የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድን በኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ በኩል ሊሸጥ ነው!
የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድን ከሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ማሻሻጥ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ አስታውቋል፡፡የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን (ዶ/ር) እንዳስታወቁት ዳያስፖራው የግምጃ ቤት ሰነድ በመግዛት በዚህ የኢንቨስትመንት መሰማራት አለበት፡፡
በዚህ ኢንቨስትመንት መንግሥት በገንዘብ ሚኒስቴር አማካይነት ለአንድ ዓመት ከሚበደረው ገንዘብ በአማካይ ከ16.5 በመቶ በላይ ወለድ እንደሚያስገኝ አስታውቀዋል ፡፡ዳያስፖራዎች ባሉበት አገር ሆነው በከፈቱት አካውንት ኢንቨስት አድርገው ያገኙትን ዋና ገንዘብና ወለድ ወደፈለጉበት የባንክአካውንት እንደሚዛወርላቸውም መናገራቸውን የአገበው ሪፖርተር ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

YeneTube
Photo
ኢትዮጵያ በሩሲያ ድጋፍ የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ግንባታን 95 በመቶ ማጠናቀቋ ተገለጸ!
ከሶስት አስርት አመታት በፊት የባህር በር ያጣችው ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ እያከናወነች ያለውን የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በቅርቡ እንደምታጠናቅቅ ተዘግቧል።የጠቅላይ መምሪያው ግንባታ 95 በመቶ መተናቀቁን ስፑትኪክ አፍሪካን ጠቅሶ አፍሪካ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል።
ይህም ኢትዮጵያ የባህር በር ባይኖራትም ብሔራዊ የባህር ኃይልን ዳግም ለመገንባት ያላትን ምኞት የሚያሳይ አንዱ እርምጃ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።በሦስት ሄክታር ስፋት ላይ የተገነባው ባለ አራት ፎቅ የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ፤ አስተዳደራዊ ቢሮዎችን፣ የሕክምና ክሊኒክን፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ የስፖርት ተቋማትንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን የሚያካትት ሲሆን ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ መሠረት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
በተጨማሪም ይህ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላትን ተፅዕኖ መልሳ ለማግኘት ለማግኘት የምታደርገው ስትራቴጂ አካል ነው ተብሏል።ከጎርጎሮሳውያኑ 1993 ጀምሮ ወደ የባህር በር ብታጣም፣ የኢትዮጵያ መንግስት የባህር ኃይል አቅሞች የንግድ መንገዶችን ለመጠበቅ፣ ለአለም አቀፍ የባህር አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት እና በጂቡቲ እና በሱዳን ወደቦች በኩል ወደ ዓለም አቀፍ ውሃዎች መድረስን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።
በመጋቢት ወር ኢትዮጵያ ከሩሲያ መንግስት ጋር የባህር ኃይል ልማትን እና ስልጠናን ለመደገፍ የትብብር ስምምነት ተፈራርማለች።ይህ ስምምነት የተደረገው ቀደም ሲል ከፈረንሳይ ጋር የነበረው የባህር ኃይል አጋርነት መቋረጡን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።
በጊዜው የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎንኝተው፤ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል አቅም ለማጠናከር ሞስኮ ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስን በተመለከተ ከሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 4 ቀን፤ 2017 የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በሥር ፍርድ ቤት የተወሰነለትን የዋስትና መብት አጽንቷል። ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በመጠየቁ ተስፋለም ወልደየስ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ሰዓት ድረስ ከእስር አልተፈታም። በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ተስፋለም ወልደየስ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ የወሰነው ትላንት ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 ነበር።
ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት የተጻፈው ትዕዛዝ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረም በመቅረቱ ተስፋለም ትላንት ማክሰኞ ሳይፈታ ቀርቷል። መርማሪ ፖሊስ የተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት እንዲከበር የተላለፈው ውሳኔ ላይ ያቀረበው አቤቱታ በዛሬው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተቀባይነት አላገኘም።
የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ በጻፈው ትዕዛዝ “ይግባኝ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ስላላገኘን” “የይግባኝ አቤቱታውን አልተቀበልንውም” ብሏል። ፍርድ ቤቱ ተስፋለም ወልደየስ “በስር ፍርድ ቤት ዋስትና መሰረት ግዴታቸውን ሲወጡ ከእስር እንዲፈቱ” ለቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ይሁንና የቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋለም እንዲፈታ ትዕዛዝ የተሰጠበትን ደብዳቤ “እናንተ ጋር አቆዩትና እኛ ለሰበር ይግባኝ እንላለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የፖሊስ ይግባኝ በአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ቢከፈትም ዛሬ ችሎት አልተሰየመም።
ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሰኔ 5 ቀን፤ 2017 የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት መርማሪዎች ባቀረቡት ይግባኝ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ያለፉትን ሶስት ሌሊቶች በፖሊስ ጣቢያ አሳልፏል። ተስፋለም በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ባለፈው እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 ነበር።
የተስፋለም መታሰር በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የዘገባ ሥራዎች፣ በተቋሙ ባልደረቦች እና በወዳጆቹ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። ተቋማችን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈትቶ ወደ ሥራው እንዲመለስ በድጋሚ በአጽንዖት ጥሪውን ያቀርባል። አሁንም ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈትቶ ወደሚወደው እና ወደሚያከብረው የጋዜጠኝነት ሙያው እስኪመለስ ድረስ ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ከፖሊስ እና ከፍርድ ቤት የሚያገኛቸውን መረጃዎች ለሚዲያው ቤተሰቦች ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።
@Yenetube @Fikerassefa

Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tgoop.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Forwarded from The Urban Center ( Kebet Eske Ketema)
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions
We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:
🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings
📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
Many thanks to our partners for making this possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign

🌺🌸 #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
@geezdistance15
የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18 መድረሱን አስታወቀ።
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ባወጡት መግለጫ እስከ ሰኔ 4 2017 ዓ.ም. ድረስ ብቻ 18 በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ገልፀዋል።በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ መከሰቱ ይፋ የሆነው ግንቦት 17/ 2017 ዓ.ም. ሲሆን በበሽታው ከተያዙት መካከል የአንድ ወር ጨቅላ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስከ ትናንት ሰኔ 04/ 2017 ዓ.ም. ድረስ 102 ለሚሆኑ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ማድረጉን እና በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች ቁጥር 18 መድረሱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።እስካሁን በበሽታዉ ከተያዙት 18 ሰዎች መካከል አምስቱ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ተገልጿል።የመጀመርያው የኤምፖክስ ታማኣሚ የተገኘው ግንቦት 16/ 2017 ዓ.ም. በኦሮምያ ክልል ሞያሌ ከተማ መሆኑ ይታወሳል።
እንደ ጤና ጥበቃ መረጃ ከሆነ የኤምፖክስ ቫይረስ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ሲሆን በኢትዮጵያ በሕክምና ላይ ካሉ ታማሚዎች የተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ የዘረመል ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረት ክሌድ 1 ቢ (Clade 1b) የተባለው ዝርያ ዓይነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል።ይህ የቫይረስ ዝርያ በአንጻሩ ከፍተኛ የሚባል የስርጭት መጠን ያለውና በዚህ የቫይረስ ዝርያ ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሞት መጠን በአንፃሩ ከፍተኛ እንደሆነ በሌሎች አገራት የተገኘ ልምድ ያሳያል።
ለኤምፖክስ በሽታ አጋላጭ ሁኔታዎች ተብለው ከተለዩት መንገዶች መካከል በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚደረግ የሰውነት ንክኪ፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲሁም ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያለውን ቁስ በጋራ መጠቀም በዋነኛነት ይጠቀሳሉ።በኢትዮጵያ በሽታው መያዛቸው ለመጀመርያ ጊዜ የተገለፀው በሞያሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የ21 ቀን ዕድሜ ያለው ሕጻን እና እናቱ ነበሩ።
Via Ethio FM

የበጀት ድልድል
የፌደራል መንግሥት ለ2018 ካዘጋጀው ሁለት ትሪሊዮን ብር ውስጥ ሦስተኛው ከፍተኛ የገንዘብ ድልድል የተደረገው ለክልሎች ለሚሰጥ የድጋፍ በጀት ነው። ክልሎች ከፌደራል መንግሥት የ314.75 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ያገኛሉ።
ይህ ገንዘብ መጠን ዘንድሮ ለክልሎች ከተላለፈው 222.69 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር የ92 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለው። በበጀት እቅዱ ውስጥ ለሁሉም ክልሎች እና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የበጀት ድጋፍ ቢመደብም፤ አዲስ አበባ ከተማ ባልተለመደ ሁኔታ በ2018 ድልድል ውስጥ አልተካተተችም።

