tgoop.com/IbnuMunewor/7947
Last Update:
ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ
~
ሱጁድ (ግንባርን መሬት ላይ ማሳረፍ) ለሁለት ይከፈላል። ንፁህ አምልኮታዊ ሱጁድ እና የሰላምታ (የአክብሮት) ሱጁድ።
1- አምልኮታዊ ሱጁድ:-
የአላህ ብቻ ሐቅ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا
"ለአላህም ስገዱ፣ ተገዙትም።" [ነጅም፡ 62]
በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፦
{لَا تَسۡجُدُوا۟ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِی خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِیَّاهُ تَعۡبُدُونَ}
"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ። ይልቁንም እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ሆናችሁ ለእዚያ ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ።" [ፉሲለት፡ 37]
2- የሰላምታ ሱጁድ:-
ይህንንም ቢሆን ለፍጡር መስጠት እንደማይቻል የሚያሳይ ሐዲሥ አለ። ከመሆኑም ጋር ከፊል ሱፍዮች ለሸይኾቻቸው ሲፈፅሙት ይታያል። በርግጥ ቀደሞ የተፈቀደ ነበር። ለዚህም ማስረጃውም የላቀው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው:-
{ وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰۤىِٕكَةِ ٱسۡجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوۤا۟}
''ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ።" [አልኢስራእ፡ 61]
እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሱጁድ አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። ይሄ ሱጁድ የአምልኮት ሱጁድ እንዳልሆነ ኢጅማዕ አለበት። [አሕካሙል ቁርኣን፣ ኢብኑል ዐረቢ፡ 1/127] [አልፈስል፣ ኢብኑ ሐዝም፡ 2/129]
የዩሱፍ ታሪክ ላይ የተጠቀሰው የነብዩላህ ዩሱፍ ወላጆች ለዩሱፍ የወረዱት ሱጁድም ይሄው አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{إِذۡ قَالَ یُوسُفُ لِأَبِیهِ یَـٰۤأَبَتِ إِنِّی رَأَیۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبࣰا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَیۡتُهُمۡ لِی سَـٰجِدِینَ}
"ዩሱፍ ለአባቱ፡- 'አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም (በህልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው' ባለ ጊዜ (አስታውስ)።" [ዩሱፍ፡ 4]
ከዘመናት በኋላ ይህ ህልማቸው እውን እንደሆነ ሲገልፅ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦
{وَرَفَعَ أَبَوَیۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدࣰاۖ وَقَالَ یَـٰۤأَبَتِ هَـٰذَا تَأۡوِیلُ رُءۡیَـٰیَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّی حَقࣰّاۖ}
"ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው። ለእርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። 'አባቴ ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው። ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት።' " [ዩሱፍ፡ 100]
ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ ሰሞኑን እነዚህን አንቀፆች መነሻ በማድረግ ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ ይቻላል እያለ የፃፈ ስላየሁ ነው። የሚገርመው ሰዎች ከስር በኮመንት እየገቡ እናንተ አዋቂዎቹ ዝም ብላችሁ ነው የማንም መጫወቻ የምታደርጉት እያሉት ነበር። እንዲህ አይነት ችግር ነው የገጠመን። ቁንፅል ነገር ይይዙና መረጃዎችን በቅጡ ሳይፈትሹ፣ የዑለማእ ንግግሮችን ሳያገላብጡ አሳሳች መልእክት ያስተላልፋሉ። የራሳቸው ጥፋት አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ያሳስታሉ። አቀራረቡ ራስን መኮፈስ፣ ሌሎችን መናቅ ሲታከልበት ደግሞ ጥፋቱ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ቢገባቸው ይሄ አካሄድ በራሳቸውም ጥፋት፣ በሚያሳስቷቸው ሰዎችም ወንጀል እጥፍ ድርብ ተጠያቂነትን ነው የሚያስከትልባቸው።
ለማንኛውም በቀደምት ሸሪዐዎች የተፈቀደ የነበረው የሰላምታ ሱጁድ በነብዩ መሐመድ ﷺ ሸሪዐ ተሽሯል። ስለዚህ ምንም የማያጠራጥር ሐራም ነው ማለት ነው። ይህንን የሚጠቁመን ተከታዩ ዐብዱላህ ብኑ አቢ አውፋ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው።
ሙዓዝ (ብኑ ጀበል ረዲየላሁ ዐንሁ) ከሻም ሲመለሱ ጊዜ ለነብዩ ﷺ ሱጁድ ወረዱ።
"ምንድነው ይሄ ሙዓዝ?" አሉ።
ሙዓዝም፡ "ሻም በሄድኩኝ ጊዜ (ክርስቲያኖች) ለጳጳሶቻቸውና ለፓትሪያርኮቻቸው ሱጁድ ሲወርዱ አገኘኋቸው። እናም ይህንን ላንተ ልፈፅመው በነፍሴ ወደድኩኝ" አሉ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦
فَلَا تَفْعَلُوا، فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ، لَأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا ...
