Telegram Web
🎖#ሊሰርቀን_መጥቶ_ነበር_እኛ_ሰረቅነዉ🎖
                  ✍🏼አሚር ሰይድ


    ማሊክ ኢብኑ ዲናር ከሱሀባ በኋላ የነበሩ ታቢዒይ ናቸው፡፡  ከነብዩ ﷺሱሀባ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እውቀትን ቀስመዋል ከሌሎች ታላላቅ ሱሀቦችና ታብእዮች ተምረዋል ለዚህች ዓለም ትኩረት የማይሰጡ አሊምና ዛሂድ ነበሩ ያገኙትን ነገር ለአኼራ እንጂ ለነገየ አይሉም ነበር፡፡

   ባንድ ወቅት አንድ ሌባ ለስርቆት እቤታቸው ገባ ቢፈልግ ቢፈልግ  የሚሰረቅ እቃ አጥቶ ተስፋ ቆርጦ ሲወጣ አገኙትና የሚሠረቅ እቃ አጣህ አይደል?? ብለው ጠየቁት
..... አዎ ሲል መለሰ
......ዱንያ ብታጣ አኼራ አትፈልግም እንዴ??ሲሉ ጠየቁት
.....ሌባዉ እፈልጋለሁ አላቸዉ ፡፡አኼራማ ከፈለክ መርሀባ ብለዉ ዱአ አድርገው ወደ መስጂድ ወሰዱት፡፡በሌብነቱ የሚያውቁት ሰዎች አዩት የሚያቁት ታዋቂ ሌባ እንደሆነ ነዉ ግራ ገባቸዉና ...ይሄ ሌባ የመጣዉ ለምንድ ነው??አሰቸገረሁ ሰረቀሁ እንዴ ብሎ ሰዉ ሲጠይቃቸዉ....  እሳቸውም #ሊሰርቀን_መጥቶ_ነበር እኛ ስረቅነው አሏቸው...ሱብሀነሏህ


    ማሊክ ኢብኑዲናር አላህን ይፈሩና ያለቅሱ ነበር በተለይ ቀብር ሲያዩና ቁርአን ሲቀሩ እምባቸዉ ወርዶ አያቆምም ነበር፡፡

ሀሪስ ኢብኑ ሰኢድ ባስተላለፉት :-አንድ ቀን ማሊክ ኢብኑ ዲናር ጋር ቁጭ ባልንበት ወቅት ቁርአን የሚቀራ ሰው ነበር እና ኢዛዙል ዚለቲል አርዱ ዚልዛ ለሀ የሚለውን አያ ላይ ሲደርስ በድንጋጤ ተውጠው እያለቀሱ ሳለ «ፈመን የእመል ሚስቃለ ዘረቲን ኸይረን የራ ወመን የእመል ሚስቃለ ዘረቲን ሸረን የራ (የብናኝ ክብደት ያክል መልካም ስራን የሰራ የሥራውን ዋጋ ያገኛል፤የብናኝ ክብደት ያክል መጥፎ ስራ የ ሥራውን ዋጋ ያገኛል ) እሚለው ላይ ሲደርሱ ራሳቸውን ሳቱ ሰዎች ሲሸከሟቸው አያውቁም ነበር፡፡ ቁርአን የዚህን ያህል ተፅእኖ ያሳድርባቸው ነበር፡፡

✨✨ ማሊክ ኢብኑ ዲናር ወደ መቃብር ሄደው ሰው ሲቀበር ካዩ እኔም ነገ እንዲህነኝ በማለት ራሳቸውን በመሳት እግራቸው መቆም አይችልም ነበር እናም ቁጭ ብለው ያለቅሱ😢 ነበር፡:

ማንኛዉም ሰው ቢገላምጣቸውና ቢሰድባቸው ቅር ከመሰኘት ይልቅ እንዳውም በስራዬ ነው የተሰደብኩት በማለት ያለቅሱ ነበር ፡፡ባንድ ወቅት አንዲት ሴት ማንነታቸውን ሳታውቅ ያስቀየማት ሰው ነበርና ያሰው መስለዋት አንተ ሲያዩህ ትልቅ ሰው ትመስላለህ እያለች ስታመናጭቃቸው ስትሰድባቸዉ “እውነትሽን ነው ትልቅ ሰው እመስላለሁ እሰው ዘንድ ትልቅ ተብዬ አላህ ዘንድ ትንሽ ሆኜ እገኝ እሆን ?ዋ የኔ ነገር በማለት ያለቅሱ ነበር::


🌙 ማሊክ ኢብኑ ዲናር እንዲህ የአላህን ፍራቻ የተላበሱት በተዉበት ምክንያት ነዉ፡፡የእሳቸዉ መቶበት ታሪኩ ረጅም ቢሆንም በአጭሩ በፊት መጠጥ የሚጠጡ ለመጠጥ ያላቸዉ ፍቅር የተለየ ነበር ...የሚወዷት ህፃን ልጅ በተደጋጋሚ አባቴ መጠጥ አትጠጣ ትላቸዉ ነበር ፡ አጀሏ ደረሰና ህፃኒቱ ልጅ ሞተች አዘኑ ተከዙ ...የሚወዷትን ልጅ በማጣት በበስጭት የብስ መጠጥ ጠጭ ሆኑ፡፡ አንድ ቀን ተኝተዉ መጥፎ አስፈሪ ህልም ያያሉ....የሞተችዉ ልጃቸዉ በዛ አስፈሪ ህልም መሀል መጥታ መጠጥ የምትጠጣበት ወንጀልህ ነዉ ቶብት ብላ መክራቸዉ ከህልማቸዉ ይነቃሉ፡፡

ጥርት ያለ ተዉበት ቶብተዉ መጠጥ መጠጣታቸዉን አቁመዉ ወደ አላህ ተመለሱ ለአለፈዉ ወንጀላቸዉን መሀርታ እየጠየቁ...ለሰዎችም ሞዴል መሆን ቻሉ፡፡


🔰🔰 የእኛ መሀበረሰብ ተዉበትን ከባድ ቀጥ ያለ ተራራ አድርጎ ይመለከተዋል...ግን ቀላል አላህ እጁን ዘርግቶ መቼ ይሆን ወደኔ የምመጡት እያለ እየጠበቀን እንደሆነ ዘንግተናል፡፡ የማሊክ ኢብኑ ዲናን ቁርጠኝነትና እቤታቸዉ ሊሰርቃቸዉ የመጣዉ ሌባ አስቶብተዉት ወደ መስጊድ ሲሄድ በፊት እኔ ሌባ ነበርኩ ሰዉ ምን ይለኛል?አላለም...ለምን የቶበተዉ ሌባ አኼራ ነበር ፍላጎቱ ለሰዉ ወሬ ደንታ አልነበረዉም፡፡ እኛም ትላንት እንዲህ ነበርኩ ዛሬ እንደዚህ ስሆን  ሰዉ ምን ይለኛል?ብለን ማንሰብ መተዉ አለብን...ሰዉ ወደ አላህ ብትመለስም ባትመለስም ማማቱ አይቀርም...ከስም አጥፊዎች ምላስ ማምለጥ አይቻልም ለምን ስራቸዉ ስም ማጥፋት ነዉና..

የተዉበት መጀመሪያዉ የተበላሸ ቀልብን ማከም ነዉ


🟢 ሀቢቡና ሙሀመድ  እንዲህ ብለዋል «ይህች ቀልብ አቅማዳ ናት፥ አንደኛዋ ከሌላኛው የበለጠ የመያዝ  የማጠራቀም አቅም አላት፤ አላህ (ሹ.ወ) ደግሞ ለቀልበ ዝንጉ ባሪያ ዱዓ ምላሽ አይሰጥም፡፡»ብለዋል
ቀልባችን ከዝንጉነት ከችለተኝነት ከክፋት ከሂስድ መጀመሪያ በሶለዋት በዚክር በፈርድ በሱና ሶላት እናፅዳት ወገን....ይህ አካሄድ የተዉበት ወሳኙ ክፍል ነዉ




ተዉበት የቆሸሸን ልብ ለማጥራት መታገል ነዉ...ከዛም ያን ትግል ንፁህ እስኪሆን ድረስ መዘዉተር ነዉ....ግን ለተዉበት ምላስ ሳይሆን የተግባር እርምጃ ግዴታ ወሳኝ ነዉ...ግዴታዉ ደግሞ ቀላል ነዉ ጀሀነምን አስታዉሶ ከዛ ወንጀል ለመራቅ አንድ ብሎ መጀመር ነዉ

#ለምሳሌ

⛔️ ነገ የዚና ቀጠሮ ይዘሽ ከሆነ ...ወይም ህይወትሽ የዚና ህይወት ሁኖ ከተቸገርሽ አንዴ ቀይ የደም ሴሌ ሂዷል ብለሽ ተስፋ ቆርጠሽ ዚና ላይ ካለሽ ....ለቀጠሮዉ ነገ አለመሄድ የበፊቱን አላህን ማረኝ ብሎ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ዚና አለመሄድ ነዉ፡፡ቀይ የደም ሴሌ በሀራም ሂዷል ቶብቻለሁ ወደ አንተ መጥቻለሁ አጥራኝ የሚረዳኝ የሚያስብልኝ የትዳር አጋር ስጠኝ ብሎ ዱአ ማድረግ ነዉ፡፡ አትጠራጠሪ ሶብሪ ዉጤቱ ያምራል

⛔️ የማያገባሽን አጂ ነብይ በሚዲያ እያወራሽ ነዉ እንደማያገባሽ ልብሽ ያቃል....ስትገናኙ ሸይጧን አዉቆ ዚና አልሰራሽ ብትሳሳሙ አብራችሁ ካፌ ብትሆኑ ችግር የለዉም ሊልሽ ይችላል ዚና ሊያሰራሽ...አንቺም በሸይጧን መስመር እየተገናኛችሁ ቀላል ነዉ በሚባል መሳሳም መነካካት ላይ ደርሰሽ ይሆናል፡፡
በቃ ወሬ ወይም መሳሳም ቱብቱ ኢለሏህ ያለፈዉንም ማረኝ  ብለሽ በቤተሰብ በበር የመጣልሽን ባል ቤተሰቦችሽ መርቀዉሽ መርሀባ ብለሽ ማግባት ነዉ፡፡ካልመጣም ዱአ አድርጊ ሶብሩ ዉጤቱ ያማረ እንደሚሆን በአላህ ተስፋ አርጊ ይሳካልና

⛔️ ልብስሽን እያሳጠርሽ...ፀጉርሽን ገልጠሽ ፈርኖ ዱቄት ተቀብትሽ እየሄድሽ ነዉ አይደል፡፡ አንተም ደግሞ ሱሪህን አስረዝመህ ፀጉርህን አበላልጠህ እየኖርክ ነዉ....እናም ፊእሉን መቀያየር ነዉ
ነብዩ   ያሉት ወንድ የሚለብሰዉን ያሳጥር ሴትም ሁሉ ገላዋ አጂ ነብይ ነዉ ትሸፈን ረጅም ትለበስ ስላሉ...ዘመኑ የምንሰራዉ ነብዩን ለመክለፍ ይመስል ሁኗል፡፡ እናም በዘመኑ ተገልባጭ ወንድ ማሳጠር ሴት ረዥም መልበስ...ምናምንቴ የምትቀቢዉንም በዚክር በሰለዋት በማብዛት በኑር ፊትሽን አድምቂዉ፡፡ፀጉርሽን ገልጠሽ የምትሄጂም አኡዙቢላህና  እኛን ወንዶችንም አሳስተሽ ☺️ፀጉር መኖርሽን አይተነዋል ለወደፊት ሸፍኝም 70,000 መላኢካ እርግማን ተረግመሽ የት ለመድረስ የት ለመግባት ነዉ? በተዉበት ዛሬዉኑ ወደ አላህ መሾመር መግባት ነዉ፡፡ ነገ የእኛ ቀን አይደለምና ላንደረስበት እንችላለን...ነገ ጀናዛ ልንባል እንችላለን ወገን👇👇👇
⛔️ አረብ ሀገር፡ ዩኒቨርስቲ ፡ከክፍለሀገር ወጥቼ የተሻለ ከተማ ላይ ነዉ ያለሁት ማንም አያየኝ ብለሽ(ህ)ወንጀል የምትሰሩ ሆይ!!! ትክክል ናችሁ ወንድም እህት አባት እናት ዘመድ ጎረቤት አያያችሁም ግን አሏህ ያያችሆል...በዚና በሀራም ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የክፍለ ሀገር ልጆች፡ የአገረብ አገር የምትኖሩ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ አሏህ ተመለሱ....ሞት አማክሮ አይመጣምና፡፡አረብ አገር ያለሽ እህቴ አንዳንዶች በዚና ህይወት ላይ ሁነዉ ብር የሚሰበስቡ እንዳሉ እየሰማን ነዉ ግን እስከ መቼ አስበሽዋል??

