Telegram Web
#China

ጥሬ የአሳማ ስጋ ለ 10 አመት በተከታታይ በልታ ሰውነቷ ተላ👇

በተራራማ የቻይና ገጠራማ መንደር የምትኖረው የ 23 አመቷ Tingting ከማህበረሰቧ ባህል በወረሰችው የአመጋገብ ባህል ከ 10 አመቷ ጀምራ ጥሬ የአሳማ ስጋ መብላት በጣም ታዘወትራለች።

እየቆየ አንዳንድ ህመም ጀመራት። ከባድ ራስ ምታት የአይን ህመም የሰውነት ማሳከክ ወዘተ..ዶክተሮቹ መጀመሪያ ህመሟ ምን እንደሆነ ግራ ተጋብተው ነበር።

ሙሉ ሰውነቷ ከጭንቅላት ቅሏ እስከ ጡንቻዋ በትላትል ተሞላ። ትሉ አይኗ ሳይቀር አቅልቶ ያስለቅሳታል አሳበጣት።

ካየናቸው በሽታዎች በጣም አስቀያሚ ህመም ነው ይላሉ ያከሟት ዶክተሮች።

ደሞ ሚያስጠላው እሷን ማከሙ ከበሽታዋ የባሰ አደገኛ ነው ለምን ከተባለ ህክምና በሚሰጣት ሰአት ሰውነቷ ለመድሀኒቱ የሚያሳየው Reaction ከህመሟ በላይ ሂወቷን አደጋ ውስጥ ሊጥል የሚችል ነው ይላሉ።

ዶክተሮቹ ሲደመድሙ ጥሬ ስጋ መጥፎ ነው በተለይ የአሳማና የከርከሮ ሲሆን ደግሞ የባሰ አደገኛ ነው ይላሉ።

አሏህ የአሳማ ስጋ መብላትን ሲከለክለን ለእኛዉ አስቦ ነዉ፡፡ የአሏህ ተአምሩ ሰፊ ነዉ

#ሱብሀነሏህ

join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ኢስላም_ዛሬም_አለ
አሚር ሰይድ

     ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለበርካታ ዓመታት በኢስላማዊ ርዕዮተ ዓለምን ያስተዳደረው ታላቁ የዑስማኒያ ኸሊፋ በውስጥ መናፍቃንና በጠላቶቹ ሴራ ወድቋል። የፈረንሳይ ኃይሎች ደቡብ ቱርክ "ካህራማማራስ” ግዛትን ተቆጣጥረዋል። ሴቶች የሚለብሱት ኒቃብ ነበር። ያ የኢስላም መገለጫ፣ የክብራቸው ማረጋገጫ፣ የውበት ማጌጫቸው።

    ታዲያ በዚህ መሐል የፈረንሳይ ጄኔራል ኒቃብ ለብሰው በመንገድ ዳር የማጓዙ ሶስት ሴቶችን ተመለከተ ውስጡ በንዴት በገነ። #ኢስላም_ዛሬም_አለ? ሲል ራሱን እየጠየቀ ተብከነከነ። ሊያጠፉት የቋመጡት ኢስላም በሕይወት በመኖሩ ልፋቱ ከንቱ የሆነ ያህል ተሰማው።

"ኸሊፋው ተወግዷል አሁን በፈረንሳይ አገዛዝ ስር ናችሁና ኒቃባችሁን አውልቁ" በማለት ጮኸ። ሴቶቹ ኒቃባቸውን ከሚያወልቁ በያዘው ጥይት ተበሳስተው ነፍሳቸውን መሰዋትን መረጡ። በኒቃባቸው ምክንያት ሸሂድ ሆነው ጌታቸውን መገናኘትን ተመኙ።
.....እሳት ጎርሶ ተጠጋቸው። የአንዷን ኒቃብ ለማውለቅ አጁን ዘረጋ። ይህን ክስተት ይመለከት የነበረ “ኢማም ሶትጆ” የተባለ ወተት ነጋዴ ሙስሊም ሴቶቹ ላይ የተጋረጠውን ጥቃት ለመከላከል የፈረንሳዩ ወታደር ላይ እንደተቆጣ ነብር ዘሎ ተጠመጠመ። ጄኔራሉ በጀርባው የሸጎጠውን ሽጉጥ ነጥቆ ተኮሰ አልሳተውም መሬት ዘረረው። ለሙስሊም ሴቶች ክብር ሲል ጥላታቸውን ጥሎ በነጠቀው ሽጉጥ አጅቦ ቤት አደረሳቸው።

    በዚህ ክስተት ምክንያት በካህራማማራስ ከተማ ግዙፍ አብዮት ፈነዳ። ሁሉም ለኢስላም ሊሰዋ መሳርያ ያለው በመሳርያ ...መሳሪያ የሌለዉ በባዶ እጁ ከፊት ተሰለፈ። ፈረንሳውያንን በማባረር ከተማዋን ነፃ አወጡ።

ከተማዋ በኢማም ሶትጆ ስም አሸብርቃ ዋለች። የተሸፈነች ሙተነቀብ ሴት መሬት የወደቀ የፈረንሳይ ጄኔራልና ኢማም ሶቶጆ ሽጉጥ አነጣጥሮ ሲገድለው የሚያሳይ ምስል በከተማው አደባባይ ላይ ተተከለ  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በስሙ ተሰየሙ። ታሪክ የማይረሳው ጀግና ሲሉ  አስከ አሁንም የቱርክ ጎዳናዎች ያስታውሱታል።

አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው።

#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ እንዴት ናቹልኝ...

#ሰደቀቱል_ጃሪያ_ስለሚባለው_የሰደቃ_አይነት_ምን_ያህሎቻችን_ነው_ምናውቀው?

#ሰደቀቱል_ጃሪያ:- ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ ቀጣይነት ያለው ሰደቃ /ምፅዋት/ ነው:: ቀጣይነት ያለው ሲባል ደግሞ ምንዳው ወይም አጅሩ በሕይወት እያለን በሰጠነው አንድ ሰደቃ ምክንያት ሕይወታችን ካለፈ በኃላም ምንዳው ሳይቋረጥ እየተጨመረልን የሚሄድ ማለት ነው::

#ዛሬ በዚህ ርዕስ ላይ የማወራችሁ በምክንያት ነው...

#ኢፋዳ የሚባል ኢስላማዊ ተቋም ይህንን የ #ሰደቀቱል_ጃሪያ ዕድል በአቅማችን ልክ እንድንሳተፍበት ስለጋበዘን ነው::

ምን መሰላችሁ የሰደቃው ሀሳብ..🤔

👉በአላህ ፍቃድ 22 #የውሃ_ጉድጓዶችን ከፍተኛ የውሃ እጥረት ባለባቸው የሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለማስወጣት እቅድ ተይዟል::

የውሃ ጉድጓድ ለተቸገሩ ሰዎች ማስቆፈር ደሞ አንዱ የሰደቀቱል ጃሪያ አይነት ነው::

በላጩ  ሰደቃ ውሀ ማጠጣት ነው እንዳሉት መልእዕተኛው 😊

👆መቼም በዚህ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ የማይጓጓ ይኖራል ብዬ አላስብም... አይደለም እንዴ ውዶች?

ይህን ያህል ከተግባባን አሁን ወደ ተግባሩ ብንሸጋገር ምን ይመስላችኃል... ዳይ ወደ ሰደቃችን👍👍👍

ሁላችሁም በምትፈልጉት የብር መጠን መሳተፍ ትችላላችሁ:: ከ100 ብር - 5000 ብር ድረስ የተዘጋጀ ኩፖን አለ...

የምታስገቡበት አካውንት:-
●የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ1000652519524
●ዘምዘም ባንክ 0048131010301
●ሂጅራ ባንክ 1006954160001
●አዋሽ ባንክ 014321422006700
●አቢሲኒያ ባንክ 200009207

ካስገባችሁ በኃላ ስክሪን ሹት በ  @Abdu979 መላክ እንዳትረሱ

ለበለጠ መረጃ👉 @Abdu979
⚡️⚡️#ፍትሕ_ከሰማይ_ሲወርድ⚡️⚡️
                አሚር ሰይድ
  

   ከማህፀናቸው ፍሬ የወጣ ልጅ፣ በክፉ ጊዜም ደራሽ ዘመድ አዝማድ የላቸውም። የሰባ ዓመት ዕድሜ ደካማ ባልቴት ናቸው። “እንዴት ሰው ያለወገን ይፈጠራል?" ይባል ይሆናል። ዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ ይህችን ዓለም ተራ በተራ እየለቀቁ ቀድመዋቸው ተጉዘዋል፡፡ የጤንነታቸው ጉዳይ ማጠራጠር ከጀመረ ሰንበትበት ብላል። "እንደምን ዋሉ? " ላላቸው ሁሉ "ጉልበቴን ይቆረጥመኛል፣ ወገቤን ያመኛል፣ ዓይኔንም ያዝ እያደረገኝ ነው" ሳይሉ አያልፉም። ይህ ብቻም አይደለም" አላህ መጨረሻዬን አሳምሮ ብርሀኔን ሳያሳጣኝ፣ መላወስ ሳይሳነኝ ቀልጠፍ አድርጐ በወሰደኝ" ሲሉ ያክሉበታል፡፡

ዋነኛ መተዳደርያቸው ከመንግስት የሚያገኙት ክፍያ ነው። ኸዲጃ ይሰኛሉ። እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለዉን የጡረታ ዋስትና የሚቀበሉት በዓመት አንድ ጊዜ ነው። መንግስት የሚሰጠውን ገንዘብ እንዲያገኙ የታገለላቸዉ የቅርብ ጎረቤታቸው አንድ ወጣት ነበር። ኸዲጃ ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ ሁሉ ካንጀታቸው ይመርቁታል።

ምግባረ ሠናዩ ወጣት አካባቢውን እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ ወይዘሮዋ ክፍያውን ለመቀበል ሲሄዱ አጃቸውን ይዞ ወገባቸውን ደግፎ ሲያመላልሳቸው ለዓመታት ሲያገለግላቸው ቆይቶ፣ በመጨረሻ አካባቢውን ለቀቀ። ወጣቱ መኖርያውን ከቀየረ ጥቂት ወራት በኋላ የደመወዝ ክፍያ ቀን ደረሰ። ወጣቱ የለም። ከአካባቢው ነዋሪዎች እምነት የሚጣልበትና አድርሶ ሊመልሳቸው የሚችል ሰው አላገኙም።

