳሌ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የያሬድ ዜማ በቂና ጥሩ ጥሩ ምሳሌ ያላቸው 8 ዐበይት ምልክቶች አሉት፡፡ እነዚህም ዜማውን ለሚማር ደቀመዝሙርና ለሚዘምረው ሁሉ ፈረንጆች ኖታ እንደሚሉት በምልክትነት ሲያገለግል ምሳሌያቸውና ምሥጢራቸው ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ስለእኛ የተቀበለውን መከራ የሚያስታውሱን ናቸው፡፡
እነዚህም ኋላ ሊቃውንት ከጨመሯቸው ከድርስና ከአንብር በስተቀር ዋናዎቹ የቅዱስ ያሬድ ብቻ ሲዘረዘሩ፡-
ይዘት ( . ) ፡- በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ
ሂደት ( — )፡- ታስሮ ለመጎተቱ
ጭረት ( ﺮ )፡- ለግርፋቱ ሰንበር
ድፋት (┌┐)፡- አክሊል ሾኽ ለመድፋቱ
ደረት (└┘)፡- ሲሰቅሉት በመስቀሉ ላይ አንጋለው ከደረቱ ላይ ቆመው እየረገጡት ለመቸንከሩ
ርክርክ ( ፡ )፡- ለደሙ ነጠብጣብ አወራረድና ለችንካሮች ምልክት
ቁርጥ ( ├ )፡- በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ለመታወቁ
ቅንአት ( ﺭ )፡- በቅንአት አይሁድ ለመግደላቸው
ከላይ የተጠቀሱት ምልክትና መስታወሻዎች ሲሆኑ 8 መሆናቸው 8ቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና ተማክረው በብዙ መከራ ለመግደላቸው ምሳሌ ነው፡፡
እነርሱም ፡- 1. ጸሐፍት ፈሪሳውያን
2. ሰዱቃውያን
3. ረበናት /አይሁድ መምህራን/
4. መገብተ ምኵራብ /የምኵራብ ሹማምንቶች/
5. ሊቀ ካህናት
6. መላሕቅተ ሕዝብ /የሕዝብ ሽማግላች/
7. ኃጥአን
8. መጸብኃን ቀራጮች ናቸው፡፡
በሊቃውንት የተጨመሩ ምልክቶች፡-
9. አንብር ( ⊏ )
10. ድርስ ( ስ )
በቀጣይ ክፍል እስከምንገናኝ
መልካም ግዜ ለሁላችን
ሠናይ ሶቤ ለኲልነ
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።»
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከእግዚአብሔር አብ ከመደኃኒታችንም ኸጌታ
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምህረት ሰላምም
ይሁን።
በጌታችን በመደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ትንሣኤ የቀረበልን ስጦታ እና በረከት፦
ሁለተኛው፦ዘላለማዊ ሕይወትን መናፈቅ ነው።
ሐዋርያው ቅ.ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ
ሲናገር"....ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር
እናፈቃለሁ ከሁሉም የሚበልጥ ነውና.... "
ፊልጲ1:23። "...ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታ ማደር ደስ ይለናል። "2ኛ ቆሮ
5:8።ይህ ሐዋርያ ከሙታን መካከል ተለይቶ
ከተነሣው ወደ ሰማይ ካረገውና በአባቱ ቀኝ
ከተቀመጠው ከርስቶስ ጋር ለመሆን ይናፍቅ
ነበር። ይህ ክርስቶስ"...እኔም ከምድር ከፍ ከፍ
ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። "
ዮሐ 12:32 በማለት የተናገረው ክርስቶስ ነው።
ይህ አባታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ እንዲህ ብሎ ተናግሯል ፦"...ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሔዳለሁና ሄጄም ስፍራ
ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ
እንዳትሆኑ ሁለተኛ አመጣለሁ ወደ እኔም አወስዳችኋለሁ። ዮሐ 14 :2-3።
የዘላለም ሕይወት ፍቅር በምድር ላይ ካለው
ሕይወት የሚለቅ ነገር እንዲናፍቁ ቅዱሳን
አባቶቻችን እናእናቶቻችንን አድርጓቸዋል።
ይህ ናፍቆት በምድር ላይ ካለው ምኞትና
ፍላጎት የሚበልጥ ኃይል ያለው ከመሆኑም
በተጨማሪ ከማንኛውም ፍሬ ነገርና መሠረታዊ ጉዳይ ይልቅ የተከበረ ነው። ቅዱስን አባቶች
እና እናቶች ይህችን ምድር የሚመለከቷት እንደ
ኋላ ቀርና ባዕድ ሐገር አድረገው ነው። ራሳቸውን የሚቆጥሩትም እንደ እንግዶችና
እንደ መጻተኞች ነው። "እነዚህ ሁሉ አምነው
ሞቱ የተሰጣቸውን የተሰፋ ቃል አላገኙምና
ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አይቱና ተሳለሙት
በመድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንደሆኑ
ታመኑ" ዕብ 11 :13 እንደተባለ።
እነርሱ የሚናፍቁት ሰማያዊዋን ማደርያ ነው።
እነርሱ የሚናፍቁት መንፈሳዊውንና
ዘላለማዊውን ሕይወት ለመምራት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ቅዱሳን የሚናፍቁት ሐዘን
ትካዜ ፣ማቃሰት፣ኃጢአት፣ጥላቻና ዘረኝነት፣
ጠብ የሌሉባትን ሌላ ዓለም ነው። ክፋ ነገር
የሌለበት ምልካም ነገሮች ብቻ የሚገለጡበት
የፍቅር የደስታ የሰላምና የንጽሕና ዓለም ይመጣል። ስለዚህ በትንሣኤው የተገኘውን
በረከት ዘላለማዊ ሕይወትን በመናፈቅ የትንሣኤውን በኣል እየተረዳን እናሳልፍ።
መልካም ጌዜ ይሁንላችሁ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from FG(Leዑል) Geremew
ቅዱስ ጴጥሮስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ  “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው።

ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን “በገሊላ ቀድሞት ነበር”። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ “ከዚህ በኋላማ...” እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ “ትወደኛለህ” ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል።

ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል!
††† እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ዕርገት እና ለጻድቁ አባ ዳንኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ዕርገተ እግዚእ †††

††† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል" : ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ : በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው : ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጓል::

ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ::

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

††† ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: †††
(መዝ. 46:6)

††† ታላቁ አባ ዳንኤል †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው:: በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው:: ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን አይቷልና:: አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ (መንኖ) ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው::

ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነበር:: በገዳመ አስቄጥስ እና በደብረ ሲሐት ይታወቃል:: ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት : ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው::

ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል:: ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል:: ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም : ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው::

በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው:: አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል::

ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም:: ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ : ድውያንን ሲፈውስ : ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል:: ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል::

+በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር:: በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል:: ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል::

እርሱ ገንዞ ቀብሮ : ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት) መጥቀስ እንችላለን::

ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን : በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ ነው" ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል::

አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል::

ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባልድሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ድሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ::

ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ::

ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች::

"ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው::

ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ : በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† በተረፈው ግን ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር:-
1.በገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ ባሳየው ትጋት::
2.በሃይማኖት ጠበቃነቱ በደረሰበት ድብደባና ስደት::
3.ብዙ የበርሃ ቅዱሳንን በየበአታቸው እየዞረ በመቅበሩ::
4.የብዙ ስውራን ቅዱሳንን ዜና ሕይወት በመሰብሰቡ::
5.በየጊዜው በእግዚአብሔር ኃይል ይፈጽማቸው በነበሩ ተአምራት:: እና
6.ለድንግል እመቤታችን ማርያም በነበረው ልዩ ፍቅር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች::

††† ቸር አምላክ ክርስቶስ ከዕርገቱና ከጻድቁ በረከት አይለየን::

††† ግንቦት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን የጌታ ቤተሰብ (120ው)
2.ቅዱስ አባ ዳንኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መክሲሞስ መስተጋድል
5.አቡነ ዮሐኒ ዘደብረ ዳሞ (አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ለምንኩስና ያበቁ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