☞ አረብ ሀገር ነን እድሜያችን ሄደ ትዳር እንዳያልፈን እያላችሁ በማህበራዊ ሚዲያ ከምታቁትም ከማታቁትም ወንድ ጋር በሚዲያ እያሳለፋችሁ ወንጀል እየሰራችሁ ነዉ ራሳችሁን ፈትሹ....በተዉበት ዛሬዉኑ ወደ አላህ እንመለስ ፡፡ ነገ የእኛ ቀን አይደለምና ላንደረስበት እንችላለን...ነገ ጀናዛ ልንባል እንችላለን እና

⛔️ የሰዉ ሀቅ ይዘሀል(ይዘሻል) በቃ የእናንተ አይደለም መልስ ለባለሀቁ አስደስቱት አለቀ ጉዳዩ ይህ ነዉ ወደ አላህ መመለስ

⛔️ ሶላት በተለያየ ምክንያት አቁማችሁ ይሆናል፡፡ወይም ጊዜዉን እያሳለፍን ይሆናል...ወንድሜ ሆይ በጫት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ሁነህ ጀመአ እያለፈህ ነዉ አይደል ባይሆን ያለፈህ ትናንት ነዉ..,ተዉበት ማለት ከዛሬ ጀምሬ በጀመአ ልሰግድ ብሎ ነይቶ ወደ መስጊድ መንቀሳቀስ ነዉ

⛔️ መጥፎ ጓደኛ አለችሽ አይደል...አላህ የምትቀሰቀሱት የምትወዱት ጋር ነዉ ብለዉናል፡፡ መጀመሪያ ራስሽ ቶብች ወደ አላህ ተመለሽ ...ወደ አላህ ከተመለሽ ቡሀላ ታገይ እሳ እንድትመለስ ድከሚ ጣሪ አብሮ ጀነት ለመግባት...ታገልሽ ካልተሳካልሽ ለተዉበትሽ አደጋ ከሆነች ነገ የዉመል ቂያማ እናት አባት እህት ወንድም የሚፈራራበት ጊዜ ነዉ ነፍሲ ነፍሲ ስለሆነ እነዚህ ቤተሰቦችሽ ለአኼራ ስለማይጠቅሙሽ ከአቅም በላይ ከሆነ ነፍሲ ነፍሲ ብለሽ ራቂያት...አንተም ቢሆን ራቀዉ፡፡እርቃችሁ አላህ ቀልባቸዉን እንዲያስተካክላቸዉ ዱአ አርጉላቸዉ

⛔️ ቤተሰብ ጋር ሆድና ጀርባ ከሆናችሁ፡፡ ዛሬዉኑ እናቴ አባቴ አዉፍ በለኝ ማለት ነዉ፡፡ ነገሮች የተወሳሰቡት አልሳኩ ያሉን በወላጆችን ቀልብ ሊሆን ስለሚችል፡፡ በድለናቸዉ አዉፍ ሳይሉን ሙተዉ ከሆነ ጀነት እንዲወፍቃቸዉ ዱአ ማድረግ ለእነሱ ነይቶ ሰደቃ መስጠት ዚክር ማድረግ...ይሄ ለራሱ የተዉበት ክፍል ነዉ




✏️✏️ አሏህ እኮ ተዉበት እስከምናደርግ እየጠበቀን ነዉ ...,እሱ እንደወነጀላችሁኝ አቃለሁ ሳትሞቱ ተመለሱ ልማራችሁ እያለን እኛ እንቢ ማለት ከቶ የት ለመድረስ ነዉ??የሰዉ ህይወት ታሪክ ሲነበብ ተወለደ ተብሎ ብዙ ከተነገረ ቡሀላ የታሪኩ ማብቂያ ሞተ ተብሎ ነዉ የሚዘጋዉ ወገን

አሏህ ለእኛ ለባሪያዎቹ እንዲህ ብሎናል፡- እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአሏህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አሏህ ሀጢያቶችን በሙሉ ይምራልና፡፡ " ዙመር 53።



📚📚 ዕውቁ የኢስላም ምሁር ሐሰን አል-በስሪ አንድ ጊዜ ጥያቄ ተጠየቁ፡-

“ሰውየው ወንጀልን ይሰራል ከዚያም ተውበት ያደርጋል፤ ነገር ግን ድጋሜ ይመለሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ እስከ መቼ ይቀጥላል?” በማለት ጠየቋቸው፡፡

“እሳቸውም ሸይጧን ከእሱ እስኪሰለች'' ድረስ በማለት መለሱ፡፡

ኢንሻ አላህ ከሚያበላን ከሚያጠጣን ከብዙ ሀዘን ጭንቀት ያወጣን...ዛሬስ ይሄን ፈተና አናልፈዉም ብለን እንድናልፍ ካረገን...ጌታ አሏህ ተስፋ አንቆርጥም የሸይጧንን ወስዋስ  እናሰለቸዋወን ኢንሻ አላህ

☑️ እህት ወንድሞቼ ለተዉበት ተዘጋጀን ወይ??እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ ዛሬ ብንሞት ነገ ጀናዛ ተብለን ተሰግዶብን ቀብር ብንገባ ዛሬ ያለንበት ህይወት ለቀብር ህይወታችን ዋስትና ጀነት ለመግባት የሚያበቃ ኸይር ስራ አለን ወይ??ነገ ቀብር ነን እንበል በተዉበት ወደ እሱ ተመልሰን ነዉ ወይ የምንገናኘዉ ወይስ እስከ ወንጀላችን??

አሏህ በቁርአኑ እንዳለን ቀብር የገቡት በህይወት ብትመልሰን ኑሮ ኸይር ስራ እንሰራ ነበር እንደሚሉት ባሪያዎች ነን ወይ??
ነብዩ  አንድ ሰዉ ሲሞት ኸይርም ሸርም የሰራ  ይቆጫል ሲሉ...እንዴት ሲሏቸዉ ኸይር የሰራዉም
ምነዉ ጨምሬበት በነበር ሲል...ወንጀል የሰራዉም ምነዉ ቶብቼ ኸይር ሰርቼ በነበር ነዉ ቁጭቱ ብለዉናል፡፡
እና እኛ ነገ ከመቆጨት ነገ ከቀብር ጨለማ ምን አለን??ኸይር ስራ ብቻ ሚዛን የሚደፋበት የሚያዋጣበት አኼራን አንዘንጋ፡፡

የእኛ ዉሳኔ ተዉበታችን አላህ ከተቀበለን ቀልባችን ከጠራ ማሊክ ኢብኑ ዲናር አይነት የአላህን ፍራቻ አላህ ቀልባችን ላይ ሊያትምልን ይችላልና ....አይዞን ወደ ቀኝም ወደ ግራም ወደፊትም ወደሆላ ስንዞር ተዉበት ለማድረግ  መሰናክሉ ብዙ ነዉ በአራቱም አቅጣጫ በጣጥሰን ወደ አላህ ተመልሰን የአላህን ፍቅር ዉዴታ እናገኛለን...,አይዞን አይዞን አይዞን

ነገ ጀነች ለመግባት ለተዉበት ዝግጁ ነን❔❔❓


━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎖 #አንተ_ተስፋ_ከቆረክ_እኔ_ምን_ላድርግህ?🎖
                 âœđŸźáŠ áˆšáˆ­ ሰይድ

    ሰይዲና ሀቢቡና  ሙሀመድ  አንድ የታመመን ሰው ሊጠይቁ ሄዱ
.....የታመመወን ሰዉ በመታመምህ ቅር ሊልህ እናልታዝን አይገባም ምን አልባት ባጠፋኸው ጥፋት ለሰራሀው ወንጀል መማሪያ ይሆናሀልና ሲሉት
...,,ታማሚዉ እሺ አሚን አላህ እንዳሉት ያድርግልኝ ማለት ሲገባው ተስፋ ቆርጦ ስለነበር “በሞት አፋፍ ላይ እኮ ነው ያለሁት ምን እያሉኝ ነው;” በማለት በተስፋ መቁረጥ የታጀበ መልስ ሰጣቸዉ
....ነብዩ ﷺ እኔ ወንጀልህን ምሮ አላህ እንዲያሽርህ እየተመኘሁልህ አንተ ተስፋ ከቆረጥክና በምለው ነገር ካልተስማማህ እማ ያልከውን ነገር አላህ ያድርግልህ አሉት
.....ተማሚወም በዚያቹ ለሊት ሞቶ እንዳደረ ተዘግቧል፡፡
በሶሂህ ቡኻሪ ሀዲስ ቁ.3616 ላይ ተመዝግቧል

   đŸŸ˘ ከዚህ ታሪክ ትምህርት መዉሰድ ያለብን  አላህ የሚያስተናግደን እንደ ኒያችን ነው፡፡
ስለዚህ የታመመ ሰው ምንም እንኳን ስቃዩ ቢበዛበት ህመሙ ቢያሰቃየዉ  አላህ እንዲያሽረው  ዱዓ ማድረግ....በህመሙ ምክንያት አላህ ወንጀሉን እንዲምረዉ ዱአ ማድረግ  እንጅ ተስፋ መቁረጥ የለበትም።  ወዳጅ ዘመድም ዱአ ካደረገለት ዱአውን ሲያንቅ  ከልብ መቀበል ይኖርበታል፡፡
በተጨማሪ በዱንያ በተደራራቢ የሚመጡ ችግሮች ሙሲባዎች ላይ ተስፋ መቆረጥ አያስፈልግም አላህን ጠበቅ አድርጎ ይዞ ነገ ለኸይር ነዉና መታገል መታገል መታገል ዱአ ላይ መበርታት ነዉ መፍትሄዉ....አይዞን እስኪያልፍ ዱንያ  ነዉና ያለፋል....ከነችግሮቹ ከነጠባሳዉ ኢንሻ አላህ ያልፋል

ከአላህ እዝነት ተስፋ አይቆረጥም👌


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🎖🎖 አንድ ጊዜ ሉቅማን ፍየል አርደው ሁለት ምርጥ ነገሮቿን እንዲያመጡ ተጠየቁ፡ ሎቅማን (ዐ.ሰ) ያረዷትን ፍየል ልብ እና ምላስ ይዘው መጡ፡፡


ከጥቂት ጊዜ ቡሀላ ሌላ ፍየል አረዱና ሁለት መጥፎ ነገሮችን እንዲያመጡ ተጠየቀ
.... ሉቅማን (ዐ.ሰ) ሄዱና አሁንም ልብ እና ምላሷን ይዘው ተመለሱ፡፡ ይህን ያደረጉበትን ምከንያት ሲጠየቁም እንዲህ ብለው መለሱ፡-

ልብና ምላስ ጥሩ ሲሆኑ ከእነዚህ የበለጠ ጥሩ ነገር የለም፡፡ ሲበከሉ ደግሞ ከነዚህ የከፋ መጥፎ ነገር የለም:: አሏቸዉ

ÂŽAmir seid


4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
    #ምንም_ረዳት_የለኝም_ምን_ይሻለኛል??
                   âœđŸźáŠ áˆšáˆ­ ሰይድ


  ማሊክ ኢብኑ አሽጀዒይ የነብዩ  ሶሀባ ሲሆን በአንድ ወቅት እሳቸው ዘንድ መጥቶ አንድ ልጄ ጦርነት በሄደበት ጠላት ማርኮ አስቀረው

