Telegram Web
ጌታ በእውነት ተነስቷል።
ሉቃ 24 ፡ 34


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በአብይ ኃይል ወስልጣን
አሰርዎ ለሰይጣን
አግዓዝዎ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም።


እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁልን።

ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላምን ያድርግልን
🙏

@etconp
👉እየሩሳሌም በሺህ የሚቆጠሩ አመታትን ያስቆጠረ ረጅም እና የበለጸገ የግንባታ ታሪክ አላት

የከተማዋ አርክቴክቸር የተለያዩ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ተጽእኖዎችን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስፍራዎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ድረስ ያሉ መዋቅሮች አሉት።

በኢየሩሳሌም ታሪክ ውስጥ በጣም ዝነኛ ከሆኑት የግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በንጉሥ ሰሎሞን በ10ኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የገነባው የመጀመሪያው ቤተመቅደስ ነው።

ይህ ቤተ መቅደስ በ586 ልክበ ዠ በባቢሎናውያን ፈርሶ ነበር፣ ነገር ግን በአይሁድ ሕዝብ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደገና ተገነባ።

ሁለተኛው ቤተመቅደስ በኋላ በሮማውያን በ70 ዓ.ም ተደምስሷል፣ እና ምዕራባዊው ግንብ፣ የቤተ መቅደሱ ግቢ ቅሪት፣ ዛሬም እንደ አይሁዶች የፅናት እና የእምነት ምልክት ነው።

ባለፉት መቶ ዘመናት ኢየሩሳሌም በተለያዩ የሃይማኖት ቡድኖች አብያተ ክርስቲያናትን፣ መስጊዶችን እና ምኩራቦችን ግንባታን ጨምሮ የበርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ማዕከል ሆና ቆይታለች።

በሮማውያን ዘመን የጀመረችው አሮጌው ከተማ፣ የሮክ ጉልላት እና የቅዱስ መቃብር ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ብዙ ታሪካዊ ሕንፃዎች እና ሀውልቶች ይገኛሉ።

በዘመናችን እየሩሳሌም በከተማዋ ውስጥ አዳዲስ የመኖሪያ እና የንግድ ሕንፃዎች በመስፋፋት ከፍተኛ መጠን ያለው የከተማ እድገት አሳይታለች።

ቢንያነይ ሃኡማ በመባል የሚታወቀው የኢየሩሳሌም አለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ግንባታ እና የኢየሩሳሌም ማእከላዊ አውቶብስ መናኸሪያ ለከተማዋ ዘመናዊ የኪነ-ህንፃ ጥበብ ማሳያዎች ናቸው።

የከተማዋ አርክቴክቸር የተለያዩ ያለፈውን እና ቀጣይ ዝግመተ ለውጥን እንደ ደማቅ እና ተለዋዋጭ የከተማ ማእከል ያንፀባርቃል።

በ ድጋሜ መልካም የ ትንሳዔ በዓል❤️

Via Fila

@etconp
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👉አሁናዊ ኪነህንጻ

🚧ደብረ እንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን።

📌ቀበና አካባቢ ከፍ ባለ ቦታ ላይ የተገነባ፣ አዲስ አበባ።

የግሪካውያን ወይም የሮማውያን ፔዲመንቶች፣ አእማዶችና ንድፍ ውሰቶች የሌሉበት ሊጎበኝ የሚገባው ነው።

📷 BCAA በኩል

@etconp
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👉የሁለት ቢሊዮን ዶላር ኤርፖርት ግንባታ

✳️የኬንያ ትልቁ ኤርፖርት የሰሞኑን ዝናብ መቋቋም አቅቶት ክፉኛ ሲያንጠባጥብ ተስተውሏል።

🚧የኬንያ መንግስት ይህንን ተግዳሮት ለማለፍ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።

✳️አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት "New Nairobi" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ግንባታው በታሰበው መሠረት ከተጠናቀቀ ባረጀ የመሠረተ ልማት ደረጃ የሚገኘውን እና 66 አመት ያስቆጠረውን የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ ኤርፖርት የመተካት ሚና ይኖረዋል።

🔰የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በሚቀጥለው ወር በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ ሊያደርጉ በተዘጋጁት ጉብኝታቸው ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀርባሉ ተብሏል።

