tgoop.com/Islam_and_Science/6335
Last Update:
በአንድ ወቅት አሳዳሪው ለጥበበኛዉ ሉቅማን መራራ ፍሬ እንዲበላ ይሰጠዋል ፡፡ ሉቅማንም ያለምንም መግደርደር የታዘዘውን ፍሬ በላ
.....በድርጊቱ የተደናገጠው አሳዳሪም ለምን ያለተቃውሞ እንደበላ ሉቅማን ጠየቀው
...... ሉቅማንም እንዲህ ሲል መለሰለት
...." አንተ ለብዙ ዓመታት በኔ ላይ ብዙ መልካም ነገሮች . አድርገሀል፤ በህይወቴ እንድበላ የጠየቅከኝን መራራ ነገር ብበላ ምንም አይደለም፡፡ እንዲህ ባለ የጠለቀ ትህትናው ስሜቱን መግታት ያቃተው አሳዳሪው ዓይኖቹ ላይ ያቆሩትን የእምባ ዘለላዎች ማቆም አቃተው፡፡ እርሱ የሚያውቀው ሉቅማንን በባርነት ንብረቱ አድርጎ እንደሚያሰራው ነው፡፡ ሉቅማን ደግሞ በተቃራኒው አሳዳሪው እያበላውና መጠለያ ስጥቶ እያኖረው መሆኑን በማሰብ ነበር ያሳለፈው፡፡ የሰዎችን ክፉ ጎን ከማየት ይልቅ መልካም ጎን ካላቸው መፈለግ እንደሚገባን ነዉ ያስተማረን
🎖 #የጥበበኛዉ_ሉቅማን_ምክሮች በጥቂቱ🎖
✏️ #ልጄ_ሆይ ! አላህን የመታዘዝ ተግባርህን ታላቅ ንግድህ አድርገው ፣ እንዲያ ካደረክ በሌላ ንግድ ሳትሰማራ ትርፍን ታገኛለህ፡፡
✏️ #ልጄ_ሆይ! አላህን ፍራ ፣ የመፍራትህ ምክንያት ግን ልብህ ጥፋተኛ ሆና በሰዎች ዘንድ ክብር ለማግኘት አይሁን››፡
✏️ #ልጄ_ሆይ ! የምትፈፅማትን ተግባር ክብደቷ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ቢሆንና ቋጥኝ ውስጥ፤ ሰማያት ወስጥ ወይም ምድር ውስጥ የትም ቦታ ብትፈፅም አላህ ያወጣታል፡፡ አላህ ምንም ነገር የማይሰወርበት ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና፡፡
✏️ #ልጄ_ሆይ! ሶላትን ደንቡን አሟልተህ ስገድ። በመልካም እዘዝ። ከክፉም ከልክል፡፡ ላገኙህ ፈተናዎች ሁሉ ታገስ፡፡ ይህ በአፅንኦት ከሚይያዙ ነገሮች ውስጥ የሚካተት ነው ጕንጭህንም ከሰዎች አታዙር፡፡ ምድርም ላይ እየተንዘጣረርክ አትሂድ፡፡ አላህ በኩራት የሚንበጣረርን ሁሉ አይወድምና፡ በእርምጃህም መካከለኛ ሁን፡፡ ስትናገርም ድምፅህን ዝቅ አድርግ። ኪድምፆች ሁሉ አስቀሚያው የአህያ ድምፅ ነውና፡፡
© አሚር ሰይድ
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6335