ኸዲጃ ከዚያ የተባረከ ወጣት ሌላ እምነት የሚጥሉበት ሰው እንደማያገኙ ተረድተዋል። ብቻቸውን ለመሄድ ቆርጠው ተነሱ።ቁና ቁና እየተነፈሱ ክፍያው ከሚፈፀምበት መስሪያ ቤት በደረሱ ጊዜ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች በሚገባ ተቀብለው አስተናገዷቸው። ድካማቸውን ተወጥተው፣ ደሞዛቸውን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ለመመሰስ ሲነሱ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች እስከ ታክሲ መሳፈርያው ድረስ ሸኛቸው።

    ሸኚዎቻቸው ቆመው ታከሲ በመጠበቅ ላይ ሳሉ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ባልቴቷን በስም ጠርቶ እጃቸውን በመሳም ሰላምታ ሰጣቸው። ወደ ሸኚዎቻቸው ዞሮ የቅርብ ጐረቤታቸው መሆኑን ነገራቸው። መኪና ይዟል። ሸኚዎቹ ታክሲ እየጠበቁ እንደሆነ ሲነግሩት “እኔ እያለሁ ምን ታክሲ ያስፈልጋል። እናንተ ተመለሱ እኔ አደርሳቸዋለሁ" በማለት ሸኚዎቹን አስናብቶ ባልቴቷን ወደ መኪናው ወሰዳቸው። ጎልማሳው ኸዲጃን ከጐኑ አስቀምጦ የባጥ የቆጡን እያወራ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከግማሽ ሰዓት በላይ ተጓዙ፡፡


   ኸዲጃ መንገዱ ያለቅጥ ረዘመባቸውና አንዳች ነገር አእምሯቸውን ከነከነው። ጥቂት አሰቡና “ምናልባትም እግረ መንገዱን መድረስ የፈለገበት ይኖር የሆናል" ሲሉ ስጋት ያደረበት ልባቸውን መልሰው አረጋጉት። ነገሩ ግን እንደዚያ አልነበረም። ሰውየው አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ግራ ታጥፎ ከዋናው መንገድ በመውጣት ጉዞውን ሽቅብ ወደ ተራራው አደረገ። የኸዲጃ ልብ በፍርሃት ይናጥ ገባ። መላ አካላቸው ተንዘፈዘፈ ...መጮህ ቃጣቸውና መልሰው ተውት። የሞት ሞታቸውን “ልጄ ወዴት ነው የምትወስደኝ?" ሲሉ ጠየቁት ቁርጥ ቁርጥ ባለ አነጋገር። “እዚህ ቅርብ ነው። የአትክልት ቦታዬን ማየት አለብኝ። እርስዎም  ፍራፍሬዎችን ይዘው ቤትዎ ይመለሳሉ" አላቸው። ያሰበው ነገር የተነቃበት ይመስል በተሳሰረ አንደበት።

   ኰሮኰንቹን ሲጨርስ መኪናውን አቆመ። ዝምታ ለደቂቃዎች ሰፈነ። ትርጉም ያለው ዝምታ ነበር፡ የባልቴቷን የሰጋት፣ የጐልማሳው ደግሞ ዘዴን የመሻት። ደቂቃዎች ተቆጠሩ። ጐልማሳው ጥጥና ጨርቃ ጨርቅ ነገር ከኪሱ አወጣ። በፍርሀት ተውጠው አቀርቅረው የተቀመጡትን ደካማ አሮጊት አንገት አነቀ። እንዳይገድላቸው ተማፀኑት። ገንዘባቸውን ወስዶ ሕይወታቸውን ብቻ እንዲያተርፍላቸው ለመኑት። ስለ ነገሩ ለማንም ትንፍሽ እንደማይሉም ገለፁለት። .....በአምሮተ ንዋይ የታወረው ጐልማሳ ግን ሊራራላቸው አልቻለም። ይልቁንም ጭካኔውን አባሰው። አፋቸው ውስጥ ጥጥ ከጐሰጐሰ በኋላ ገዘባቸውን ከጉያቸው አወጣ። አጆቻቸውን ከተቀመጡበት ወንበር ጋር የፊጥኝ አሰራቸው። ከመኪናው ወርዶ ከኋላኛው የመኪናው ኪስ አካፋና ዶማ አወጣ።

ደካማዋን ባልቴት ገድሎ ከቀበረ በኋላ በገንዘባቸው ዓለም ዘጠኝ ሊሰኝ በመወሰን ቁፋሮውን ተያያዘው። መጠኑ ብዙ በሆነው ብር የሚያገኘው ደስታ እየታየው በጥድፊያ ይቆፍር ጀመር። ቢሆንም ግን ጉድጓዱን ቆፍሮ ሳይጨርስ ድንገተኛ ፍትህ ከአላህ ዘንድ ወረደ። ርዝማኔው ከአንድ ሜትር በላይ የሆነ ኮብራ እባብ አቀርቅሮ በሚቆፍረው በዚያ አረመኔ ሰው ጀርባ ላይ ተከመረ። አራት የተለያየ ቦታ ከነደፈው በኋላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመ። ወጣቱ ደካማዋን አሮጊት ለቀብርባት በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ተዘረረ።

    ይህ ሠማያዊ ፍትሕ ከመውረዱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሰውየው ጉድጓዱን በመቆፈር ላይ ሳለ የተጨነቁት ባልቴት ደጋግመው አላህን ይለምኑታል “በእርግጥም ያንተ ፍጡር ነኝ። በንፁህ ልቤም ተገዝቼሀለሁና ከዚህ ድንገተኛ መአት አድነኝ። የማሳድጋትን የቲም ልጅ ለወግ ማዕረግ ሳላበቃ አትግደለኝ" ይሉ ነበር ደጋግመው።

#ባርያውን_የማይረሳው ጌታ የእኒህን ደካማ ሴት ጥሪ ሰምቶ ፈጣን ምላሹን ሰጠ። ሕይወታቸውንም ታደገ።

ሰዓታት አንድ ሁለት ተብለው ተቆጠሩ። ህፃናት እረኞች የከብት መንጋ አየነዱ በአካባቢው ሲያልፋ የቆመ መኪና ተመልከተው ተጠጉ። በአእምሯቸው የሚከብድ ነገር አይተዋልና ለወላጆቻቸዉ ሊነግሩ ፈጠኑ። የህፃናቱ ወላጆች የሰሙትን ለፓሊስ አሳውቀው ወደ ሥፍራው ተጓዙ።
....አፋቸው በጥጥና በጨርቅ የታፈነውና እጆቻቸውም የፊጥኝ የታሰሩት አሮጊት ፖሊስ ደርሶ ከአፈናውና ከእስራቱ ነጻ አወጣቸው “አልሐምዱሊላህ" ሲሉ ተሰማ። ጉድጓድ ውሰጥ የተዘረረውን ሰው ሁኔታ ለማጣራት ፖሊሶች ፊታቸውን ወደዚያ አዞሩ። ወደ ሰውየው በማምራት ላይ ሳሉም በሰውየው አንገት ላይ የተጠመጠመው እባብ ቀስ በቀስ ተፈትቶ ወደ ጥሻ ውስጥ ተፈተለከ። የሰውየው ነገር አብቅቷል። የደም ዝውውሩ አቁሟል። አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ሲላክ ደካማዋ አሮጊት ወደ ቤታቸው ተወሰዱ። አጀብ የአላህ ስራ!

#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

አብሽሩ አይዞን ....ጥሎ የማይጥል በችግር በጭንቅ በሀሳብ ከሰዉ መፍትሄ የጠፋ ጊዜ የሚሰማ ለእኛ መፍትሄ ቅርብ የሆነ ጌታ አለን አልሀምዱሊላህ፡፡ አልቅሰን ሰደቃ ኸይር ስራ አብዝተን ወይም ተዉበተን አድርገን  እንቅረበዉ እንጠይቀዉ አላህን ጠይቆ ያፈረ ባዶ እጁን የተመለሰ የለምና

🔰🔰ብቻ ብቻ ጠይቀነዉ ዘግይቶ ይሆናል እንጂ የጠየቅነዉ አይቀርም.አላህ የኛን ዉስጥ ስለሚያቅ የጠየቅነዉን ቢሰጠን ለኛ የማይጠቅም ከአላህ የሚያጣላ ሊሆን ስለሚችል አስቀርቶት በአጅር በምንዳ ወይ በሌላ ለኛ በሚጠቅም
ነገር ቀይሮት ይሆናል ለምሳሌ በጤና እና ድንገተኛ አደጋ የሚመጣን በላዕ ችግር አስቀርቶልን ይሆናል፡፡ የአላህን በር አንኳክቶ ቦዳዉን ላይመልስ ቃልገብቷል፡፡ እስኪ ለሰዉ ነግረነዉ ያልተፈፀመ ከሰሚዉ ጆሮ ያላለፈዉን ጉዳይ ያአሏህ ያዘል ጀላሊ ወልኢክራም ብለን እንገረዉ ..መልስ አለ አይዞን የምን ተስፋ መቁረጥ ጠበቅ አድርገን የአላህን ደጅ ከመፅናት እንዳናቆም .የጠየቅነዉ ሁሉ አላህ የጠየቃችሁት ከኔ የማያጣላችሁ ብሰጣችሁ  እኔን ወንጅላችሁ ጀነቴን ታጣላችሁ ብሎ አስቦልን ይሆናል ያልሰጠን እንጂ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ዱአ ስናደርግ የተደረገዉ ዱአ የሚደርስ ወይም ወንጀል እንደሚያብስ ወይም ለአኼራ እንደሚቀመጥ ነግረዉናል፡፡
አይዞን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልጅ የአሏህ ስጦታ እንጂ በሰዉ ምርጫ አይሆንም

join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
💚#በረሱል_ፍቅር_ሰጥሜ_መስጂዳቸውን_ጎጆዬ     
............. #ላደርግ_ለአላህ_ቃል_ገባሁ.............
          አሚር ሰይድ