"እንዲህ አታድርጉ። ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ እንዲወርድ አንድንም የማዝዝ ቢሆን ኖሮ ሴት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ አዝ ነበር። ... " [ኢብኑ ማጀህ፡ 1853]
ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - "ሐሰኑን ሶሒሕ" በማለት ለማስረጃነት የሚያበቃው ጥንካሬ እንዳለው ገልፀዋል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1515]
ብዥታ የሚያነሳ ሰው እንዳይኖር የዑለማኦችን ንግግር ላስከትል:-
1- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
وَأَجْمَعَ الْمُسْلِمُونَ عَلَى: أَنَّ السُّجُودَ لِغَيْرِ اللَّهِ مُحَرَّمٌ
"ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ መውረድ የተከለከለ እንደሆነ ሙስሊሞች ወጥ ስምምነት አድርገዋል።" [አልመጅሙዕ፡ 4/358]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
فإن نصوص السنة، وإجماع الأمة: تُحرِّم السجودَ لغير الله في شريعتنا، تحيةً أو عبادةً، كنهيه لمعاذ بن جبل أن يسجد لما قدمَ من الشام وسجدَ له سجود تحية
"የሱና መረጃዎችና የህዝበ ሙስሊሙ ወጥ ስምምነት በሸሪዐችን ውስጥ ሱጁድን ከአላህ ውጭ ለሌላ አካል ማድረግን ይከለክላሉ። ሱጁዱ ለሰላምታ (ለማክበር) ይሁን ወይም ለአምልኮም ይሁን ምንም ለውጥ የለውም። ልክ ሙዓዝ ብኑ ጀበል ከሻም ሲመጡ የደረጉትን ሱጁድ እንደከለከሏቸው። (ሙዓዝ) ያደረጉት ሱጁድ የሰላምታ ሱጁድ ነበር።" [ጃሚዑል መሳኢል፡ 1/25]
2- ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል፦
"وَهَذَا السُّجُودُ الْمَنْهِيُّ عَنْهُ : قَدِ اتَّخَذَهُ جُهَّالُ الْمُتَصَوِّفَةِ عَادَةً فِي سَمَاعِهِمْ، وَعِنْدَ دُخُولِهِمْ عَلَى مَشَايِخِهِمْ وَاسْتِغْفَارِهِمْ ، فَيُرَى الْوَاحِدُ مِنْهُمْ إِذَا أَخَذَهُ الْحَالُ ـ بِزَعْمِهِ ـ يَسْجُدُ لِلْأَقْدَامِ ، لِجَهْلِهِ ؛ سَوَاءٌ أَكَانَ لِلْقِبْلَةِ أَمْ غَيْرِهَا ، جَهَالَةً مِنْهُ ، ضَلَّ سَعْيُهُمْ وَخَابَ عَمَلُهُمْ"
"ይህ የተከለከለው ሱጁድ አላዋቂ ሱፊያዎች በዜማቸው ላይ፣ ሸይኾቻቸው ዘንድ ሲገቡ እና ምህረትን ሲለምኑ ልማድ አድርገው ይዘውታል።
ከእነሱ ውስጥ አንዱ - እንደሚሞግቱት - 'ሐሉ' ሲነሳበት ጊዜ በእግራቸው ላይ ሲወድቅ ይታያል። ይህን የሚያደርገው ባለማወቁ ነው። ወደ ቂብላ ቢዞርም ባይዞርም ያደርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከእውቀት ማነስ የተነሳ ነው። ጥረታቸው ሁሉ ጠፋ፤ ስራቸውም ከሰረ።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 1/294]
ሰሞኑን ለ "ሙፍቲው" የተወረደውን ሱጁድ እዚህ ላይ እናገኘዋለን።
3- ኢብኑ ከሢር እንዲህ ብለዋል፦
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7947