Telegram Web
👉በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ድልድይ አሁናዊ ገፅታ

🚧በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ተንጣሎ በሚገኘው የዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ ድልድይ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል ቁመና ላይ መድረሱን የባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

@etconp
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👉GRP ፓይፕ ምንድ ነው?

✳️GRP (glass reinforced plastic) ፓይፕ በመባል ይታወቃል፡፡

🚧በተለይ ከጎሮ ወደ ቱሉ ዲምቱ ስትጓዙ ይህንን ምርት አይታችሁ ይሆናል? ይህ ምርት ምንድነው? የማን ነው? ለምን አገልግሎት ይውላል …ሌላም ሌላም… ብላችሁ እየጠየቃችሁ ይሆናል?

🔰እስቲ ስለ GRP ፓይፕ ትንሽ እናስተዋውቃችሁ፦

⏺ይህ ምርት አውሮፓውያኑ ከዛሬ 30 አመት ጀምሮ እንደሚጠቀሙበት ይነገራል፡፡

⏺ከአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት መጠቀም የጀመረው ደግሞ አንጋፋው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነው፡፡

❇️GRP ከተለያዩ ውህዶች የሚሰራ ሲሆን፣ ባለስልጣኑ ከ200 እስከ 2000 ሚሊ ሜትር ስፋት ያለውን GRP ፓይፕ ይጠቀማል፡፡

⏺GRP ከሌላው ፓይፕ (UPBC) ፓይፕ የሚለየው በፍሳሽ ማስተላለፊያነት ጥቅም ላይ ሲውል ቶሎ ለብልሽት አይዳረግም፣ ከለር አይቀይርም፣ በቀላሉ አይሰበርም፣ አይዝግም፣ ይለጠጣል፣ ቆሻሻ አይዝም፡፡

❇️ባለስልጣኑ GRP መጠቀም ሲጀምር፤
እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል? እንዴት ይቆረጣል ? እንዴት ይገጠማል? እንዴት ይዘረጋል?

🚧የተለያዩ ኬሚካል ውህድ እንደመሆኑ ሲሰራ ምን አይነት ጥንቃቄ መደረግ አለበት ? የሚለውን በዘርፉ ባለሙያዎች በቂ ስልጠና በመስጠት ነው፡፡

📌በአሁኑ ሰዓትም ይህንን ምርት በከተማው ውስጥ በምስራቅ ተፋሰስ ስር ለሚሰራው የፍሳሽ መሰረተ ልማት የ40 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።

Via AAWSA

@etconp
👉በታላቁ ወንዝ ላይ በርዝመት ትልቁ የትስስር መንገድ ተገነባ

🚧በባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ ትልቅ የትስስር መንገድ ግንባታ በውጤታማት ተጠናቅቋል።

✳️የግንባታው ውል በ2011 ዓ.ም ሲፈረም ሥራውን የቻይናው ኮምኑኪዬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ በኃላፊነት ተቀበለው።

✳️ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የቱርክ ድርጅት እና ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች የተባለ ሀገር በቀል ተቋም በጋራ በመሆን ነበር ግንባታውን እውን ለማድረግ የማማከር ስራውን የሰሩት።

✳️የትራንስ አፍሪካ ሀይዌይ ኔትወርክ አካል የሆነው ይህ ድልድይ ኔትወርኩ ከሚያገናኛቸው 10 ኮሪደሮች አንዱ ነው።

🔰65.683 ኪሜ የሚሸፍነው፤ ከግብፅ ተነስቶ፤ በሱዳን በማቋረጥ ኬንያ እና ታንዛንያን አልፎ እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚያገናኘው የኔትዎርክ መንገድ አካልም ነው።

🔰ድልድዩ የተንጠልጣይ እና የሳጥን ቅርፅ ያላቸውን ረጃጅም ድልድዮች ዲዛይንን በማዋሃድ በአዲስ ጥበብ የሚገነባው ኤክስትራዶስድ የሚሰኘው ዓይነት ነው።

🔰የ380 ሜትር ርዝማኔ አለው የጎን ስፋቱም 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል።

