tgoop.com/yenetube/54684
Create:
Last Update:
Last Update:
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በስድስተኛው ቀን ከእስር ተፈታ!
የ'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ወልደየስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው አቶ ቤተማርያም አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ።ተስፋለም ከእስር የተፈታው ዛሬ አርብ፣ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኘው የፖሊስ መምሪያ መሆኑን ቤተማሪያም ገልጸዋል።
ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 3/ 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ የቄርቆስ ምድብ ችሎት በ15 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኖ ነበር። ሆኖም ፖሊስ ለአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ በማቅረቡ ሳይፈታ ቀርቷል።ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰኔ 4/ 2017 ዓ.ም. ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የፖሊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ጋዜጠኛው የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት በድጋሚ በይኗል።
ነገር ግን ፖሊስ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት በድጋሜ አቤቱታ አቅርቧል።ሰበር ሰሚ ችሎቱ ትላንት ሐሙስ የፖሊስ ይግባኝ አቤቱታ "አያስቀርብም" በሚል መወሰኑን የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ባለቤት ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube

Share with your friend now:
tgoop.com/yenetube/54684