ISLAM_AND_SCIENCE Telegram 6327
#ለምን_ለብቻዋ_መቆየትን_እንደመረጠች_ታቃለህ?

በዚህ ዘመን እውነተኛ ፍቅርን መፈለግ ከንቱ ድካም እየመሰለ መጥቷል። አየህ ለብቻዋ መሆንን የመረጠችው ወንድ አጥታ አይደለም። የምትፈልገውን ፍቅር የሚያፈቅር፣ የምትመኘውን ፍቅር የሚፈቀር ሰው ነው ፈልጋ ያላገኘችው። ያ የድሮውን የ90'ዎቹን ፍቅር .... ከልብ የነበረውን፣ ምግብ የማያስበላ የነበረውን፣ እንቅልፍ የሚያሳጣውን፣ ጥልቅ የነበረውን፣ ያለህን ሁሉ አለስስት የምትሰጥበትን .... ያንን ፍቅር ነው ያጣችው።

ዛሬ ዛሬ የጠበሳ መርሆዎች ተቀይረዋል። ዛሬ አካሄዶች ተለውጠዋል።

{ እያወራን ነው }

ዛሬ ፍቅር የሚጀምረው "እያወራን ነው" ከሚለው ነው። ለማያውቁት ሰው " ሀይ " ብሎ መፃፍ የፍቅር መነሻ ሆኗል። በየቀኑ መፃፃፍ ነው፣ በየጊዜው መደዋወል ነው፣ መጀናጀን ነው .... ከፍ ሲልም መገናኘት ይኖረዋል። ከዛ .... ምን ላይ ናችሁ ሲባል ... እያወራን ነው

እያወራን ነው ውስጥ ቃልኪዳን የለም። ፍቅረኛዬ ናት ... ፍቅረኛዬ ነው የለም። በተመሳሳይ ሰዓት ስድስት ሴቶችን ያወራል ... በተመሳሳይ ሰዓት አስራ አምስት ወንዶችን ታወራለች (የሴቷ የበዛው እሷ ማውራት ከፈለገች የሚመልሱላት ወንዶች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑን ለማሳየት ብቻ ነው)

ለጊዜው ችግር ያለበት ባይመስልም አስቀያሚ ነገር ይዞ ሊመጣ ይችላል። በይፋ የሚጠቀስ አካሄድም ሆነ ስርዓት ስለሌለው ... አንደኛው ወገን በትክክል ወደ ፍቅር እያመሩ እየመሰለው ሌላኛው ወገን እንደ ጊዜ ማሳለፊያ እየተደበረበት ሊሆን ይችላል። አንቺ የምትሰሪው ነገር ስለሌለሽ ታወሪው ይሆናል። እሱ ለጓደኞቹ ተጣብሰናል ይላል። ነገ ከሌላ ወንድ ጋር አየናት ሲባል ካልገደ|ልኳት ወይንም ራሴን ካላጠ|ፋሁ አገር ይያዝልኝ ውስጥ ነው።

{ ፈታ እያልን ነው }

ማውራቱ ወደ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ያድጋል። መገናኘት ... እየተገናኙ መላፋት ... እየተላፉ መሳሳም ... እየተሳሳሙ መተኛት ... እየተኙ "ኧረ ምንም የለም"፣ "ፈታ እያልን ነው"፣ " ወንድም እና እህት ነን" ... ይሆናል።

ስለነገ ማውራት ..... ምን እየሆንን ነው ማለት .... የለም። ቢያንስ አንደኛው ወገን "ዋናው ደስተኛ መሆናችን ነው" የምትለውን ቀልድ አስጠብቆ ይሄዳል። ዛሬን ደስታ ይሰጥ ይሆናል። ግን መታመን፣ ጥረት፣ ድካም ... ውስጡ የለውም። ፈታ ለማለት ፍቃደኛ ከሆነው ጋር ሁሉ ፈታ ይላሉ። አንደኛው ወገን እንዴ? ማለት ሲያመጣ .... ምን ታካብጃለሽ ካልፈለግሽ ንኪው ነው መልሱ።

አረገዝኩ ስትይ "እንዴት" ይልሻል ። ኮንዶም እንጠቀም ስትይ ስሜትሽ ይበርዳል ያለሽ፣ ፒልስ ተጠቀሚ ስትላት ጨጓራዬን ያመኛል ያለችው በኋላ ማህፀኗ "ሲታመም" ለቅሶ ይሆናል። "አስወርጅው" የሚለው ትቶሽ ከመሄዱ በፊት የሚለግስሽ የመጨረሻው ምክሩ ይሆናል። ምክንያቱም ጭንሽ ስር የነበረው "ፈታ" ለማለት እንጂ አባት ለመሆን አልነበረም።

{ እየተያየን ነው }

ይሄ በጓደኝነት እና በትዳር መሀል ያለው ነው። ቅልጥ ያለ የፍቅር ጨዋታ እስከ ማባያው (እንጧዬ) ይቀርብበታል። መላፋት፣ አብሮ ማምሸት፣ አብሮ ማደር፣ መሳሳም ይኖረዋል .... ሁሉም ግን በር ተዘግቶ እንጂ በአደባባይ አይደረግም። ለምን? ገና እየተያዩ ነዋ።

ከጓደኛ ወይም ከቤተሰብ ጋር ድንገተኛ እያስመሰሉ መተዋወቅ ይኖራል። ጓደኛዬ ነው ... ጓደኛዬ ናት ማስተዋወቂያ ታርጋዎቹ ናቸው። ለብቻ መቆየትን ካለመፈለግ፣ ቋሚ ግንኙነትን ወደ ትዳር አሳድጎ አብሮ ለመኖር ካለመፈለግ ወይም ትዳርን ከመፍራት፣ ሀላፊነት ከመሸሽ፣ የአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ በማየሉ ሊሆን ይችላል።

ሴቷ ሚስት ለመሆን ምን ቀራት እስኪባል ድረስ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በፍቃደኝነት ታደርጋለች። የቤቱ ቁልፍ አላት፣ አልጋውን የምታነጥፈው እሷ ናት፣ ልብሱን የምታጥበው እሷው፣ የተዝረከረከው ቤት መልክ የሚይዘው እሷ ስትመጣ ይሆናል፣ ካልሲዎቹ ከተወረወሩበት የሚለቀሙት በእሷ ነው፣ በትምህርት ቤት ነኝ ሰበብ ውሎዋ እዛው ነው .... በድንገት ኮንዶም እስክታገኝ ድረስ

ጋባዧ እሱ ነው፣ ካርድ የሚሞላው እሱው፣ ከእነ ጓደኞቿ የሚያዝናናት እሱ ነው፣ እነዛን በስክሪንሹት የምትሰበስባቸውን ቦርሳ እና ሹል ጫማዎች የሚገዛው እሱ ነው .... ስልክ ማንሳት እስኪያቆም ድረስ ... ያኔ በሌላ ሴት ተክቷታል

እነዚህ አዙሪቶች ሲደጋገሙ ማንነትን ያሳጣሉ። ሁሉም ሰው በህይወቱ የሆነው ጊዜ ላይ ነገሮች አንድ ደረጃ እንዲያድጉ እና ወደትዳር እንዲሄዱ ይፈልጋል። መዋደድ፣ መፈላለግ ወይም አብሮ መተኛት ብቻ በቂ አለመሆኑን ይገነዘባሉ።

የሚያከብራት፣ በክፉም በደጉም አብሯት የሚቆም፣ የምታምነው እና የምትተማመንበት ወንድ ትፈልጋለች። በስሜትም በእይምሮም የበሰለ እና ፍቅር ማለት ከማውራት፣ ፈታ ከማለት እና ከመተያየት የዘለለ ቁምነገር ያለው ነገር እንደሆነ የሚገባው ወንድ ትፈልጋለች።

የሚያወራላት፣ የሚሰብክላት፣ የሚጀነጅናት ሳይሆን በተግባር የሚያሳያት ወንድ። ያልቻለበትን ሰበብ እና ምክንያት የሚደረድር ሳይሆን ጥረቱን የሚያሳያት። ግራ የሚያጋባት ሳይሆን ሁልጊዜም ጥርት ያለ አካሄድ የሚመርጠውን ወንድ ትፈልጋለች። አብሯት እያወራት የሚተኛውን እንጂ ከተኛች በኋላ የሚፅፍላትን አትፈልግም። ታማኝነት መገለጫው የሆነውን እንጂ ውሸት የማያልቅበትን አትፈልግም። ጥንቅቅ ያለ ሰው አይደለም እየፈለገች ያለችው ራሱን የሆነውን ነው።

ግማሽ ፍቅር አዝሏታል። በፍቅር ስም መንዘላዘል አድክሟታል። የተረጋጋ እና የሚጨበጥ ነገር ብቻ ነው የምትፈልገው። የሚሰብራት ሳይሆን እየሰራት የሚኖረውን ትፈልጋለች።

የሚገባትን የሚሰጣትን እየጠበቀች ነው .... ብቻዋን የምትቆየው እሱ እስኪመጣ ነው !!

ብቻዋን የምትቆየው የሚገባትን የሚሰጣት እስኪመጣ ነው !!

© Abby Junior

◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
             www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group

tgoop.com/Islam_and_Science/6327
Create:
Last Update:

BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6327

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram offers a powerful toolset that allows businesses to create and manage channels, groups, and bots to broadcast messages, engage in conversations, and offer reliable customer support via bots. Telegram message that reads: "Bear Market Screaming Therapy Group. You are only allowed to send screaming voice notes. Everything else = BAN. Text pics, videos, stickers, gif = BAN. Anything other than screaming = BAN. You think you are smart = BAN. “[The defendant] could not shift his criminal liability,” Hui said. The administrator of a telegram group, "Suck Channel," was sentenced to six years and six months in prison for seven counts of incitement yesterday. Ng was convicted in April for conspiracy to incite a riot, public nuisance, arson, criminal damage, manufacturing of explosives, administering poison and wounding with intent to do grievous bodily harm between October 2019 and June 2020.
from us

Telegram ISLAMIC SCHOOL
FROM American