Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰበር ዜና!!

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ጀመረች!!

የእስራኤል አየር ሃይል በኢራን የኒውክሊየር ኢላማዎች፣ ወታደራዊ ጣቢያዎች እና ጄኔራሎች ላይ ጥቃት መፈጸም ጀምሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ ዋና አዛዥ ሆሴን ሳላሚ ዛሬ ምሽት እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ላይ ባካሄደችው ጥቃት መገደሉን የኢራን የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢራን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጀር ጀነራል መሀመድ ባገሪ ዛሬ ምሽት እስራኤል በቴህራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት መገደላቸው ተረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሌሊቱ ከባድ ጥቃት አፀፋ ኢራን 100 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ እስራኤል ልካለች።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tgoop.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በስድስተኛው ቀን ከእስር ተፈታ!

የ'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ወልደየስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው አቶ ቤተማርያም አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ።ተስፋለም ከእስር የተፈታው ዛሬ አርብ፣ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኘው የፖሊስ መምሪያ መሆኑን ቤተማሪያም ገልጸዋል።

ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 3/ 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ የቄርቆስ ምድብ ችሎት በ15 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኖ ነበር። ሆኖም ፖሊስ ለአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ በማቅረቡ ሳይፈታ ቀርቷል።ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰኔ 4/ 2017 ዓ.ም. ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የፖሊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ጋዜጠኛው የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት በድጋሚ በይኗል።

ነገር ግን ፖሊስ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት በድጋሜ አቤቱታ አቅርቧል።ሰበር ሰሚ ችሎቱ ትላንት ሐሙስ የፖሊስ ይግባኝ አቤቱታ "አያስቀርብም" በሚል መወሰኑን የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ባለቤት ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው 100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለ100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክትን የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር አስመረቀ።የሶላር ፕሮጀክቱ 200 ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገበት እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መገንባቱ ተገልጿል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ እንደ ሀገር በዚህ ደረጃ ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው የሶላር ፕሮጀክት አለመኖሩን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ያሉት ፕሮጀክቱ 100 ኪሎ ዋት የሚያመርት መሆኑ የመጀመሪያው ያደርገዋል ብለዋል።ከሚመነጨው ኃይል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚፈልገውን ተጠቅሞ ስራ በማይኖር ጊዜ የተመረተውን ሀይል ወደ ብሔራዊ ግሪድ ማስገባት መቻሉ ፕሮጀክቱን ልዩ ያደርገዋል ሲል ገልጸዋል።

ሀብታሙ ኢተፋ፤ ፕሮጀክቱ ሌሎች ተቋማት በግቢያቸው ያለውን ቦታ ለዚህ ዓላማ ማዋል እንደሚቻል ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ በቀጣይ የሶላር ሀይልን በስፋት ለማምረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ሶማሊላንድ እንደሀገር እውቅና እንድታገኝ ሐሳብ አቀረቡ!

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ስኮት ፔሪ ዛሬ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ የነጻነት ህግን አስተዋውቀዋል። ይህም ሶማሊላንድን ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ ሀገር እንድትሆን በይፋ እውቅና ለመስጠት ያለመ ደፋር እርምጃ ነው። ዛሬ ላይ ይፋ የሆነው ይህ ምክረ ሃሳብ፣ ሶማሊላንድ ለ30 ዓመታት ያስመዘገበችውን የራስ ገዝ አስተዳደር፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲያዊ እድገት የሚያደንቅ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የ2001 ህገ መንግስቷ እና ነጻ ምርጫዎችን ማድረጓን ያነሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ቁጥጥር ስር ዋለ

ሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታው ቢሮ ሃላፊነት ላለፉት ሳባት አመታት በመምራት ያሳለፈዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ፤ ትናንትና ለፎርማልቲ የክልሉ ምክርቤት መንግስት ፍንቀላ እና በከፍተኛ ሙስና ወንጀል ማስረጃ በማቅረብ ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
እስራኤል አዲስ ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ !

የእስራኤል አየር ሃይል አመሻሹ ላይ በኢራን መአከላዊ ክፍል በመዝለቅ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ።

የእስራኤል የስለላ ድርጅት እንደገለፀዉ ከሆነ አመሻሹ ላይ የፈፀመዉ ጥቃት የኢራንን የጸጥታ ተቋም ልብ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቦታዎች ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የአየር መከላከያ እና የባለስቲክ ሚሳኤል ማዕከላትን ኢላማዎች መምታቱን ገልጿል ።

የእስራኤል ፕሬዘዳንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ለኢራን ህዝብ ምንም ነገር እንደሌለን በቀጥታ እየነገርኳቸው ነው። እየተሰቃዩ መሆናቸውን እናውቃለን። የሚኖሩበትን ሁኔታ አይተናል… ትግላችን ከኢራን ህዝብ ጋር አይደለም ። ጥቃቱ የተካሄደው (ቦታው) ሰዎች በጎዳና ላይ በማይገኙበት ጊዜ ነው ፣ እናም በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል" ብለዋል ።

ጥቃቱን በተመለከተ ከቴህራን በኩል በተገኘ መረጃ በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባው ፎርዶ የኑክሌያር ማብሊያ ጣቢያ ጨምሮ በርካታ ሰዉ የሚኖርባቸዉ አካባቢዎች በቦንብ መደብደቡን በጥቃቱ 78 ሰዎች መሞታቸውን እና ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ሲቪሎች እንደሚገኙበት የኢራን መንግስት ቲቪ ገልጿል ።
ኢራን ዛሬ ከመሸ በኋላ በሁለት ዙር በቴልአቪቭ በ7 ቦታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማለች።

በጥቃቱ የተነሳ የእስራኤል ዋና የጦር ማዘዣ አካባቢ እሳት መታየቱ ተዘግቧል።

Source: BBC

@Yenetube
አሜሪካ የኢራን ሚሳኤሎችን በማምከን መሳተፏ ተገለፀ

የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል ያቀኑትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት ረድቷል ሲሉ ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ባለስልጣናቱ፣ ተዋጊ ጄቶች ወይም የጦር መርከቦች በመጠቀም የመከላከል ሥራውን ስለመፈጸማቸው ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tgoop.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ” ሆኖ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” አለ!

የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ ሆኖ” 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” ሲል ገለጸ።ኮከሱ፤ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድን “በወገኝተኝነት” እና “ለገዢው ፓርቲ በታዛዥነት” ከሷል። በዚህም "የገዢው ፓርቲ አሸናፊነት አስቀድሞ የሚታወቅ ነው" ብሏል።

መግለጫው፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከነባር አመራሮቹ “ሶሰቱን (60 በመቶ) ለመቀየር ጫፍ መድረሱን እያሳወቀን ነው” ብሏል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ “ልምድ በሌላችው ኮሚሽነሮችና በወቅታዊው የፖለቲካ ያለመረጋጋት፣ የግጭትና ጦርነት ውጥረትና ሁለንተናዊ ውስብስብ ተጨባጭ ሁኔታ” ውስጥ የሚደረግ ምርጫ “ጣጣና መዘዙ” እንደሚያስከትሉ አስጠንቅቋል።በመሆኑም በዚህ ተጨባጭ እውነታ ምርጫ ቦርድ "ነጻና ገለልተኛ" ሆኖ ምርጫውን ለማስፈጸም "አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም" ያለው ኮከሱ፤ “ጉዳዩ ወደከፋ አደጋና ትርምስ እንዳንገባ በእጅጉ የሚያሳስብና የሚያሰጋ ነው” ሲል በአጽንዕኦት ገልጿል።

ኮከስ ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይም ትችት ሰንዝሯል። በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቀረቡ የማሻሻያ ኃሣቦችና የተነሱ ጥያቄዎች “ቦታ ሳይሰጣቸው”፣ እንዲሁም የኮሚሽነሮች ሹመት “የብልጽግናውን አዋጅ እንኳ ያልተከተለና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው” ብሏል።በመሆኑ የተሰጠውን ከፍተኛ ተግባርና ኃላፊነት “በህግ፣ በዕውቀትና እውነት በነጻነትና ገለልተኝነት በሚዛናዊነት ከአገራዊ ተልዕኮው አንጻር ለመፈጸም ይቸገራል” ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከምስረታው ጀምሮ ኮሚሽኑ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎችና ባከናወናቸው ተግባራት ኮከሱ ያነሳቸውን ችግሮች የሚያረጋግጡ አፈጻጸሞች፣ በተለይም የኮከሱን “የመፍትሄ ኃሳቦች ከመቀበል ይልቅ እንደተጻራሪና ተቃዋሚው በማየት ሲያገለኝ ቆይቷል” በማለት ከሷል፡፡አክሎም፤ “በያዘው አግላይ አካሄድ ቀጥሎ”፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሥራውን “ሊያጠናቅቅ ቀርቶ አጀንዳ አሰባስቦ ባለመጨረሱ” የአንድ ዓመት ተጨማሪ ዕድሜ ተሰጥቶታል ሲል ተችቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
2025/06/14 14:58:38
Back to Top
HTML Embed Code: