IBNUMUNEWOR Telegram 7940
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አንዳንድ ነገሮች
~
በሐቅ እና በባጢል መካከል ያለው ግጭትና ፍልሚያ ሁሌም የሚቀጥል ነው። ይህንን በማወቅ ለማንም ወከባና ግርግር ሸብረክ ማለት አይገባም። የባጢል ሰዎች አይነተ ብዙ እና ተለዋዋጭ ናቸው። አንዳንዱ ለነውረኛ ድርጊቱ ጭፍራ ፍለጋ ወደ ብሄሩ ዘሎ ሊወተፍ ይችላል። አንዳንዱ ባህሌ ትውፊቴ ሊል ይችላል። ሌላው የሒክማና methodologyን ጉዳይ ያላግባብ እየሰነቀረ ለአጥፊዎቹ ሽፋን የሚሰጥ ነው። አጥፊዎች ላይ የዶለዶመ ብእሩ "ለምን?" የሚሉት ላይ እሳት ሊተፋ ይነሳል። ሀይሃት!!

በሰሞኑ የዘፈንና የመውሊድ ጉዳይ ከቁራአት ሰፈር የሌሉ አርቲስቱም፣ ጠበቃውም፣ ባንከሩም፣ ደላላውም፣ ፖለቲከኛውም፣ ... ናቸው ግንባር ፈጥረው የተነሱት። በተግባር የማውቃቸውን እየተከታተልኩ ስለነበር ነው ይህን የምለው። የድፍረታቸው ድፍረት አንዳንድ ሰለምቴ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ቢድዐን በማውገዛቸው የተነሳ ሊያሸማቅቋቸው ሲሞክሩ ነበር። እንደነሱ በቢድዐ ካልሻገቱ፣ እንደነሱ ቆሞ ቀር ካልሆኑ በቃ ባይሰልሙ ይሻላል ማለት ነው። እዚህ ድረስ ነው የደረሱት።

በነገራችን ላይ "ሙፍቲውን" ከሳመችው ሴት ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥፋት የሰውየው ነው። ጥፋቱን ማረም የነበረበት እሱ ነበር። የወሎ ባህል ስትሉ የነበራችሁ ደግሞ ከየት ሃገር ነው የመጣችሁት? የራሳችሁ ሌላ ወሎ አላችሁ'ንዴ? ማንን ለመሸወድ ነው በዚህ መጠን የምታምታቱት? ለማንኛውም ወሎ ውስጥ #ለአቅመ_ሄዋን_የደረሱ_ሴቶች #ሸይኾችን ይስማሉ ማለት ከእውነት የራቀ ብቻ አይደለም። መሻይኾቹንም፣ የወሎ ሴቶችንም፣ ባህሉንም መስደብ ነው ቢገባችሁ። ሸይኽነት ደረጃ ደርሰው የተማሩት ኢስላም አጅነቢያ መንካት እንደማይፈቅድ አያውቁም እያላችሁ ነው ያላችሁት። አጉል ውግንና ይህንን ነው የሚያመጣው። አላዋቂ ሳሚ ንፍ - ጥ ይለቀልቃል። እንኳን ሸይኾች ጀማሪ ደረሶችም ይህን አያደርጉም። ሴቶቹም ሸይኾችን እስከ መሳም የሚያደርስ ድፍረት የላቸውም። ለምን ይዋሻል?! ነውር አይደለም ወይ? ደግሞስ አይደለም እንጂ የወሎ ባህልስ ቢሆን የምንጨነቅ ይመስላችኋል'ንዴ? ኢስላም በርካታ የዐረብ ልማዶችን አጥፍቷል'ኮ። የማንም ባህል ከኢስላም በታች ነው። ተቃርኖ ከኖረው ይጣላል።

"አማራ እንደሆንኩ ... " የሚለው የሴትዮዋ ንግግርም ህሊና ቢኖር ነውረኛ አካሄድ ነው። እዚያ ሰፈር ያሉ ነሷራዎችን ለመቀስቀስ ከሆነ ሰርቶላታል። ብዙዎቹ ሲያራግቡ የነበሩት እነሱ ናቸው። ከዚያ ውጭ የአማራ ሴቶች እና ቄሶች ዘንድ ካልሆነ በስተቀር የአማራ ክልል ሸይኾች እና ሴቶች እንዲህ አይነት ልማድ የላቸውም። ነው ወይስ ፉቅራ እና ሸይኽ አትለዩም?

አንዱ የከሰረ የዘር ፖለቲከኛ ደግሞ "የአረብ አሮጌ ጀለቢያ ለቃቅመህ መጥተህ ... " እያለ ለቅልቆ አይቻለሁ። ሰው እንዴት ሸብቶም ጧት ማታ የሚፅፈው ሃሳብ ከህፃን የባሰ ይሆናል? ይሄ የሽማግሌ ነው ^ ረኛ ከጥንት ጀምሮ የሃገራችን መሻይኽ ጀለቢያ እንደሚለብሱ አያውቅም። ለዚያ ነው በማይገናኝ ጉዳይ የጀለቢያ ጥላቻውን ያቀረ ሸው። ውሎው ይሆናል በዚህ መጠን ያደነ ^ ቆረው። ቢገባው ቄሶቹ የሚለብሱት ቀሚስ'ኮ ራሱ ጀለቢያ ነው። እነሱ ላይ ግን ይህንን ል ቅ አፉን አይከፍትም። ጥላቻቸው ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ያነጣጠረ ነው። ደግሞም ባህሉ እንዲከበር የሚሻ አካል የሌላ ባህል አይሳደብም። የሌላውን እያጣጣልክ ያንተ የሚከበር ይመስልሃል'ንዴ? በተረፈ የምትለብሰው ሱሪም የፈረንጅ ባህል ነው። ለምን ወደ ጥብቆ ቁምጣህ ወይም ወደ ተነፋነፍ ሱሪህ አትመለስም? አንዳንዶቹ ለዐረብ ያላቸው ጥላቻ ማሰብ እስከማይችሉ ነው የሚያሰክራቸው። ኧረ ለማሰብ ሞክሩ! ምንድነው እንደዚህ ድንቁ ^ ርናችንን ካልተቀበላችሁ ብሎ መረባረብ?!
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

tgoop.com/IbnuMunewor/7940
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7940

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

According to media reports, the privacy watchdog was considering “blacklisting” some online platforms that have repeatedly posted doxxing information, with sources saying most messages were shared on Telegram. Unlimited number of subscribers per channel ‘Ban’ on Telegram On June 7, Perekopsky met with Brazilian President Jair Bolsonaro, an avid user of the platform. According to the firm's VP, the main subject of the meeting was "freedom of expression." Ng Man-ho, a 27-year-old computer technician, was convicted last month of seven counts of incitement charges after he made use of the 100,000-member Chinese-language channel that he runs and manages to post "seditious messages," which had been shut down since August 2020.
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American