tgoop.com/IbnuMunewor/7944
Create:
Last Update:
Last Update:
የወሊድ ደም (ኒፋስ)
~
የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ልክ የወር አበባ ላይ እንዳለች ሴት ሶላት አትሰግድም፡፡ ፆም አትፆምም፡፡ ጦዋፍ አታደርግም፡፡ ግንኙነት አይፈቀድም፡፡
1. የወሊድ ደም ዝቅተኛው ጊዜ ስንት ነው?
በአራቱም መዝሀቦች ስምምነት ለዝቅተኛው የወሊድ ደም ቆይታ ገደብ የለውም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም ጊዜ ከአርባ ቀን በፊት ደም ከቆመ እንደማንኛዋም ንፁህ ሴት ነው የምትታየው፡፡ ከአንድ ከሁለት ቀን በኋላ ቢሆን እንኳ፡፡ ስለዚህ አርባ ቀን መጠበቅ የለባትም፡፡ ታጥባ ሶላቷን ትሰግዳለች፡፡
2. ከፍተኛው ጊዜ ስንት ነው?
ከፍተኛው የጊዜ ገደብ አርባ ቀን ነው፡፡ ይሄ ከብዙ ሶሐቦች የተረጋገጠ ሲሆን ቲርሚዚይ - ረሒመሁላህ - ኢጅማዕ አለበት ብለዋል፡፡ ስለዚህ እስከ አርባ ቀን እና ከዚያ በላይ ከቀጠለ ከአርባ ቀን በኋላ ያለው እንደ ወሊድ ደም ሳይሆን ልክ እንደ በሽታ ደም (ኢስቲሓዷህ) ነው የሚቆጠረው፡፡ ስለዚህ ደሙ አልቆመልኝም ብላ ከሶላት ልትዘናጋ አይገባም፡፡ ቀጥታ አርባ ቀን ሲሞላት ታጥባ ሶላቷን ትጀምራለች፡፡
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7944