   ቁመቱ አጭር መልኩም የቀይ ዳማ ነው። ጀለቢያ መልበስ ያዘወትራል። ከዘምዘም ዉሀ በመዳፉ እየጨለፈ ይጎነጫል። ካገኘ ፍራፍሬ ይመገባል። ካጣም ሆዱን አጣጥፎ የጌታውን ቁርአን እያነበበ ፆሙን ያድራል። መሬት ፍራሹ፣ ብርድ ልብሱም ሠማይ ነው። የነቢ መስጂድ ውስጥ ጎጆውን ቀልሶ ለአስርት ዓመታት ኖሯል። ሰውነቱ የኮሰሰ ቀጫጫ ትውልደ አልባኒያዊ ነው።

ከነቢ ቀብር ፊት ለፊት ከሐረም አን-ነበዊ መታጠቢያ ቤት የወጣውን ይህን ወጣት አራት የሰዑዲ ፖለሶች ዘለው ተከመሩበት። በሆዱ አስተኝተው እጆቹን ቀፍድደው የፊጥኝ አሰሩት “ሽፍታም ሌባም አይደለሁም” እያለ መጮኽን መማፀን ጀመረ።

በዕድሜ የገፉ አንድ ሽማግሌ ክስተቱን ተመልክተው ቢጠጉ ገፅታው አልጠፋቸውምና “ይህን ወጣት አውቀዋለሁ” አሉ

“የረሱል መስጂድ ውስጥ እየሰገደ ሲያለቅስ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አላህን ሲማፀን አውቀዋለሁ አዎ ራሱ ነው" አሉ መሬት ላይ የሚንፈራገጠውን ወጣት ትኩር ብለው እየተመለከቱ።

ጣል ጣል ብለው የሚታዩ የፂም ፀጉሮች ባለቤት ነው። ቀለል ያለ ሰው ፊቱ ላይ የሚንፀባረቀው ነጭ ኑር ከሩቅ ያብለጨልጫል። ሸይኹ ቀጠሉ "ምን አጥፍቶ ነው ያሰራችሁት?" ብለው ጠየቁ።
.... “አንተ ሽማግሌ!" አሉ ፖሊሶቹ" ጣልቃ አትግባ ይህ አንተን አይመለከትም" አላቸው።

“ሲሰርቅ አይታችሁታል?! ገዳይስ ነው ነፍስ ሲያጠፋስ ደርሳችሁበታል?! ወይስ ምን ወንጀል ሰርቷል?!" ሸይኹ ዳግም ግራ በመጋባት መንፈስ ጠየቁ፡፡

......“ይህ ወጣት" አሉ ፖሊሶቹ ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ይህ ወጣት... ኑሮውን እዚህ መስጂድ ውስጥ ማድረግ ከጀመረ አስርት ተከታታይ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመኖርያ ፈቃድ ኢቃማም ሆነ ፓስፖርት የለውም። በነቢ መስጂድ ስለተቀመጠ አባረን ልንዘው አልቻልንም ነበር። ስናሳድደው ሲያመልጠን ይሄው አስር ዓመታት ተቆጠሩ። ዛሬ ግን በእጃችን ገባ። ወደ ኤርፖርት ወስደን ወደ ሀገሩ አልባኒያ ልንመልሰው እንዳያመልጠን አድርገን አሰርነው" አሉ።

ወጣቱ የፖሊሶቹን ንግግር ሲሰማ ስቅስቅ ብሎ አያለቀሰ😢😢 “አልሰረቅኩም ነፍስም አላጠፋሁም በረሱል ፍቅር ሰጥሜ መስጂዳቸውን ጎጆዬ ላደርግ ለአላህ ቃል ገባሁ። ሽፍታም አይደለሁም። የአላህ መልዕክተኛን ስለምወድ እዚህ ቀረሁ። ከረሱል ﷺ መስጂድ ከሳቸው ጉርብትና ተነጥዬ እንዴት መኖር ይቻለኛል?? አለ ትካሻውን አያወዛወዘ

"ተቀባይነት የሌለው ምክንያት ነዉ ። እዛዉ ወደ ሀገርህ ትመለሳታለህ አሉ ፊታቸው በንዴት የቀላው ፖሊሶች




    ወጣቱ ፊቱን ወደ መስጂድ አን-ነበዊ አቅጣጭቶ : -

“አላህዬ ስምምነታችን አንዲህ ነበር? " አለ አንገቱን ወደ ሰማይ አቅንቶ “ከአላህ መልክተኛ ጎን አኑረህ አንድትገለኝ አልነበር የጠየቅኩህ?! እናትና አባቴን ትቼ ሱቄን ዘግቼ የመጣሁትስ ለዚሁ አይደል?! ፍቅራቸው ንግዱን አስትቶ እዚህ አመጣኝ። መስጂዳቸውን መኖርያዬ ላደርግ ጉርብትናቸውን ትቼ ሀገሬ ላልገባ በአንተ ቃል ገባሁ። አሁን አነዚህ ሰዎች እየከለከሉኝ መሆኑን ተመልከት....ያ አላህ ጣልቃ ገብተህ ለምን በጠየቅኩህ ዱዓ ምላሽ አትሰጥም?! ያረቢ የረሱልን ጉርብትና እለምንሀለው😔" ሲል በምሬት እያነባ ጌታውን ጠየቀ።

......ከመቅፅበት በቆመበት ቦታ ተዝለፍልፎ መሬት ተደፋ። ፖሊሶቹ “ተነስ አንተ አታላይ” እያሉ በያዙት ዱላ አንድ ሁለቴ አቀመሱት። ወጣቱ ግን ምላሽ አልሰጠም መሬት አንደወደቀ ነው። ውሀ ደፉበት ሊነቃ ግን አልተቻለውም። አምቡላንስ በአስቸኳይ አስጠርተው ይዘውት ወደ ሆስፒታል አቀኑ።

ፖሊሱ ክስተቱን ሲያወጋ እንዲህ ይላል፡-

“ለሞት የሚያበቃ ዱላ አልሰነዘርንበትም። ሆስፒታል አንዳደረስነው ሀኪሞቹ የልብ ምቱን አዳምጠው ሩሑ ከጀሰዱ የመላቀቁን ዜና አረዱን። አዎ ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው ጌታ አላህ ምሳሹን ሰጠ። በረሱል ሀገር በሳቸው መስጂድ አቅራቢያ ሩሁን እንዲያወጣ መለከል መውትን አዘዘ"

ፖሲሶቹ በትዕይንቱ ዕንባ እየተናነቃቸው በሀዘን ተብረከረኩ። በድርጊታቸው ተፀፅተው በዕንባ ተዋጡ።

"ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ያህል ፍቅር እንዳለው ብናውቅ ኖሮ ይህን ባላደረግን” እያሉ በድንጋጤ ተዋጡ።

አምቡላንሱ ጀናዛውን ይዞ ወደ በቂዕ መቃብር ጉዞውን ጀመረ። ታላላቅ ሰሐቦች ወደተቀበሩበት ሥፍራ ከነፈ።



   ሸይኹ “ክስተቱን ከጀምሩ እስከ ፍፃሜው እየተከታተልኩ ነበር" ይላሉ። ታጥቦ ተከፈነ ሰላተል ጀናዛ ከተሰገደበት በኋላ ወደ ቀብሩ ልናስገባው ስንሄድ ፖሊሶቹ በትከሻቸው ተሸክመውት ነበር። ጠጋ አልኩና አኔም ጀናዛውን ልሸከም አቀበለኝ አልኩት ለአንደኛው ፓሊስ። እሱም ዓይኖቹ አያነቡ "ወንጀላችን ይብቃን ምናልባት አላሁ ተዓላ ይቅር ይለን ዘንድ ጀናዛውን እኛ አንጂ ማንም እንዲሸከመው አንፈቅድም" አለኝ

ጌታህን አብዝተህ ስታወሳ መጨረሻህ የምራልና አላህዬን ይዘህ ፅና!!

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ




⚡️⚡️ነብዩን መዉደድ ማለት ሙዚቃ የሚመስል ነሺዳን በሌላ አገላለፅ የአሁን ነሺዳ እሩብ ጉደይ ለሙዚቃ የሆነን በማዳመጥ ...አብሮ ነሺዳን በማለት በየመድረኩ ነቢይ በማለት አይደለም፡፡ የነቢይ ዉዴታ ሲኖርህ መድረክ ለመድረክ በየሚዲያዉ ነቢይ ስላልን ወደናል ማለት ራስን ማታለያ ነዉ፡፡ ራስን ማታለል ይቻላል አላህን ግን ማታለል አይቻልም፡፡ ነቢዩ ስም ልናነሳ ስንል እስክታዉ ዝላዩ ዉዝዋዜዉ ሳይሆን እንባችን ይቀድመን ነበር ወገን👌

በፊት የነበሩት ትዉልዶች ነቢይ ሙሀመድ ﷺ እንዴት እንደሚወዷቸዉ በኡሁድ ጦርነት ጊዜ ነቢይ ሙሀመድ ﷺ ይወዱ የነበሩ ሱሀቦች እና አሁን እኛ ባለንበት ሀቢቡና ﷺ እንዴት እንደምንወድ ራሳችንን እንፈትሽ ለምን....ነገ የምንቀሰቀሰዉ የስራችን ሚዛን የሚለካዉ ከእነሱ ጋር ስለሆነ...እኛ የነቢይ መሀመድ ﷺ ኡመት ነንና

በቀንም በሌትም በጧትም በማታም ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ💚


30 አመት ያህል ነሺዳ ከማዳመጥ የአንድ ደቂቃ
ሶለዋት አለረሱል በላጭ ነዉ::
አንድ ሺህ ነሺዳ ከማዳመጥ አንድ ሶለዋት አለረሱል ብናወርድ ነዉ ለኛ ነገ ሙተን ቀብር ገብተን ለአኼራ ጥያቄ የሚጠቅመን ..

