ETCONP Telegram 10672
👉የመኖሪያ ቤት እጥረትን የሚያስወግዱ የፕሪካስት ሕንፃዎች

✳️ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ ፈጣን የሆነ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በሚታይባቸው ሀገራት ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወይም አፓርትመንት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡

🚧የሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት ለኑሮ አመቺ በሆነ ቦታ እና ተገቢ በሆነ ወጪ ማግኘት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን እጥረት እና ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስችሉ የግንባታ ዘዴዎች ውስጥ ቀደም ብለው በተለያዩ ሳይቶች የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት የወለል ምንጣፎች፣ ግርግዳዎች እና ቋሚ ማዕዘኖች "ፕሪካስት ኮንክሪቶች" ትኩረት ከሚሹ የግንባታ ዘዴዎች መካል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

በፕሪካስት ቴክኖሎጂ በፋብሪካ ውስጥ እየተመረቱ በሰለጠነ መንገድ የሚገጣጠሙ የሕንፃ ቁሳቁሶች፣ የመኖሪያ ቤትን ዕጥረትን በፍጥነት ለመቅረፍ ከሚያስገኙት ተጨማሪ ጠቀሜታዎች እና የአመራረት ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

▪️የጥራት ደረጃን መጨመር እና መጪን መቀነስ

❇️ለሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ ተገጣጣሚ ኮንክሪቶች የሚዘጋጁት ለቁጥጥር አመቺ በሆኑ ገላጣ ቦታዎችና መጠኑ ባልተዛባ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ውኃ በመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በመሆኑ አላስፈላጊ ብክነት ወይም ዕጥረትን በማስወገድ ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

❇️ኮንክሪቶቹ የሚዘጋጁት ከሰው ፍላጎት እና ተጽዕኖ በጸዳ፣ በፕሮግራም በሚታዘዝ (አውቶማቲክ) የማምረት ዘዴ በመሆኑ የተፈለገውን ምርት በተፈለገው ፍጥነት በማምረት የጊዜ ብክነትን ያስወግዳሉ፡፡

❇️በተለመደው የሕንፃ ግንባታ ዘዴ በግንባታ ሳይት ላይ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ዲዛይኖችን ለመስራት የሚያስፈልጉ ውስብስብ የእንጨት እና የብረት ድጋፎችን በማስወገድ ለሚፈለገው ቅርፅ ሞልድ (ቅርፅ) ማውጫ በማዘጋጀት የተፈለገውን ዲዛይን በፍጥነት ለማምረት የባለሙያን ወጪን ይቀንሳል፡፡

▪️አስተማማኝ የስራ ዕድል ይፈጥራል

🔰አንድ የፕሪካስት ማምረቻ ድርጅት ወደ ማምረት ሂደት የሚገባው አንድ አስገንቢ ድርጅት ለሚሠራው ሕንፃ የሚያስፈልገውን የተገጣጠመ ኮንክሪት መጠን እና ዲዛይን መነሻ በማድረግ ቀደም ያለ የውል ስምምነት በመፈረም ነው፡፡

ከዚህ የተነሳ አምራች ድርጅቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የማያቋርጥ አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርለት ያደርጋል፡፡

▪️የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳል

🔰በፕሪካስት የሚገነቡ ሕንፃዎች ትርፍ የሆነ ሙቀትን በማመቅ በዝግታ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ እንዲወገድ በማድረግ፣ በሕንፃ ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ክብደት ወይም ጭነት በማስወገድ፣ በተለመደው መንገድ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ሕንፃዎች ከ50 በመቶ የበለጠ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

ይህን ብቃት እንዲላበሱ ከሚያደርጋቸው ውስጥ ለምሳሌ፣ የተለያዩ ፎቅ ባላቸው ሕንፃዎች ለወለል የሚዘጋጁ ውስጣቸው ክፍት በሆነ ብሎኬት እና ኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት ምንጣፎች ከተለመደው ግንባታ ከ50 እስከ 60 በመቶ ክብደታቸው የቀነሰ ከመሆኑም በላይ ጥራታቸው በተጠበቀ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና የመሳሰሉት የግንባታ ቁሶች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ፣ እንደየአስፈላነቱ ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ ያለውን የከባቢ አየር ድምጽ መስተጋባት፣ የመሬት ርደት ወዘተን መነሻ አድርገው ስለሚመረቱ አላስፈላጊ የሆነ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን በመቀነስ የበለጠ ዕድሜ እና ጥንካሬን እንዲኖራቸው የሚያደርግ ብቃት የተላበሱ ያደርጋቸዋል፡፡

▪️ለዕድሳት፣ ለግንባታ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ጊዜ እና ወጪን ይቀ ንሳል።

@etconp

tgoop.com/ETCONp/10672
Create:
Last Update:

BY Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

Share with your friend now:
tgoop.com/ETCONp/10672

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

While some crypto traders move toward screaming as a coping mechanism, many mental health experts have argued that “scream therapy” is pseudoscience. Scientific research or no, it obviously feels good. The administrator of a telegram group, "Suck Channel," was sentenced to six years and six months in prison for seven counts of incitement yesterday. 2How to set up a Telegram channel? (A step-by-step tutorial) To delete a channel with over 1,000 subscribers, you need to contact user support The channel also called on people to turn out for illegal assemblies and listed the things that participants should bring along with them, showing prior planning was in the works for riots. The messages also incited people to hurl toxic gas bombs at police and MTR stations, he added.
from us

Telegram Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
FROM American