❇️ይህ አዲሱ የናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ የመገንባት ግዙፍ እቅድ ኬንያ በአካባቢው ወሳኝ የአቪዬሽን ማዕከል ለመሆን የያዘችው ውጥን አካል ነው።

❇️የአዲስ ናይሮቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ወጪን በመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት (PPP) ለመገንባት ታሳቢ ተደርጓል።

🚧በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያለው ደካማ መሠረተ ልማት ኤርፖርቱ ቀስ በቀስ አገልግሎት መስጠት ወደ ማቆም ሊያመራል የሚል ስጋትም ተፈጥሯል።

❇️አሁን ያለው የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማት የመንገደኛ ተርሚናሎች ጣሪያ ዝናብ የሚያንጠባጥብ ሁኔታን በሚመለከት የኬንያ የወደብ ባለስልጣን በኤርፖርቱ የሚያንጠባጥቡ ጣሪያዎች የማደስ ሥራው የተጀመረው ከባድ ዝናብ ከመጀመሩ በፊት በመጋቢት ወር ነው ብሏል።

❇️ይህ የሚያመለክተው የኤርፖርቱ እድሳት የመሠረተ ልማት ችግሩ እንደ ስጋት መነሳት ከጀመረ ከአምስት ወራት በኋላ ነው።

❇️ይህ የመሠረተ ልማት ሁኔታ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቂ የሆነ የመገልገያ እና የመሠረተ ልማት ጥገና እና ማሻሻያ ያለመኖሩን ያሳያል ተብሏል።

🔰በኤርፖርቱ ላይ ያሉ አንዳንድ ጣሪያዎችም እያፈሰሱ ይገኛሉ፣ በዚህም የኳታር አየር መንገድን፣ ሉፍታንዛን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የቱርክ አየር መንገድን እና የሩዋንዳ አለም አቀፍ አየር መንገዶችን የሚያገለግሉ ተርሚናሎች ሥራዎቸውን ማቋማቸው ተነግሯል።

@etconp
👉በኢትዮጵያ በ600 ሚሊዮን ብር 11 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

🔰የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 11 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት ከስድስት ሥራ ተቋራጮች ጋር የ600 ሚሊየን ብር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

✳️የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ፦ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በአምስት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለመጠጥ ውሃ፣ ለመስኖ ልማት እና የከርሰ-ምድር ውሃ ሀብት አስተዳደር ሥራዎችን ለመደገፍ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

❇️ለሶስት ሀገራት ከአለም ባንክ ከተገኘው የ385 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ኢትዮጵያ 210 ሚሊየን ዶላር ድጋፉን አግኝታለች።

❇️በዚህም በ55 ወረዳዎችና በ110 የገጠር ቀበሌዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በመገንባት 1.4 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡

🚧ፕሮጀክቶቹ በኦሮሚያ ቦረና ዞን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን፣ በሲዳማ ዳራ ዞን እና በሶማሌ ክልል በዳሌ ዞን ይገነባሉ፡፡

📌ግንባታውን በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

🚧ተቋራጮቹ በገቡት ውል መሠረት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ሠርተው እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ቁጥጥሬ እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

@etconp
"Hello everyone,
I am conducting a research study on "The Role of BIM in Enhancing Construction Cost and Time Performance." And I would greatly appreciate your help by filling out a Google form that I have created. Your participation is important for the success of this study.

👉Anyone who is in a construction field and have an experience starting from one can fill it.

https://forms.gle/t3d9mtYKeagq24i1A

thank you in advance.🙏
ቻይና አዲስ ድልድይ ይዛ መጥታለች

✳️ይህ በሎንግሊ ወንዝ ላይ የተሠራው ድልድይ የሚገኘው፦ በጉዋንዡ ክፍለ ግዛት ውስጥ ሲሆን፣ የድልድዮን መጠናቀቅ ተከትሎ ባገኘው የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ባለፈው ቅዳሜ አፕሪል 27 ቀን 2024 ቀን ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

@etconp
👉በደቡብ አፍሪካ ህንፃ ተደርምሶ የአምሥት ሰዎች ህይወት አለፈ

✳️በደቡብ አፍሪካ በተከሰተ የህንፃ መደርመስ አደጋ የአምሥት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

🚧በሀገሪቱ ዌስተርን ኬፕ ግዛት ጆርጅ ከተማ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ወለል ህንጻ ተደርምሶ በስራ ላይ ከነበሩ አጠቃላይ 75 ሰዎች አምሥቱ ህይወታቸው ሲያልፍ 24 ሰዎችን ከፍርስራሹ ማውጣት ተችሏል ተብሏል።