ህይወት ትላንት ወይ ነገ አይደለችም ህይወት አሁን ናት ለቀብር የሚጠቅምህን ስራ፡፡አሁን ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁን ደግሞ ነገ ይሆናል
....ግን ነገን ማየት ላንችል እንችላለን ጀናዛ ልንባል እንችላለንና በአገኘነዉ አጋጣሚ ጊዜን በነሺዳ(እሩብ ጉዳይ ሙዚቃ) ከማዳመጥ ይልቅ ሶለዋት አንዘንጋ



ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ ﷺ ﷺ💚💚💚


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
በኳታር አደራዳሪነት ሲደረግ የነበረው የሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት 464 የግፍ ቀናቶች ቡሀላ ተፈፀመ።

በዚህም መሰረት በሀማስ እጅ ያሉ እስራኤላውያን የሚለቀቁ ሲሆን በእስራኤል እጅ ያሉ ፍልስጤማዊያንም ይለቀቃሉ። የተኩስ ድምፅ የማይሰማ ሲሆን የእስራኤል ጦር ከጋዛ ለቆ ይወጣል።
በመደመሪያዎቹ ቀናትም አስቸኳይ እርዳታን የያዙ 600 መኪኖች ወደ ጋዛ ይገባሉ።
በጋዛ ላይ የሚደረጉ የጦር በረራዎች የሚቆሙ ሲሆን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል።

ከዚያም ጋዛን እንደገና የመገንባት ስራ በአለምአቀፍ ዘመቻ ይጀመራል።

የሞቱትን ከሸሂዶች ጋር አላህ ይቀስቅሳቸዉ፡፡ ግን እስኪ እስራኤልና አሜሪካን የሚታመኑ አይደሉምና ፈረጃዉ ከአሏህ ያድርግላቸዉ፡፡ የሁዶችና አሜሪካን በቃላቸዉ ይገኙ ይሆን??

እስኪ እናያለን ብቻ የጋዛን ሰላም ነዉ የምንፈልገዉ፡፡



ፍልስጤማዊያንን በጅምላ ሐገር አስጥሎ ወደ ሲና በረሐ እንዲሰደዱ የተደረገው ሙከራ ሁሉ አልተሳካም።
የጄኔራሎቹ እቅድና ውጥን ከሽፏል።
ከኔትዛሪም አንወጣም።
ፊላደልፊያን አንለቅም ሲሉ የፎከሩበት ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰራዊታቸውን ማጋዝ ጀምረዋል።
ሃማስን እናጠፋለን እስረኞቻችንን እናስለቅቃለን ብለው የደነፉበት ሁሉ ገደል ገብቷል።

ጋዛ ከነ ውድመቷ ራሷን ቀና አድርጋ ኃያላንን ሁሉ ሰባብራለች ምስጋና ለአላህ ክብርም ለቀሳሞች ይሁን

 

ዛሬ ለሰማነዉ ኸበር አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀል!! እዉነት ሁኖ የሚፈፀም ያድርገዉ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
⚠️የሲህር የድግምት ምንነት
☞ሲህር የተደረገበት ሰዉ ምልክት
☞ሲህር የተደረገበት ሰዉ ህክምና
☞የጠንቋዮች ምልክቶች

የተለያዩ ድግምት ጋር የተያያዙ ብዥታዎችን የሚመልስ ምርጥ ሙሀደራ ነዉ እስከ መጨረሻዉ በማዳመጥ ራሳችንን እንፈትሽ

#ኡስታዝ_ሱለይማን አብደሏህ የቀረበ ትምህርት

🕞 የትምህርቱ ቆይታ 1ሰአት ከ19 ደቂቃ ያህል እርዝመት አለዉ፡፡
ያዳምጡት ጠቃሚ ትምህርት ነዉ፡፡



join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#በሕይወቱ_አንድ_ጊዜ_የሱብሒን_ሶላት   
    #ባሰመስገዱ_ተንሰቅስቆ_ሲያነባ
          አሚር ሰይድ


አነስ አብኑ ማሊክ አነባ

   አለቀሰ ያውም ስቅስቅ ብሎ የእንባ ዘለላዎች በጉንጮቹ ላይ እየፈሰሱ ለረዥም ሰዓት ቆየ። ሙስሊሞች ቱስቱር ከተማን ድል አድርገው የከፈቱበት ዘመቻ በተወሳ ቁጥር አንገቱን ሰበር አድርጎ ያነባል።

ስለቱስቱር ምን አሳወቃችሁ እሷ የፋርስ ከተማ አልነበረችምን? ሙስሊሞች ለአንድ ዓመት ያህል የከበቧት። ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከተማይቱ በሙስሊሞች እጅ ወደቀች። ግልፅ የሆነ ድልን ተጎናፅፈው ከፈቷት፡፡

ታዲያ አነስ ኢብኑ ማለክ የቱስቱርን ዘመቻ ሲያስታውስ ለምን ያለቅሳል??

    ገና ጎህ ሳይቀድ ነበር የኢስላም ሰራዊት ወደ ቱስቱር ምሽግ የዘለቀው። ሰላሳ ሺህ ሙጃሂዶች ከአንድ መቶ ሀምሳ ሺህ የመስቀል ሠራዊቶች ጋር ገጠሙ። መራር ውጊያ ተካሄደ። ከባድ ጦርነት ተከናወነ። ሙስሊሞች ደማቸውን እያንጠባጠቡ ሰውነታቸውን በጨርቅ እያሰሩ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አደረጉ። እጅግ በጣም አስቸጋሪ እጀግ ከበዛ እልቂት በኋላ ለአላህ ምስጋና ይግባውና ሙስሊሞች ድል ተጎናፅፈው በጠላታቸው ላይ ድልን ተቀናጁ ይህ ድል ፀሀይ ከወጣች ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሙጃሂዶቹ በእጃቸው የያዙትን ሠይፍ ወደሰገባው ሲመልሱ የሰብሒ ሶላት እንዳመለጣቸው አወቁ። ጎህ ከመቅደዱ በፊት ሰዓቱን ጠብቀው የሱብሐን ሰላት መስገድ አልተቻላቸውም ነበር። እጅግ አዘኑ ምክንያታዊ ሆነው ዑዝር ኖሯቸው እንኳ አቅልለው አላለፏትም።

   አነስ ኢብኑ ማለክ በሕይወቱ አንድ ጊዜ የሱብሒን ሰላት ባለመስገዱ ተንሰቅስቆ አነባ። አቀርቅሮ አለቀሰ። የሙስሊሙ ጦር በእስልምና ሻኛ በአላህ መንገድ በጂሃድ ተጠምዶ አላህ ዑዝር ሰጥተቸው አነሱ ግን አነቡ።

አነስ እንዲህ ይላል፦ “ቱስቱር ምንድነው?! የሰብሂ ሶላት አምልጣኛለች ዓለም ሁሉ በዚህ ሶላት ልዋጭ ትሁንህ ብባል እንኳ አልቀበልም ብሏል፡፡


አሁንስ ለምን አላህ ድል አንደተጎናፀፋቸው ገባህ? እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸውን ሙሉ ለአላህ ሰዉ። እኛስ ስለኢማናችን እንቅልፋችንን መስዋዕት ማድረግ ችለናልን?

ካልቻልን...የምን ድል የምን ከፍታን እንመኛለን?

በልባችንና በሕይወታችን ውስጥ የሶላት ዋጋ ተገፎ ኃያልነታችንንና  ክብራችንን አጥተናል። ዱንያ ጠባ አጣብቃናለች። ጠላቶቻችን ወረው ከዚህም ከዚያም ይቦጫጭቁናል።

   የእውነት ኢስላምን እንኑር “ምእመናን አንደሆናችሁ የበላይ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ" ተብሎ በአላህ ቃል ተገብቶልን ሳለ ለምን የበታች የሆንን ይመስላችኋል?? ራሳችሁ መልሱት
#ጣትህን_ወደሌላው_ከመቀሰርህ_በፊት_ወደራስህ_አቅጣጫት



ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላለዉ መፅሀፍ

ሚዲያ ላይ አፍጠን ሱብሂን የምናሳልፍ ሰንቶቻችን ነን?? አነስ አንድ ቀን አልፎት ሲያለቅስ የኖረዉ እኛ
ብዙ ቀን አልፎናል ቢለቀስ እምባ ይበቃን ይሆን


ሙተን ጀነት እንገባለን ብለን እየታገልን ሱብሂ ሶላት እያለፈን የጀነት መግቢያችንና እርዚቃችንን እያጣበብን መሆኑን አንዘንጋ⚠️⚠️


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
     🎖🎖 #ለእርሷ_እንባ_ሲል🎖🎖
                አሚር ሰይድ

   ውዷ እህቴ! በታሪክ ውስጥ ለሚመከርበት ሰው ታላቅ ተግሳፅ አለና ከዚህ ታሪክ ትማሪ ዘንድ ታሪኩን እነሆ ጀባ አልንሽ።

    በአልጀርስ አውሮፕላን ማረፊያ አንዲት ሴት ተንበርክካ ታለቅሳለች። የአላህን ቤት ለመጎብኘት ረዥም ዓመት ጓጉታ ስትናፍቅና ልቧ ሲዋልል ከርማ እሷን ትቶ የሐጅ ተጓዦችን ጭኖ አውሮፕላኑ ጥሏት በመሄዱ አምርራ ታነባ ይዛለች።

    በሰማይና በምድር መሐል የሚበረው ፕሌን በድንገት እንግዳ ጩኸትን ያሰማ ጀመር። ከምድር ሀያ አራት ጫማ ከፍታ ላይ ሆኖ መርገፍገፉን ተያያዘው። በዚህ ጊዜ ነበር ፓይለቱ መሪውን በመጠምዘዝ አቅጣጫውን ወደ አልጄሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ያደረገው።   
    ተሳፋሪዎቹን አውርዶ የጥገና ሠራተኞቹ ሥራቸውን ጀመሩ። የጥገና መሐንዲሶቹ ብልሽቱን ለማወቅ ጣሩ። ግን አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ሰላም ነበር። ምንም ችግር የለበትም ሲሉ ተናገሩ።

   ስለሷ ዕንባ ሲል አላህ ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን የጫነውን አውሮፕላን ከመሐል መንገድ መለሰላት።


