IBNUMUNEWOR Telegram 7959
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ግርዶሽ ስለሚከሰትበት ጊዜ መናገር ዒልመል ገይብ ነው?
~
የፀሐይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ ከመከሰቱ ቀድሞ የሚከሰትበትን አካባቢውንና ጊዜውን መናገር በፍጡር ከማይደረስበት የሩቅ እውቀት (ዒልመል ገይብ) የሚቆጠር አይደለም። ይህንን ፈትዋ ይመልከቱ፡-

ጠያቂ፡- አንዳንዴ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ግርዶሽ በዚህ በዚህ ቀን፣ በዚህ ወር፣ በዚህ አካባቢ፣ በዚህ ሰዓት ይከሰታል ብለው ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። የሚሉትም በተጨባጭ ይረጋገጣል። ይሄ ነገር ከሩቅ እውቀት ነው ወይስ አይደለም? አላህ ያድላችሁና።

መልስ በሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ፡-

ስለ ፀሐይ እና ጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ መናገር ከሩቅ እውቀት አይደለም። ይልቁንም ይሄ የሂሳብ እውቀት ነው። የፀሐይና የጨረቃን እንቅስቃሴ በጥልቅ በመከታተል ብዙ የስነ ፈለክ አጥኚዎች ይህንን ነገር ያውቁታል። እናም ለፀሐይ ወይም ለጨረቃ የተለየ መለያ ሲኖር ጊዜ በአላህ ፈቃድ በዚያ ወቅት እንደምትጋረድ በስሌት ያውቁታል። ይሄ የሂሳብ እውቀት ነው። እንጂ የሩቅ ማወቅ አይደለም። ይልቁንም የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ በመመልከት የስነ ፈለክ ሰዎች የሚደርሱበት ደቂቅ የሆነ ስሌት ነው። እንዳሉት የሚሆንበት ጊዜ አለው። ሊሳሳቱም ይችላሉ። አንዳንዴ ይሳሳታሉ። አንዳንዴ ደግሞ ልክ ይሆናሉ። አቡል ዐባስ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-

“የነዚህ ሰዎች መረጃ የበኑ ኢስ - ራኢል ዘገባዎች አይነት ነው። አይታመንም አይስተባበልም። ፀሐይ በዚህ ጊዜ ትጋረዳለች ብለው የማይከሰትበት ጊዜ አለ። ስሌቱን በሚገባ በመስራታቸው የተነሳ እንዳሉት የሚከሰትበት ጊዜም አለ። ሲጠቃለል መረጃዎቻቸው ስህተት ሊገጥማቸው ይችላሉ። ስለሆነም አይታመኑም፣ አይስተባበሉም። ባይሆን የተናገሩት ይታያል። ግርዶሹ ከተከሰተ ሰዎች በግርዶሹ ጊዜ አላህን ማውሳት፣ ኢስቲግፋር ማድረግ፣ መስገድ፣ ሶደቃ መስጠት፣ ባሪያን ነፃ ማውጣት፣ አላህን ማውሳት፣ ጥራት ይገባውና አላህን ማላቅ ተደንግጓል። ምክንያቱም መልእክተኛው እንዲህ ሲሉ በዚህ አዘዋልና፡- “ይህንን ካያችሁ አላህን ወደ ማውሳት፣ ወደ መማፀንና ምህረቱን ወደ መጠየቅ ሽሹ።” እንዲሁም “ይህንን ስታዩ ስገዱ። ዱዓ አድርጉ” ብለዋል። በተክቢርም አዘዋል። ባሪያን ነፃ በማውጣትም አዘዋል። ይሄ ሁሉ ሱና ነው። የተደነገገም ነው። ከነብዩም ﷺ የተረጋገጠ ነው። የስነ ፈለክ ሰዎች መረጃዎች ግን ከሩቅ እውቀት አይደሉም። ባይሆን ሊሳሳቱም፣ ሊያገኙም ይችላሉ። አዎ ሊሳሳቱም፣ ሊያገኙም ይችላሉ።” [ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ፣ ኢብኑ ባዝ፡ 4/11]

የዚህ የኢብኑ ባዝ ፈትዋ መልእክት ጭብጥ ከሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ መጅሙዑል ፈታዋ ውስጥ ይገኛል። ኢብኑ ተይሚያ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ከመለሱት ፈትዋ ውስጥ ቀንጨብ ላድርግ፡-

“የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰትበትን ኡደት ማወቅ ይህንን የሚያውቀው የእንቅስቃሴያቸውን ስሌት የሚያውቅ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው የሂሳብ አዋቂ መረጃ ከሩቅ እውቀት አይደለም።” “በስሌት የሚታወቀው ግን የአመት ወቅቶችን እንደማወቅ ነው። የፀደይ፣ የክረምት፣ የመኸርና የበጋ መግቢያዎችን ይመስል። …” እያሉ በሰፊው ይተነትናሉ። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 24/254-262]

ማስታወሻ፦
1- የሰው ልጅ የሳይንስ እውቀት፣ የዘመናት ተሞክሮ እና የተራቀቁ አጋዥ መሳሪያዎች ጋር ሲሆን ስለ ክስተቱ ጊዜና አካባቢ የሚስሰጠው መረጃ ላይ ስህተት የመከሰት እድሉ በጣም እየጠበበ ይሄዳል።
2- ይሄ ክስተት ሲከሰት በክስተቱ መመሰጥ፣ ጨረቃዋ ደስ ስትል እያሉ መቦረቅ ሳይሆን ተውበት፣ አስቲግፋር ማድረግ፣ ሶላት መስገድ፣ ... ነው የሚገባው።

ከትንሽ ጭማሪ ጋር በድጋሚ የተለጠፈ።
=
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

tgoop.com/IbnuMunewor/7959
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7959

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

6How to manage your Telegram channel? Members can post their voice notes of themselves screaming. Interestingly, the group doesn’t allow to post anything else which might lead to an instant ban. As of now, there are more than 330 members in the group. The administrator of a telegram group, "Suck Channel," was sentenced to six years and six months in prison for seven counts of incitement yesterday. In handing down the sentence yesterday, deputy judge Peter Hui Shiu-keung of the district court said that even if Ng did not post the messages, he cannot shirk responsibility as the owner and administrator of such a big group for allowing these messages that incite illegal behaviors to exist. fire bomb molotov November 18 Dylan Hollingsworth yau ma tei
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American