tgoop.com/IbnuMunewor/7955
Last Update:
"أَنَّ امْرَأَةً كَانَ فِي عَقْلِهَا شَيْءٌ ، فَقَالَتْ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ لِي إِلَيْكَ حَاجَةً؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: (يَا أُمَّ فُلَانٍ، خُذِي أَيَّ الطُّرُقِ شِئْتِ، فَقُومِي فِيهِ حَتَّى أَقُومَ مَعَك) فَخَلَا مَعَهَا رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يُنَاجِيهَا، حَتَّى قَضَتْ حَاجَتَهَا"
"አንዲት አእምሮዋ ትንሽ ችግር ያለባት ሴት 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ካንተ ጉዳይ አለኝ' አለች። የአላህ መልእክተኛም ﷺ 'የእከሌ እናት ሆይ! የፈለግሽውን መንገድ ይዘሽ ተነሽ አብሬሽ እቆማለሁ' አሏት። ከዚያም ጉዳዩዋን እስከምታጠናቅቅ ድረስ ከሷ ጋር ገለል ብለው አወያዩዋት።" [ሶሒሕ ኢብኒ ሒባን፡ 4527]
ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“በጥቅሉ ነብዩ (አጅነቢያ) ሴትን በእጃቸው እንደጨበጡ የሚያመላክት ጭራሽ አንድ እንኳን ትክክለኛ ማስረጃ አልመጣም፡፡ እንዲሁ ሲገናኙ መጨባበጥ ቀርቶ በቃል ኪዳን ጊዜ እንኳን አላደረጉትም፡፡ ነብዩ ከሴት ጋር ከመጨባበጥ የራቁ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ግልፅ መልእክት ያላቸውን ሐዲሶች ትተው መጨባበጡ ያልተገለፀበትን የኡሙ ዐጢያን ሐዲስ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ በእውነት ሙኽሊስ ከሆነ ሙእሚን የሚመነጭ አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ ያልተፈቀደችለትን በሚጨብጥ ሰው ላይ ከባድ ዛቻ ከመምጣቱ ጋር፡፡” [አሶሒሓህ፡ 2/28]
* ንክኪው በልብስ ወይም በጓንት ቢሆንስ? ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ፡ "አንድ ሰው ሴትን በሰላምታ መጨበጥ ይችላልን?" ተብለው ሲጠየቁ፡
لا وشدد فيه جداً، قلت يصافحها بثوبه. قال: لا
"አይሆንም" ብለው በጣም የከረረ ምላሽ ሰጥተዋል። ጠያቂው "በልብሱስ ቢጨብጣት?" ሲላቸው "አይቻልም" ብለዋል። [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 2/257]
ወደ ጥፋት አሻጋሪ መንገዶችን መዝጋት (ሰደ ዘሪ0ህ) ዋጋ ያለው የሸሪዐ መርህ መሆኑም ይሰመርበት።
አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
#ማሳሰቢያ:-
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት ክልከላው ወንዱ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ሴቷንም እኩል የሚመለከት ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 15/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7955