     በፍርሐት እየተንቀጠቀጠች አምርራ ያለቀሰችው እንስት ወደ ጌታዋ የዘረጋቻቸው መዳፎች ምላሽን በፍጥነት ተችረው ዳግም እንደ አዲስ ፕሌኑ ሴትዮዋን ጭኖ ጉዞውን ወደ መካ ጀመረ።

👌ሁሉም በሮች ቢዘጉብህ ደጃፎች ሁሉ ቢጠረቀሙብህ አጅህን ዘርግተህ ወደ አላህ ዱዓ ከማድረግ አትዘንጋ።‼️‼️


ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ሱሐቦቹ_ለምን_ቀደሙ_እኛስ_ለምን_ዘገየን?!
          አሚር ሰይድ

   በወርሀ ረጀብ በ13ኛው ዓመተ ሒጅራ ስፍራው በሻም ምድር በዛሬዋ ሶሪያ የርሙክ ወንዝ ስር ሁለት በመጠንና በአደረጃጀት ፍፁም የተለያዩ ሀይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ተፋጠዋል። አርባ ሺህ ሙስሊም ወታደሮች ሁለት መቶ ሺህ የሮም ሠራዊትን ሊገጥሙ በተጠንቀቅ ቁመዋል።

   ኻለድ አብኑል ወለድ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ሱረቱል አንፋል አንዲቀራ አዘዘ። አቡ ሁረይራ ተነስቶ ዳዕዋ አደረገ አቡ ሡፍያንም ቀጠለ። የሱሀቦች የውጊያ ወኔ ተቀሰቀሰ። በቁጥር አናሳዎቹ ግዙፉን የሮም ጦር አንበርክከው በሙስሊሞች ድል አድራጊነት ጦርነቱ ተደመደመ።

   የሮሞች መሪ ሂረቅል ወደ አንጣኪያ አቅጣጫ አመለጠ። ያ ሁሉ ሰራዊት በአናሳ ጦር እንደዚህ መበታተኑ ንድድ አድርጎታል። አንጣኪያ ከተማ ላይ ሆኖ ከውጊያ ግንባር ሸሽተው የመጡትን ወታደሮች አነጋገረ :-

“አነዚያ የሚጋደሏችሁ እንደናንተው ሰዎች አይደሉምን? " ሲል ጠየቃቸው።

" አዎ ናቸው" አሉት።

"በሁሉም ግንባር ከእነሱ በእጥፍ ትበዛላችሁ ታዲያ ለምን ትሸነፋላችሁ?" አለ በብስጭት።

ከጦር አለቆቹ መሐል የተሰየመ አዛውንት ተነሳና : -

“እነሱ” አለ ንግገሩን ሲጀምር።
.... “እነሱ ለሊቱን ለጌታቸው ቆመውና ሱጁድ ተደፍተው ያነጋሉ። ቀኑን በሐሩር ይፆማሉ። ቃላቸውን ሁሌም ይሞላሉ። በመልካም የሚያዙ ከመጥፎም የሚከለከሉ ትውልዶች ናቸው። እርስ በርስ የሚተዛዘኑ የሚተባበሩ የሚረዳዱ ናቸዉ....

አኛ ግን በተቃራኒው አስካሪ መጠጥ አየጠጣን ሰዎችን የምንበድል.... ቃላችንን የምናፈርስ ነን። ሙስሊሞች እንደኛ በእኩይ ተግባር ካልተሳተፉና ከጌታቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ካልሻከረ እርስ በርሳቸው ያላቸው ውዴታና መተናነስ ተንዶ ወደ ጥላቻ ካልተለወጠ በፍፁም እነሱን ማሸነፍ አንችልም" አለ።

ሂረቅል የጦር አለቃዉን ንግግር ሰምቶ ሲያበቃ “አንተ እውነቱን ነገርከኝ" ሲል ተደመጠ።


‼️ ይሄዉ ዛሬ ዘመን ላይ የጦር አለቃዉ እንዳለዉ ሀራም ላይ ሙስሊሙ እየተሳተፈ..ሰዎችን እየበደልን የሰዉ ሀቅ
መፍራት ትተን በእኩይ ነገር በማንኛዉም ሶሻል ሚዲያ ላይ ሀያዕ አጥተን እየታየን ....ከጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት ከአንገት በላይ ስለሆነ ...በትንሹም በትልቁም እርስ በራሳችን ቁርአንና ሀዲስ እያለ ለስሜታችን የሚመቸን እንዲሆን ክርክር የኔ ትክክል ነዉ የአንተ ጥመት ነዉ እያልን ጊዜያችንን እንጨርሳለን የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች እንደፈለጉ ያሸከረክሩን ይዘዋል...በሂጃብ ጉዳይ የተናቅነዉ አንድ ተራ ሰዉ ተነስቶ ሂጃብን ከልክሎ ተማሪዎችን የሚያሰቃየዉ የኛን ልብ አይቶ እንደሆነ ሁላችንም ልናቅ ይገባል፡፡


-----------------------------
ታላቁ ዓለም አብኑ ቁተይባ ዑዩኑል አክባር በተባለ ከታባቸው ላይ ቀጣዩን ታሪክ አስፍረዋል።

ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርና ዐብዱልመሊክ ኢብኑ መርዋን እርስ በርስ መዋጋት በጀመሩበት ሰዓት የሮማዋያን መኳንንቶችና የጦር አበጋዞች ተሰባስበው ንጉሳቸው ዘንድ አመሩ። “ንጉሥ ሆይ! አሁን ሙስሊሞች እርስ በርስ መጣላት ጀምረዋል። ይህ ዕድል ሳያመልጠን እንፋለማቸው" አሉት።
.... ንጉሡ ግን "በፍፁም እንዳታደርጉት!" በማለት ግርምትን የሚያጭር መልስ ሰጣቸው።

መኳንንቶቹ በመልሱ በመደነቅ ምክኒያቱን ጠየቁ። ንጉሡም ሁለት ውሻዎችን አስመጣና እንዳያናክሳቸው አስደረገ። ውሻዎቹ እርስ በርስ እየተናከሱ ጠባቸው ሲፋፋም ንጉሡ ቀበሮ አስመጣና ወደ ውሾቹ ላከ። በዚህ ጊዜ ውሻዎቹ ጠባቸውን ትተው በመተባበር ቀበሮውን አሳደው ገደሉት። በዚህ ጊዜ ንጉሱ

“የኛና የሙስሊሞች ምሳሌ ይህ ነው! ካጠቃናቸው አንድ ሆነው ይጨርሱናል  ከተውናቸው ግን እርስ በርስ ይጨራረሳሉ" አላቸው።...ይኸው ነው ምሳሴያችን ዛሬ ዘመን ላይ በሚዲያዉ በየመስጊዱ እርስ በራሳችን በቃላት እንነካከሳለን....እነ ፉላን ግን ሂጃብ የለበሱ ሙስሊም እህቶቻንን ትምህርት አትማሩም አትፈተኑም ምን ታመጣላችሁ.... ዩኒቨርስቲ አትገቡም ተብለዉም እዉጭ ያሳድሯቸዋል የዚህ የኛ በቃላት የመነካከስ ዉጤት ነዉ፡፡


የበላይ የሆነውን እምነት እስልምናን ይዘን ፤የበታች የሆኑ ትውልዶች ሁነን እምነታችንን ከሀዲያን እንዲያስከብሩልን እንለምናለን😔

ወንድሜ! እህቴ ! ታሪኩ እርስ በርስ መናከሳችን ትርፉ
ለጠላት መሆኑን ነው የሚነግረን!

ግን መቼ ይሆን ከተኛንበት  የምንነቃዉ !!!???🤔


በቅንነት ለ10 ሰዉ ሼር ያድርጉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️ #ሰላዩ_የመስጂደል_አቅሷው_ኢማም⚡️⚡️
                 አሚር ሰይድ

ፋዲል የሁዛ ይባላል። ቅዱስ ቁርአን ከነተፍሲሩ ተምሯል። በቃሉም ሸምድዷል፡፡ የአል-አቅሳ መስጂድ ኢማም ነው፡፡

አብዛኛው ጊዜውን የሚያሳልፈው ቁርአንን በማንበብ፣ በዒባዳና፣ ስለ ኢስላም በማስተማር ነው፡፡ የከተማው ሰዎች ሁሉ ይወዱታል። ከየአቅጣጫውም በዙሪያው ተሰብስበው ያዳምጡታል። በፍልስጤም ውስጥ ለሚገኙት ሙጃሂዶች ጠንካራ ድጋፍ አድርጓል። አላህ ድልን እንዲያጎናፅፋቸውም ዘወትር አላህን ይለምናል። በመልካም ስብዕናና በኢማን ራሱን ገንብቷል።

   የፅዮናዊያን ጦርነት ግንቦት 1948 ሲጀመር በየቀኑ እኩለ ለሊት ላይ ወደ ፅዮናዊያን ካምፕ አየሄደ የሙስሊሞችን ወታደራዊ መረጃ ያቀብላል።

ለብዙ ሰዓታት ከዓይን የሚሰወረው ፋዲል በሙስሊሞች ላይ ጥርጣሬን ፈጥሯል። እኩለ ለሊት ከግብፅ የሽምቅ ተዋጊ ካምፖች ወደ ፅዮናዊው የሽምቅ ተዋጊ ካምፖች ሲገባ በተደጋጋሚ ተስተዉሏል፡፡

በፅዮናውያን እና በሙስሊሞች መካከል ድርድር ተካሂዶ ሰላም ከሰፈነ ቀናት አልፈዋል፤ የፅዮናውያን መኮንን አንገቱ ውስጥ ዘልቆ የገባውን ከባድ ጉዳት ማከም አቅቷቸው አስፈላጊውን የህክምና መሳርያዎችንና ሐኪም እንዲልኩላቸውም ሙስሊሞችን ጠየቁ።

የመስሊሞች ሐኪም ፅዮናዊውን መኮንን ለማከም የሚያስፈልገውን መድኃኒት ተሸክሞ ወደ ካምፑ ዘለቀ። ሐኪሙ ሌላ ስራም ተሰጥቶታል በጠላት ካምፕ ውስጥ መረጃን መሰብሰብ እንዳለበት ተነግሮታል።

