tgoop.com/yenetube/54685
Create:
Last Update:
Last Update:
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው 100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ!
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለ100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክትን የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር አስመረቀ።የሶላር ፕሮጀክቱ 200 ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገበት እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መገንባቱ ተገልጿል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ እንደ ሀገር በዚህ ደረጃ ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው የሶላር ፕሮጀክት አለመኖሩን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ያሉት ፕሮጀክቱ 100 ኪሎ ዋት የሚያመርት መሆኑ የመጀመሪያው ያደርገዋል ብለዋል።ከሚመነጨው ኃይል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚፈልገውን ተጠቅሞ ስራ በማይኖር ጊዜ የተመረተውን ሀይል ወደ ብሔራዊ ግሪድ ማስገባት መቻሉ ፕሮጀክቱን ልዩ ያደርገዋል ሲል ገልጸዋል።
ሀብታሙ ኢተፋ፤ ፕሮጀክቱ ሌሎች ተቋማት በግቢያቸው ያለውን ቦታ ለዚህ ዓላማ ማዋል እንደሚቻል ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ በቀጣይ የሶላር ሀይልን በስፋት ለማምረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube

Share with your friend now:
tgoop.com/yenetube/54685