tgoop.com/Islam_and_Science/6325
Last Update:
#ምንም_ረዳት_የለኝም_ምን_ይሻለኛል??
✍🏼አሚር ሰይድ
ማሊክ ኢብኑ አሽጀዒይ የነብዩ ﷺ ሶሀባ ሲሆን በአንድ ወቅት እሳቸው ዘንድ መጥቶ አንድ ልጄ ጦርነት በሄደበት ጠላት ማርኮ አስቀረው
ከዛም ወደ ነብዩ ﷺ በመሄድ ምንም ረዳት የለኝም እኔንና እናቱን እሱ ነበር የሚካድመን ምን ይሻለኛል?? ሲላቸው
.....ነብዩ ሙሀመድ ﷺ አላህን ፍራ ታገስ ባለቤትህም አንተም #ላሀውለዉላ_ቁወተኢላቢላህ (ከአላህበስተቀር ኃይልም ብልሀትም የለም) ዚክር በተደጋጋሚ አብዙ ብለዉ መለሱለት
ወደባለቤቱ ዘንድ ተመልሶ ሲሄድ ለባለቤቱም የተባለውን ሲነግራት በዚሁ ተስማምታ እሷም እሱም ቀንም ለይልም በተደጋጋሚ ለሀዉለዉላ ቁወተ ኢሊቢላህ እያሉ እያለ ልጁ በአላህ እርዳታ የተሳረበት ከጠበባቂዎች እጅ እንዲያመልጥ አድርጎት ይወጣል፡
መውጣትም ብቻ ሳይሆን ጠላት ከየትም ማርኮ ያከማቸውን በጎችና ግመሎች ይዞ ነበር ያመለጠው፡፡ አንዳንድ ኡለማዎች እንደሚሉት 4000 በጎችና 50 ግመሎች ይዞ ወደቤቱ ሲመጣ አባትየው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ በመሄድ ልጄ በሰላም መጥቶልኛል የጠላትን ብረት ነውና ይዞ የመጣው መጠቀም እንችላለን?? ሲላቸው
.... አዎ ትችላላችሁ ይህ የተቅዋ ውጤት ነው አንተና ባለቤትህ ያደረጋችሁት የተቅዋና የትእግስት ውጤት ነው ሰው ሁሉ እነዚህን ነገሮች አጥብቀው ቢይዙ ኖሮ ይሄ በቂያቸው ነበር።ወዲያውኑ ይሄንን አስመልክቶ የተቅዋና የትእግስት ውጤት መሆኑን የሚገልፅ የቁርአን አያ ወረደ
وَمَن یَتَّقِ ٱللَّهَ یَجۡعَل لَّهُۥ مَخۡرَجࣰا
{ وَیَرۡزُقۡهُ مِنۡ حَیۡثُ لَا یَحۡتَسِبُۚ وَمَن یَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسۡبُهُۥۤۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَـٰلِغُ أَمۡرِهِۦۚ قَدۡ جَعَلَ ٱللَّهُ لِكُلِّ شَیۡءࣲ قَدۡرࣰا }
አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡
ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡[Surah At-Talâq2- 3]
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6325