Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አንዳንድ ነገሮች
~
በሐቅ እና በባጢል መካከል ያለው ግጭትና ፍልሚያ ሁሌም የሚቀጥል ነው። ይህንን በማወቅ ለማንም ወከባና ግርግር ሸብረክ ማለት አይገባም። የባጢል ሰዎች አይነተ ብዙ እና ተለዋዋጭ ናቸው። አንዳንዱ ለነውረኛ ድርጊቱ ጭፍራ ፍለጋ ወደ ብሄሩ ዘሎ ሊወተፍ ይችላል። አንዳንዱ ባህሌ ትውፊቴ ሊል ይችላል። ሌላው የሒክማና methodologyን ጉዳይ ያላግባብ እየሰነቀረ ለአጥፊዎቹ ሽፋን የሚሰጥ ነው። አጥፊዎች ላይ የዶለዶመ ብእሩ "ለምን?" የሚሉት ላይ እሳት ሊተፋ ይነሳል። ሀይሃት!!
በሰሞኑ የዘፈንና የመውሊድ ጉዳይ ከቁራአት ሰፈር የሌሉ አርቲስቱም፣ ጠበቃውም፣ ባንከሩም፣ ደላላውም፣ ፖለቲከኛውም፣ ... ናቸው ግንባር ፈጥረው የተነሱት። በተግባር የማውቃቸውን እየተከታተልኩ ስለነበር ነው ይህን የምለው። የድፍረታቸው ድፍረት አንዳንድ ሰለምቴ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ቢድዐን በማውገዛቸው የተነሳ ሊያሸማቅቋቸው ሲሞክሩ ነበር። እንደነሱ በቢድዐ ካልሻገቱ፣ እንደነሱ ቆሞ ቀር ካልሆኑ በቃ ባይሰልሙ ይሻላል ማለት ነው። እዚህ ድረስ ነው የደረሱት።
በነገራችን ላይ "ሙፍቲውን" ከሳመችው ሴት ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥፋት የሰውየው ነው። ጥፋቱን ማረም የነበረበት እሱ ነበር። የወሎ ባህል ስትሉ የነበራችሁ ደግሞ ከየት ሃገር ነው የመጣችሁት? የራሳችሁ ሌላ ወሎ አላችሁ'ንዴ? ማንን ለመሸወድ ነው በዚህ መጠን የምታምታቱት? ለማንኛውም ወሎ ውስጥ #ለአቅመ_ሄዋን_የደረሱ_ሴቶች #ሸይኾችን ይስማሉ ማለት ከእውነት የራቀ ብቻ አይደለም። መሻይኾቹንም፣ የወሎ ሴቶችንም፣ ባህሉንም መስደብ ነው ቢገባችሁ። ሸይኽነት ደረጃ ደርሰው የተማሩት ኢስላም አጅነቢያ መንካት እንደማይፈቅድ አያውቁም እያላችሁ ነው ያላችሁት። አጉል ውግንና ይህንን ነው የሚያመጣው። አላዋቂ ሳሚ ንፍ - ጥ ይለቀልቃል። እንኳን ሸይኾች ጀማሪ ደረሶችም ይህን አያደርጉም። ሴቶቹም ሸይኾችን እስከ መሳም የሚያደርስ ድፍረት የላቸውም። ለምን ይዋሻል?! ነውር አይደለም ወይ? ደግሞስ አይደለም እንጂ የወሎ ባህልስ ቢሆን የምንጨነቅ ይመስላችኋል'ንዴ? ኢስላም በርካታ የዐረብ ልማዶችን አጥፍቷል'ኮ። የማንም ባህል ከኢስላም በታች ነው። ተቃርኖ ከኖረው ይጣላል።
"አማራ እንደሆንኩ ... " የሚለው የሴትዮዋ ንግግርም ህሊና ቢኖር ነውረኛ አካሄድ ነው። እዚያ ሰፈር ያሉ ነሷራዎችን ለመቀስቀስ ከሆነ ሰርቶላታል። ብዙዎቹ ሲያራግቡ የነበሩት እነሱ ናቸው። ከዚያ ውጭ የአማራ ሴቶች እና ቄሶች ዘንድ ካልሆነ በስተቀር የአማራ ክልል ሸይኾች እና ሴቶች እንዲህ አይነት ልማድ የላቸውም። ነው ወይስ ፉቅራ እና ሸይኽ አትለዩም?
አንዱ የከሰረ የዘር ፖለቲከኛ ደግሞ "የአረብ አሮጌ ጀለቢያ ለቃቅመህ መጥተህ ... " እያለ ለቅልቆ አይቻለሁ። ሰው እንዴት ሸብቶም ጧት ማታ የሚፅፈው ሃሳብ ከህፃን የባሰ ይሆናል? ይሄ የሽማግሌ ነው ^ ረኛ ከጥንት ጀምሮ የሃገራችን መሻይኽ ጀለቢያ እንደሚለብሱ አያውቅም። ለዚያ ነው በማይገናኝ ጉዳይ የጀለቢያ ጥላቻውን ያቀረ ሸው። ውሎው ይሆናል በዚህ መጠን ያደነ ^ ቆረው። ቢገባው ቄሶቹ የሚለብሱት ቀሚስ'ኮ ራሱ ጀለቢያ ነው። እነሱ ላይ ግን ይህንን ል ቅ አፉን አይከፍትም። ጥላቻቸው ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ያነጣጠረ ነው። ደግሞም ባህሉ እንዲከበር የሚሻ አካል የሌላ ባህል አይሳደብም። የሌላውን እያጣጣልክ ያንተ የሚከበር ይመስልሃል'ንዴ? በተረፈ የምትለብሰው ሱሪም የፈረንጅ ባህል ነው። ለምን ወደ ጥብቆ ቁምጣህ ወይም ወደ ተነፋነፍ ሱሪህ አትመለስም? አንዳንዶቹ ለዐረብ ያላቸው ጥላቻ ማሰብ እስከማይችሉ ነው የሚያሰክራቸው። ኧረ ለማሰብ ሞክሩ! ምንድነው እንደዚህ ድንቁ ^ ርናችንን ካልተቀበላችሁ ብሎ መረባረብ?!
