tgoop.com/IbnuMunewor/7943
Create:
Last Update:
Last Update:
ባልቴቶችን (እርጅና ላይ ሴቶችን) ለሰላምታ መጨበጥ
~
ጥያቄ፦
ባልቴትን ለሰላምታ መጨበጥ ይቻላልን?
መልስ፦
ጋብቻን ከማይፈልጉ ተቀማጮች ብትሆን እንኳ (አጅነቢይ ወንድ ሊጨብጣት) አይፈቀድም። መልእክተኛው ﷺ "እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም" ብለዋል። ታዲያ ባልቴት ከሴቶች ናት ወይስ ወንድ ሆናለች?! ከሴቶች መሆኗ ግልፅ ነው። እንግዲያው "እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም" የሚለው ሐዲሥ ከሷም ጋር የሚሰራ ነው።
አንዳንድ ባልቴቶች ሊቆጡ ይችላሉ። ቀላል ነው። ተዋት ትቆጣ። ኢንሻ አላህ ቁጣው ኋላ ይጠፋል። "መልእክተኛው ﷺ 'እኔ ሴቶችን በሰላምታ አልጨብጥም' ስላሉ በቃል ነው ሰላም የምልሽ" በላት። ስለዚህ ባልቴት እንኳ ብትሆን እንዳትነካት፣ ባረከላሁ ፊኩም።
.
ፈትዋውን የሰጡት :- ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አልቡረዒይ ናቸው።
ምንጭ፦ https://www.tgoop.com/ElBorai
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7943