🔰5ሜትር የእግረኛ መሄጃ የተሰራለት ሲሆን በሁለቱም አቅጣጫ ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚሆን መስመርን ያካተተም ነው።

🔰ቀድሞ የነበረው ድልድይ ከ60 ዓመታት በላይ ለማህረሰቡ የትራንስፖርት ማመላለሻ መንገድ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ለአዲሱ ቦታውን የሚያስረክብም ይሆናል።

❇️ግንባታው በአንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን ብር (1,437,000,000) የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።

Via EBC

@etconp
👉የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ባደረገው 23ተኛው አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አርክቴክት ራሄል ለማ ን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

🚧ራሄል ለማ በ 1999 ዓም በኪነህንጻ ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ከ EiABC ተቋም የመጀመርያ ዲግሪዋን  ያገኘች ሲሆን በ2009 ዓም ደግሞ እዛው EiABC በ ከተማ እና ኪነህንጻ ቅርስ አጠባበቅ ሁለተኛ ዲግሪዋን አግኝታለች።

✳️በኢቲጂ፣ ኤዲት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቋሞች ውስጥ በሙያዋ የሰራች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በእውቁ የፋሲል ጊዮርጊስ አማካሪ ቢሮ በሙያዋ እየሰራች ትገኛለች ።

❇️የተክለሐይማኖት፣ የግቢገብርኤል፣ የስላሴ አብያተ ክርስትያናት እድሳት፣ የጅማአባጅፋር ፣ የቢትወደድ ኃይለጊዮርጊስ ቤት እንዲሁም የኢዮቤልዩ ቤተመንግስት እድሳት ስራ ላይ በማማከር ተሳትፋለች።

Congregations Rahel Lema

       @etconp
👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን አስጀመሩ

🚧ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

✳️የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታው የተጀመረው በአዳማ እና ሞጆ ከተሞች መካከል በምትገኘው ሉሜ ወረዳ ነው።

✳️የኢኮኖሚ ዞኑ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርምን፣ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምን እና የአነስተኛ ቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን ለማጎልበት እንዲሁም የማይበገር የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ለመገንባት ታስቦ በጨፌ ኦሮሚያ ውሳኔ መሠረት ወደ ሥራ የገባ ነው።

✳️የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፕሮጀክት ዋና ዓላማም በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድ ማዕከል መገንባት እንዲሁም የአፍሪካ የፋይናንስ ማዕከል በመሆን የቀጣናውን ኢኮኖሚ ፈጣን እና ጠንካራ ማድረግ ነው።

✳️የፕሮጀክቱ ግንባታ ከ24 ሺህ ሔክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚከናወን እንደሆነም የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

@etconp
Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
Photo
👉አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ

✳️የውል ስምምነት፡- መጋቢት 18 ቀን 2011 ዓ.ም.

✳️የሥራ ተቋራጭ፡- አለማቀፉ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ

✳️አማካሪ ድርጅት፡- ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የቱርክ አማካሪ ድርጅት ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች ድርጅት ከተባለ አገር በቀል ንኡስ አማካሪ ጋር በጋራ በመሆን ያከናውኑታል

✳️የግንባታ ወጪ፡- 1,437,000,000 (አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ብር)

🚧የግንባታውን ወጪ የሸፈነው፡- የኢትዮጵያ መንግስት

🚧የግንባታው አይነት፡- ዲዛይንና ግንባታ /ተቋራጭ ድርጅቱ ዲዛይንና ግንባታን በጋራ አካቶ የሚሰራበት የኮንትራት ውል አይነት ነው/፡፡

🚧የድልድዩ አይነት፡- የተንጠልጣይና የሳጥን ቅርፅ ያላቸውን ረጃጅም ድልድዮችን ዲዛይን በማዋሀድ በአዲስ የዲዛይን ጥበብ የሚገነባው ኤክስትራዶስድ የተባለውን አይነት ድልድይ ነው፡፡

🔰ርዝመት፡- 380 ሜትር

🔰የጎን ስፋት፡- 43 ሜ. የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ግዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፡፡

⏺በተጨማሪም የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር በሁለቱም አቅጣጫ እንዲሁም 5 ሜ. የእግረኛ መሄጃን ያካተተ ነው።