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የኪታብ ጥቆማ #25
~
* የኪታቡ ስም፦ أجوبة شيخ الإسلام ابن تيمية عن الشبهات التفصيلية للمعطلة في الصفات الذاتية
* ብዛቱ ፡ አንድ ሙጀለድ (ከ 600 ገፅ በላይ)
* በርእሱ ላይ ምርጥ ስራ ነው።
* አገር ውስጥ ይኑር አይኑር አላውቅም። እኔም ተውሼ ነው እያነበብኩት ያለሁት።
* pdf ፋይል ቀጥሎ ማግኘት ትችላላችሁ። ብታነቡት ትጠቀማላችሁ ኢንሻአለህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦

Forwarded from 𝑻𝒐𝒍𝒆𝒉𝒂 𝑨𝒉𝒎𝒆𝒅
أجوبة_شيخ_الإسلام_ابن_تيمية_عن_الشبهات_التفصيلية_للمعطلة_في_الصفات.pdf
5 MB
أجوبة شيخ الإسلام ابن تيمية عن الشبهات التفصيلية للمعطلة في الصفات الذاتية
فيراندا أندرجيا بن عابدين
فيراندا أندرجيا بن عابدين
ባልቴቶችን (እርጅና ላይ ሴቶችን) ለሰላምታ መጨበጥ
~
ጥያቄ፦
ባልቴትን ለሰላምታ መጨበጥ ይቻላልን?
መልስ፦
ጋብቻን ከማይፈልጉ ተቀማጮች ብትሆን እንኳ (አጅነቢይ ወንድ ሊጨብጣት) አይፈቀድም። መልእክተኛው ﷺ "እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም" ብለዋል። ታዲያ ባልቴት ከሴቶች ናት ወይስ ወንድ ሆናለች?! ከሴቶች መሆኗ ግልፅ ነው። እንግዲያው "እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም" የሚለው ሐዲሥ ከሷም ጋር የሚሰራ ነው።
አንዳንድ ባልቴቶች ሊቆጡ ይችላሉ። ቀላል ነው። ተዋት ትቆጣ። ኢንሻ አላህ ቁጣው ኋላ ይጠፋል። "መልእክተኛው ﷺ 'እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም' ስላሉ በቃል ነው ሰላም የምልሽ" በላት። ስለዚህ ባልቴት እንኳ ብትሆን እንዳትነካት፣ ባረከላሁ ፊኩም።
.
ፈትዋውን የሰጡት :- ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አልቡረዒይ ናቸው።
ምንጭ፦ https://www.tgoop.com/ElBorai
=
የቴሌግራም ቻናል፡-

የወሊድ ደም (ኒፋስ)
~
የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ልክ የወር አበባ ላይ እንዳለች ሴት ሶላት አትሰግድም፡፡ ፆም አትፆምም፡፡ ጦዋፍ አታደርግም፡፡ ግንኙነት አይፈቀድም፡፡
1. የወሊድ ደም ዝቅተኛው ጊዜ ስንት ነው?
በአራቱም መዝሀቦች ስምምነት ለዝቅተኛው የወሊድ ደም ቆይታ ገደብ የለውም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም ጊዜ ከአርባ ቀን በፊት ደም ከቆመ እንደማንኛዋም ንፁህ ሴት ነው የምትታየው፡፡ ከአንድ ከሁለት ቀን በኋላ ቢሆን እንኳ፡፡ ስለዚህ አርባ ቀን መጠበቅ የለባትም፡፡ ታጥባ ሶላቷን ትሰግዳለች፡፡
2. ከፍተኛው ጊዜ ስንት ነው?
ከፍተኛው የጊዜ ገደብ አርባ ቀን ነው፡፡ ይሄ ከብዙ ሶሐቦች የተረጋገጠ ሲሆን ቲርሚዚይ - ረሒመሁላህ - ኢጅማዕ አለበት ብለዋል፡፡ ስለዚህ እስከ አርባ ቀን እና ከዚያ በላይ ከቀጠለ ከአርባ ቀን በኋላ ያለው እንደ ወሊድ ደም ሳይሆን ልክ እንደ በሽታ ደም (ኢስቲሓዷህ) ነው የሚቆጠረው፡፡ ስለዚህ ደሙ አልቆመልኝም ብላ ከሶላት ልትዘናጋ አይገባም፡፡ ቀጥታ አርባ ቀን ሲሞላት ታጥባ ሶላቷን ትጀምራለች፡፡

برِئْنَا إِلَى اللهِ منْ معْشَرٍ ... يهِمْ مَرَضٌ مِنْ سَمَاعِ الغِنَا
وكم قلْتُ يَاقَوْمُ، أَنْتُمْ عَلَى ... شَفَا جُرُفٍ مَابِهِ مِنْ بِنَا
شَفَا جُرُفٍ تحْتَهُ هُوَّة ... إِلى دَرَكٍ، كم بِهِ مِنْ عَنا
وتَكْرَارُ النُّصْحِ مِنا لهم ... لنُعْذِرَ فِيهِمْ إِلى ربَّنا
فَلمَّا اسْتَّهانُوا بَتَنْبِيهنا ... رَجَعْنَا إِلى اللهِ فى أَمْرِنا
فعِشْنَا عَلَى سُنَّةِ المُصْطَفَى ... وَمَاتوُا عَلَى تِنْتِنَا تِنْتِنا

ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ
~
ሱጁድ (ግንባርን መሬት ላይ ማሳረፍ) ለሁለት ይከፈላል። ንፁህ አምልኮታዊ ሱጁድ እና የሰላምታ (የአክብሮት) ሱጁድ።
1- አምልኮታዊ ሱጁድ:-
የአላህ ብቻ ሐቅ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا
"ለአላህም ስገዱ፣ ተገዙትም።" [ነጅም፡ 62]
በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፦
{لَا تَسۡجُدُوا۟ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِی خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِیَّاهُ تَعۡبُدُونَ}