አለመታደል ሆኖ ፋዳል በለሊት የሙስሊሞችን መረጃ ለፅዮናዊያን በማድረስ ሥራው ላይ ሳለ ነበር ከሙስለሞቹ ሀኪም ጋር ዓይን ለዓይን የተገጣጠመው። ሐኪሙም አይቶት እንዳላየ ሆነ።

ሐኪሙ ወደ ካምፕ ሲመለስ ፋዲል በፅዮናውያን ካምፕ ውስጥ እንደነበረ ለሙስሊሞች መሪ ተናገረ። ፋዲል ብልህ ሰላይ ስለነበር እንደተባነነበት ስላወቀ የሙስሊሞችን ካንፕ ለቆ ተሰወረ።

3 ሙስሊሞች ለዚህ ኦፕሬሽን ተላኩ፡፡ ለሊትን ተገን  አድርገው ገደሉት። አስከሬኑን ተሸክመው ፅዮናዊያን ሰፈር ዘልቀው በመግባት የፋዲልን አስክሬን አስቀመጡ።


ስለ እስልምና ያስተምር የነበረ፣ ቁርአንን በአግባቡና ማራኪ በሆነ አንደበቱ የሚፈስር፣ ሙስሊሞችን በአል-አቅሳ መስጂድ ኢማም ሆኖ የሚያሰግድ ሰላይ፡

   ዛሬም ከመካከላችን ስንት የካፊሮች ቅጥረኛ በየሀገሩ አለ ቁርአንን የሚያነብ ሙስሊሞችንም የሚያሰግድ... የሙስሊሞች መሪና አሊም የሚመስል መልኩን የቀየረ ፋዲል ስንት አለ።

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

ሼር ማድረግ ቅንነት ነዉ ለሌሎች ሼር በማድረግ ያካፍሉ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
>>>>>>>🎖#እንደዚህ_ሰው_አትሁን🎖<<<<<
                   አሚር ሰይድ

   ጊዜው በኸሊፋው ወሊድ ኢብኑ አብዱልመሊክ ዘመን ነው። ስፍራው ሐጅ በሚያደርጉ ሰዎች ተሞልቷል። ከፊሎቹ ሱጁድ ተደፍተው አላህን ይማፀናሉ። ሌሎች ደግሞ ጠዋፍ እያደረጉ ወደ ጌታቸው ይቃረባሉ። አንድ በደዊ ከካዕባ ፊት ለፊት ቆሞ ይታያል። ወደ ዘምዘም ጉድጓድ እየሄደ ግራና ቀኙን ያማትራል። ማንም አላስተዋለውም። ሁሉም በዒባዳው ተጠምዷል....ወደ ጌታው በመተናነስ ይዋደቃል። ይህ በደዊ ንፁሁ የዘምዘም ጉድጓድ ውስጥ ሽንቱን መሸናትና መፀዳዳት ጀመረ። ድምፁን አውጥቶ መሳደብ ያዘ።

    ሰዎች ትኩረታቸውን ወደዚህ ተሳበ። ፈጥነው ወደርሱ አመሩ። መሬት ዘርረው ይደበደቡት ጀመር። ከወታደሮች መካከል አንዱ እብድ ነህን? ሲል ጠየቀው። .....አይደለሁም ጤናማ አዕምሮ አለኝ ሲል መለሰ። ከዚህ በፊት ማንም የልደፈረውን ተግባር እንድትፈፅም ያነሳሳህ ማነው? ዳግም ተጠየቀ።
.....“ሰዎች ዘንድ በእርግማንም እንኳ ቢሆን ስሜ ይገን ዘንድ ተመኘሁ እገሌን አላህ ይርገመውና እየተባልኩ ለዘልዓለም እወሳ ዘንድ ከጀልኩ በዚህ ምክንያትም የዘምዘም ውሀ ጉርጓድ ውስጥ ተፀዳዳሁ” ሲል ተናገረ።


⚠️   #እናንተ_ሰዎች_ሆይ! በዘመናችን እንደዚህ ሰው  ታዋቂ መሆን የሚፈልግ ብዙ አለና ለሙፍሲዶች እድል አትስጡ ውሸትና ቅጥፈትን በዝምታችሁ ግደሉ። ማህበራዊ ሚዲያዎች  ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ ቲክቶክ እና የቴሌቪዥን መስኮቶች ዝናን በሚወዱ በሽተኞች ተሞልተዋልና የሰሩትን ያወሩትን ሁሉ በማራገብ ላይክ በማድረግ አታግዛቸው ምኞታቸውንም ተፈፃሚ አታድርጉ።

#ምንጭ ☞ ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ሼር በማድረግ ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🎖 #ምስጢሮችህን_ራስህ_ጋር_ማቆየት_ቻል🎖
                 አሚር ሰይድ

      ከጀርመን እስር ቤቶች በአንዱ ጠባቂዎቹ የጭካኔና የበደል ዱላቸውን ዘወትር በታሳሪዎች ላይ ያሳርፋሉ። “ሽሚት” የተባለ ረጅም የእስራት ጊዜ የተፈረደበት አንድ ሰው በፍርግርጉ ውስጥ አለ። ይህ እስረኛ በጥበቃዎች አክብሮት የተሞላበት መልካም አያያዝ ሲደረግለት ቀሪዎቹ የእስርቤቱ እስረኞች እነሱን ሊሰልል የመጣ ሰው አድርገው ይገምቱታል።
....በአንድ ወቅት በዚህ ግምታቸው ምላሽ ይሆን ዘንድ ከፖሊሶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው እየማለ ነገራቸው። ማንም አላመነውም “የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ለምን ከእኛ የተለየ እንክብካቤና አያያዝ እንደሚያደርጉልህ ማወቅ አንፈጋለን" አሉት።

ሸሚትም “እስኪ ንገሩኝ ለዘመዶቻችሁ የምትፅፉትን ሳምንታዊ ደብዳቤ ምን ብላችሁ ነው የምትጀምሩት??"

“ስለ እነዚህ የተረገሙ ጠባቂዎች የእስርና የግፍ ጭካኔያቸው በደብዳቤዎቻችን ላይ አንነግራቸዋለን" አሉት።

“እኔ ግን በየሳምንቱ ለባለቤቴ ደብዳቤ እፅፋለሁ። በመጨረሻው መስመር ላይ የእስር ቤቱንና የጠባቂዎቹን መልካም አያያዝ እጠቅሳለሁ። አንዳንዴም ስማቸውን እየዘረዘርኩ አወድሳቸዋለሁ"

"አያያዛቸው ጭካኔ የተሞላበትና ከባድ መሆኑን እያወቅክ እንዴት ታወድሳቸዋለህ?" ብለው

ጠየቁት።

“ምክንያቱም ደብዳቤዎቻችን በጥበቃዎች ሳይነበቡ ከእስር ቤት አይወጡምና በፁሁፋችን ውስጥ የሰፈረውን እያንዳንዷን ነገር ጠንቅቀው ያውቃሉ የደብዳቤያችሁን የአፃፃፍ ዘይቤ ለውጡ" በማለት መከራቸው።

በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉም እስረኞች የአፃፃፍ ስልታቸውን ቀይረው ወደ ቤተሰቦቻቸው ደብዳቤን ላኩ። ከቀናት በኋላ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች አያያዛቸው በከፋ መልኩ ተቀየረ። ሁሉንም እስረኞች ማሰቃየት ጀመሩ። አሁን ሽሚትም አልቀረለትም አብሯቸው ይደበደብ ጀመር።


ሁኔታው ግራ የገባው ሸሚት ከጥቂት ቀናት በኋላ እስረኞቹን “በደብዳቤያችሁ ላይ የፃፋችሁት ምንድን ነው? " ሲል ጠየቃቸው።

እንዲህ አሉት "የተረገሙትን ጠባቂዎች አታለን ጥሩ አያያዝ የምናገኝበት ዘዴ እንዳስተማርከን ፅፈናል" አሉት።

ሸሚት ጉንጮቹን እየደበደበና ፀጉሩን እንደ እብድ እየነጨ አቀርቅሮ ተቀመጠ።



⚠️⚠️ #እናም_ወዳጄ

    ሌሎችን መርዳት መልካም ተግባር ቢሆንም ከማን ጋር ማውራት እንዳለብህ ልታውቅ ይገባሀል። ሁሉም አድማጭ ሚስጥር ጠባቂ አይደለም። ልብህን ለሁሉም ሰው ክፍት አታድርግ። የመኖርህ ጌጥ የሆኑትን ሚስጥሮችህን ራስህ ጋር ማቆየት ካልቻልክ እመነኝ ሌሎች ሰዎች ሚስጥርህን ለመጠበቅ የሚችል ልብ አይኖራቸውም።

#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


🔰#ለሌሎች_ያጋራሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️...... #ቁርአንን_ስንኖርበት .....⚡️⚡️
                  አሚር ሰይድ

      በሀገረ አሜሪካ በሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ጫጫታ ነግሷል። ሁለት እናቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰላም ተገላግለው “ሴቷ የአንቺ ናት እኔ የወለድኩት ወንድ ነው" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ ሆስፒታሉ በጩኸታቸው ተናውጧል። ሐኪሞቹ ልጆቹ ተምታቶባቸው ግራ ተጋብተዋል። ማንኛዋ ሴት የትኛዋስ ወንድ እንደወለደች ማወቅ ተስኗቸው መፍትሄ ሊያበጁ ከመሀል ገብተዋል።

በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ ውጤት መጠባበቅ ጀመሩ። አሁንም ግራ አጋቢ ነገር ተፈጠረ። ተቀራራቢ ውጤት በመታየቱ ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆኗል በማለት ለሆስፒታሉ ሀላፊዎች አሳወቁ። ኃላፊዎቹም ረጅም ሰዓት ከተወያዩ በኋላ ይህንን ችግር መፍታት የሚችሉት ሙስሊም አሊሞች ናቸው በሚል ከመግባባት ላይ ደረሱ።

   ወደ አንድ ሙስሊም ለቃውንትም አቀኑ። የተፈጠረውን ሁሉ በዝርዝር አስረዱ። ምናልባት በሀይማኖታችሁ መፍትሄ ካለው ብለን እዚህ መጣን አሉ።

እሱም ክስተቱን አዳምጦ እንዳበቃ “መፍትሄው በጣም ቀላል ነው” አለ።
.....ዶክተሮቹ እርስ በእርስ ተያዩ ፡ ንግግሩን ቀጠለ “አላህ በልጆቻችሁ ያዛችሆል፡፡ ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው" የሚለውን የቁርአን አንቀፅ ከነትርጉሙ አነበበላቸው

"ከሁለቱም እናቶች የወተት ጠብታዎችን ውሰዱና መርምሩ። በጣም የበለፀገና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘችው የወተት ጡት ወንድ ልጅን የወለደችው እርሷ ናት” አለ።

ንግግሩን ሰምተው እንዳበቁ አመስግነው ወደ ሐኪም ቤት አመሩ። ከሁለቱም እንስቶች የወተት ናሙና ወስደው ላብራቶሪ አስገብተው መረመሩ። በመካከላቸው ያለውን ልዩነትም ተመለከቱ። ወንድና ሴት ልጅ የወለደው ማን እንደሆነ በዚህ መንገድ አወቁ።

“ (ይኽም) ከአላህ የተደነገገ ነው፤ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና” [ሱረቱ ኒሳእ]


#ቁርአንን_ስንኖርበት_ብሎም_ስንዳኝበት_እንዲህ_ነው። ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ተገባ!