#የድልድዩ_ግንባታ_ስራ፡-

📌ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡
ይህ ድልድይ ኤክስትራ ዶዝድ የሚባል ስያሜ የተሰጠው ተንጠልጣይ ድልድዮች (ሰስፔንሽን) ከሚባሉት ድልድዮች የተለየና ይልቁን የመኪና ተሸካሚው ዴክ ከፊትና ከሁዋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (በገመዶች የተወጠረ) ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካይነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፡፡

☄ይህ አይነቱ ድልድይ የረጃጅም ኬብል ስቴይድ (በገመድ የተወጠረ) ድልድዮችና የረጃጅም ቦክስ ገርደር አይነት ድልድዮች ውሁድ ሆኖ ስፋታቸው ከ 250 ሜትር እከ 500 ሜትር በሚደርሱ ወንዞች ላይ አመቺና ወጪ ቆጣቢ ሆነው እንዲሰሩ በመጀመሪያ በፈረንሳይ ሀገር የተፈለሰፈ በቀጣይ ግን በብዛት ጃፓን ሀገር ስራ ላይ የዋለ የድልድይ አይነት ነው፡፡

☄የተጠናቀቀው የድልድዩ የምህንድስና ሰነዶች እንደሚያመለክቱት የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ (piers) 7 ሜትር ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሀና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፡፡

✅ለድልድይ ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ #ዋና_ዋና_ግብዓቶች

✳️የተለያዩ የጥንካሬ ደረጃ (Grade C-30, C-40, C-50, and C-55) ያላቸው አርማታ 54,138.68 ሜ.ኩ

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የአርማታ ብረት 9,241.45 ቶን

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የማንጠልጠያ እና መወጠሪያ 474.37 ቶን

👍የድልድይ ግንባታ ሥራውን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ከተሠሩት #የተለየ_የሚያደርገው

🔰የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጅ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ

🔰ድልድዩ በከተማ ውስጥ እንደመሠራቱ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የቱሪሰት መስህብ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማገናዘብ ቅንጡ ተደርጎ መሠራቱ

🔰በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራት የተገጠመ መሆኑ ይገኙበታል፡፡

❇️#የኘሮጀክቱ_ሁለንተናዊ_ፋይዳ

⏺በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡

⏺ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል።

⏺ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘጋጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም ከስጋት ነጻ ያደርጋቸዋል፡፡

⏺ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

⏺በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡

☄ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡

📌አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናወኑም ይረዳል ፡፡

@etconp
"Hello everyone,
I am conducting a research study on "The cause and consquence of contract termination on building projects " And I would greatly appreciate your help by filling out a Google form that I have created. Your participation is important for the success of this study. Anyone who is in a construction field and have an experience .... can fill it.

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSd0GgNli_cFaXfc6Kw1ddJp2R0_nnv5LaJWSXLRGwlHjUFo2Q/viewform?usp=sf_link
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👉የመኖሪያ ቤት እጥረትን የሚያስወግዱ የፕሪካስት ሕንፃዎች

✳️ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ ፈጣን የሆነ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በሚታይባቸው ሀገራት ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወይም አፓርትመንት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡

🚧የሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት ለኑሮ አመቺ በሆነ ቦታ እና ተገቢ በሆነ ወጪ ማግኘት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

⏺ይህንን እጥረት እና ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስችሉ የግንባታ ዘዴዎች ውስጥ ቀደም ብለው በተለያዩ ሳይቶች የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት የወለል ምንጣፎች፣ ግርግዳዎች እና ቋሚ ማዕዘኖች "ፕሪካስት ኮንክሪቶች" ትኩረት ከሚሹ የግንባታ ዘዴዎች መካል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

⏺በፕሪካስት ቴክኖሎጂ በፋብሪካ ውስጥ እየተመረቱ በሰለጠነ መንገድ የሚገጣጠሙ የሕንፃ ቁሳቁሶች፣ የመኖሪያ ቤትን ዕጥረትን በፍጥነት ለመቅረፍ ከሚያስገኙት ተጨማሪ ጠቀሜታዎች እና የአመራረት ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