"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ። ይልቁንም እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ሆናችሁ ለእዚያ ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ።" [ፉሲለት፡ 37]
2- የሰላምታ ሱጁድ:-
ይህንንም ቢሆን ለፍጡር መስጠት እንደማይቻል የሚያሳይ ሐዲሥ አለ። ከመሆኑም ጋር ከፊል ሱፍዮች ለሸይኾቻቸው ሲፈፅሙት ይታያል። በርግጥ ቀደሞ የተፈቀደ ነበር። ለዚህም ማስረጃውም የላቀው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው:-
{ وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰۤىِٕكَةِ ٱسۡجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوۤا۟}
''ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ።" [አልኢስራእ፡ 61]
እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሱጁድ አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። ይሄ ሱጁድ የአምልኮት ሱጁድ እንዳልሆነ ኢጅማዕ አለበት። [አሕካሙል ቁርኣን፣ ኢብኑል ዐረቢ፡ 1/127] [አልፈስል፣ ኢብኑ ሐዝም፡ 2/129]
የዩሱፍ ታሪክ ላይ የተጠቀሰው የነብዩላህ ዩሱፍ ወላጆች ለዩሱፍ የወረዱት ሱጁድም ይሄው አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{إِذۡ قَالَ یُوسُفُ لِأَبِیهِ یَـٰۤأَبَتِ إِنِّی رَأَیۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبࣰا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَیۡتُهُمۡ لِی سَـٰجِدِینَ}
"ዩሱፍ ለአባቱ፡- 'አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም (በህልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው' ባለ ጊዜ (አስታውስ)።" [ዩሱፍ፡ 4]
ከዘመናት በኋላ ይህ ህልማቸው እውን እንደሆነ ሲገልፅ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦
{وَرَفَعَ أَبَوَیۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدࣰاۖ وَقَالَ یَـٰۤأَبَتِ هَـٰذَا تَأۡوِیلُ رُءۡیَـٰیَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّی حَقࣰّاۖ}
"ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው። ለእርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። 'አባቴ ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው። ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት።' " [ዩሱፍ፡ 100]
ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ ሰሞኑን እነዚህን አንቀፆች መነሻ በማድረግ ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ ይቻላል እያለ የፃፈ ስላየሁ ነው። የሚገርመው ሰዎች ከስር በኮመንት እየገቡ እናንተ አዋቂዎቹ ዝም ብላችሁ ነው የማንም መጫወቻ የምታደርጉት እያሉት ነበር። እንዲህ አይነት ችግር ነው የገጠመን። ቁንፅል ነገር ይይዙና መረጃዎችን በቅጡ ሳይፈትሹ፣ የዑለማእ ንግግሮችን ሳያገላብጡ አሳሳች መልእክት ያስተላልፋሉ። የራሳቸው ጥፋት አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ያሳስታሉ። አቀራረቡ ራስን መኮፈስ፣ ሌሎችን መናቅ ሲታከልበት ደግሞ ጥፋቱ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ቢገባቸው ይሄ አካሄድ በራሳቸውም ጥፋት፣ በሚያሳስቷቸው ሰዎችም ወንጀል እጥፍ ድርብ ተጠያቂነትን ነው የሚያስከትልባቸው።
ለማንኛውም በቀደምት ሸሪዐዎች የተፈቀደ የነበረው የሰላምታ ሱጁድ በነብዩ መሐመድ ﷺ ሸሪዐ ተሽሯል። ስለዚህ ምንም የማያጠራጥር ሐራም ነው ማለት ነው። ይህንን የሚጠቁመን ተከታዩ ዐብዱላህ ብኑ አቢ አውፋ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው።
ሙዓዝ (ብኑ ጀበል ረዲየላሁ ዐንሁ) ከሻም ሲመለሱ ጊዜ ለነብዩ ﷺ ሱጁድ ወረዱ።
"ምንድነው ይሄ ሙዓዝ?" አሉ።
ሙዓዝም፡ "ሻም በሄድኩኝ ጊዜ (ክርስቲያኖች) ለጳጳሶቻቸውና ለፓትሪያርኮቻቸው ሱጁድ ሲወርዱ አገኘኋቸው። እናም ይህንን ላንተ ልፈፅመው በነፍሴ ወደድኩኝ" አሉ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦
فَلَا تَفْعَلُوا، فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ، لَأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا ...
"እንዲህ አታድርጉ። ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ እንዲወርድ አንድንም የማዝዝ ቢሆን ኖሮ ሴት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ አዝ ነበር። ... " [ኢብኑ ማጀህ፡ 1853]
ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - "ሐሰኑን ሶሒሕ" በማለት ለማስረጃነት የሚያበቃው ጥንካሬ እንዳለው ገልፀዋል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1515]
ብዥታ የሚያነሳ ሰው እንዳይኖር የዑለማኦችን ንግግር ላስከትል:-
1- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
وَأَجْمَعَ الْمُسْلِمُونَ عَلَى: أَنَّ السُّجُودَ لِغَيْرِ اللَّهِ مُحَرَّمٌ
"ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ መውረድ የተከለከለ እንደሆነ ሙስሊሞች ወጥ ስምምነት አድርገዋል።" [አልመጅሙዕ፡ 4/358]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
فإن نصوص السنة، وإجماع الأمة: تُحرِّم السجودَ لغير الله في شريعتنا، تحيةً أو عبادةً، كنهيه لمعاذ بن جبل أن يسجد لما قدمَ من الشام وسجدَ له سجود تحية
"የሱና መረጃዎችና የህዝበ ሙስሊሙ ወጥ ስምምነት በሸሪዐችን ውስጥ ሱጁድን ከአላህ ውጭ ለሌላ አካል ማድረግን ይከለክላሉ። ሱጁዱ ለሰላምታ (ለማክበር) ይሁን ወይም ለአምልኮም ይሁን ምንም ለውጥ የለውም። ልክ ሙዓዝ ብኑ ጀበል ከሻም ሲመጡ የደረጉትን ሱጁድ እንደከለከሏቸው። (ሙዓዝ) ያደረጉት ሱጁድ የሰላምታ ሱጁድ ነበር።" [ጃሚዑል መሳኢል፡ 1/25]
2- ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል፦
"وَهَذَا السُّجُودُ الْمَنْهِيُّ عَنْهُ : قَدِ اتَّخَذَهُ جُهَّالُ الْمُتَصَوِّفَةِ عَادَةً فِي سَمَاعِهِمْ، وَعِنْدَ دُخُولِهِمْ عَلَى مَشَايِخِهِمْ وَاسْتِغْفَارِهِمْ ، فَيُرَى الْوَاحِدُ مِنْهُمْ إِذَا أَخَذَهُ الْحَالُ ـ بِزَعْمِهِ ـ يَسْجُدُ لِلْأَقْدَامِ ، لِجَهْلِهِ ؛ سَوَاءٌ أَكَانَ لِلْقِبْلَةِ أَمْ غَيْرِهَا ، جَهَالَةً مِنْهُ ، ضَلَّ سَعْيُهُمْ وَخَابَ عَمَلُهُمْ"
"ይህ የተከለከለው ሱጁድ አላዋቂ ሱፊያዎች በዜማቸው ላይ፣ ሸይኾቻቸው ዘንድ ሲገቡ እና ምህረትን ሲለምኑ ልማድ አድርገው ይዘውታል።
ከእነሱ ውስጥ አንዱ - እንደሚሞግቱት - 'ሐሉ' ሲነሳበት ጊዜ በእግራቸው ላይ ሲወድቅ ይታያል። ይህን የሚያደርገው ባለማወቁ ነው። ወደ ቂብላ ቢዞርም ባይዞርም ያደርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከእውቀት ማነስ የተነሳ ነው። ጥረታቸው ሁሉ ጠፋ፤ ስራቸውም ከሰረ።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 1/294]
ሰሞኑን ለ "ሙፍቲው" የተወረደውን ሱጁድ እዚህ ላይ እናገኘዋለን።
3- ኢብኑ ከሢር እንዲህ ብለዋል፦

وَقَدْ كَانَ هَذَا سَائِغًا فِي شَرَائِعِهِمْ؛ إِذَا سلَّموا عَلَى الْكَبِيرِ يَسْجُدُونَ لَهُ، وَلَمْ يَزَلْ هَذَا جَائِزًا مِنْ لَدُنْ آدَمَ إِلَى شَرِيعَةِ عِيسَى عَلَيْهِ السَّلَامُ، فَحُرِّمَ هَذَا فِي هَذِهِ الْمِلَّةِ، وجُعل السُّجُودُ مُخْتَصًّا بِجَنَابِ الرَّبِّ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى"
“ይህ (ሱጁድ) በቀድሞ ሸሪ0ዎች የተፈቀደ ነበር። ለአንድ ታላቅ ሰው ሰላምታ ሲሰጡ ሱጁድ ያደርጉ ነበር። ይህ ተግባር ከኣደም ጊዜ ጀምሮ እስከ ነብዩ ዒሳ - ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን - ሸሪዐ ድረስ የተፈቀደ ነበር። ነገር ግን በዚህ (በእኛ) ሃይማኖት ውስጥ ተከለከለ። ሱጁድ ከጌታችን ሱብሓነሁ ወተዓላ - ጋር ብቻ እንዲገደብ ተደረጓል።” [ተፍሲሩል ቁርኣኒል 0ዚም፡ 4/412]
4- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦
"مَا يَفْعَلُهُ كَثِيرٌ مِنْ الْجَهَلَةِ مِنْ السُّجُودِ بَيْنَ يَدَيْ الْمَشَايِخِ .. ذَلِكَ حَرَامٌ قَطْعًا، بِكُلِّ حَالٍ، سَوَاءٌ كَانَ إلَى الْقِبْلَةِ أَوْ غَيْرِهَا، وَسَوَاءٌ قَصَدَ السُّجُودَ لِلَّهِ تَعَالَى، أَوْ غَفَلَ، وَفِي بَعْضِ صُوَرِهِ مَا يَقْتَضِي الْكُفْرَ، أَوْ يُقَارِبُهُ، عَافَانَا اللَّهُ الْكَرِيمُ"
“ብዙ መሀይማን ከሸይኾች ፊት ለፊት የሚያደርጉት ሱጁድ ... ፍፁም ሐራም ነው። በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን፣ ወደ ቂብላ ቢዝዞርም ባይዞርም፣ ሱጁዱን ለአላህ ብሎ ቢያደርገውም ባያስበውም፣ ይህ ድርጊት የተከለከለ ነው።
እንዲያውም አንዳንድ ገፅታው ከእስልምና የሚያስወጣ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ወደ እሱ የሚያቀርብ ሊሆን ይችላል። ክቡሩ አላህ ከዚህ ይጠብቀን።” [አልመጅሙዕ ሸርሑል ሙሀዘብ፡ 4/69]
5- አሩሐይባኒይ እንዲህ ብለዋል፦
"السُّجُودُ لِلْحُكَّامِ وَالْمَوْتَى بِقَصْدِ الْعِبَادَةِ : كَفْرٌ ، قَوْلًا وَاحِدًا ، بِاتِّفَاقِ الْمُسْلِمِينَ. وَالتَّحِيَّةُ لِمَخْلُوقٍ بِالسُّجُودِ لَهُ: كَبِيرَةٌ مِنْ الْكَبَائِرِ الْعِظَامِ"
"ለገዢዎችና ለሞቱ ሰዎች በአምልኮ ሐሳብ ሱጁድ ማድረግ ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባር ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የሙስሊሞች ሁሉ አቋም አንድ ነው። ለአንድ ፍጡር ለማክበር ሲባል ሱጁድ ማድረግ ደግሞ እጅግ ከባባድ ከሆኑ ወንጀሎች ውስጥ ነው።" [መጧሊቡ ኡሊኑሃ፡ 6/278]
6- ዐብዱልዐዚዝ ዐብዱለጢፍ እንዲህ ብለዋል፦
"فمن المعلوم أن سجود العبادة، القائم على الخضوع والذل والتسليم والإجلال لله وحده: هو من التوحيد الذي اتفقت عليه دعوة الرسل، وإن صرف لغيره فهو شرك وتنديد.
ولكن لو سجد أحدهم لأب أو عالم ونحوهما، وقصده التحية والإكرام: فهذه من المحرمات التي دون الشرك ، أما إن قصد الخضوع والقربة والذل له فهذا من الشرك"
“ነገር ግን አንድ ሰው ለአባቱ፣ ለዓሊም ወይም ለመሳሰሉት ሰላምታና ክብር ለመስጠት ሱጁድ ቢያደርግ ይህ ድርጊት ከሽርክ በታች ያለ የተከለከለ ተግባር ነው። ሆኖም፣ አንድ ሰው ሱጁዱን ያደረገው ለዚያ አካል ለመተናነስ፣ ለመቃረብ ወይም ለመገዛት ከሆነ ያኔ ሺርክ ይሆናል።” [ነዋቂዱል ኢማን አልቀውሊየህ ወልዐመሊየህ፡ 278]
ማጠቃለያ፦
የአምልኮትም ይሁን የአክብሮት ሱጂድ የተከለከሉ ናቸው። ይሁን እንጂ የጥፋቱ ደረጃ ይለያያል። የአምልኮት ሲሆን ፍጡርን ማምለክ ስለሆነ ከኢስላም የሚያስወጣ ሺርክ ይሆናል። የአክብሮት ከሆነ ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች (ከባኢር) የሚቆጠር ጥፋት ይሆናል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 14/ 1447)
=
የቴሌግራም ቻናል :-

አንድ ሰው ወደ አቡ ዙርዐ አር-ራዚይ ዘንድ መጥቶ፣
- “እኔ ሙዓውያን እጠላዋለሁ” አላቸው።
* "ለምን?" አሉት።
- “ምክንያቱም እሱ ዐሊይን ስለተዋጋቸው” አለ።
* “የሙዓውያ ጌታ እጅግ በጣም አዛኝ ጌታ ነው፤ የሙዓውያ ባላንጣ ደግሞ የተከበረ ባላንጣ ነው። አንተ በመካከላቸው ምን ጥልቅ አደረገህ?” አሉት።
[ታሪኹ ዲመሽቅ፣ ኢብኑ ዐሳኪር፡ 602]

ግለሰባዊ ነፃነት ማለት ቡናህ በስኳር ይሁን ወይስ ያለ ስኳር? የሚለውን ልትመርጥ ነው።
እንጂ የአላህ ዲንን በተመለከተ ግለሰባዊ ነፃነት የሚባል የለም።
እንዳሰኘህ ሳይሆን "እንደታዘዝከው ቀጥ በል" ነው የተባለው።
عبد الملك الإبي
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
እንጂ የአላህ ዲንን በተመለከተ ግለሰባዊ ነፃነት የሚባል የለም።
እንዳሰኘህ ሳይሆን "እንደታዘዝከው ቀጥ በል" ነው የተባለው።
عبد الملك الإبي
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Forwarded from AbulAbasNasir (አቡል ዓባስ)
ጾታ፡ ለሁለቱም (ለወንድም ለሴትም)
እድሜ: ለወንድ ከ10 - 25 ዓመት
ለሴት ከ 10 አመት በላይ
ፆታ: ለሁለቱም
እድሜ: ከ 4 አመት በላይ ለሁሉም የእድሜ ክልል
+251913939993 /+251928844757
+251911119260 /+251930547776
https://www.tgoop.com/merkezabumussa1
https://www.tgoop.com/merkezabumussa1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አጅነቢያ ሴት በሰላምታ መጨበጥ
~
በኢስላም ለአንድ ወንድ አጅነቢያ የሆነችን (ማግባት በሚፈቀድለት ርቀት ላይ ያለችን) ሴት መንካት አይፈቀድለትም። ለሴቷም እንዲሁ አጅነቢይ የሆነን ወንድ መንካት አይፈቀድላትም።
#ማስረጃ_አንድ፦
ያልተፈቀደ ንክኪ የዝሙት አንድ መንገድ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
العينان زِناهما النَظر، والأُذنان زِناهما الاستماع، واللسان زِناه الكلام، واليَدُ زِناها البَطْش، والرِّجل زِناها الخُطَا، والقلب يَهْوَى ويتمنى، ويُصَدِّق ذلك الفَرْج أو يُكذِّبُه
"አይኖች ዝሙታቸው እይታ ነው። ጆሮዎች ዝሙታቸው ማደመጥ ነው። ምላስ ዝሙቱ ንግግር ነው። እጅ ዝሙቷ መያዝ ነው። እግር ዝሙቷ እርምጃ ነው። ልብ ይፈልጋል፣ ይመኛልም። ብልት ያንን ወይ ያረጋግጠዋል ወይ ያስተባብለዋል።" [ቡኻሪይ፡ 6612] [ሙስሊም፡ 2657]
በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:-
واليدُ زِناها اللَّمسُ
"እጅ ዝሙቷ መንካት ነው።"
ኢብኑ ሒባን [ሶሒሕ ኢብኒ ሒባን፡ 4422]፣ ኢብኑ ኹዘይመህ በሶሒሐቸው [1/149]፣ ኢብኑ ከሢር በተፍሲራቸው [2/277]፣ አሕመድ ሻኪር በዑምደቱ ተፍሲር [1/514]፣ አልባኒይ [አሶሒሐ፡ 2804]፣ ሹዐይብ አልአርነኡጥ በተኽሪጁል ሙስነድ [8598] ሐዲሡ ሶሒሕ እንደሆነ ገልፀዋል።
#ማስረጃ_ሁለት፦
እናታችን ዓኢሻ ረዲያለሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች:-
وَاللهِ مَا مَسَّتْ يَدُ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَدَ امْرَأَةٍ قَطُّ ، غَيْرَ أَنَّهُ يُبَايِعُهُنَّ بِالْكَلَامِ
