tgoop.com/IbnuMunewor/7948
Last Update:
وَقَدْ كَانَ هَذَا سَائِغًا فِي شَرَائِعِهِمْ؛ إِذَا سلَّموا عَلَى الْكَبِيرِ يَسْجُدُونَ لَهُ، وَلَمْ يَزَلْ هَذَا جَائِزًا مِنْ لَدُنْ آدَمَ إِلَى شَرِيعَةِ عِيسَى عَلَيْهِ السَّلَامُ، فَحُرِّمَ هَذَا فِي هَذِهِ الْمِلَّةِ، وجُعل السُّجُودُ مُخْتَصًّا بِجَنَابِ الرَّبِّ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى"
“ይህ (ሱጁድ) በቀድሞ ሸሪ0ዎች የተፈቀደ ነበር። ለአንድ ታላቅ ሰው ሰላምታ ሲሰጡ ሱጁድ ያደርጉ ነበር። ይህ ተግባር ከኣደም ጊዜ ጀምሮ እስከ ነብዩ ዒሳ - ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን - ሸሪዐ ድረስ የተፈቀደ ነበር። ነገር ግን በዚህ (በእኛ) ሃይማኖት ውስጥ ተከለከለ። ሱጁድ ከጌታችን ሱብሓነሁ ወተዓላ - ጋር ብቻ እንዲገደብ ተደረጓል።” [ተፍሲሩል ቁርኣኒል 0ዚም፡ 4/412]
4- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦
"مَا يَفْعَلُهُ كَثِيرٌ مِنْ الْجَهَلَةِ مِنْ السُّجُودِ بَيْنَ يَدَيْ الْمَشَايِخِ .. ذَلِكَ حَرَامٌ قَطْعًا، بِكُلِّ حَالٍ، سَوَاءٌ كَانَ إلَى الْقِبْلَةِ أَوْ غَيْرِهَا، وَسَوَاءٌ قَصَدَ السُّجُودَ لِلَّهِ تَعَالَى، أَوْ غَفَلَ، وَفِي بَعْضِ صُوَرِهِ مَا يَقْتَضِي الْكُفْرَ، أَوْ يُقَارِبُهُ، عَافَانَا اللَّهُ الْكَرِيمُ"
“ብዙ መሀይማን ከሸይኾች ፊት ለፊት የሚያደርጉት ሱጁድ ... ፍፁም ሐራም ነው። በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን፣ ወደ ቂብላ ቢዝዞርም ባይዞርም፣ ሱጁዱን ለአላህ ብሎ ቢያደርገውም ባያስበውም፣ ይህ ድርጊት የተከለከለ ነው።
እንዲያውም አንዳንድ ገፅታው ከእስልምና የሚያስወጣ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ወደ እሱ የሚያቀርብ ሊሆን ይችላል። ክቡሩ አላህ ከዚህ ይጠብቀን።” [አልመጅሙዕ ሸርሑል ሙሀዘብ፡ 4/69]
5- አሩሐይባኒይ እንዲህ ብለዋል፦
"السُّجُودُ لِلْحُكَّامِ وَالْمَوْتَى بِقَصْدِ الْعِبَادَةِ : كَفْرٌ ، قَوْلًا وَاحِدًا ، بِاتِّفَاقِ الْمُسْلِمِينَ. وَالتَّحِيَّةُ لِمَخْلُوقٍ بِالسُّجُودِ لَهُ: كَبِيرَةٌ مِنْ الْكَبَائِرِ الْعِظَامِ"
"ለገዢዎችና ለሞቱ ሰዎች በአምልኮ ሐሳብ ሱጁድ ማድረግ ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባር ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የሙስሊሞች ሁሉ አቋም አንድ ነው። ለአንድ ፍጡር ለማክበር ሲባል ሱጁድ ማድረግ ደግሞ እጅግ ከባባድ ከሆኑ ወንጀሎች ውስጥ ነው።" [መጧሊቡ ኡሊኑሃ፡ 6/278]
6- ዐብዱልዐዚዝ ዐብዱለጢፍ እንዲህ ብለዋል፦
"فمن المعلوم أن سجود العبادة، القائم على الخضوع والذل والتسليم والإجلال لله وحده: هو من التوحيد الذي اتفقت عليه دعوة الرسل، وإن صرف لغيره فهو شرك وتنديد.
ولكن لو سجد أحدهم لأب أو عالم ونحوهما، وقصده التحية والإكرام: فهذه من المحرمات التي دون الشرك ، أما إن قصد الخضوع والقربة والذل له فهذا من الشرك"
“ነገር ግን አንድ ሰው ለአባቱ፣ ለዓሊም ወይም ለመሳሰሉት ሰላምታና ክብር ለመስጠት ሱጁድ ቢያደርግ ይህ ድርጊት ከሽርክ በታች ያለ የተከለከለ ተግባር ነው። ሆኖም፣ አንድ ሰው ሱጁዱን ያደረገው ለዚያ አካል ለመተናነስ፣ ለመቃረብ ወይም ለመገዛት ከሆነ ያኔ ሺርክ ይሆናል።” [ነዋቂዱል ኢማን አልቀውሊየህ ወልዐመሊየህ፡ 278]
ማጠቃለያ፦
የአምልኮትም ይሁን የአክብሮት ሱጂድ የተከለከሉ ናቸው። ይሁን እንጂ የጥፋቱ ደረጃ ይለያያል። የአምልኮት ሲሆን ፍጡርን ማምለክ ስለሆነ ከኢስላም የሚያስወጣ ሺርክ ይሆናል። የአክብሮት ከሆነ ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች (ከባኢር) የሚቆጠር ጥፋት ይሆናል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 14/ 1447)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7948