🔰ከፍርስራሹ ስር ይገኛሉ የተባሉ 50 ያክል ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

🚧የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።

📌በነፍስ አድን ስራው ከመቶ በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአነፍናፊ ውሾች ጋር እንደተሰማሩ ዘገባው ጠቁሟል።

#FirstSafety

@etconp
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👉ሲሲሲሲ የግዙፉን “ኤግል ሂልስ” ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ እያካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽርክና ከሚያሠራቸው ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ግዙፉ የ"ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት የምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ከመሬቱ አለታማነት አንፃር የተወሰነ ጊዜ ቢወስድም የፕሮጀክት ግንባታ ሥራ በጥሩ አፈፀፃም ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የፕሮጀክት ግንባታ ሥራውን የቻይናው ኮሚዩኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (CCCC) እያከናወነ ሲሆን፣ በአሁን ወቅት የግንባታ ሥራው 24 ሰዓት ሙሉ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡

የ"ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት ኮርዲኔተር አቶ ሰለሞን ከፈለኝ እንደገለጹት፣ በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር ግንባታው እየተካሄደ የሚገኘው "ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት የምዕራፍ አንድ የመኖሪያ አፓርትመንት መዋቅር ሥራ ተጠናቆ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

የዚሁ ምዕራፍ ግንባታ አካል የሆነው ሌላኛው የሦስት በጣም ትልልቅና ዘመናዊ የሆነ ሞል፣ አፓርትመንትና ሆቴል ግንባታ ሥራ የሚሆነው መሬት አለታማ በመሆኑ ለማስተካከል ጊዜ የወሰደ እና አሁን ላይ ለግንባታ ምቹ የማድረግ ሥራ የተጠናቀቀ በመሆኑ የኮንክሪት ሥራውን ለመሥራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታው አሁን ባለው አቅም ለ200 ሰዎች በቋሚና ጊዜያዊነት የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ፣ የመዋቅር (structure) ግንባታ ስራው ሲጀመር ደግሞ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታ ሥራው በርካታ ተግባራትን በአንድ ጊዜ እና ተመሳሳይ ሰዓት ማከናወን የሚያስችል አቅም ፈጥሮ የሚንቀሳቀስ እንደመሆኑ ጥሩ ልምድና ትምህርት የሚወሰድበት የመዲናችን ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

@etconp
👉ኣዲሱ ቻናላችን ተቀላቅለዋል?

⚡️ዛሬ የወጡ የ ጨረታዎች ጨምሮ

🌟አዳዲስ የስራ ቅጥሮች እና የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ሲወጡ በቀላሉ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE በማረግ አዳርሱ።

https://www.tgoop.com/ETCONpWORK
ነፃ የስልጠና ዕድል ማስታወቂያ

ኢንስቲትዩታችን በ2016 በጀት ዓመት ለኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች በኮንስትራክሽን ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራች የሆናችሁ እና በዚህ የስልጠና እድል ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ አምራቾችና ባለሙያዎች በተቋማችን ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ መንገድ Hansem Office Park ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602 እየቀረባችሁ ወይም በስልክ ቁጥር 0118276909 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2016ዓ.ም. መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የስልጠናው ቀን እና ቦታ በተመሳሳይ ማስታወቂያ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Via Construction Management Institute

@etconp
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👉ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ለኮሪደር ልማት 3,250 አባወራዎች ይነሳሉ

◉ ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል

🚧ከፒያሳ በመነሳት በሳር ቤት በኩል እስከ ወሎ ሠፈር ድረስ የሚገነባው አዲሱ የኮሪደር ልማት፣ 3,250 አባወራዎችን ወይም ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ተመላከተ፡፡

✳️ተነሺዎችን ለማስፈር 21 ሔክታር መሬትና ስድስት ቢሊዮን ብር የካሳ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡

✳️ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከፒያሳ በመነሳት እስከ ብሔራዊ፣ ከብሔራዊ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳር ቤትና ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ተብሎ በአምስት ንዑስ ፕሮጀክቶች ተከፋፍሎ ዲዛይን እንደወጣለት ሪፖርተር የተመለከታቸው የዲዛይን ዶክመንቶች ያሳያሉ፡፡