††† "እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" †††
(ሉቃ. 24:50-53)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
የእግዚአብሒር ሰላም ከእናተ ጋር ይሁን።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው
ከሞት ይበልጥ ኃያል መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ በመሆኑም ሞቱና ለፍርድ ሲቀርብ
የገለጠው ዝምታ በውስጡ ካለው ፍርሐት አልመሆኑን እንረዳለን።
ቢናገር ኖሮ አፈቸውን በማስያዝ አድማጮቺን
ማሳመን ይችል ነበር። ይሁን እንጂ የእርሱ ዓለማ ይህ አልነበረም። የእርሱ ዓለማ እኛን ነጻ
ማውጣት ነበር። ስለሆንም ከመሰቀል ላይ
እንዲወርድ በጠየቁት ጊዜ መውረድ
ቢችልም እንኳ ምንም ዓይነት መልስ አልሰጣቸውም። የእርሱ ብቸኛ ዓለማ ስለ እኛ
ሕማምን ተቀብሎ በመሞት የኃጢአትን ዋጋ
በእኛ በመክፈል ለእኛ ስረየትና ድኅነት
ማስገአት ነበር።
የክሮስቶስ ዝምታ ድካም አለመሆኑን ትንሣኤው አረጋግጧል።
የትንሣኤው ኃይል ክርስቶስን በድካም ለሚወነጅሉት ወይም ስቅለቱ የአቅም የማጣቱ
ምልክት እንደ ሆነ አድርገው ለማያስቡ ሰዎች
ሁሉ ብርቱ ምላሽ ነው።
ትንሣኤው ዝምታ የላቁ ዓለማዎች እንዳሉት
አረጋግጧል። እርሱ ዝም ያለው ራሱን ለእኛ
ሊሰጠን ስለ ወደደ ነው። ቢናገር ኖሮ ለፍርድ
ያቀረብት ጠላቶቹን አፍ በማስያዝ አድማጮቹን ማሳመን ይችል ነበር።
ራሱን ቢከላከል ኖሮ የተከሰሰባቸውን ያለ ምንም ጥርጥር ያሸንፍ ነበር።
ከዚህ ሌላ ገና የአስራሁለት ዓመት ብላቴና ሳለ
ይናገራቸው የነበሩት ቃላት ኃይል እነርሱ ራሳቸው በመደነቅ መስክረውለታል።
"ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል
ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጢይቃመቸውም
በመቅደስ አገኙት የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።" ሉቃ 2:46-
47። አድማጮቹም ቢሆኑ በሥልጣን መናገሩን
በአግራሞት መስክረውለታል። "....ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን
እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበረ። " ማቴ
7:28-29። ከዝህ ከፍል የምንረዳው ጌታችን
በአስራሁለት ዓመቱ በአይሁድ መምህራን
መካከል ሲነጋገር እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው የነበረ አምላካችን ነው።
በትንሣኤው ከሞቱ ይበልጥ ኃያል መሆኑን
አረጋግጦልናል። በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብርና ጽንዕ ሐአንተ ይገባል ከእርሱ ጋራ
ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም
ለዘላለም ለዘለአለሙ አሜን። መልካም ጊዜ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል።
በራሱ ኃይል ስልጣን።

የእግዚአብሔር ሰለም ከእናተ ጋር ይሁን።
የጌታችን የመደኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ሞቱ በራሱ መሥዋዕትነት እንጂ በኃይል ወይም በግዳጅ አለመሆኑ ትንሣኤው አረጋግጧል።የክርስቶስን ትንሣኤ ማመን ማለት በእርሱ ፍቅር በእርሱ ምሥዋዕት ሆኖ
መቅረብና በእርሱ የሰው ልጆችን ከሞት ባርነት
ነጻ ማውጣት ማመን ነው። ከዚህ ተጨማሪ
በእርሱ ኃይል አስቀድሞ ስለራሱ በተናገራቸው
ቃላትና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ በመሆኑ
ማመን ነው። ይህ ኃይል በሥጋው ሞቶ በመለኮቱ ሕያው የሆነው የአንድዬ የአምላካችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው።
ይህ ኃይል ለዮሐንስ በራዕዩ እንደሚከተለው
የተነገረው የአንድዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል
ነው።".....አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እንሆም ከዘላለም አስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ
የሞተና የሲዖል መክፈቻ አለኝ።"ራእ 1:8።
ስለዚህ ኃይል አንድዬ ሐዋርያውን ቅዱስ
ጴጥሮስን በሐምሣኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ
በወረደባቸው ጊዜ ሰክረዋል የሚል ቃል
ከአይሁድ በተነገረባቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ
አናግሮታል"እግዚአብሔር ግን የሞትና ጣር
አጥፍቶ አስነሰው ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋ 2:24። ዳዊትንም ትንቢት
አናግሮታል"...ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና
ቅዱስ መበስበስን ያይ ዘንድ አተሰጠውም። "
መዝ 15: 8-11።ቅዱስ ጳውሎስም ፦
"....ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት
እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው
እናውቃለንና። " ሮሜ 6 :9። ስለዚህ የጌታችን
ትንሣኤ የሚያስተምረን ወደፊት የማይምት ሞት የማይገዛው አምላካችን ነው። አለም ያላት
አምላክ ግን "የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን
አሳብ አሳወረ" 2ኛ ቆሮ 4:4 ተብሎ እንደተነገረ
አለም ያላት አምላክ ወደውጭ የሚጣል እና የሚፈረድበት ነው። ዮሐ 12:31-32 ራእ 20:10። መልካም ጊዜ።
2024/05/18 00:41:25
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243