ETCONP Telegram 10666
Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
Photo
👉አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ

✳️የውል ስምምነት፡- መጋቢት 18 ቀን 2011 ዓ.ም.

✳️የሥራ ተቋራጭ፡- አለማቀፉ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ

✳️አማካሪ ድርጅት፡- ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የቱርክ አማካሪ ድርጅት ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች ድርጅት ከተባለ አገር በቀል ንኡስ አማካሪ ጋር በጋራ በመሆን ያከናውኑታል

✳️የግንባታ ወጪ፡- 1,437,000,000 (አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ብር)

🚧የግንባታውን ወጪ የሸፈነው፡- የኢትዮጵያ መንግስት

🚧የግንባታው አይነት፡- ዲዛይንና ግንባታ /ተቋራጭ ድርጅቱ ዲዛይንና ግንባታን በጋራ አካቶ የሚሰራበት የኮንትራት ውል አይነት ነው/፡፡

🚧የድልድዩ አይነት፡- የተንጠልጣይና የሳጥን ቅርፅ ያላቸውን ረጃጅም ድልድዮችን ዲዛይን በማዋሀድ በአዲስ የዲዛይን ጥበብ የሚገነባው ኤክስትራዶስድ የተባለውን አይነት ድልድይ ነው፡፡

🔰ርዝመት፡- 380 ሜትር

🔰የጎን ስፋት፡- 43 ሜ. የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ግዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፡፡

በተጨማሪም የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር በሁለቱም አቅጣጫ እንዲሁም 5 ሜ. የእግረኛ መሄጃን ያካተተ ነው።

#የድልድዩ_ግንባታ_ስራ፡-

📌ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡
ይህ ድልድይ ኤክስትራ ዶዝድ የሚባል ስያሜ የተሰጠው ተንጠልጣይ ድልድዮች (ሰስፔንሽን) ከሚባሉት ድልድዮች የተለየና ይልቁን የመኪና ተሸካሚው ዴክ ከፊትና ከሁዋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (በገመዶች የተወጠረ) ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካይነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፡፡

ይህ አይነቱ ድልድይ የረጃጅም ኬብል ስቴይድ (በገመድ የተወጠረ) ድልድዮችና የረጃጅም ቦክስ ገርደር አይነት ድልድዮች ውሁድ ሆኖ ስፋታቸው ከ 250 ሜትር እከ 500 ሜትር በሚደርሱ ወንዞች ላይ አመቺና ወጪ ቆጣቢ ሆነው እንዲሰሩ በመጀመሪያ በፈረንሳይ ሀገር የተፈለሰፈ በቀጣይ ግን በብዛት ጃፓን ሀገር ስራ ላይ የዋለ የድልድይ አይነት ነው፡፡

የተጠናቀቀው የድልድዩ የምህንድስና ሰነዶች እንደሚያመለክቱት የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ (piers) 7 ሜትር ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሀና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፡፡

ለድልድይ ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ #ዋና_ዋና_ግብዓቶች

✳️የተለያዩ የጥንካሬ ደረጃ (Grade C-30, C-40, C-50, and C-55) ያላቸው አርማታ 54,138.68 ሜ.ኩ

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የአርማታ ብረት 9,241.45 ቶን

✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የማንጠልጠያ እና መወጠሪያ 474.37 ቶን

👍የድልድይ ግንባታ ሥራውን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ከተሠሩት #የተለየ_የሚያደርገው

🔰የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጅ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ

🔰ድልድዩ በከተማ ውስጥ እንደመሠራቱ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የቱሪሰት መስህብ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማገናዘብ ቅንጡ ተደርጎ መሠራቱ

🔰በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራት የተገጠመ መሆኑ ይገኙበታል፡፡

❇️#የኘሮጀክቱ_ሁለንተናዊ_ፋይዳ

በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡

ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል።

ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘጋጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም ከስጋት ነጻ ያደርጋቸዋል፡፡

ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡

ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡

📌አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናወኑም ይረዳል ፡፡

@etconp

tgoop.com/ETCONp/10666
Create:
Last Update:

BY Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

Share with your friend now:
tgoop.com/ETCONp/10666

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Today, we will address Telegram channels and how to use them for maximum benefit. Telegram desktop app: In the upper left corner, click the Menu icon (the one with three lines). Select “New Channel” from the drop-down menu. Ng Man-ho, a 27-year-old computer technician, was convicted last month of seven counts of incitement charges after he made use of the 100,000-member Chinese-language channel that he runs and manages to post "seditious messages," which had been shut down since August 2020. How to Create a Private or Public Channel on Telegram? The public channel had more than 109,000 subscribers, Judge Hui said. Ng had the power to remove or amend the messages in the channel, but he “allowed them to exist.”
from us

Telegram Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
FROM American