  ከዛም ወደ ነብዩ  በመሄድ ምንም ረዳት የለኝም እኔንና እናቱን እሱ ነበር የሚካድመን ምን ይሻለኛል?? ሲላቸው
.....ነብዩ ሙሀመድ ﷺ አላህን ፍራ ታገስ ባለቤትህም አንተም #ላሀውለዉላ_ቁወተኢላቢላህ (ከአላህበስተቀር ኃይልም ብልሀትም የለም) ዚክር በተደጋጋሚ አብዙ ብለዉ መለሱለት

ወደባለቤቱ ዘንድ ተመልሶ ሲሄድ ለባለቤቱም የተባለውን ሲነግራት በዚሁ ተስማምታ እሷም እሱም ቀንም ለይልም በተደጋጋሚ ለሀዉለዉላ ቁወተ ኢሊቢላህ  እያሉ እያለ ልጁ በአላህ እርዳታ  የተሳረበት ከጠበባቂዎች እጅ እንዲያመልጥ አድርጎት ይወጣል፡

መውጣትም ብቻ ሳይሆን ጠላት ከየትም ማርኮ ያከማቸውን በጎችና ግመሎች ይዞ ነበር ያመለጠው፡፡ አንዳንድ ኡለማዎች እንደሚሉት 4000 በጎችና 50 ግመሎች ይዞ ወደቤቱ ሲመጣ አባትየው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ በመሄድ ልጄ በሰላም መጥቶልኛል የጠላትን ብረት ነውና ይዞ የመጣው መጠቀም እንችላለን?? ሲላቸው
.... አዎ ትችላላችሁ ይህ የተቅዋ ውጤት ነው አንተና ባለቤትህ ያደረጋችሁት የተቅዋና የትእግስት ውጤት ነው ሰው ሁሉ እነዚህን ነገሮች አጥብቀው ቢይዙ ኖሮ ይሄ በቂያቸው ነበር።ወዲያውኑ ይሄንን አስመልክቶ የተቅዋና የትእግስት ውጤት መሆኑን የሚገልፅ የቁርአን አያ ወረደ


وَمَن یَتَّقِ ٱللَّهَ یَجۡعَل لَّهُۥ مَخۡرَجࣰا
{ وَیَرۡزُقۡهُ مِنۡ حَیۡثُ لَا یَحۡتَسِبُۚ وَمَن یَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسۡبُهُۥۤۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَـٰلِغُ أَمۡرِهِۦۚ قَدۡ جَعَلَ ٱللَّهُ لِكُلِّ شَیۡءࣲ قَدۡرࣰا }


አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡
ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡[Surah At-Talâq2- 3]


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ያነብየሏህ_ዚና_ሰርቻለሁ_አጥሩኝ😢
              ✍🏼አሚር ሰይድ

  ማኢዝ ወጣት ሰሀባ ነበር...በመዲና አግብቶ ይኖራል:: አንድ ቀን ሸይጧን ወሰወሰዉ እና በአንዲት ልጅ ላይ ለሀራም አነሳሳው፡፡ እሷን ይዟት ከሰዎች ዓይን ተሰወረ ሸይጧን ሶስተኛቸው ነበር ሸይጧን ሀራም ላይ እስኪወድቁ ድረስ አንደኛቸውን ለሌላኛቸው አሳምሮ ከማሳየት አልተወገደም፡፡

ማኢዝ ሀጥያቱን ፈፅሞ በጨረሰ ጊዜ… ሰይጣን ከሱ ገለል አለለት ራሱን ተሳሰበና አለቀሰ😰 ነፍሱን ወቀሳት... የአላህን ቅጣት ፈራ… ህይወቱ ጠበበችበት ወንጀሉ ቀልቡን እስኪያቃጥለው ድረስ ሀጢያቱ ዙሪያውን ከበበው:: የልብ ዶከተር ወደሆኑት ሀቢቡና
ሙሀመድ ﷺ ዘንድ መጣ… ፊት ለፈታቸው ላይ ቆመና ውስጡ ላይ በተፈጠረው ቃጠሎ የተነሳ እንዲህ ሲል ጮኸ
... የአላህ መልእከተኛ ሆይ!!!!ዝሙት ሰርቻለሁና አንፁኝ አላቸው፡፡
.....ረሱል ﷺከእሱ ዘወር አሉ
....… በሌላኛው ጎናቸው  መጥቶ ያረሱለላህ ዝሙት ሰርቻለሁ አጥሩኝ አላቸው::
........ረሱል ﷺ ወዬልህ ተመለስ አላህን ምህረት ጠይቀው ወደ እርሱም ተውበት አድርግ አሉት፡፡ከዛም ሄደ

ማኢዝ ግን የዝሙት ወንጀሉ የአኼራ ቅጣቱ ከእይኑ አልወገድለት ሲል ብዙም ሳይርቅ ተመለሰ፡፡ ወንጀሉን መቋቋም አልቻለም እንደገና ወደ ሀቢቡና  ሙሀመድﷺ
ዘንድ ተመልሶ ያ ረሱሉላህ አጥሩኝ አላቸው
....... ረሱል ﷺ ወዮልህ... ተመለስ አላህን ምህረት ጠይቀው ወደ እሱም ተውበት አድርግ አሉት...

በድጋሜ አሁንም መጣ... ያ ረሱሉላህ ዚና ሰርቻለሁ አጥሩኝ አላቸው
....... ደጋግሞ የጠየቃቸው ጊዜ ረሱል ﷺዘመዶቹን አብደት አለበት እንዴ? ብለው ጠየቋቸው
......ዘመዶቹም ምንም ችግር የለበትም ብለው መለሱ፡፡

ረሱል ﷺ ምናልባት ኸምር ጠጥቶ ይሆን እንዴ?? ብለዉ ጠየቁ
........ አንድ ሰው ተነስቶ አፉን አሸተተው
....... ከእሱ ምንም የኸምር ምልክት አላገኘም… አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ መጠጥ አልጠጣም አላቸዉ
.....ከዚያም ረሱል ﷺ ዚና ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህን??? አሉት
… እሱም፡- አዎ! አንድ ሰው ሚስቱን በሀላል እንደሚያደርገው እኔ ያልተፈቀደችልኝን ሴት በሀራም ግንኙነት አድርጌያለሁኝ አላቸው

    ይህን የምትናገረው ምን ፈልገህ ነው? ብለዉ
ረሱል ﷺ ጠየቁት
....እሱም እንድታጠሩኝ ፈልጌ ነው አለ፡፡
ረሱል ﷺ እሺ አሉትና እንዲወገር አዘዙ፡፡ እስኪሞትም ድረስ ተወገረና ሞተ😔😔



   ✨ ሀቢቡና ሙሀመድ  ከሰገዱበትና ከተቀበረ በኋላ ከተወሰኑ ባልደረቦቻቸው ጋር በእሱ ቦታ ላይ አለፉ…

ከባልደረቦቻቸው ሁለት ሰዎች አንዱ ለሌላኛው "አላህ ሰትሮት ሳለ ውሻ እንደሚወገረው እስኪወገር ድረስ ችክ ያለውን ይህን ሰውየ ተመልከትክ?” ሲለው ሰሙ::
..... ረሱል ﷺዝም አሉ፡፡ ትንሽ ከተጓዙ በኋላ በአህያ ጥንብ አጠገብ አለፉ… እስኪነፋፋና እግሩ ወደ ላይ እስኪነሳ ድረስ አህያዉን ፀሀይ አቃጥላዋለች...

ረሱል ﷺ እነዛን ሁለት ሰዎች እንትና እና እንትና የት ናቸው? አሉ፡፡
.....ሁለቱ ሰዎች መርሀባ አለን አሉ...
ረሱል ﷺ ውረዱና ከዚያ ጥምብ አህያ ብሉ አሏቸው .....የአላህ ነቢይ ሆይ… አላህ ይቅር ይበልህ ከዚህ ማን ይበላል? አሉ…
..... ረሱል ﷺ አሁን ስንመጣ ከወንድማችሁ ክብር ያገኛችሁት (ያማችሁት) ነገር በክትን ከመብላት የበለጠ ነው.. እሱ በኡማው መካከል ቢከፋፈል የሚበቃቸውን የሆነን ተውበት በእርግጥ ቶብቷል፡፡ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ…
#እሱ_አሁን_በጀነት_ወንዝ_ውስጥ _እየተነከረ ነው አሉ

✏️✏️ለማኢዝ ኢብን ማሊክ ምነኛ አማረለት?! አዎ! ዚና ላይ ወደቀ_ ጌታው ግርዶ ያደረገውን ነገር ደፈረ… ነገር ግን በኡማው መሀከል ቢከፋፈል የሚበቃ የሆነን ተውበት ቶበተ፡፡ (ሐዲስ ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ያለ ነው)


🚫 ዛሬ ላይ አማዉ á‰ á‹šáŠ“ ተጨማልቆ ነገ የአኼራ ቅጣት ጀሀነምን ዘንግቷል...በዝሙት ትዳር ሽሽት ሁኗል, ፍች ተበራክቷል, የፊትችን ኑር ተገፏል, እርዚቃችን ሸሽቶ ድህነት ጭንቀት አለመረጋጋት አኗኗሯችን ሁኗል፡፡

ወላሂ ቢላሂ በሸሪአ የምንተዳደር ሀገር ብንሆን ዝሙት የሰራ ሰዉ በዲንጋይ ተቀጥቅቆ መገደል ቢገኝ እድል ነበር...ተቀጥቅጦ የመሞት ከዛ ጀነት መግባት እድል ከየት ይገኛል???ከየትም አይገኝም ብቻ

♦ ሁለተኛዉ እድል አለ መቶበት መቶበት ..
አላህ እንዲህ ብሏል

ለነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸዉ በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታዉሱና ለሀጥያታቸዉ ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑ ጀነት ተደግሳለች(አል-ኢምራን 135)

በነጋ በመሸ በዝሙት የተሸከምኩት ወንጀል አለ ማረኝ እያሉ እስከ ሞት ድረስ ምህረት መጠየቅ እድል አለ
ሞት አማክሮ አይመጣም...በዲንጋይ ተወግሮ ተቀጥቅጦ የመሞት እድል ባናገኝም እስከ ምንሞት ድረስ ከዝሙት ርቀን ቶብተን አላህ ማረኝ አጥራኝ የማለቱ እድል በንጠቀምበት መልካም ነዉ፡፡

⚠️ እነዚህን የአላህ ቃል አንዘንጋ
☞ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ(አል ሙዕሚን15-16)

☞ የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርን ኑሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ዉስጥ ባልሆን ነበር(አል ሙልክ 10)

☞የቅርቢቱ ህይወት ጥቅም አነስተኛ ነዉ፡፡መጨረሻይቱም አለም አላህን ለሚፈራ ሰዉ በላጭ ናት(አል ኒሳዕ 77)

☞ዛሬ በአፎቻቸዉ ላይ እናትምና እጆቻቸዉ ያናግሩናል እግሮቻቸዉ ይሰሩት የነበረዉ ሁሉ ይመሰክራል(ያሲን 65)


ለሌሎች ሸር በማድረግ ያካፍሉ
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ለምን_ለብቻዋ_መቆየትን_እንደመረጠች_ታቃለህ?