🚧አጠቃላይ ፕሮጀክቱ አምስት ክፍላተ ከተሞችን የሚነካ ሲሆን እነዚህም አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክና ቦሌ ናቸው፡፡

✳️ጠቅላላ ፕሮጀክቱ 460 ሔክታር መሬት ይዞታ የሚነካ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 114 ሔክታር ለመልሶ ማልማት ነፃ እንደሚደረግ ዶክመንቱ ያሳያል፡፡

🔰ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ከዚህ ውስጥ ለአብነት ያህል ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለፈጣን የአውቶቡስ መስመር ግንባታ ይውላል፡፡

🚧ስድስት ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ ቤቶች ግንባታ፣ ስድስት ቢሊዮን ለተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ አራት ቢሊዮን ብር ለመንገድ ግንባታ፣ ሦስት ቢሊዮን ለፓርክ (Green Park) ተመድቧል፡፡

🚧በተጨማሪም የፓርኪንግ ቦታዎች፣ ሰባት ያህል ድልድዮች፣ የመሠረተ ልማትና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ይገነባሉ፡፡

✳️ወጪ የሚደረገውን 40 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ለማስመለስ መታቀዱንም ሰነዱ ያመለክታል፡፡

🔰በኮሪደር መስመሩ ላይ መንግሥት 114 ሔክታር መሬት ነፃ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ይኼንን መሬት 70 ሺሕ ብር በካሬ ለአልሚዎች በማከራየት በአምስት ዓመት ውስጥ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዶክመንቱ ያሳያል፡፡

❇️ከዚህ በተጨማሪ በዚህ መስመር ላይ መንግሥት ሊያከራያቸው ካቀዳቸው የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃና ቤት ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ በየዓመቱ ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ታውቋል፡፡

ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ አብዛኛው ቦታ ለአረንጓዴ ልማት ማለትም ለሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ታቅዷል፡፡

አምባሳደር አካባቢ ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ሙዚየም፣ ካፌና መዝናኛ የሚኖረው የባህል ማዕከል እንደሚቀየር ዲዛይኑ ያሳያል፡፡

የሰይጣን ቤት ተብሎ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ያለው ቦታ ወደ ባህል ማዕከልና መዝናኛ ቦታ በመጠነኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡

ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት ያለው 1.2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ‹‹የአፍሪካ ማዕከል›› ለመገንባት ይውላል፡፡

ማዕከሉ ሙዚየም፣ ላይብረሪ፣ የባህልና መዝናኛዎች ሲኖሩት አጠቃላይ አካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ ወዳለው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አገልግሎት ይቀየራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሜክሲኮ ሳር ቤት ባለው ንዑስ ፕሮጀክት ከታሰቡት ብዙ ዕቅዶች ውስጥ ሆስፒታልና አዲሱ ቱሞሮ (Adisu Tomorrow) ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ይገኝበታል፡፡

በዚህ አካባቢ ከአራት ወለል ሕንፃ (G+4) በታች የሆኑ ሕንፃዎች ሁሉም ይፈርሳሉ፡፡

የኮሪደር ልማቱን ለማስፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአዲስ አበባ ዕቅድና ልማት ኮሚሽንን ጨምሮ ሃያ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

@etconp
👉አዳማ

🚧በአዳማ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ የሁለት ሰራተኞች ህይወት ማለፉን የከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

✳️በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት አደጋው ትናንት በከተማው ደጋጋ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀጠና አራት አካባቢ የደረሰ ነው፡፡

❇️በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም ሌሎች ሁለት የጉልበት ሰራተኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ሕንፃ አሰሪዎች ለሚያሰሯቸው ሰራተኞች የስራ ደህንነት ሊጠብቁና ዋስትና ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል ብሎ የዘገበው ፋና ሬድዮ ነው።

#FirstSafety

@etconp
#አሳዛኝ_ዜና

ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው።

እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር።

የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል።

#FirstSafety

@etconp
👉በጥቂት ቀናት ውስጥ በጃፓን አሮጌውን መንገድ ለመጠገን ሲባል ጊዚያዊ አዲስ ድልድይ ለመገንባት ተችሏል።

🚧ይህ ሊሆን የቻለው በጃፓን ውስጥ ብቻ ነው !

@etconp
2024/05/29 03:17:32
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243