▪️የጥራት ደረጃን መጨመር እና መጪን መቀነስ

❇️ለሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ ተገጣጣሚ ኮንክሪቶች የሚዘጋጁት ለቁጥጥር አመቺ በሆኑ ገላጣ ቦታዎችና መጠኑ ባልተዛባ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ውኃ በመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በመሆኑ አላስፈላጊ ብክነት ወይም ዕጥረትን በማስወገድ ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

❇️ኮንክሪቶቹ የሚዘጋጁት ከሰው ፍላጎት እና ተጽዕኖ በጸዳ፣ በፕሮግራም በሚታዘዝ (አውቶማቲክ) የማምረት ዘዴ በመሆኑ የተፈለገውን ምርት በተፈለገው ፍጥነት በማምረት የጊዜ ብክነትን ያስወግዳሉ፡፡

❇️በተለመደው የሕንፃ ግንባታ ዘዴ በግንባታ ሳይት ላይ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ዲዛይኖችን ለመስራት የሚያስፈልጉ ውስብስብ የእንጨት እና የብረት ድጋፎችን በማስወገድ ለሚፈለገው ቅርፅ ሞልድ (ቅርፅ) ማውጫ በማዘጋጀት የተፈለገውን ዲዛይን በፍጥነት ለማምረት የባለሙያን ወጪን ይቀንሳል፡፡

▪️አስተማማኝ የስራ ዕድል ይፈጥራል

🔰አንድ የፕሪካስት ማምረቻ ድርጅት ወደ ማምረት ሂደት የሚገባው አንድ አስገንቢ ድርጅት ለሚሠራው ሕንፃ የሚያስፈልገውን የተገጣጠመ ኮንክሪት መጠን እና ዲዛይን መነሻ በማድረግ ቀደም ያለ የውል ስምምነት በመፈረም ነው፡፡

⏺ከዚህ የተነሳ አምራች ድርጅቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የማያቋርጥ አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርለት ያደርጋል፡፡

▪️የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳል

🔰በፕሪካስት የሚገነቡ ሕንፃዎች ትርፍ የሆነ ሙቀትን በማመቅ በዝግታ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ እንዲወገድ በማድረግ፣ በሕንፃ ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ክብደት ወይም ጭነት በማስወገድ፣ በተለመደው መንገድ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ሕንፃዎች ከ50 በመቶ የበለጠ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

✅ይህን ብቃት እንዲላበሱ ከሚያደርጋቸው ውስጥ ለምሳሌ፣ የተለያዩ ፎቅ ባላቸው ሕንፃዎች ለወለል የሚዘጋጁ ውስጣቸው ክፍት በሆነ ብሎኬት እና ኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት ምንጣፎች ከተለመደው ግንባታ ከ50 እስከ 60 በመቶ ክብደታቸው የቀነሰ ከመሆኑም በላይ ጥራታቸው በተጠበቀ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና የመሳሰሉት የግንባታ ቁሶች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

✅ከዚሁ በተጨማሪ፣ እንደየአስፈላነቱ ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ ያለውን የከባቢ አየር ድምጽ መስተጋባት፣ የመሬት ርደት ወዘተን መነሻ አድርገው ስለሚመረቱ አላስፈላጊ የሆነ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን በመቀነስ የበለጠ ዕድሜ እና ጥንካሬን እንዲኖራቸው የሚያደርግ ብቃት የተላበሱ ያደርጋቸዋል፡፡

▪️ለዕድሳት፣ ለግንባታ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ጊዜ እና ወጪን ይቀ ንሳል።

@etconp
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👉የ ግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ

የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሼል ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም  ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል።

ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት።

ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት። ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት።

አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል።

ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት።

ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል።

ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት። በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ   አለበት።

በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።

@etconp
👉ሌላኛው ቻናላችን ተቀላቅለዋል?

⚡️ዛሬ የወጡ ጨረታዎች ጨምሮ

🌟አዳዲስ የስራ ቅጥሮች እና የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ሲወጡ በቀላሉና በ ትኩሱ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE በማረግ አዳርሱ።

https://www.tgoop.com/ETCONpWORK
2024/05/14 20:55:47
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243