“ወላሂ የአላህ መልእክተኛ እጅ ፈፅሞ (የአጅነቢያ) እጅ ነክቶ አያውቅም፡፡ ባይሆን በንግግር ነበር ከነሱ ጋር ቃል ኪዳን የሚገቡት።” [ቡኻሪ፡ 4891] [ሙስሊም፡ 1866]
"ምናልባት እሷ ስላላየች እንዳይሆን" የሚል ካለ ቀጣዩ ሐዲሥ ይህንን በር ይዘጋል።
#ማስረጃ_ሶስት፦
ኡመይመህ ቢንቲ ሩቀቀህ ረዲያለሁ ዐንሃ እንዳለችሁ ከተወሰኑ ሴቶች ጋር ሆነን ነብዩን ﷺ በመጨባበጥ ቃል ኪዳን ልንገባ ስንቀርብ እንዲህ አሉን:-
إنِّي لا أُصافِحُ النِّساءَ
“እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም።" [ነሳኢይ: 4181]
#ማስረጃ_አራት፦
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
لَأَنْ يُطعَنَ في رأسِ أحَدِكُمْ بِمَخْيَطٍ من حَدِيدٍ خَيرٌ له من أنْ يَمسَّ امْرأةً لا تَحِلُّ لَهُ
“አንዳችሁ ያልተፈቀደለትን ሴት ከሚነካ አናቱን በብረት መርፌ ቢውወጋ ይሻለዋል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ: 5045]
#ማስረጃ_አምስት፦
ከዐርሹ በላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፦
{قُل لِّلۡمُؤۡمِنِینَ یَغُضُّوا۟ مِنۡ أَبۡصَـٰرِهِمۡ} (30) {وَقُل لِّلۡمُؤۡمِنَـٰتِ یَغۡضُضۡنَ مِنۡ أَبۡصَـٰرِهِنَّ (31) }
"ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ።" "ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ።" [አንኑር፡ 30 - 31]
የሩቅ እይታ የማይፈቀድ ከሆነ፣ የእጅ ንክኪ የበለጠ አይፈቀድም። ይህንን ብዙ ዓሊሞች ገልፀውታል።
ይሄ እንግዲህ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። አቋማቸው ክብደት ያለው ባይሆንም ልቅ በሆነ መልኩ ባይሆንም ከዚህ የተለየ የተናገሩ አሉ። ከመሆኑም ጋር የማስረጃዎችን ጥንካሬ በማየት ሳይሆን ስሜታቸውን ተከትለው በየርእሰ ጉዳዩ ወጣ ያሉ የዑለማእ ንግግሮችን እያሳደዱ የሚከተሉ ሰዎች አሉ። በዚህ የተነሳ ከላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች ዋጋ ለማሳጣት የተለያዩ ብዥታዎችን ያነሳሉ። ለምሳሌ ያህል:-
#ብዥታ_አንድ
=
“እኔ (አጅነቢያ) ሴቶችን አልጨብጥም" የሚለውን ሐዲሥ “እኔ አልጨብጥም አሉ'ንጂ እናንተ አትጨብጡ አላሉም" የሚሉ አሉ።
ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ፦
1ኛ:- እንዲያውም ነብዩ ﷺ ምራቃቸውን የዋጡ፣ ስሜታቸውን የሚቆጣጠሩ፣ ከአጉል ስሜት የሚጠብቅ የተሟላ ተቅዋን የተቸሩ ከመሆናቸው ጋር በዚህ መጠን እሳቸው ከተጠነቀቁ ሌላው በየትኛው ተቅዋውና ጥንቃቄው ነው ለኛ ግን ይቻላል ብሎ የሚኮፈሰው?!
2ኛ:- ደግሞም አንድ የነብዩ ﷺ ተግባርና ንግግር እሳቸው ላይ ብቻ የሚገደብ እንደሆነ የሚጠቁም ግልፅ መረጃ እስካልመጣ ድረስ ሁሉንም ሙስሊሞች የሚመለከት ጠቅላይ ህግ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ
"አላህ አማኞችን ያዘዘው መልእክተኞችን ባዘዘበት ነው።" [ሙስሊም፡ 1015]
ስለዚህ “እኔ (አጅነቢያ) ሴቶችን አልጨብጥም" የሚለው ሐዲሥም በሳቸው ላይ ብቻ የተገደበ እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ ባልመጣበት ሌሎች ሙስሊሞችን አይመለከትም አይባልም። እንዲያውም ፈለጋቸውን እንድንከተል ነው የታዘዝነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
{لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِی رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةࣱ}
"በርግጥም በአላህ መልእክተኛ ላይ መልካም ምሳሌ አለላችሁ።" [አሕዛብ፡ 21]
{وَمَاۤ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمۡ عَنۡهُ فَٱنتَهُوا۟ۚ}
"መልእክተኛው ያመጣላችሁንም ያዙ፤ መልእክተኛው የከለከላችሁን ነገርም ተከልከሉ።" [ሐሽር፡ 7]
3ኛ:- ጌታችን አላህ ወንዶችም ይሁን ሴቶች ካልተፈቀደ እይታ እንዲቆጠቡ አዟል። [ኑር: 30-31] የክልከላው አላማም በግልፅ የሚታወቅ ነው። ታዲያ እይታን ከልክሎ መጨባበጥን ይፈቅዳል ብሎ ማሰብ ምን የሚሉት ስሌት ነው? አይንህን ጨፍነህ ልተጨባበጥ ነው?!