በዚህ ዘመን እውነተኛ ፍቅርን መፈለግ ከንቱ ድካም እየመሰለ መጥቷል። አየህ ለብቻዋ መሆንን የመረጠችው ወንድ አጥታ አይደለም። የምትፈልገውን ፍቅር የሚያፈቅር፣ የምትመኘውን ፍቅር የሚፈቀር ሰው ነው ፈልጋ ያላገኘችው። ያ የድሮውን የ90'ዎቹን ፍቅር .... ከልብ የነበረውን፣ ምግብ የማያስበላ የነበረውን፣ እንቅልፍ የሚያሳጣውን፣ ጥልቅ የነበረውን፣ ያለህን ሁሉ አለስስት የምትሰጥበትን .... ያንን ፍቅር ነው ያጣችው።

ዛሬ ዛሬ የጠበሳ መርሆዎች ተቀይረዋል። ዛሬ አካሄዶች ተለውጠዋል።

{ እያወራን ነው }

ዛሬ ፍቅር የሚጀምረው "እያወራን ነው" ከሚለው ነው። ለማያውቁት ሰው " ሀይ " ብሎ መፃፍ የፍቅር መነሻ ሆኗል። በየቀኑ መፃፃፍ ነው፣ በየጊዜው መደዋወል ነው፣ መጀናጀን ነው .... ከፍ ሲልም መገናኘት ይኖረዋል። ከዛ .... ምን ላይ ናችሁ ሲባል ... እያወራን ነው

እያወራን ነው ውስጥ ቃልኪዳን የለም። ፍቅረኛዬ ናት ... ፍቅረኛዬ ነው የለም። በተመሳሳይ ሰዓት ስድስት ሴቶችን ያወራል ... በተመሳሳይ ሰዓት አስራ አምስት ወንዶችን ታወራለች (የሴቷ የበዛው እሷ ማውራት ከፈለገች የሚመልሱላት ወንዶች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑን ለማሳየት ብቻ ነው)

ለጊዜው ችግር ያለበት ባይመስልም አስቀያሚ ነገር ይዞ ሊመጣ ይችላል። በይፋ የሚጠቀስ አካሄድም ሆነ ስርዓት ስለሌለው ... አንደኛው ወገን በትክክል ወደ ፍቅር እያመሩ እየመሰለው ሌላኛው ወገን እንደ ጊዜ ማሳለፊያ እየተደበረበት ሊሆን ይችላል። አንቺ የምትሰሪው ነገር ስለሌለሽ ታወሪው ይሆናል። እሱ ለጓደኞቹ ተጣብሰናል ይላል። ነገ ከሌላ ወንድ ጋር አየናት ሲባል ካልገደ|ልኳት ወይንም ራሴን ካላጠ|ፋሁ አገር ይያዝልኝ ውስጥ ነው።

{ ፈታ እያልን ነው }

ማውራቱ ወደ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ያድጋል። መገናኘት ... እየተገናኙ መላፋት ... እየተላፉ መሳሳም ... እየተሳሳሙ መተኛት ... እየተኙ "ኧረ ምንም የለም"፣ "ፈታ እያልን ነው"፣ " ወንድም እና እህት ነን" ... ይሆናል።

ስለነገ ማውራት ..... ምን እየሆንን ነው ማለት .... የለም። ቢያንስ አንደኛው ወገን "ዋናው ደስተኛ መሆናችን ነው" የምትለውን ቀልድ አስጠብቆ ይሄዳል። ዛሬን ደስታ ይሰጥ ይሆናል። ግን መታመን፣ ጥረት፣ ድካም ... ውስጡ የለውም። ፈታ ለማለት ፍቃደኛ ከሆነው ጋር ሁሉ ፈታ ይላሉ። አንደኛው ወገን እንዴ? ማለት ሲያመጣ .... ምን ታካብጃለሽ ካልፈለግሽ ንኪው ነው መልሱ።

አረገዝኩ ስትይ "እንዴት" ይልሻል ። ኮንዶም እንጠቀም ስትይ ስሜትሽ ይበርዳል ያለሽ፣ ፒልስ ተጠቀሚ ስትላት ጨጓራዬን ያመኛል ያለችው በኋላ ማህፀኗ "ሲታመም" ለቅሶ ይሆናል። "አስወርጅው" የሚለው ትቶሽ ከመሄዱ በፊት የሚለግስሽ የመጨረሻው ምክሩ ይሆናል። ምክንያቱም ጭንሽ ስር የነበረው "ፈታ" ለማለት እንጂ አባት ለመሆን አልነበረም።

{ እየተያየን ነው }

ይሄ በጓደኝነት እና በትዳር መሀል ያለው ነው። ቅልጥ ያለ የፍቅር ጨዋታ እስከ ማባያው (እንጧዬ) ይቀርብበታል። መላፋት፣ አብሮ ማምሸት፣ አብሮ ማደር፣ መሳሳም ይኖረዋል .... ሁሉም ግን በር ተዘግቶ እንጂ በአደባባይ አይደረግም። ለምን? ገና እየተያዩ ነዋ።

ከጓደኛ ወይም ከቤተሰብ ጋር ድንገተኛ እያስመሰሉ መተዋወቅ ይኖራል። ጓደኛዬ ነው ... ጓደኛዬ ናት ማስተዋወቂያ ታርጋዎቹ ናቸው። ለብቻ መቆየትን ካለመፈለግ፣ ቋሚ ግንኙነትን ወደ ትዳር አሳድጎ አብሮ ለመኖር ካለመፈለግ ወይም ትዳርን ከመፍራት፣ ሀላፊነት ከመሸሽ፣ የአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ በማየሉ ሊሆን ይችላል።

ሴቷ ሚስት ለመሆን ምን ቀራት እስኪባል ድረስ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በፍቃደኝነት ታደርጋለች። የቤቱ ቁልፍ አላት፣ አልጋውን የምታነጥፈው እሷ ናት፣ ልብሱን የምታጥበው እሷው፣ የተዝረከረከው ቤት መልክ የሚይዘው እሷ ስትመጣ ይሆናል፣ ካልሲዎቹ ከተወረወሩበት የሚለቀሙት በእሷ ነው፣ በትምህርት ቤት ነኝ ሰበብ ውሎዋ እዛው ነው .... በድንገት ኮንዶም እስክታገኝ ድረስ

ጋባዧ እሱ ነው፣ ካርድ የሚሞላው እሱው፣ ከእነ ጓደኞቿ የሚያዝናናት እሱ ነው፣ እነዛን በስክሪንሹት የምትሰበስባቸውን ቦርሳ እና ሹል ጫማዎች የሚገዛው እሱ ነው .... ስልክ ማንሳት እስኪያቆም ድረስ ... ያኔ በሌላ ሴት ተክቷታል

እነዚህ አዙሪቶች ሲደጋገሙ ማንነትን ያሳጣሉ። ሁሉም ሰው በህይወቱ የሆነው ጊዜ ላይ ነገሮች አንድ ደረጃ እንዲያድጉ እና ወደትዳር እንዲሄዱ ይፈልጋል። መዋደድ፣ መፈላለግ ወይም አብሮ መተኛት ብቻ በቂ አለመሆኑን ይገነዘባሉ።

የሚያከብራት፣ በክፉም በደጉም አብሯት የሚቆም፣ የምታምነው እና የምትተማመንበት ወንድ ትፈልጋለች። በስሜትም በእይምሮም የበሰለ እና ፍቅር ማለት ከማውራት፣ ፈታ ከማለት እና ከመተያየት የዘለለ ቁምነገር ያለው ነገር እንደሆነ የሚገባው ወንድ ትፈልጋለች።

የሚያወራላት፣ የሚሰብክላት፣ የሚጀነጅናት ሳይሆን በተግባር የሚያሳያት ወንድ። ያልቻለበትን ሰበብ እና ምክንያት የሚደረድር ሳይሆን ጥረቱን የሚያሳያት። ግራ የሚያጋባት ሳይሆን ሁልጊዜም ጥርት ያለ አካሄድ የሚመርጠውን ወንድ ትፈልጋለች። አብሯት እያወራት የሚተኛውን እንጂ ከተኛች በኋላ የሚፅፍላትን አትፈልግም። ታማኝነት መገለጫው የሆነውን እንጂ ውሸት የማያልቅበትን አትፈልግም። ጥንቅቅ ያለ ሰው አይደለም እየፈለገች ያለችው ራሱን የሆነውን ነው።

ግማሽ ፍቅር አዝሏታል። በፍቅር ስም መንዘላዘል አድክሟታል። የተረጋጋ እና የሚጨበጥ ነገር ብቻ ነው የምትፈልገው። የሚሰብራት ሳይሆን እየሰራት የሚኖረውን ትፈልጋለች።

የሚገባትን የሚሰጣትን እየጠበቀች ነው .... ብቻዋን የምትቆየው እሱ እስኪመጣ ነው !!

ብቻዋን የምትቆየው የሚገባትን የሚሰጣት እስኪመጣ ነው !!

Š Abby Junior


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔸🔸🔸 #ሸህ_ኑር_ሁሴን(ባሌ)🔸🔸🔸
                ✍🏼አሚር ሰይድ


     ሸህ ኑር ሁሴን የዘር ሀረጋቸዉ ከነብዩ አጎት ልጅ ከአቂል ኢብኑ አቡጧሊብ 12ኛ የዘር ሀረጋቸዉ ይመዘዛል፡፡አረባዊ ዜጋ ቁረይሽ ናቸዉ የተወለዱት በ690 ሂጅራ የዛሬ 746 አመት በፊት ገዳማ የነበሩ አሊም ነበሩ::


🔶 የሼህ ኑር ሁሴን አባት ሸህ ኢብራሂም አብደላ ወደ ማያቁት ህዝብ ሀበሻ መጥተዉ  ባሌ ዉስጥ  ኢስላምን አስፋፍተዋል፡፡ሸህ ኢብራሂም ማኪዳ የምትባለዉን የባሌ ተወላጅ አግብተዉ ሶስት ልጆች ወለዱ የልጆችም ስም
➊ ሙሀመድ
➋ ሱለይማንና
➌ሁሴን ይባላሉ::

     የባሌዉ ሸህ ሁሴን ኢብኑ ኢብራሂም በደንብ የሚታወቁት ሼህ ኑር ሁሴን በሚለዉ አጠራር ነው ትርጉሙ ብርሀማዉ ሁሴን እንደማለት ነው፡፡ይህም ወደ ፊት ሀገሩን በእስልምና ብርሀን ያበረዋል በሚል መልካም ምኞት የወጣላቸዉ ቅጥል ስም ነዉ ይባላል፡፡ የተወለዱት አናጂር በምትባለዉ የገጠር ቀበሌ ነው፡፡

     ታዳ ልጃቸዉ ሁሴን የአባታቸዉን የደአዋ ሾል በማስቀጠል በባሌና አርሲ ባሉ ማህበረሰቦችን የኢስላም የተዉሂድ እዉቀትን አሳፋፍተዋል፡፡

እናጂና የሚባል መስጂድ ነበራቸዉ መስጂዱም በወቅቱ በ10ሺ የሚገመት ህዝብ የጀመአ ሶላት ይሰግድበት ነበር፡ ሰዉን ለጀመአ ሶላት የዲን እዉቀት ቀን ማታ ሳይሉ ያስተምሩ ነበር ፡፡ ኑርሁሴን አመትን በሁለት በመክፈል 6 ወር ደረሶቻቸዉን ከቤትና ከቤተሰብ በማራቅ በሸለቆዋማ ቦታ ዉስጥ በመሰብሰብ ሲያስቀሯቸዉ፤ 6 ወር ደሞ ደረሶቻቸዉ ወደየ ትዉልድ ስፈራቸዉ እንዲሄዱና መስጂድ እንዲሰሩና ህብረተሰቡን ወደ ኢስላም እንዲጣሩ ያደርጓቸዉ ነበር፡፡


🔶 #አለመታደል_ሆኖ እሳቸዉ ወደ አኼራ ከሄዱ በኋላ ተግባራቸዉ ተዘንግቶ አላማቸዉ ተረስቶ ስለሳቸዉ ማንነትና ምንነት የሚያሳዉቅ ጠፍቶ የማያዉቋቸዉ ስብስቦች ወዳጆቻቸዉ ተብለው ተፈጠሩ፡፡የኑር ሁሴን ቀን ተብሎ በሳምንት ዉስጥ ይከበር ይዟል፡፡

ኑር ሁሴንን ላይከተሉዋቸዉ ተከታዮች የተባሉት ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በአኗኗራቸዉ! በአለባበሳቸዉ! በባህሪያቸዉ ለየት ባለ ሁኔታ እንዲታወቁና ከየአገሪቱ ክፍል እንዲሰበሰቡ ተደረገ፡፡

ዛሬ ላይ መሰብሰቢያ የተደረገዉ ቦታ አናጂና በመባል ይታወቃል፡፡እናጂና ለኑር ሁሴን ባሌ የእውቀትና የደእዋ ስልጠና ማዕከላቸዉ ለስድስት ወራት ደረሶቻቸዉን የሚሰበስቡባትና ለተለያዩ እስላማዊ ስልጠና ሲገለገሉባት የነበረች ልዩ ስፍራ ነበረች፡፡

መስጂዱም በወቅቱ በ10ሺ የሚገመት ህዝብ የጀመአ ሶላት ይሰግድበት ነበር፡፡ ዛሬስ ላይ ምን ያህል ሰው ይሰግድበት ይሆን? ዛሬ ላይ በየአመቱ ወደዚያ ስፍራ የሚሰበሰበው በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ስለ ሽህ ኑር ሁሴን ማንነት ቢጠየቅ ምናልባት በአፈ ታሪክ የተነገረዉን፤ ስለወዳጅነቱ የሚያንጎራጉርና ከዚያም አልፎ ከተዉሂድ ጋር የሚጋጩ ቃላትን በግጥም ከማዜም የዘለለ አብዛኛውሰው ጨርሶም አያዉቃቸዉም ለማለት ያስደፍራል፡፡ምክንያቱም ወዳጆችነን የሚሉት የዋሆች የሚተገብሩት ከሸህ ኑር ሁሴን ህይወትና ተግባር ጋር የማይገናኝ እጅግም ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለንና፡፡

የኑር ሁሴን አባት ከአረቦች ቁረይሾች መጥተዉ እስልምናን ሀባሻ ላይ አስፋፍተዋል እኛ ግን እዚሁ ተቀምጠን ኢስላም ላይ ምን ሰራን?? እስኪ አንተ አንቺ እኔም ለኢስላም ምን አበርክተናል??