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
📚📚 #የአንድ_ሺህ_ዲናሩ_ገጠመኝ
           አሚር ሰይድ

መነሻቸውን ከበስራ አድርገው መድረሻው ወዳልታወቀ ስፍራ ተቅጣጭተዋል። ሐዲስን የሚያውቅ ሰው አለ ተብለው ከምንጩ ሊቀስሙ ፈልገዋል። ጉዞው አድካሚ ነው። መንገዱም ሲበዛ የረዘመ። በረሀውን አቋርጠው ሲጨርሱ ገደል ገደሉን ሲያልፉ ጋራ ይጠብቃቸዋል። ዕድሜ ያቸው የገፋ አንድ አዛውንት አብረው በፍጥነት ይራመዳሉ። በዕውቀት የመጠቁ ዓሊም ናቸው። ኢማሙል ቡኻሪ ይሰኛሉ። ከእልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ ከተማውን ለቀው በመውጣት በጀልባ ተሳፍረው ባህሩን ያቋርጡት ይዘዋል። አንድ ሺህ ዲናር በከረጢታቸው ቋጥረው ከቦርሳቸው አኑረዋል። ከጎናቸው ለተቀመጠው ሰው ስለያዙት ገንዘብ ነግረውታል።

   ገንዘብ የመያዛቸውን ወሬ የሰማው ሰው ቀይሉላ ሰዓት ወገቡን ከመጋደሚያው አሳርፎ ከእንቅልፉ እንደነቃ ስቅስቅ ብሎ አያለቀሰ እሪታውንና ኡኡታውን ያሰማ ጀመር። ልብሱን እየቀዳደደ ፊቱን እየቧጨረ ጭንቅላቱን እየመታ መሬት ላይ ይንከባለል ጀመር። ሰዎች ሁኔታውን ሲያዩ ግራ ተጋብተው ምን እንደሆነ ጠየቁት።

አንድ ሺህ ዲናር ከነቦርሳዬ ጠፋ አላቸው። ለካስ የኢማሙን ብር ከጀሎ ኖሯል።

.....በመርከቡ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች አንድ በአንድ እየተፈተሹ ገንዘቡን ያፈላልጉት ጀመር። ኢማም አል-ቡኻሪ በከረጢቱ ያስቀመጡትን ገንዘባቸውን አውጥተው ሰው ሳያያቸው ወደ ባህሩ ወረወሩት። መርከቡ ላይ የተሳፈሩት ፈልገው አፈላልገው አንድ ሺህ ዲርሀሙን ሲያጡ ተወሰደብኝ ብሎ የሚጮኸውን ሰው ወቅሰውና ሰድበው ከአጠገባቸው አገለሉት።

ከመርከቡ እንደወረዱ ሽማግሌው ሰው ወደ አማም አል-ቡኻሪ ተጠጋና ከበስራ ይዘውት የመጡትን አንድ ሺህ ዲናር የት አንዳደረጉት ጠየቃቸው።

“ወደ ባህር ወረወርኩት” አሉት።

"ይህን ታላቅ ገንዘብ በከንቱ ሲጠፋ ማየት አንዴት አስቻለህ?" አላቸው።

ኢማሙም እንዲህ አሉ "የአላህ መልአክተኛ ﷺ
ሐዲስ በመሰብሰብ ዕድሜዬን ሙሉ እንደፈጀሁ ታውቃለህ። ዓለምም ታማኙ የሐዲስ ሰው እያለ ይጠራኛል። ታዲያ በገዛ ሀቄም ቢሆን በስርቆት ተወንጅዬ አማናዬን አጥቼ የደከምኩበት የረሱል ﷺ ሀዲስ ተቀባይነት እንዳይኖረው ላደርግ አይገባም። በሕይወቴ ያገኘሁትን ውድ ዕንቁ ታማኝነትንና ፍትሀዊነትን ለጥቂት ዲርሃም ብዬ አንዴት አጠፋዋለሁ? "
ብለዉ መለሱለት

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
#በስነምግባር_ባልሽን_አክሚ
አሚር ሰይድ

85 ዓመቱ ሸይኽ ዐብደላህ በሳተላይት ቻናል ላይ የፈትዋ ፕሮግራም እየሰጡ አንዲት ትውልደ አልጄሪያዊት ሴት ደወለችና እንዲህ አለች፦

"ሙስሊም ነኝ ለጌታዬ ታዛዥ። ትውልዴም በሀገረ አልጄሪያ ነው። የአላህን ትዕዛዝ የባሌን ሐቅ እየተወጣሁ ለብዙ በደሎቹ ትዕግስትን ተላብሼ እኖራለሁ። ባሌ ዘወትር መጠጥ ሲጠጣ አምሽቶ እየተንገዳገደ ወደቤት ይገባል። ትላንት በዛ ሁኔታ ላይ ሆኖ ሲመጣ ቁርአን እየቀራሁ ነበር። እየተሳደበ ከእጄ ላይ ነጠቀኝና ሽንት ቤት ወረወረው። በንዴት ተቃጠልኩ ድንበር ማለፉ ከኔ አልፎ በክቡር የአላህ ቃል ቁርአን ላይም ደረሰ። እኔም ከዚህ በላይ መታገስ ከበደኝ ፍች መጠየቅ እችላለሁን?"

በማለት ጥያቄዋን ሰነዘረች።

“ስንት ልጆች አሉሽ” ሲሉ ጠየቋት

“አምስት ወንዶች ልጆች አሉኝ ገና ልጆች ናቸው" አለች።

ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ። ጥንቃቄን የተሞሉ ቃላቶች ከአፋቸው እየሰነዘሩ ንግግራቸውን ቀጠሉ“ፍቺ አትጠይቂ ስሞታም ሳታቀርቢ ታግሰሽ ኑሪ የሚመጣብሽን ችግር ተቋቁመሽ በስነምግባርሽ ባልሽን አክሚ

በመሀል ጣልቃ ገብታ ንግግራቸውን አቋረጠች “ግን እንዴት ከዚህ በላይ መታገስ ይቻለኛል??" እያለች ተንሰቅስቃ አነባች።

"ልጆችሽ የእሱን ባህሪ ከሚላበሱ በጀሀነም እሳት ከሚማገዱ ታግሰሽ እሱን መመለስ አይሻልምን?!

ደሞስ በወንጀል ላይ ላለው ባለቤትሽ ችግሩን የሚረዳ ካንቺ በላይ ማን አለው?! ካንቺ በቀር ይህን ተግባሩን ታግሶና ወንጀሉን ደብቆ ከሰጠመበት ማዕበል ሊያወጣው የሚጥር ማንም የለም። ብትፈቸው እየሰከሩ ቁርአንን  ሽንት ቤት የሚጥሉ ልጆችን ያፈራልና እባክሽ ታገሺ እዘኚለት ፍቺ ጠይቀሽ ማምለጥ መፍትሄ አይደለም። ነገ ለልጆችሽ ድልድይ መሆኑን አውቀሽ ለሊት ተነስተሽ አምርረሽ ዱዓ አድርጊለት አሏት


ቀናቶች ወራቶችን ወልደው ድፍን አንድ ዓመት ተቆጠሩ። ሸይኹ በሕንድ የሳተላይት ጣቢያ ላይ ተጥደው ፈትዋ እየሰጡ ስልኩ አቃጨለ።

"አሰላሙ ዓለይኩም ያ ሸይኽ አልኮል እየጠጣ ቁርአንን ስለሚቀዳድደው ባሌ ከአንድ ዓመት በፊት የደወልኩህ አልጀሪያዊቷ ሴት ነኝ"

“ወላሂ አስታወስኩሽ ልጄ እንዴት ነሽ?? የባልሽስ ሁኔታ ምን ላይ ነው? "ብለዉ ጠየቋት

"በአላህ ይሁንብኝ መስጂድ ቀድሞ ገብቶ አዛን የሚል፣ ሶለተ ተሀጁድ ቆሞ የሚያነጋ፣ ቁርአንንም በአግባቡ የሚቀራ ሰው ሆናል። ግዴታ የተደረጉበትን ሶላቶች ከነሱናቸው የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆናል። እኔ እንድፀና እርስዎን ሰበብ አርጎ አላህ እሱን ወደ ቀጥተኛ መንገድ መራው” አለችና የደስታ እንባ ከዓይኗ እየዘረገፈች ተንሰቀሰቀች። ለጌታዋ የቀረበች አማኝ ሴት በመሆኗ ንፅህናዋንና የልቧን ቅንነት አይቶ በዱዓዋ መልስ ሰጣት።

#አንድ ሰው ከወንጀል አዘቅጥ ይወጣ ዘንድ ትዕግስትን ከዕዝነት ጋር ተላብሳችሁ በጥበብ አስተምሩ!

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
       #የምላስ_ወለምታ

ሶስት ሰዎች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ውሳኔው ተግባራዊ ሊሆን ህዝብ በተሰበሰበበት ሜዳ ከፍ ካለው ቦታ ላይ ተደረደሩ። አሊም፣ የህግ ጠበቃና የፊዚክስ ሊቅ ናቸው።
     ገመዱ ተዘጋጅቶ አሊሙን ወደ ፊት አስጠጉት። አንገቱን ከገመዱ በታቸ አጠለቁት። ለመናገር ለምትፈልገው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ።


አላህ አላህ....የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ነው" ሲል ተናገረ። ገመዱ አንገቱ ላይ እንደጠበቀ አልሸመቀቅ አለ። ሕዝቡ ተገረመ። የአላህን ስም ጠርቷልና ገመዱን ፍቱለት ተብሎ ተለቀቀ። ነፍሱንም በአላህ ስም ታደገ። ‎

የሕግ ባለሙያው ተራ ደረሰ። አንገቱ ላይ ገመድ ጠለቀ። ለእርሱም የምትናገረው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ። እንዲህም አለ አንደ ኡስታዙ ከአላህ ጋር አልተዋወቅም ግን ፍትሕ እንደሚያድነኝ በሚገባ አውቃለሁ። ፍትሕ ፍትሕ ሲል ጮኸ። ገመዱ በአንገቱ ውስጥ እንደጠለቀ አልሸመቀቅ አለ። ጠበቃውን ፍቱት ስሰ ፍትሕ ተሟግቷልና መሰቀያ ገመዱ እንኳ ነፍሱን ለመንጠቅ አልደፈረችም ተባለ። ጠበቃውም በፍትሕ ስም ነፍሱን አዳነ።

የፊዚክስ ሊቁ ተራ ደረሰ። እርሱም ተጠየቀ መናገር የምትፈልገው የመጨረሻ ቃል አለን? ተባለ።

"እኔ አላህን አንደ ኡስታዙ አላውቀውም። እንደ ጠበቃውም ስለ ፍትሕ አልለፈልፍም። ግን መስቀያ ገመዱ እስካሁን አንገታቸው ላይ ጠልቆ ያልተሸመቀቀው አናቱ ላይ ያለዉ ቋጠሮ ስለጠበቀ ነው" አለ። ገመዱን ሲመለከቱት በትክክል ቋጠሮው በመጥበቁ ምክንያት ነው ያልተሸመቀቀው። ቋጠሮውን አስተካክለው የፊዚክስ ሊቁ አንገት ላይ ገመዱን ሸምቅቀው ገደሉት።

   አንዳንዴ እውነታውን እንኳ እያወቅከ ምላስህን መያዝ ይኖርብሀል። ሞኝ መሆን ብልጠት የሚሆንባቸው በርካታ ቦታዎች አሉና አፍህን በመዳፍህ ላይ አድርገህ ዝም በል።


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
❤️ #ሱሀቦች_ለነብዩ_ﷺ_የነበራቸዉ_ፍቅር
            አሚር ሰይድ


በሀቢቡና ሙሀመድ  ﷺ ጊዜ በተፏፏመዉ በኡሁድ ዉጊያ ጊዜ ነብዩ ﷺ ተገድለዋል የሚል የዉሸት ዜና መዲናን እየናጣት ነበር ..የመዲና ሰማይ በዚህ አሳዛኝ ወሬ በሀዘን አጥልሏል..መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ኡሁድ አቅጣጫ እየተመመ ነዉ

    ከአንሶሮች መካከል የሆነችዉ ሱመይራ(ረ.ዐ) ሁለት ልጆቿ አባቷ ባለቤቷና ወንድሟ ሰማዕት መሆናቸዉን ተረዳች ..ሱመይራ እነዚህ ሁሉ ወገኖቿ ቢሞቱባትም በዚህ ሁሉ የሀዘን ዉርጅብኝ አልተናወጠችም ..እልቁንስ እሷን ያስጨነቃት በእዉነት የታወቀዉ የጓጓችለት አንድ ዜና አለ ይህም የነብዩ ﷺ በሒወት መኖር ነዉ
..በእርሳቸዉ ላይ የደረሰ አንዳች ክፉ ነገር አለ??በማለት ጠየቀች
...የነብዩ ባልደረባዎችም ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እርሳቸዉ በሒወት ይገኛሉ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ አሏት
ሱመይራ እንዲህ አለች ፡-እሳቸዉን እስከማይ ድረስ እረፍት አላገኝም የአላህ መልዕክተኛን ﷺአሳዩኝ አለች
....እሳቸዉን እንዳሳዩዋትም በቀጥታ ወደ እርሳቸዉ በመሄድ የካባቸዉን ጫፍ ከያዘቼ ቡሀላ እንዲህ አለች
"""""እናቴና አባቴ መስዋት ይሁንለልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እርስዎ በሂወት እስካሉ ድረስ የቤተሰቦቼም ሞት ቀላል ነዉ ...አለቻቸዉ

.ያ በነብዩ ዙሪያ የነበሩ የተባረከ ትዉልድ ለእርሳቸዉ ይህን የመሰለ ድካ የሌለዉ ፍቅር ይለግሳቸዉ ነበር ...ሱመይራ አባቷ ልጇ ባለቤቷ ወንድሟ ሙተዉ እሷ ያሳሰባት ነብዩ ﷺ💚 በህይወት እንዲተርፉላት ነበር....

⚠️...እኛስ ነብዩን መዉደዳችንን የምንገልፀዉ በነሺዳ የተቀናበረ የራሳችንን ፎቶ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመልቀቅ ነዉ እንዴ??
እስልምና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል ...ነብዩን መዉደድ ነሺዳ በማዳመጥ የሚመስስላቸዉ ብዙ ሚስኪን ሙስሊሞች ሞልተዋልና ሙተን አላህ ፊት ስንቀርብ ከነሱመይራ ረዐ ጎን ሁነን ስንጠየቅ የሰራነዉን ኸይር ስራ ፈትሸነዋልን???

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#የጀሀነም_ቅጣትን_ሲያስታዉስ_የሞተዉ_ወጣት
               አሚር ሰይድ

መንሱር ኢብን አማር እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “አንድ ሌሊት የነጋ መስሎኝ ከቤቴ ወጥቼ ስሄድ ንጋቱ አለመቀረቡን ተገነዘብኩ፡፡ ከዚያም በአንድ ሰው ቤት አጠገብ ሳልፍ አንድ ወጣት ምርር ብሎ እያለቀሰ ጌታውን እንዲህ በማለት ሲማፀን ሰማሁት፡-

    ጌታዬ ሆይ! እኔ ብዙ ሀጢያቶችን ፈፅሜያለሁ፡፡ በዚህም ድርጊቴ ራሴን መቀመቅ አውርጃለሁ። ዓላማዬ ያንተን ትዕዛዝ መጣስ አልነበረም። ሆኖም ግን ነፍሴ አሸነፈችኝ፡፡ ምንም እንኳን እኔ እራሴን ብበድልና መጥፎ ድርጊቶችን ብፈፅምም አንተ ግን ለዚህ ድርጊቱ የወሰድክብኝ ብቀላ የለም፡፡ በዚህ ቻይነትህና ይቅር ባይነትህም ተዘናግቼ ተወሰድኩ። ሀጢያቶቼንም የሠራኋቸው ባለማወቅ ነው፡፡ አሁን ግን መሳሳቴን ተገነዘብኩ። የምትቀጣኝ ከሆነ ምን ይውጠኛል? ወዮልኝ ለራሴ! ጌታዬ ሆይ! ባሮችህን ሁሉ በሲራጥ ድልድይ ላይ እንዲያልፉ በምታደርግበት ቀን የተወሰኑት ወድቀው ጀሀነም ሲገቡ የቀሩት ደግሞ ጀነት ይገባሉ፡፡ እኔ የአንተ ባሪያህ ከየትኛው ወገን ይሆን የምሆነው?' ይህን ካለ በኋላ ስለ ጀሀነም የሚናገር የቁርአን አንቀፅ ሲያነብ ሰማሁት፡፡ ከዚያም ረዥም ትንፋሽ ሲያወጣ ከሰማሁት በኋላ ፀጥታ ሰፈነ። ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓሁ፡፡ ለራሴም:- 'ይህ ወጣት ያለበትን ቤት በሚገባ እስካላየሁት ድረስ የተፈጠረውን ነገር ሲነጋ መስማቴ አይቀርም:: አሁን ወደ ቤቴ ልግባ' በማለት ወደዚያው አመራሁ፡፡


ነግቶ ወደዚያ ስፍራ ስሄድ ከቤቱ በር ላይ የሰው አስከሬን ተመለከትኩ፡፡ ምን እንደተፈጠረ ስጠይቅም እናቱ እንዲህ አለችኝ፡-

የሞተው የእኔ ልጅ ነው፡፡ ከነብዩ ﷺ ጋር የሚያያዝ የዘር ሀረግ አለው፡፡ ጨለማው ያዝ ካደረገ ጀምሮ እስኪነጋ ድረስ ሲሰግድና ሲያለቅስ ያነጋል፡፡ ያለውን ነገር ደግሞ ቀኑን ሙሉ ለድሆች ሲመፀውት ይውላል፡፡ ስለ ጀሀነም የሚናገር የቁርዓን አንቀፅ ከሰማ ፈፅሞ መቋቋም ስለማይችል ያለቅሳል፡፡ በዚህ ዓይነት ሲያለቅስ ሌሊት ላይ ወድቆ ሞተ፡፡አለችኝ
.... እኔም እንዲህ አልኳ ት፡-
እንቺ የተከበርሽ ሴት ሆይ! ልጅሽ በቀጥታ ያመራው ወደ ጀነት ነው ምክንያቱም አላህን ፈርቶ ይህን ያክል የሚያነባ ሰው ጀሀነብ ሊገባ አይችልም: በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነፍሱን ስቶ የሞተ ሰው እንዴት ጀሀነም ይገባል? አላህን አመስግኚው።'አልኳት

አሏህ ጀሀነምን ፈርተዉ ከሚያለቅሱ ..ጀነትን ከሚለምኑ አቢድ ዛሂድ ያረገን ዘንድ አላህን እንማፀነዋለን....


join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
2025/06/19 06:09:23
Back to Top
HTML Embed Code: