tgoop.com/Islam_and_Science/6330
Last Update:
🔸 #የጌታዬን_ግርዶ_እንዴት_እዳፈራለሁ?🔸
✍🏼አሚር ሰይድ
አንድ ደሀ ወጣት እየዞረ እቃ የሚሸጥ ነበር፡፡በመንገዶች ላይ እየተዘዋወረ ይሸጣል አንዲት ባዶ አላህን የማትፈራ የሆነች ሴት ነበረች… ሀራምን ከመስራት አትቆጠብም፡፡የሸይጧን ተላላኪ ነበረች…
አንድ ቀን በቤቷ አጠገብ አለፈ… በበሩ በኩል ብቅ ብላ ስለ ሸቀጦቹ ጠየቀችውና ነገራት.. እቃዎቹን እንድታይ እቤት እንዲገባ ጠየቀችው ፡፡ ቤት ሲገባ በሩን ቆለፈችበትና ወደ ሀራም ጋበዘችው... ወጣቱ ልጅ ጮኸ፡፡ …ጊዜያዊ ጣፋጭ ነገሩ ጠፍቶ ፀፀቱ በሚቀርበት ጊዜ የሚኖረውን ሁኔታ አስታወሰ… ዚና የሰራባቸው አካላቶች... የተራመደባቸው እግሮቹ... የዳበሰባቸው እጆቹ... የተናገረበት ምላሱ… በእሱ ላይ የሚመሰከሩበትን ቀን አስታወሰ... የእሳትን አቃጣይነትና የአላህን ቅጣት አስታወሰ...
✏️ዝሙተኞች በእሳት ውስጥ እንዲንጠለጠሉ ተደርገው ከብረት በሆነ አለንጋ ይገረፋሉ... ከዝሙተኞች አንደኛው ከቅጣቱ እንዲያድኑት ጩሆ ሲጠይቅ መላኢኮች.. አላህን ሳትፈራና ይቆጣጠረኛል ሳትል ሀራም በመስራት ስትስቅ ስትደሰት- ስትፈነድቅ ... ይሄ አሁን ያሰማሀው ድምፅ የት ነበር? ይሉታል...
ወጣቱ ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለው የተናገሩትን ሐዲስ አስታወሰ፡፡ “የሙሐመድ ህዝቦቸ ሆይ! ወላሂ እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽን ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር፡፡”
በአንድ ወቅት ረሱል ﷺ በህልማቸው ያዩትን አስታወሰ... ከታች ሰፊ ከላይ ጠባብ በሆነ ምድጃ በሚመስል ጠባብ ቦታ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ራቁታቸውን ሆነው ይጮሀሉ ያጓራሉ..…. የእሳት ነበልባል ከስራቸው ይመጣባቸዋል ነበልባሉም በመጣባቸው ጊዜ ከግለቱ ብርታት የተነሳ ይጮሀሉ ረሱልም ﷺ
ጂብሪል ሆይ! እነዚህ ምንድን ናቸው? ብለው ጠየቁት ጂብሪልም፡- እነዚህ ሴት ዝመተኞችና ወንድ ዝሙተኞች ናቸው እስከ የውመል ቂያማ ይህ ቅጣታቸው ነው፡፡ " ብሎ መለሰላቸው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የአኼራ ቅጣት እጅግ የበረታና ዘልአለማዊ ነው… አላህ (ሱ.ወ) ምህረት እንዲያደርግልንና ሰላም እንዲያደርገን እንጠይቀዋለን…
✨✨ነፍስያውም፡- “ስራና ትቶብታለህ” አለችው፡፡ እሱም አዑዙቢላህ የጌታዬን ግርዶ እንዴት እዳፈራለሁ? የተከበረውና የተላቀው አላህ ከበላያችን ሆኖ እየተመለከተን የማትፈቀድልኝን ሴት እንዴት እመለከታለሁ? _እንዴት ከፍጡራን እየተደበቅን ፈጣሪ ፊት እናምፃለን? …አለ፡፡
ወደ በሩ እየተመለከተና እንዴት መውጣት እንደሚችል እያሰበ ዝም አለ… አመፀኛዋ ሴትም:- ወላሂ የምፈልገውን ካልፈፀምክ ጮኼ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አደርግና ይህ ወጣት ዘሎ ቤቴ ገባብኝ እላለሁ የዚህ ጊዜ ሞት ወይም እስር እንጂ ሌላ አይጠብቅህም” አለችው፡፡ ጥብቁ ወጣት ይንቀጠቀጥ ጀመር.. በአላህ አስፈራራት ምንም አልመሰላት ይህን ሁኔታ ያየ ጊዜ ከሷ የሚገለልበትን ዘዴ ማሰብ ጀመረ… ከዚያም ሻወርና ሽንት ቤት እፈልጋለሁ አላት፡፡ እሷም ወደ ሽንት ቤቱ አመለከተችው
መፀዳጃ ቤት ሲገባ ወደ መስኮቱ ተመለከተ… ነገር ግን በመስኮቱ ማምለጥ አይችልም... ከእሷ የሚላቀቅበትን መንገድ አሰላሰለ…… ሠገራ ወደሚጠራቀምበት ሄደና ከሰገራው እያነሳ ልብሱን እጁንና ሰውነቱን መቀባት ያዘ ከዚያም እሷ ጋር መጣ… ያየችው ጊዜ ጮኸች… እቃውን ፊቱ ላይ ወርውራለት ከቤቷ አባረረችው
ቤቱ እስኪደርስ ድረስ ህፃናት ከኋላው ሆነው እብድ! ... እያሉ ይጮሁበት ነበር፡፡ ቤት ሲደርስ ነጃሳውን አስወገደና ገላውን ታጠበ … ከዚያም በኋላ ወጣቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ሰውነቱ የሚስከ ሽታ የሚስክ ሽታ ይሸት ነበር፡፡ (ታሪኩን ኢብኑ ጀውዚ ጠቅሰውታል)
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━ ◈
4 another channal👇
www.tgoop.com/Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6330