4ኛ:- “አንዳችሁ ያልተፈቀደለትን ሴት ከሚነካ አናቱን በብረት መርፌ ቢውወጋ ይሻለዋል” የሚለው ሐዲሥ ይበልጥ የብዥታን ቀዳዳ የሚዘጋ ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 5045]
#ብዥታ_ሁለት
=
አጅነቢያ ሴትን መጨበጥ ይቻላል የሚሉ ሰዎች ተከታዩን ዘገባ ሲጠቅሱ ያጋጥማል፦
إِنْ كَانَتِ الأَمَةُ مِنْ إِمَاءِ أَهْلِ المَدِينَةِ، لَتَأْخُذُ بِيَدِ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ، فَتَنْطَلِقُ بِهِ حَيْثُ شَاءَتْ
"በርግጥም ከመዲና ሴት ባሪያዎች ውስጥ አንዷ የአላህ መልእክተኛን ﷺ እጅ ይዛ ከምትፈልገው ቦታ ትወስዳቸው ነበር።" [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 3386]
መልስ፦
1ኛ:- የዚህ ሐዲሥ መልእክት ነብዩ ﷺ የሰዎችን ጉዳይ ለመፈፀም ሌላው ቀርቶ ለባሪያ እንኳ በዚህ መጠን ትሁት፣ አዛኝና ተባባሪ ነበሩ ለማለት እንጂ የእጅ ንክኪ ነበር ማለት አይደለም ይላሉ ኢብኑ ሐጀር፣ አልቀስጦላኒይ እና ሙላ ቃሪ [አልፈትሕ፡ 10/490] [ኢርሻዱ ሳሪ: 9/51] [ሚርቃቱል መፋቲሕ፡ 9/3713]
ይሄ ደግሞ በዐረብኛ ቋንቋ የተለመደ አነጋገር ነው። ለምሳሌ ዱዓእ ላይ اللهم خذ بأيدينا إليك (አላህ ሆይ! እጆቻችን ይዘህ ወዳንተ ውሰደን) ሲባል አውዳዊ ፍቺው "ለታዛዥነት አድለን" ለማለት እንጂ ቀጥታ እጃችንን እንዲይዘን መጠየቅ አይደለም።
2ኛ፦ የሐዲሡ መልእክት በሌላ ዘገባ ላይ ግልፅ ተደርጓል። አነስ ብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ:-

"أَنَّ امْرَأَةً كَانَ فِي عَقْلِهَا شَيْءٌ ، فَقَالَتْ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ لِي إِلَيْكَ حَاجَةً؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: (يَا أُمَّ فُلَانٍ، خُذِي أَيَّ الطُّرُقِ شِئْتِ، فَقُومِي فِيهِ حَتَّى أَقُومَ مَعَك) فَخَلَا مَعَهَا رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يُنَاجِيهَا، حَتَّى قَضَتْ حَاجَتَهَا"
"አንዲት አእምሮዋ ትንሽ ችግር ያለባት ሴት 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ካንተ ጉዳይ አለኝ' አለች። የአላህ መልእክተኛም ﷺ 'የእከሌ እናት ሆይ! የፈለግሽውን መንገድ ይዘሽ ተነሽ አብሬሽ እቆማለሁ' አሏት። ከዚያም ጉዳዩዋን እስከምታጠናቅቅ ድረስ ከሷ ጋር ገለል ብለው አወያዩዋት።" [ሶሒሕ ኢብኒ ሒባን፡ 4527]
ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“በጥቅሉ ነብዩ (አጅነቢያ) ሴትን በእጃቸው እንደጨበጡ የሚያመላክት ጭራሽ አንድ እንኳን ትክክለኛ ማስረጃ አልመጣም፡፡ እንዲሁ ሲገናኙ መጨባበጥ ቀርቶ በቃል ኪዳን ጊዜ እንኳን አላደረጉትም፡፡ ነብዩ ከሴት ጋር ከመጨባበጥ የራቁ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ግልፅ መልእክት ያላቸውን ሐዲሶች ትተው መጨባበጡ ያልተገለፀበትን የኡሙ ዐጢያን ሐዲስ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ በእውነት ሙኽሊስ ከሆነ ሙእሚን የሚመነጭ አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ ያልተፈቀደችለትን በሚጨብጥ ሰው ላይ ከባድ ዛቻ ከመምጣቱ ጋር፡፡” [አሶሒሓህ፡ 2/28]
* ንክኪው በልብስ ወይም በጓንት ቢሆንስ? ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ፡ "አንድ ሰው ሴትን በሰላምታ መጨበጥ ይችላልን?" ተብለው ሲጠየቁ፡
لا وشدد فيه جداً، قلت يصافحها بثوبه. قال: لا
"አይሆንም" ብለው በጣም የከረረ ምላሽ ሰጥተዋል። ጠያቂው "በልብሱስ ቢጨብጣት?" ሲላቸው "አይቻልም" ብለዋል። [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 2/257]
ወደ ጥፋት አሻጋሪ መንገዶችን መዝጋት (ሰደ ዘሪ0ህ) ዋጋ ያለው የሸሪዐ መርህ መሆኑም ይሰመርበት።
አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
#ማሳሰቢያ:-
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት ክልከላው ወንዱ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ሴቷንም እኩል የሚመለከት ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 15/1447)

እሬቻ ሃይማኖታዊ በዓል መሆኑ ግልፅ ቢሆንም ባህል ብቻ ነው በማለት የሚከራከሩ አካላት እንዳሉ ይታወቃል። ይሄው የእምነቱ ባለቤቶች (የዋቄፈና ሃይማኖት ተከታዮች) የእሬቻ በዓል ሃይማኖታዊ እንደሆነ አስረግጠው ገልፀዋል። እንከባበር ብለው ከእምነታቸው ውጭ ላሉ ሁሉ የላኩት ማሳሰቢያ ያልነቁ ይነቁ ዘንድ የሚያግዝ ነው። ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ! ይህንን አውቃችሁ አላህን በመፍራት እንዲህ ዓይነት ቦታ ላይ ፈፅሞ አትገኙ። ምናልባት ለአንዳንዶች መንቃት ሰበብ ሊሆን ስለሚችል ያልደረሰው ዘንድ እንዲደርስ ብናሰራጨው ጥሩ ነው፣ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Forwarded from Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ኪታብ
በገበያ ላይ ዋለ
አዲስ አበባ ላይ ላላቹህ
ወንድማችን አቡ ዘከሪያ ጋር ማግኘት ይችላሉ ብዛት የምትፈልጉ ያላቹሁበት ቦታ ድረስ እንልክላቹሀለን
በ ፍሬም የሚፈልግ ያናግረን
ስልክ :-0908869945
ወንድም አቡ ዘከሪያ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ
ሓቲም)
https://www.tgoop.com/UstazKedirAhmed/8749

ግርዶሽ ስለሚከሰትበት ጊዜ መናገር ዒልመል ገይብ ነው?
~
የፀሐይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ ከመከሰቱ ቀድሞ የሚከሰትበትን አካባቢውንና ጊዜውን መናገር በፍጡር ከማይደረስበት የሩቅ እውቀት (ዒልመል ገይብ) የሚቆጠር አይደለም። ይህንን ፈትዋ ይመልከቱ፡-
ጠያቂ፡- አንዳንዴ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ በዚህ በዚህ ቀን፣ በዚህ ወር፣ በዚህ አካባቢ፣ በዚህ ሰዓት ይከሰታል ብለው ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። የሚሉትም በተጨባጭ ይረጋገጣል። ይሄ ነገር ከሩቅ እውቀት ነው ወይስ አይደለም? አላህ ያድላችሁና።
መልስ በሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ፡-
ስለ ፀሐይ እና ጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ መናገር ከሩቅ እውቀት አይደለም። ይልቁንም ይሄ የሂሳብ እውቀት ነው። የፀሐይና የጨረቃን እንቅስቃሴ በጥልቅ በመከታተል ብዙ የስነ ፈለክ አጥኚዎች ይህንን ነገር ያውቁታል። እናም ለፀሐይ ወይም ለጨረቃ የተለየ መለያ ሲኖር ጊዜ በአላህ ፈቃድ በዚያ ወቅት እንደምትጋረድ በስሌት ያውቁታል። ይሄ የሂሳብ እውቀት ነው። እንጂ የሩቅ ማወቅ አይደለም። ይልቁንም የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ በመመልከት የስነ ፈለክ ሰዎች የሚደርሱበት ደቂቅ የሆነ ስሌት ነው። እንዳሉት የሚሆንበት ጊዜ አለው። ሊሳሳቱም ይችላሉ። አንዳንዴ ይሳሳታሉ። አንዳንዴ ደግሞ ልክ ይሆናሉ። አቡል ዐባስ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“የነዚህ ሰዎች መረጃ የበኑ ኢስ - ራኢል ዘገባዎች አይነት ነው። አይታመንም አይስተባበልም። ፀሐይ በዚህ ጊዜ ትጋረዳለች ብለው የማይከሰትበት ጊዜ አለ። ስሌቱን በሚገባ በመስራታቸው የተነሳ እንዳሉት የሚከሰትበት ጊዜም አለ። ሲጠቃለል መረጃዎቻቸው ስህተት ሊገጥማቸው ይችላሉ። ስለሆነም አይታመኑም፣ አይስተባበሉም። ባይሆን የተናገሩት ይታያል። ግርዶሹ ከተከሰተ ሰዎች በግርዶሹ ጊዜ አላህን ማውሳት፣ ኢስቲግፋር ማድረግ፣ መስገድ፣ ሶደቃ መስጠት፣ ባሪያን ነፃ ማውጣት፣ አላህን ማውሳት፣ ጥራት ይገባውና አላህን ማላቅ ተደንግጓል። ምክንያቱም መልእክተኛው እንዲህ ሲሉ በዚህ አዘዋልና፡- “ይህንን ካያችሁ አላህን ወደ ማውሳት፣ ወደ መማፀንና ምህረቱን ወደ መጠየቅ ሽሹ።” እንዲሁም “ይህንን ስታዩ ስገዱ። ዱዓ አድርጉ” ብለዋል። በተክቢርም አዘዋል። ባሪያን ነፃ በማውጣትም አዘዋል። ይሄ ሁሉ ሱና ነው። የተደነገገም ነው። ከነብዩም ﷺ የተረጋገጠ ነው። የስነ ፈለክ ሰዎች መረጃዎች ግን ከሩቅ እውቀት አይደሉም። ባይሆን ሊሳሳቱም፣ ሊያገኙም ይችላሉ። አዎ ሊሳሳቱም፣ ሊያገኙም ይችላሉ።” [ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ፣ ኢብኑ ባዝ፡ 4/11]
የዚህ የኢብኑ ባዝ ፈትዋ መልእክት ጭብጥ ከሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ መጅሙዑል ፈታዋ ውስጥ ይገኛል። ኢብኑ ተይሚያ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ከመለሱት ፈትዋ ውስጥ ቀንጨብ ላድርግ፡-
“የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰትበትን ኡደት ማወቅ ይህንን የሚያውቀው የእንቅስቃሴያቸውን ስሌት የሚያውቅ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው የሂሳብ አዋቂ መረጃ ከሩቅ እውቀት አይደለም።” “በስሌት የሚታወቀው ግን የአመት ወቅቶችን እንደማወቅ ነው። የፀደይ፣ የክረምት፣ የመኸርና የበጋ መግቢያዎችን ይመስል። …” እያሉ በሰፊው ይተነትናሉ። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 24/254-262]
ማስታወሻ፦
1- የሰው ልጅ የሳይንስ እውቀት፣ የዘመናት ተሞክሮ እና የተራቀቁ አጋዥ መሳሪያዎች ጋር ሲሆን ስለ ክስተቱ ጊዜና አካባቢ የሚስሰጠው መረጃ ላይ ስህተት የመከሰት እድሉ በጣም እየጠበበ ይሄዳል።
2- ይሄ ክስተት ሲከሰት በክስተቱ መመሰጥ፣ ጨረቃዋ ደስ ስትል እያሉ መቦረቅ ሳይሆን ተውበት፣ አስቲግፋር ማድረግ፣ ሶላት መስገድ፣ ... ነው የሚገባው።
ከትንሽ ጭማሪ ጋር በድጋሚ የተለጠፈ።