242 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ
242 ሰዎችን ከአሕመዳባድ አሳፍሮ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡
ቦይንግ 787- 8 የሚል ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ በምዕራብ ሕንድ አሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ምድር እንደለቀቀ በቅጽበት መከስከሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአደጋው አውሮፕላኑ በእሳት ተያይዞ ሲቃጠል የሚያሳዩ ምስሎች የወጡ ሲሆን ÷ እስካሁን የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት የወጣ ዝርዝር መረጃ አለመኖሩ ተመላክቷል።
Via FBC

የአቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
" በሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር እና በከፍተኛ የኮንትሮባንድ እና አደንዛዥ ዕፆች ንግድ ተሰማተዋል " የተባሉት ባለስልጣን በቁጥጥር ስር ውለው ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን ተሰምቷል።
የፌደራል ብልፅግና ፖርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የሲዳማ ክልል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት 5 ዓመትት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፦
- ሥልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ወንጀል
- በከባድ የሙስና ወንጀል
- በኮንትሮባንድ ንግድ
- በአደንዛዥ ዕፆች ዝዉዉር
- በሕገወጥ የመሳሪያ ዝዉዉር
- በክልሉ መንግሥት ላይ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ መመሞከር
- ላልተገባቸዉ ሰዎች የጦር መሳሪያ ማስታጠቅ
- ግለሰቦችን ያለአግባብ በግፍ አስሮ ማሰቃየትና ለማስለቀቅ ከፍተኛ እጅ መንሻ መቀበል
- በህገወጥ መንገድ ለግል ጥቅም በርካታ ገንዘብ መሰብሰብ እና በሌሎችም መሰል ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቶ ማሩ ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርበዉ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ያለመከሰስ መብታቸውን አንስቷል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሕንድ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ፣ ቢያንስ 110 ሰዎች ሞተዋል ሲል ታይምስ ናው ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው አውሮፕላኑ የተከሰከሰው።
ከ240 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው አውሮፕላኑ የተከሰከሰው።
ከ240 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት እንዲከበር አዘዘ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት ላይ ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ አስተላለፏል። የሰበር ሰሚ ችሎቱ የፖሊስን ማመልከቻ ጭብጥ ከመመልከቱ በፊት የቀረበለት ጉዳይ “ይግባኝ ያስቀርባል” ወይስ “አያስቀርብም” የሚለውን ዛሬ ጠዋት መርምሯል። በዚህም ሰበር ሰሚ ችሎቱ ባሳለፈው ውሳኔ የፖሊስን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ አፅንቷል። ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና መብቱ ተረጋግጦለታል። ይሁንና ይህ መግለጫ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ ከእስር አልተፈታም።
በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ወልደየስ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የቂርቆስ ምድብ ችሎት በ15,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የወሰነው ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 ነበር።
መርማሪ ፖሊስ ለአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የተፈቀደው የዋስትና መብት ላይ ያቀረበው ይግባኝ ትላንት ሰኔ 4 ቀን፤ 2017 ተቀባይነት አላገኘም። የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ለሁለተኛ ጊዜ የጋዜጠኛ ተስፋለምን የዋስትና መብት በድጋሚ አክብሮለታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ሐሙስ የተሰየመው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የህግ ስሕተት አለበት በማለት ፖሊስ አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ነበር። የፖሊስ ይግባኝ አቤቱታ “ያስቀርባል” ወይስ “አያስቀርብም” የሚለውን የመረመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት “አያስቀርብም” የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።
በተጨማሪም የስር ፍርድ ቤቶች የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስን የዋስትና መብት እንዲከበር መፍቀዳቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት እና ህግን የተከተለ ሆኖ ስላገኘው ውሳኔዎቹ እንዲጸኑ ትዕዛዝ ሰጥቷል።ሶስቱም ፍርድ ቤቶች ያስተላለፉት ውሳኔ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ በፖሊስ አልተተገበሩም።

በሕንድ አይሮፕላን አደጋ በ11A መቀመጫ ላይ የተቀመጠ አንድ እንግሊዛዊ ተሳፋሪ መትረፉ ተገለጸ
👉 የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የሃዘን መግለጫ በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ
በሕንድ አህመዳባድ ከተማ አቅራቢያ ከ242 ሰዎችን አሳፍሮ በተነሳ የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ በደረስው አደጋ፤ እስካሁን በአውሮፕላኑ 11 A መቀመጫ ላይ የተቀመጠ አንድ እንግሊዛዊ ተሳፋሪ መትረፍ መቻሉ ተነግሯል፡፡
የአህመዳባድ ፖሊስ ኮሚሽነር ጂ.ኤስ ማሊክ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት፤ ወደ ለንደን ሲያቀና በተከሰከሰው የኤር ኢንዲያ ቦይንግ 787-8 የመንገደኞች አውሮፕላን ውስጥ በ11A መቀመጫ ላይ ተቀምጦ የነበረ አንድ እንግሊዛዊ በህይወት ተገኝቷል፡፡
በባለሥልጣናት የተጋራው የበረራ መግለጫ እንደሚያስረዳው፤ በዚያ መቀመጫ ላይ ያለው ተሳፋሪ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩመር ራምሽ በመባል የሚጠራ ግለሰብ ነው።
ይህንንም ተከትሎ የህንድ መገናኛ ብዙኃን ስሙን እና የመቀመጫ ቁጥሩን የሚያሳየውን ፓስፖርት አጋርተዋል።
መገናኛ ብዙኃኑ ግለሰቡን በሆስፒታል ውስጥ እንዳናገሩት የገለጹ ሲሆን፤ “ከተነሳ ከሰላሳ ሰከንድ በኋላ ከፍተኛ ድምጽ ተሰማ እና አውሮፕላኑ ተከሰከሰ። ሁሉም ነገር በፍጥነት ሆነ” ሲል መናገሩን ዘግበዋል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩ 242 ሰዎች መካከል 217ቱ ጎልማሶች እና 11 ሕጻናት እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን፤ 230 መንገደኞች እና 12 የበረራ ሠራተኞች መሆናቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 169 የሕንድ ዜግነት ያላቸው፣ 53 የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው፣ 7 የፖርቱጋል እና 1 የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተሳፋሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው እንደነበር አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድረስም የ204 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የሀገሪቱ ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን፤ አደጋው አስከፊ በመሆኑ የተሳፋሪዎች በሕይወት የመገኘት ዕድል አነስተኛ መሆኑን ተነግሯል፡፡
አደጋውን ተከትሎም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የሃዘን መግለጫ በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "በአህመዳባድ የደረሰው አደጋ አስደንግጦናል እና አሳዝኖናል ከቃላት በላይ ልብ የሚሰብር ነው" ብለዋል፡፡
"በዚህ አሳዛኝ ሰዓት ሀሳቤ ለተጎዱት ሁሉ ነው። የተጎዱትን ለመርዳት እየሰሩ ካሉ ሚኒስትሮች እና ባለስልጣናት ጋር ተገናኝቻለሁ" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በበኩላቸው በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "በሕንድ አህመዳባድ ከተማ በርካታ የእንግሊዝ ዜጎችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ያቀናው አውሮፕላን በሕንድ አህመዳባድ ተከስክሶ የታየበት ትዕይንት እጅግ አሳዛኝ ነው" ብለዋል፡፡
የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ በበኩላቸው "እኔና ባለቤቴ ዛሬ ማለዳ በአህመዳባድ በተከሰተው አሰቃቂ ድርጊት በጣም አስደንግጦናል" ያሉ ሲሆን፤ ልዩ ጸሎታችን እና ጥልቅ ሀዘናችን በዚህ አሰቃቂ አደጋ ለተጎዱ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሁሉ ይድረስ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔሴ፣ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካኤል ማርቲን፣ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን እንዲሁም የቫቲካን እና የባንግላዲሽ መሪዎች የሃዘን መግለጫቸውን ካስተላለፉት ውስጥ ይገኙበታል፡፡
በኢዮብ ውብነህ