መስራቱ ማስፋፋቱ ቀርቶብን ኢስላምን በላሰደብን ....


🟢 ሽህ ኑር ሁሴን ባሌ ከተናገረውቸው ጠቃሚ ንግግሮች በከፊል

✏️ ዝናብ ሲዘንብ በንፁህ መሬት እና ንፁህ ባልሆነም መሬት ላይ ነው፡፡በንፁህ መሬት ላይ የወረደ ዝናብ ለሰው ልጅ እንደሚጠቅም ሁሉ ቁርአንና እስላማዊ እውቀት በንፁህ ልቦና እና ንፁህ ባልሆነ ልቦና ውስጥ ከገባ ልዩነቱ የዚያኑ ያክል የተለያየ ነው፡፡ አላህን በሚፈራ ሰው ውስጥ ያለው ቁርአን ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ይጠቅማል፡፡

✏️ #ስለ_ነፍሲያ_አስቸጋሪነት_ሲያብራሩ
✔ነፍሲያ የመሬትና የአለም ስፋት እንጂ የቀብር ጥበት አይታያትም፡፡
✔ነፍሲያ  ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ እነማን ሰብስበው ጥለው እንደሄዱ አይታያትም፡፡
✔ ነፍሲያ ሰፊ ምኞት እንጂ ሞት በአቋራጭ ሊመጣ እንደሚችል አይታያትም፡፡
✔ ነፍሲያ የሰው ነውር እንጂ የራስዋ ነውር (ገበና) አይታያትም››
✔ የነፍሲያ ሽር (ተንኮል) ከሰባ ሺህ ሸይጧን ተንኮል (ሸር) ይበልጣል› እናም ሌባው ቤት ውስጥ ከሆነ በር መዝጋቱ ትርጉም የለውም፡፡ ሌባው ነፍስያ ስትሆን ቤቱ የሰው ልብ ማለት ነው፡፡ ብለዋል

✏️ #በኸይር_መሽቀዳደምን_ሲገልፁ
☞በአንዱ ቢቀድምህ አንተ በሌላው ቅደመው፡፡
☞በቁርኣን ቢቀድምህ አንተ በዒልም ቅደመው፡፡
☞ በዒልም ቢቀድምህ በስራ ቅደመው።
☞በመልካምሥራ ቢቀድምህ አንተ ለአላህ ታማኝ በመሆን (በኢኽላስ) ቅደመው፡፡
☞በኢኽላስ ቢቀድምህ በትዕግስት ቅደመው፡፡
☞በትዕግስት ቢቀድምህ በውዴታ ቅደመው።
☞በውዴታ ከቀደመህ አንተ በምንም ነገር መቅደም አትችልም፡ አንተ ከእሱ አብልጠህ ካልወደድከው በቀር...ብለዋል፡፡

✏️ አንዳንድ በእውቀት የተካኑ ሰዎችን
#የምላስን_አደገኛነት ሲናገሩ:-ለምላሴ በአፌ ውስጥ አንበሳ አለ እና አስሬ ከያዝኩት እድናለሁ ከለቀቅኩት ግን እበላለሁ በማለት ይናገራሉ፡፡ ከምላስ ወለምታ አላህ ይጠብቀን፡፡

ኑር ሁሴን ተብሎ ማክሰኞ ቀንን ለይቶ ማክበር አግባብ አይደለም ልናስተዉል ይገባል🚫

⚡️⚡️ #አሏህ ይዘንላቸዉ ቀብራቸዉን ኑር ያድርግላቸው... ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔸🔸🔸 #ሸህ_አብደልቃድር_ጄይላኒ🔸🔸🔸
                   ✍ አሚር ሰይድ

   የሙሀመድ ዲን አጥሩ እየፈራረሰ፣ መሰረቱ እየተናጋ ነው፡፡የምድርላይ ነዋሪዎች ሆይ፣ ኑ የፈረሰውን እንገንባ፡፡ የወደቀውን እናቅና፡፡ይህ ሊፈፀም የሚችለው በተግባር ስንቀሳቀስ ነው፡፡ ጨረቃ ሆይ፣ፀሐይ ሆይ፣ ቀን ሆይ፣ ኑ ተባብረን ይህን ዲን እንታደግ(ሸህ አብደል ቃድር ጄይላኒ)

    🔷 ሸህ አብደልቃድር ጄይላኒ ማን ናቸዉ?የኛ ሀገር በተለይ በገጠሩ ያሉ ወይም ከተማ እየኖሩ ያልነቁ ሰዎች ሾለ እሳቸዉ ትክክለኛ መረጃ ሳያቅ እሮብን ቀን እየመረጡ ዛሬ አብደልቃድር ናቸዉ እያሉ በአቅማቸዉ በቡናዉ በቡና ቁርሱ ቤት ባፈራዉ ነገር አብደል ቃድር ድረሱልን አማልዱን የሚሉ ጫት የሚቅሙ ወገኖች አሉ?አብደል ቃድር ግን ማን ናቸዉ??እንደ አሁን ዘመን ሰዎች የሽርካ ሽርክ አሊም ሳይሆኑ የተዉሂድ ጠንካራ አሊም ነበሩ፡፡


  đŸŸ˘ ሽህ አብዱልቃድር ጄይላኒ የተወለዱት እንደ ሂጅሪያ አቆጣጠር በ470 ወይም እ.ኤ. አበ1075 ጂላኒ በተባለች ከተማ ውስጥ ነው፡፡ የዘር ሀረጋቸው በአባት በኩል ከሀሰን ኢብኑ አሊ ኢብን አቡ ጣሊብ በእናት ደግሞ ከሁሴን ኢብን አሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ ጋር ይገናኛሉ፡፡ እናታቸው ሴቶች መውለድ በማይችሉበት የእድሜ ክልል በ60 አመታቸው ነበር የወለዱዋቸው፡፡ወንድም እህት የላቸዉም ብቸኛ ልጅ ነበሩ፡፡


#የመጀመሪያ_ደረጃ_ትምህርታቸውን ጀይላኒ ከተማ ውስጥ ተከታተሉ፡፡የአብደል ቃድር ጀይላኒ እናት ለዲናቸዉ ጠንካራ እንዲሆኑ ፍላጎት ነበራት፡፡ ያላትን ብር ሰጥታ ዲናቸዉን እንዲማሩ በ488 ሂጅሪያ በ18 እድሚያቸው  የበለጠ ትምህርት ለማግኘት ወደ ባግዳድ አመሩ፡፡ ወደ ባግዳድ ማምራታቸው በወቅቱ በሁሉም መስኮች ባግዳድ ውስጥ የነበረውን ማእበል ተከትሎ በእርሳቸው ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ አስከተለ፡፡


   🟢 የመጀመሪያ የዲን ትምህርታቸውን በኢራቅ ባግዳድ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሄደው ከእናታቸው ጋር እያሉ በአካባቢያቸው እየተንቀሳቀሱ ሳሉ በአንድ በሬ ኋላ ኋላ ሲሄዱ በሬው ዞረና በሰውኛ ቋንቋ አንተ ለዚህ አልተፈጠርክም እዚህም እንድትሰራ አልመክርህም ብሎ ሲላቸው.... በፍጥነት ወደቤታቸው ሄደው እናታቸውን ፈቃድ ጠይቀው ለሁለተኛ ጊዜ የዲን ትምህርታቸውን ለመማር ወደ ባግዳድ ተመለሱ
እናታቸውም በእርጅና ጊዜያቸው ማንም ወላጅ የልጁን የሞራል እና የገንዘብ ድጋፍን በሚፈልግበት ወቅት አንድ ልጃቸውን ያለምንም ማቅማማት ፈቀዱላቸው፡፡

      አብዱልቃድር ጄይላኒ #ቁድስ(እየሩስአሌምን) የከፈተዉ ጀግናዉ #ሰልሀዲን_አልአዩብ ዘመን የነበሩ አሊም ናቸዉ፡፡ ሰልሀዲን አልአዩብ ጋር ጦር እንዲዘምቱ በደአዋ ያግዙት ነበር፡፡
አብደል ቀድር ጂላኔ የኢስላም መደፈሩ ሁሌ  ይቆጫቸዋል፡፡ፍጡራን በአጠቃላይ ኢስላምን ለመርዳት ቢሰማሩ ይመኛሉ፡፡በአንድ ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር፡፡

የሙሀመድ ዲን አጥሩ እየፈራረሰ፣ መሰረቱ እየተናጋ ነው፡፡የምድር ላይ ነዋሪዎች ሆይ፣ ኑ የፈረሰውን እንገንባ፡፡ የወደቀውን እናቅና፡፡ይህ ሊፈፀም የሚችለው በተግባር ስንቀሳቀስ ነው፡፡ ጨረቃ ሆይ፣ፀሐይ ሆይ፣ ቀን ሆይ፣ ኑ ተባብረን ይህን ዲን እንታደግ ይሉ ነበር

🔺🔻 በሰልሀዲን አልአዩብ ዘመን የነበሩ ሙስሊሞች በፊርቃ ሆድና ጀርባ ነበሩ አብደል ቃድር ጄይላን በቁርአንና በሀዲስ እየታገዙ የሚያጨቃጭቁ ነገሮችን ፈትዋ እየሰጡ ብዙዎችን አንድ አድርገዋል፡፡
    አብዱልቃድር ጄይላኒ  84 ያላነሱ ኪታቦች በእጃቸዉ ፅፈዋል፡፡ትዳር አላሰቡም ነበር ግን ሰዎች የነብዩን ሱናን አትቃረን አግባ ብለዉ በ51 አመታቸዉ አገቡ፡፡ በተለያዩ ጊዜ ካገቧቸዉ አራት ሚስቶቻቸዉ...መዲና/ሳድቃ/ሙእሚናህ/መህቡባህ ከተባሉ ሚስቶቻተዉ
የ27 ወንዶች የ22ሴቶች በአጠቃላይ የ49 ልጆች አባት ናቸዉ፡፡

🟡  በአብዱልቃድር በጀይላኒ እይታ ግለሰቦችና ህብረተሰቡ ኢስላምን መርዳትን ከተው በፍራንክ ከተመኩ፣ ጥቅም አሳዳጅነት ከተጠናወታቸው ሾለ ጀነት እና እሳት ቢያወሩም በአላህ አጋርተዋል፡- «እናንተ የፍጡራን ባሮች ናችሁ፡፡ይሉ ነበር

   ተማሪዎቻቸውን ደካማ አሊሞችን እንዳይቀርቡ : አስጠንቅቀዋል እንዲህም ይሏቸዉ ነበር፡- አላህን የማያውቁ አሊሞች አያታሏችሁ እውቀታቸው ሁሉ በነርሱ ላይ የተቆለለ እዳ ነው፡፡ቅንጣት አይጠቅማቸውም።የአላህን ሁክም ያውቃሉ፡፡ አላህን ግን አያውቁትም ከእርሱ ይሸሻሉ፡፡ በወንጀልና በእኩይ አድራጎት ይዳፈሩታል፡ (አልፈትሁልረባኒ 43)

    ሕብረተሰቡም እንዲህ አይነት አሊሞችን እንዳይሰማ ጥሪ አድርገዋል። (የአላህ ባሮችሆይ፣ እነዚያን በቃላቸው ነፍሳችሁን የሚያስደስቱትን እኩያን አሊሞች አትስሙ፡፡ ከሹማምንት ፊት ተዋርደው ቅንጣት ታክል ይሆናሉ፡፡ አላህ ያዘዘውን አያዟቸውም፤ ከከለከለውም አይከለክሏቸውም ይህን ቢያደርጉም ለማስመሰል ነው፡፡ አላህሆይ፣ እባክህ ምድርህን ከእንዲህ አይነት እኩያን አፅዳ፡፡ ወይም ወደ መቀናት ምራቸው፡፡በልባቸው ሌላን አካል ቋጥረው በምላሳቸው የአላህን ስም ሲያወሱ ውስጤ በንዴት ይቃጠላል፡፡ ብለዉ ያስተምሩ ነበር አልፈትሁልረባኒ 245)

☑️☑️ የሸይህ ዐብዱል ቃድር ጂላኒ
#ወርቃማ_አባባሎች በጥቂቱ


☞አስቀያሚ ጠላትህ ክፉም ግባር ያለው ጎደኛህ ነው

☞ንግግርህ አላህን የማያረካ ከሆነ ዝምታህ ይበልጣል።
☞ ሕይወትህ በቀጥተኛ መንገድ ላይ ካልሆነ ሞትህ ላንተ በላጭ ነው፡፡
☞አላህን ለሚገዛ ሰው አላህ ሌሎች እንዲታዘዙለት ያደርጋል፡፡
☞ቅርቡ ዓለም ከቀጣዩ ዓለም ጋር በፍፁም በአንድ አይቀላቀሉም፡፡
☞ነፍስህን በአእምሮህ ጋልባት ካልሆነ እርሷ ትጋልብሃለች
☞ የሰውነት ፅዳት በነፍስ መፅዳት ካልታገዘ ጥቅም የለውም።
☞ለሰዎች በጎ በጎውን አስብ፣እንዲያ ስታደርግ ራስህንም ሌሎችንም ትጠቅማለህ፡፡

☞በጎ ምግባርና እዝነት ያልታከለበት ተግባር ውጤታማ አይደለም፡፡
☞አማኝ ሰው እድሜው በጨመረ ቁጥር ኢማኑም የሚጨምር ነው፡፡
☞አላህን እንድትዘነጋ የሚያደርግህ ሁሉ ለአንተ ክፉነው።
ብለዋል፡፡

  ➡️ አብደል ቃድር ጀይላኒ አሊም ናቸዉ ወልይም ባለከራማም ናቸዉ...አንዳንድ ሰዎች ድንበር ረገጥ ጥላቻ ያላቸዉ አሉ ..ጥላቻዉ ስህተት ነዉ ለምን
የነብዩ ﷺቤተሰብ (አህለል በይት) ናቸዉ፡፡ወሰን ያለፈ ዉዴታ እሮብ ቀን መርጦ እስከ ማክበር የደረሰም ስህተት ነዉ ....የኛ ማህበረሰብ የገጠሩ ወይም ትላልቅ ሰዎች አብደል ቃድር እንዲህ ብለዉ...እንዲህ ሂደዉ...እንዲህ አርገዉ እየተባለ ብዙ ወሬ ይወራል ፡፡ ይሄን ማወራት አግባባም አይደለም ለምን የእሳቸዉን ታሪክ እንዲህ አድርገዉ እንዲህ ብለዉ ከራማቸዉ ምናምን ተብሎ የተፃፈዉ የተዘጋጀዉ በሸአዎች ስለሆነ እዉነቱን ዉሸቱን ለመለየት አዳጋች ነዉ፡፡ብቻ አላህን ፈሪ የዲን ጠበቃ ከራማ እንዳላቸዉ ግን እርግጥ ነዉ ...ለምሳሌ ከላይ እንደጠቀስኩት በሬዉ ዙሮ በሰዉኛ ቋንቋ ተናግሯቸዋልና ..
ኑር ሁሴን ማክሰኞ አብደልቃድርን እሮብ ቀን ለይቶ ማክበሩ ስህተት መሆኑን ልናስተምር ይገባል፡፡


አብደል ቃድር ጀይላኒ  በ91 አመታቸዉ  ነበር ከዚች አለም በሞት የተለዩት....አላህ ይዘንላቸዉ ቀብራቸዉን ኑር ያድርግላቸዉ

◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔸 #የጌታዬን_ግርዶ_እንዴት_እዳፈራለሁ?🔸
                   ✍🏼አሚር ሰይድ

    አንድ ደሀ ወጣት እየዞረ እቃ የሚሸጥ ነበር፡፡በመንገዶች ላይ እየተዘዋወረ ይሸጣል አንዲት ባዶ አላህን የማትፈራ የሆነች ሴት ነበረች… ሀራምን ከመስራት  አትቆጠብም፡፡የሸይጧን ተላላኪ ነበረች…

  አንድ ቀን በቤቷ አጠገብ አለፈ… በበሩ በኩል ብቅ ብላ ሾለ ሸቀጦቹ ጠየቀችውና ነገራት.. እቃዎቹን እንድታይ እቤት እንዲገባ ጠየቀችው ፡፡ ቤት ሲገባ በሩን ቆለፈችበትና ወደ ሀራም ጋበዘችው... ወጣቱ ልጅ ጮኸ፡፡ …ጊዜያዊ ጣፋጭ ነገሩ ጠፍቶ ፀፀቱ በሚቀርበት ጊዜ የሚኖረውን ሁኔታ አስታወሰ… ዚና የሰራባቸው አካላቶች... የተራመደባቸው እግሮቹ... የዳበሰባቸው እጆቹ... የተናገረበት ምላሱ… በእሱ ላይ የሚመሰከሩበትን ቀን አስታወሰ... የእሳትን አቃጣይነትና የአላህን ቅጣት አስታወሰ...


✏️ዝሙተኞች በእሳት ውስጥ እንዲንጠለጠሉ ተደርገው ከብረት በሆነ አለንጋ ይገረፋሉ... ከዝሙተኞች አንደኛው ከቅጣቱ እንዲያድኑት ጩሆ ሲጠይቅ መላኢኮች.. አላህን ሳትፈራና ይቆጣጠረኛል ሳትል ሀራም በመስራት ስትስቅ ስትደሰት- ስትፈነድቅ ... ይሄ አሁን ያሰማሀው ድምፅ የት ነበር? ይሉታል...

    ወጣቱ ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ  እንዲህ ብለው የተናገሩትን ሐዲስ አስታወሰ፡፡ “የሙሐመድ ህዝቦቸ ሆይ! ወላሂ እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽን ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር፡፡”

በአንድ ወቅት ረሱል ﷺ በህልማቸው ያዩትን አስታወሰ... ከታች ሰፊ ከላይ ጠባብ በሆነ ምድጃ በሚመስል ጠባብ ቦታ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ራቁታቸውን ሆነው ይጮሀሉ ያጓራሉ..…. የእሳት ነበልባል ከስራቸው ይመጣባቸዋል ነበልባሉም በመጣባቸው ጊዜ ከግለቱ ብርታት የተነሳ ይጮሀሉ ረሱልም ﷺ
ጂብሪል ሆይ! እነዚህ ምንድን ናቸው? ብለው ጠየቁት ጂብሪልም፡- እነዚህ ሴት ዝመተኞችና ወንድ ዝሙተኞች ናቸው እስከ የውመል ቂያማ ይህ ቅጣታቸው ነው፡፡ " ብሎ መለሰላቸው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የአኼራ ቅጣት እጅግ የበረታና ዘልአለማዊ ነው… አላህ (ሱ.ወ) ምህረት እንዲያደርግልንና ሰላም እንዲያደርገን እንጠይቀዋለን…

✨✨ነፍስያውም፡- “ስራና ትቶብታለህ” አለችው፡፡ እሱም አዑዙቢላህ የጌታዬን ግርዶ እንዴት እዳፈራለሁ? የተከበረውና የተላቀው አላህ ከበላያችን ሆኖ እየተመለከተን የማትፈቀድልኝን ሴት እንዴት እመለከታለሁ? _እንዴት ከፍጡራን እየተደበቅን ፈጣሪ ፊት እናምፃለን? …አለ፡፡

ወደ በሩ እየተመለከተና እንዴት መውጣት እንደሚችል እያሰበ ዝም አለ… አመፀኛዋ ሴትም:- ወላሂ የምፈልገውን ካልፈፀምክ ጮኼ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አደርግና ይህ ወጣት ዘሎ ቤቴ ገባብኝ እላለሁ የዚህ ጊዜ ሞት ወይም እስር እንጂ ሌላ አይጠብቅህም” አለችው፡፡ ጥብቁ ወጣት ይንቀጠቀጥ ጀመር.. በአላህ አስፈራራት ምንም አልመሰላት  ይህን ሁኔታ ያየ ጊዜ ከሷ የሚገለልበትን ዘዴ ማሰብ ጀመረ… ከዚያም ሻወርና ሽንት ቤት እፈልጋለሁ አላት፡፡ እሷም ወደ ሽንት ቤቱ አመለከተችው

መፀዳጃ ቤት ሲገባ ወደ መስኮቱ ተመለከተ… ነገር ግን በመስኮቱ ማምለጥ አይችልም... ከእሷ የሚላቀቅበትን መንገድ አሰላሰለ…… ሠገራ ወደሚጠራቀምበት ሄደና ከሰገራው እያነሳ ልብሱን እጁንና ሰውነቱን መቀባት ያዘ ከዚያም እሷ ጋር መጣ… ያየችው ጊዜ ጮኸች… እቃውን ፊቱ ላይ ወርውራለት ከቤቷ አባረረችው

ቤቱ እስኪደርስ ድረስ ህፃናት ከኋላው ሆነው እብድ! ... እያሉ ይጮሁበት ነበር፡፡ ቤት ሲደርስ ነጃሳውን አስወገደና ገላውን ታጠበ … ከዚያም በኋላ ወጣቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ሰውነቱ የሚስከ ሽታ የሚስክ ሽታ ይሸት ነበር፡፡ (ታሪኩን ኢብኑ ጀውዚ ጠቅሰውታል)



◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለኢደል አድሀ በአል በሰላም አደረሰን.,,ለሚመጣዉ አመት ጤና አፍያ አድርጎ ለሀጅ ይወፍቀን....የወሎ ሰዉ ሲመርቅ አላህ ዙር ገጣሚ  ያርግህ ይላሉ፡፡ ለሚመጣዉ አመት የምንደርስ ዙር የምንገጥም ያርገን🥰🥰

ዛሬ በወሎዋ እምብርት ደሴ ከተማ እንደዚህ አምረን ደምቀን ፈክተን ተዉበን ነበር

Produce by☞kalido production

             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
[ ጨዋታ ዘ ስጋ ]

⛔️ ከ21 አመት በላይ አልያም በአይምሮ ብስለት ለአቅመ እውቀት ለደረሱ ብቻ ‼️

ወሲብ ሀያል የሆነ እና በጥልቅ ስሜት የሚፈፀም ነገር ቢሆንም ብቻውን የየትኛውም ግንኙነት መሰረት ሊሆን አይችልም። የትኛዋም ሴት ወንድ ልጅን በወሲብ ብቻ አስራ ልታስቀምጠው አትችልም። ወንድ ልጅ የወሲብን ያህል በስሜት መተሳሰር፣ የጋራ የሆነ የህይወት እሴት እና መከባበር በሌለበት ዘላቂ ግንኙነትን መስርቶ አይቀመጥም።

የትኛዋም ሴት ከፍቅረኛዋ ጋር ስለወሲብ ካወራች በኋላ ሁለት አይነት እሮሮ አላት: ስጪኝ አለኝ ... የወደደኝ ስለመሰለኝ እና እኔም ስለወደድኩት ሰጠሁት .... ከዛ ትቶኝ ሄደ .... ወይም .... ስጪኝ አለኝ ... እኔ ደግሞ አላማ ስላለኝ እና የማስበውም ለቁምነገር ስለነበር ስንጋባ ካልሆነ ማድረግ አልፈልግም አልኩት ... ከዛ ትቶኝ ሄደ ...

በሁለቱም ውስጥ ወሳኟ ሴቷ ናት
በሁለቱም ውስጥ ጠያቂዋ ሴቷ ናት
በሁለቱም ውስጥ ትቶ ሂያጁ ወንዱ ነው

ሴት ልጅ አትጠይቅም? .... ብትጠይቅስ ሁሌም መልሱ "ከሰጠሽኝማ አልምርም" ነው? ወንድ ልጅ አይ አልፈልግም አይልም?

ብዙ አላማ ያለን፣ ልባችን ከብልታችን ጋር ያልተሳሰረ፣ አገኘን ብለን የማንጋደም፣ ለምነን አይደለም ተለምነን የማንፈልግ፣ ስቶሪሽን ስናይ የማይ|ቆምብን፣ ፍቅርሽ ከአይምሮ ወደ ልባችን እንጂ ከአይን ወደ ብልት የማይፈስብን ወንዶችም አለን። አዎ አለን ... እመኝኝ

ወደ ቀደመ ጨዋታችን እንመለስ
እህቴ ስሚኝ .... እንጧዬን መስጠትሽ ብቻውን ለግንኙነታችሁ መሳካት ምንም አይነት ዋስትና አይሰጥሽም። እንጧዬን መከልከልሽም ታማኝነት እና ክብርን አያጎናፅፍሽም። ለመንገደኛ ሁሉ ስታድዪ ከከረምሽ የወደደሽ ወንድ ጋር ስትደርሺ "ጨዋ ጨዋ" የምትጫወችበት ምንም አመክንዮ የለሽም። ከንፈርሽን የሳመ ሁሉ ሲደርሰው የነበረውን ለአሁኑ አፍቃሪሽ መከልከል ራስን ማታለል ይሆናል። በሌላ መልኩ ሳላገባ አላስነካም ብለሽ አስራ አራት ወንዶችን እምቢ ብለሽ ፥ ገና ለገና እድሜዬ ሳላስበው ሮጠ ብለሽ ለስንት አመት ያቆየሽውን ድንግልና አሁን ስለወደድኩሽ ላስደስትሽ ላለሽ ወንድ ከፍተሽ ከሰጠሽ .... አንቺም ባለቀ ሰዓት ተበላሽ። ከዚህ በፊት የነበሩት ሁሉ ቀምሰው ዞር ስላሉ .... ከዚህ በኋላ ያገኙት መሰላቸው ብለሽ ከልክለሽ መቀመጥም፣ ከአመታት ክልከላ በኋላ ይኼኛውስ ካቀመስኩት አይለቀኝም ብለሽ ከሰጠሽ .... አንቺም በተበላሽ።

ፍቅርን በምንም መንገድ ከእንጧዬ ጋር አታስተሳስሪው።

ፍቅር መሰረቱ የተገነባበት ነገር ላይ እንጂ የደቂቃዎች ሲቃ ላይ አይፀናም። በሰውነት ውበትሽ እና ማማለልሽ ላይ ከነገባሽው .... አንዴ ሲበላሽ ነገሩ ይበላሻል። ድካሙም፣ ጥረቱም፣ ትግሉም፣ ካፌ ለካፌ መዞሩም፣ በየሬስቶራንቱ መጓተቱም፣ በየእምነት ቦታው ፃድቅ መምሰሉም፣ በጠራራ ፀሀይ ለፊልም መሰለፉም፣ በየደቂቃው መደዋወሉም፣ ቴሌግራም እና መሴንጀር ላይ መጣዱም .... እንጧዬን ለመብላት ነው። አንቺም ኖሮሽ መስጠት የምትችይው እሱን ነው ፥ እሱም የሚፈልገው ይሄንን ነው።

ግንኙነትን በጋራ ራዕይ፣ በጥልቅ ስሜታዊ መፈላለግ፣ የጋራ በምትሉት ነገ ላይ ከመሰረታችሁት ብዙ ርቀት የመሄድ የተሻለ እድል አለው። እንጧዬ ሰጠሽው አልሰጠሽው ብዙም ለውጥ የለውም። ብትሰጭውም እሰየው እያጣጣመ ይቀጥላል። እንቆይ ብትይውም "ይደርሳል የት ይሄዳል" ይልሻል።

ጥያቄው አለኝ የምትይው ነገር ምንድነው? የሚለው ነው

የትኛውም ግንኙነት የጋራ ጥምረት ነው። ዋናው ነገር ሁለታችሁም ምን ይዛችሁ ተገናኛችሁ ነው።

በሰከነ መንገድ ተነጋግሮ የመግባባት አቅም፤ ጥሩ የማሰብ እና የማገናዘብ አቅም

ግጭትን እና አለመግባባትን የመፍታት ልምድ፤ ፍቅርን በአግባቡ የመግለጽ ችሎታ፤ አጋራሽን የማገዝ ጥበብ

ብቻሽን የመቆም አቅም ቢኖርሽም አብሮ ማደግን መርጠሽ የተገኘሽ

የማህበረሰቡን ባህል እና እሴት ተከትለሽ "በስርዓት" ታንፀሽ የኖርሽ

በህይወት መድረስ ያለብሽ የምትይው ቦታ ጋር ለመድረስ አልመሽ እየተጓዝሽ ያለሽ

እንዲህ አይነት ሴት ከሆንሽ የትኛውም ወንድ እንደ እንቁ ተንከባክቦ ይይዝሻል። ጥሎሽ የሚሄደው እድሜ ልኩን ባሰበሽ ቁጥር ይቆጭብሻል።

ይዘሽ የቀረብሽው ግን መልክሽን፣ ጡትሽን፣ ዳሌሽን ወይም መቀመጫሽን ከሆነ አይደለም ለዘላቂ ህይወት ለፌስቡክ ፖስት እንኳን ብዙ አይን የሚስቡት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው።

የፍቅር ግንኙነት ገበያ አይደለም። መሸጥ እና መግዛትን መሰረት ማድረግ የለበትም።

ወንድ ልጅ ራሷን አክብራ የምታስረክብ፣ ቤቴ ቤቴ የምትል እና አሳብ ያላት ሴትን ለዘላቂ ህይወቱ ይመርጣል። ሜካፕ ዋጋሽን አያሳይም። ገላሽ ላይ የምታርከፈክፊው ሽቶ ዋጋሽን አያሳይም። ጠዋት ተነስተሽ ፍርፍር መስራት እና ሻይ መቀቀል መቻል ዋጋሽን አያሳይም።

ወንድ ልጅ ራስሽን መግለጽ መቻልሽ፣ ሀላፊነት የሚሰማሽ ሰው መሆንሽ፣ መልካም እና ጥሩ ረዳት መሆንሽ፣ የማደግ ጉጉት ያለሽ፣ ነገን አርቀሽ የምታይ መሆንሽ ..... የበለጠ ያሸንፈዋል።

ወንድ ልጅ ጀግና ሴት ታንበረክከዋለች።

ወሲብ የረከሰ የሆነው በየቦታው ከተለያዩ ሴቶች የሚገኝ በመሆኑ አይደለም። ወሲብ የሚረክሰው ሌላ ድክመትን ለመሸፈን ወይም ወንድን ለማጥመድ በሚል አለአግባብ ስትጠቀሚበት ነው።

ሁልጊዜም ወደ ግንኙነት ስትገቢ

ከዚህ ግንኙነት ምንድነው የምፈልገው?

ዋጋዬ ምንድነው?

ለዚህ ግንኙነት በአይምሮ እና በስሜት ዝግጁ ነኝ?

ምንድነው ልሰጥ የምችለው ነገር? የምቀበለውስ ምንድነው?

ብለሽ ጠይቂ

ለወንድ ልጅ ልትሰጭው የምትችይው ብቸኛ ነገር እንጧዬ ከሆነ .... ግንኙነት የሚባል ነገር ይቅርብሽ


                    Š Abby Junior


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🎖#የምትወደውን_መጠጥ_ይምጣልህ_እንዴ?🎖
                 ✍🏼 አሚር ሰይድ


   ኢማም አቡ ሐኒፋ የሌሊቱን ብዙውን ክፍል የለይል ሶላት በመስገድ ማሳለፍ ልማዳቸው ነበር። ከእርሳቸው ተጥሎ ያለው ጐረቤታቸው ግን  መጠጥ በጣም የሚወድና ሁልጊዜም እየሰከረ በመምጣት የሚረብሻቸው  ወጣት ነበር፡፡

ይህ ወጣት በተለይም ማታ ማታ ሰክሮ በመምጣት እየዘፈነ ለረዥም ጊዜ ሲረብሻቸው ያመሻል፡፡ ኢማሙ ይህን ወጣት በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ቢመክሩት ምንም ለዉጥ አያመጣም ይባስ ብሎ እልክ ይዞት ቀን በቀን ረብሻዉን ይቀጥልበት ይዟል...

✏️✏️አቡ ሐኒፋ እንደ ማያዳምጣቸው ተገንዝበዋል።ያላቸዉ አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነበር ወጣቱ እየሰከረ መጥቶ አዳሩንን ሲጨፍር ሲዘፍን ያድራል እሳቸዉ ግን ይህን ተቋቁመዉ ከአላህ ጋር የሚያገናኛቸዉን የለይል ሶላት መስገድ የእለት ተእለት ተግባራቸዉ ሁኗል....ጎረቤት መጥፎ ከሆነ ምን ይደረጋል ...በዚህ ሁኔታ እየኖሩ ለምደዉታል ...


ታዳ አንድ ቀን የዛች ቀን  ምሽት ላይ ኢማሙ ሐኒፋ  የዚያን ወጣት ድምፅ አልሰሙም ነበር፡፡ እንዴ ጎረቤቴ ምን ሆነ??ብለዉ ከቤት ወጥተዉ የሰፈር ሰወችን ጎረቤቴ ዛሬ የለም ያየዉ አለ?? ከቤት ያልመጣዉ መጥፎ ነገር ገጥሞት ይሆን እንዴ?? ብለዉ ሲጠይቁ
....ጎረቤቱህን ታቁታለሁ አንቱንም የሰፈር ሰዉን እየሰከረ እንደሚያስቸግረን ...ዛሬ ምስጋና ለአላህ ይገባዉና  ሰክሮ በመገኘቱ በመንግስት ሀይሎች ታስሯል አሏቸዉ

    አቡ ሐኒፋ ግን የጎረቤታቸዉ መታሰርን እንደ ኸይር ነገር ይዘዉ በዚህ አጋጣሚ  እንዲቶብትላቸዉ ከጀሉ ። በዚሁ ውሳኔያቸው መሠረትም እሱ ታስሮ እኔ እቤቴ ማደር አግባብ አይደለም አላድርም ብለዉ ወደ ታሰረበት ቦታ ሄደው ለአሰሩት የፀጥታ ሀይሎች ወጣቱን እንዲፈቱላቸው ልመናቸውን አቀረቡ፡፡

ያገኙትም መልስ “ወጣቱ ሁለጊዜም እየሰከረ አካባቢን የሚረብሽ ነው˚ የሚል ነበር፤ ይሁን እንጂ ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ግን ልጁን ሳያስፈቱ ከዚያ ቦታ እንደማይሄዱ ተናገሩ፡፡ በስንት ልመና ቡሀላ በመጨረሻም ልጁን አስፈቱት.... ኢማም አቡ ሐኒፋ በበቅሏቸው ላይ ከኋላ አፈናጥጠውት ወደ ሰፈራቸው ተጓዙ።

🔰 ቤታቸዉ አካባቢ እንደደረሱም ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ለወጣቱ ጥያቄ አቀረቡለት፡
....  የምትወደው መጠጥ  ይምጣልህ እንዴ?" አሉት
.....ወጣቱም "በፍፁም! በአላህ ይሁንብኝ ከዚህ በኋላ መጠጥ የሚባል ነገር አልቀምስም፡፡አላቸዉ...እንዳለዉም ከዛ ቀን ቡሀላ መጠጥን እርግፍ አድርጎ ተወዉ፡፡

     ትሁት የሆነ አቀራረብና ማሪኪ ስብዕና ሰዎችን እንዴት ወደ ቀናው ጐዳና እንደሚያስገባቸው ታዘባችሁ⁉️


#ዛሬስ⁉️
ዛሬማ ሙስሊም ወንድም እህት በጠማማ መንገድ ወይ በወንጀል ላይ ሲሆኑ ወገኖችን ወደ አላህ ከመጥራት ከማስቶበት ይልቅ ስም እያወጡ ማሸማቀቅ ስራችን ሁኗል፡፡ ደግሞ ከሁሉም ገርሞ የሚገርመዉ የእኔ አይነት አቂዳ ካልያዝክ እያሉ ሙስሊምን የሚያከፍር ሀይል እየታዘብን ነዉ ፡፡

ኢስላምን ከላይ እስከታች መርምረዉ ተረድተዉ በቀን ሰዉ ወደ እስልምና እየገባ ባለበት ሰአት ደግሞ ያሰለማችሁ እከሌ ስለሆነ ከኩፍር ወደ ኩፍር ነዉ የገባችሁት አልሰለማችሁም የሚል የሀሳብ ምች የመታዉ አእሞሮ ምላስ እየታዘብን ነዉ...

⛔️ቆይ ግን እኛ ሙስሊሞች የምንኖረዉ ኑሮ ግን ምንድን ነዉ ራሳችን ታዝበንዋልን?? የእኛ ባህሪ ለሙስሊሞችም ለሌላ ሀይማኖት ተከታዮች የሚመች ነዉ ወይስ የሚጎረብጥ ነዉ??
እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ


ሼር ማድረግ አይዘንጉ

www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
    በአንድ ወቅት አሳዳሪው ለጥበበኛዉ ሉቅማን መልል ፍሬ እንዲበላ ይሰጠዋል ፡፡ ሉቅማንም ያለምንም መግደርደር የታዘዘውን ፍሬ በላ
.....በድርጊቱ የተደናገጠው  አሳዳሪም ለምን ያለተቃውሞ እንደበላ ሉቅማን ጠየቀው
...... ሉቅማንም እንዲህ ሲል መለሰለት

...." አንተ ለብዙ ዓመታት በኔ ላይ ብዙ መልካም ነገሮች . አድርገሀል፤ በህይወቴ እንድበላ የጠየቅከኝን መራራ ነገር ብበላ ምንም አይደለም፡፡ እንዲህ ባለ የጠለቀ ትህትናው ስሜቱን መግታት ያቃተው አሳዳሪው ዓይኖቹ ላይ ያቆሩትን የእምባ ዘለላዎች ማቆም አቃተው፡፡ እርሱ የሚያውቀው ሉቅማንን በባርነት ንብረቱ አድርጎ እንደሚያሰራው ነው፡፡ ሉቅማን ደግሞ በተቃራኒው አሳዳሪው እያበላውና መጠለያ ስጥቶ እያኖረው መሆኑን በማሰብ ነበር ያሳለፈው፡፡ የሰዎችን ክፉ ጎን ከማየት ይልቅ መልካም ጎን ካላቸው መፈለግ እንደሚገባን ነዉ ያስተማረን


🎖 #የጥበበኛዉ_ሉቅማን_ምክሮች በጥቂቱ🎖


✏️ #ልጄ_ሆይ ! አላህን የመታዘዝ ተግባርህን ታላቅ ንግድህ አድርገው ፣ እንዲያ ካደረክ በሌላ ንግድ ሳትሰማራ ትርፍን ታገኛለህ፡፡

✏️ #ልጄ_ሆይ! አላህን ፍራ ፣ የመፍራትህ ምክንያት ግን ልብህ ጥፋተኛ ሆና በሰዎች ዘንድ ክብር ለማግኘት አይሁን››፡

✏️ #ልጄ_ሆይ ! የምትፈፅማትን ተግባር ክብደቷ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ቢሆንና ቋጥኝ ውስጥ፤ ሰማያት ወስጥ ወይም ምድር ውስጥ የትም ቦታ ብትፈፅም አላህ ያወጣታል፡፡ አላህ ምንም ነገር የማይሰወርበት ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና፡፡

✏️ #ልጄ_ሆይ! ሶላትን ደንቡን አሟልተህ ስገድ። በመልካም እዘዝ። ከክፉም ከልክል፡፡ ላገኙህ ፈተናዎች ሁሉ ታገስ፡፡ ይህ በአፅንኦት ከሚይያዙ ነገሮች ውስጥ የሚካተት ነው ጕንጭህንም ከሰዎች አታዙር፡፡ ምድርም ላይ እየተንዘጣረርክ አትሂድ፡፡ አላህ በኩራት የሚንበጣረርን ሁሉ አይወድምና፡ በእርምጃህም መካከለኛ ሁን፡፡ ስትናገርም ድምፅህን ዝቅ አድርግ። ኪድምፆች ሁሉ አስቀሚያው የአህያ ድምፅ ነውና፡፡


         Š አሚር ሰይድ



◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
✨አንድ ቀን  አቡበከር ሲዲቅ(ረ.ዐ) በእንድ የአትክልት ስፍራ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ አንዲት ወፍ ተመለከቱ:: በዚህን ጊዜ ከፍተኛ የጭንቀት ትንፋሽ ወደ ውስጥ በመሳብ፡-

....“ #ወፊት_ሆይ! በእርግጥ እድለኛ ነሽ። እንደ ልብሽ ትጠጫለሽ፣ ትበያለሽ፣ ትበሪያለሽም፡፡ ግን የትንሣኤ ቀን ፍራቻ የለብሽም።
#እንደ_አንቺ ብሆን ምንኛ በታደልኩ😔፡፡” በማለት ለትንሳኤ ቀን ያላቸውን ፍራቻ ገልፀዋል፡፡


  🔶የዉመል ቂያማን ሲያስታዉሱ:- “ምነው በአንድ እንሰሳ በመበላት ሕይወቱ የሚያቆመውን የሳር ቅጠል ወይም በመቆረጥ የሚወገደውን ዛፍ ሆኜ በቀረሁ ይሉ ነበር፡፡

#እኛስ_ለነገዉ_ሞት_ለትንሳኤዉ ቀን ምን አዘጋጅተናል???


✏️አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ብሏል

እናንተ ሰዎች ሆይ የሰአቲቱ መናወጥ በጣም ከባድ ነዉ፡፡በምታዩት ቀን አጥቢ ሁሉ ከአጠባችዉ ልጅ ትፈዝዛለች፡፡የእርግዝና ባለቤት የሆነችዉ ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋፉች፡፡ሰዎች በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ ሆነዉ ታያለህ(ሐጅ1-2)

         Š አሚር ሰይድ


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የትዳር_ምርጫህ_ማን_መሆን_አለባት??

የአሁን ወንድ ወንድ አይደለም ደዩስ ነዉ🙄

4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️ነብዩሏህ ዙልቀርነይን (ዐ.ሰ) ከመሞታቸው በፊት ኑዛዜ ትተው ነበር...


ኑዛዜያቸዉም
   ስሞት እጠቡኝ፣ ከፍኑኝ፣ አካሌን ሏሳ ሳጥን ውስጥ አኑሩት፡፡ ነገር ግን እጆቼን ወደ ውጭ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ አገልጋዮቼ ሁሉ ከኋላዬ ይከተሉ፡፡ ንብረቶቼን በበቅሎ ጫኑ፡፡ ምንም እንኳ በብዙ ዓለማዊ ፀጋዎች ተከብቤ ብኖርም፣ ምንም ያህል ትልቅ ኃይል የነበረኝ ሰው ብሆንም ያ ሁሉ አልፎ ወደማይቀረው ዓለም ወደ አኼራ ባዶ እጄን እየሄድኩ መሆኔን ሰው ሁሉ እንዲያይ እፈልጋለሁ፡፡

እጠቀምባቸው የነበሩ ነገሮች ሁሉ አብረውኝ ወደ አኼራ እንዳልተጓዙ ሕዝቤ ይመልከት፡፡ አታላይና ዋሾ በሆነችው ዱንያ እንዳይታለሉ ያደርጋቸዋል፡፡”ብለዉ ስለነበር ከሞቱ ቡሀላ ንዛዜያቸዉ እንዳሉት ሆኖላቸዋል፡፡

አላህ በቁርአን እንደዚህ ማለቱን አስታውስ፡-
ከህዝቡም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸዉ፡፡ጊዚያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰአት አይቆዩም ከጊዚያቱ አይቀድሙም(አል አዕራፍ 34)


✏️✏️ #ነብዩሏህ_ዙልቀርነይን ለህዝቦቻቸዉ ሲያስተምሩ
እንዲህ ብለዋል

☞ #ቁጣህን_ተቆጣጠር፤ ሸይጧን ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ሰውየውን ለከፉ ድርጊት የሚያነሳሳው በተቆጣበት ወቅት ነው፡፡

☞ #እትቸኩል፣ ከቸኮልከ ማግኘት የሚገባህን ሳታገኝ ትቀራለህ፡፡

☞ላንተ ቅርብም ይሁን እሩቅ ለሰዎች ሁሉ የተመቸህ ሁን፡፡ ከማን አለብኝነት፤ ከክህደት እና ከበደል ተጠንቀቅ!”

ብለዋል፡፡
=======\\=====\\=====\\=====\\\===


✏️✏️ ኸድር #ነብዩላህ_ሙሳ(ዐ.ሰ.) ጋር ተገናኝተው ሲለያዩ ሙሳ ኸድርን ምክር እንዲለግሷቸው ሲጠይቋቸው

ኸድር እንዲህ በማለት መከሯቸው 
☞ ሰውን ጠቃሚእንጂ ጎጂ መሆንየለብህም፡፡
☞ ፈገግተኛ እንጂ ቁጡ መሆን የለብህም
☞ ክርክር አታብዛ በሆነው ባልሆነው አትከራከር
☞ ያለምንምጉዳይጉዞ (ዙረት) አታብዛ፣
☞ በሚያስገርምሁኔታ እንጂ በማይረባ ነገር ሳቅ አታብዛ፡፡
ብለዋቸዋል



            Š አሚር ሰይድ


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🎖🎖 ዳዉድ (ዐ.ሰ) ለሱለይማን (ዐ.ሰ) እነዚህን ጣፋጭ ምከሮች ለገሷቸው:-

☞ #ልጄ ሆይ! ከቀልድ ተጠንቀቅ፡፡ ጥቅሙ ትንሽ ነው፡፡ ፀፀትን እንጅ ሌላ እታተርፍበትም፡፡

☞ #ቁጣንም_ተጠንቀቅ! ቁጣ የባለቤቱን ልክ ያሳጣል፡፡ ከተቆጣህ ቦታውን ለቅቀህ ሒድ፡፡

☞ እርባና ቢስ፣ ቆሻሻ ጓደኝነት አትመሥርት!

☞ ወደ ሰዎች አትመልከት፡፡አላህ (ሱ.ወ) ለሌሎች በሰጠው ፀጋ መጎምዠት በራሱ ድህነት ነው፡፡

☞ ነፍስህንም ሆነ ምላስህን እውነትን ብቻ አስለምዳቸው፡፡

☞ዛሬህ ከነገህ የበለጠ እንዲሆን ጣር፡፡ዛሬን በቀልድ አታሳልፍ ተጠቀምበት፡፡

☞ ተቅዋን ተላበስ፤ ታዘልቅሃለች!

☞ ከአላህ ራሕመት ተስፋ አትቁረጥ! ረሕመቱ ሁሉንም ያዳርሳልና!


               Š አሚር ሰይድ
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ â—ˆ
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
2025/06/18 09:05:11
Back to Top
HTML Embed Code: