Telegram Web
እኔም ስልጤ ነኝ
~
ከሆነ ጊዜ ወዲህ እየተለመደ የመጣ 'ትሬንድ' አለ። በሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ግፎችን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቃወሙ ሙስሊሞችን ሁሉ "ስልጤ" እያሉ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ማጨቅ። ሙስሊም ብዙሃን በሆነበት ወሎ፣ በሃሰት የመቻቻል ተምሳሌት ተደርጎ በሚዘመርበት ወሎ፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በግፍ የተፈጁበት አዋጅ በተነገረበት ወሎ ቦሩ ሜዳ፣ በዚህ አገር እንደ ቆዳ በተወጠረችበት ከባድ ጊዜ ሙስሊሞችን ነጥሎ ትንኮሳ ሲፈፀም "ለምን?" ያላሉ አካላት የሚቃወሙ ሙስሊሞችን በብሄር እየለዩ አፍ ሊያሲዙ ሲሞክሩ እያየን ነው። እነሱ የግፍ ተባባሪ ሲሆኑ ያላፈሩትን እኛ ልናፍር አይገባም። የመብት ጥያቄያችንን አቅጣጫና ቅርፅ የሚወስንልን የሌላ እምነት ተከታይ አይደለም። "አያገባችሁም" ልንላቸው ይገባል። አስረግጬ የምነግርህ በቋንቋ ከምትመስለኝ አንተ በእምነት የሚመስለኝ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ... የበለጠ ይቀርበኛል። እምነት ከዘርም ከቋንቋም በላይ ነው።

ስለዚህ የክልሌ ጉዳይ ያላግባብ ይለጠጥብኛል፣ ነገር ይገንብኛል የሚል ካለ ከሚፈጽመው ግፍ እጁን ይሰብስብ። በእጅ አዙር የበዳዮች ደጋፊም አይሁን። ቤቱን ያጥራ። ቀጥተኛ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በተደጋጋሚ ሴረኛ አካሄድ እየሄደ ያለው የደሴ አስተዳደር ስርአት ይያዝ። በየዋህነት የምታወዳድሱት አካላትም ይበቃችኋል። ስንት ዘመን ነው የምትሸወዱት? አካፋን አካፋ ዶማን ዶ .ማ ማለት ያስፈልጋል።

በተረፈ "እንትና ጋ ችግር ሲኖር ለምን ዝም አልክ?" የሚለውን የከፋፍለህ ብላ ሴራንም ልንነቃበት ይገባል። መገፋት መበደላችን እንዲቆም ድምፅ አይሆኑም። ሌላ አካል ድምፅ ሲሆን ደግሞ የሴራ ፖለቲካ እየተነተኑ ከወንድሞቻችን ሊያቆራርጡን ይባዝናሉ። ጩኸታቸው ከመቆርቆር የመነጨ ቢሆን ኖሮ ህመማችን አሟቸው እስከጥግ ከጎናችን ይሆኑ ነበር። በንዲህ አይነት ቅቤ አንጓች ከፋፋዮች እስከ መቼ እንሸወዳለን?

አንድ የአክሱም ሙስሊም የአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ መሀል አገር እንዳለ ሰው ጠንከር አድርጎ ለማውገዝ ስጋት ሊኖርበት፣ ድፍረት ሊያጥረው ይችላል። ቢፈራም ተጨባጭ ምክንያት አለው። ኦሮሚያ ላይ የተፈጸመን ግፍ ሲያወግዝ "የአክሱም ጊዜ የት ነበርክ?" አይባልም። ሌላ አካል ቢል አይደንቅም። ከሙስሊም ግን ይሄ አይጠበቅም። ኦሮሚያ ላይ የተፈጸመን ግፍ ለማውገዝ ነፃ የሆነ የጎንደር ሙስሊም ጎንደር ላይ የሚፈጸመውን ለማውገዝ ግን ህይወት ሊያስከፍለው ይችላል። ስለዚህ "የኦሮሚያ ላይ ሲሆን ነው የምታወግዘው? የጎንደሩ ጊዜ የት ነበርክ?" አይባልም። አማራ ክልል ውስጥ የሚፈፀምን በደል ጠንከር አድርጎ ያወገዘ ሰው ኦሮሚያ ላይ ስላለው ለደህንነቱ ሰግቶ ለስለስ ቢል ሌላው እሱን ከመክሰስ ይልቅ የራሱን ስራ ይስራ። ሌሎችም ጋር እንደዚሁ ነው። የትም ቦታ ያለ ወገናችን ለህይወቱ ሰግቶ ዝም ሲል ከጎኑ መቆም፣ ቀዳዳውን መሸፈን እንጂ ለጅብ አሳልፈን ልንሰጠው አይገባም። ሃይማኖቱን የሚያስቀድም ሙስሊም ብልጥ ሊሆን ይገባል። አገሪቱ በብዛት ሙስሊሙን በመግፋት የታወቀች ናት። ሌሎች በዘርና በቋንቋ እየከፋፈሉ ድምፃችንን ሊያፍኑ ሲሞክሩ በሞኝነት በዘር ወጥመዳቸው ልንጠለፍላቸው አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
📚السلام عليكم ورحمة الله وبركاته📚

📲ዘሐጉስ ዜና ንደልይቲ ፍልጠት📲
https://www.tgoop.com/Alikhlasderstat
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
☑️ኣብዚ ቻናል ብትግርኛ ተቐሪኦም ዝተወድኡ ናይ ዝተፈላለዩ ኪታብ ደርስታት ቅዳሕ ድምፂ ምስ Pdfን ሙሓደራታትን  ይርከብ።
☑️ንኹሉ ማሕበረ ሰብ ሙስሊም ክባፃሕ ሼር  ብምግባር ንተሓባበር።

☑️መዳለዊ👇👇👇
https://www.tgoop.com/alikhlasislamiccenter

«ቅድሚ ዘረባን ተግባርን ፍልጠት ይቅድም»

جزاكم الله خيرا
https://www.tgoop.com/Alikhlasderstat
https://www.tgoop.com/Alikhlasderstat
https://www.tgoop.com/Alikhlasderstat

ተቀሪኦም ዝተወድኡ ደርስታት ማውጫ

📚ዓቂዳ
1,ኡሱሉ ሰላሳ
2,ሓጀቱል ኡማ ሊመንሃጁ ሰለፊ
3,ሚን ኡሱሊ ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ
4,ኩሉ ቢድዐቲን ደላላ
5,ሸርሑ ሱና ሊል ኢማም ኣል-በርበሃሪ
6,ከሽፉ ሹቡሃት
7,ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ
8,ፈድሉል ኢስላም
9,ነዋቂዱል ኢስላም
10,ቀዋዒዱል ኣረበዓ
11,ተዕሊሙ ሲብያኑ ተዉሒድ
12,ኡሱሉ ሲታ
13,ኣልሙዕተቀዱ ሰሒሕ
14,ኡሱሉ ሱና
15,ሃዚሂ ዳዕወቱና ወዓቂደቱና
16,ኣል-ዋጂባቱ ሙተሓቲማት
17,ማሂየ ሰለፍያ
18,ዓቂደቱል ዋሲጢያ
19,መሳኢሉ ጃሂልያ
20,ፈትሑ ረቢል በርያ
21,ኪታቡ ተውሒድ ናይ ሸኽ ፈውዛን
22,ሙኽተሰር ፊኡሱሊል ዓቃኢድ
23,ዓቂደቱ ኣህሊ ሱነቲ ወል-ጀማዓ ብሸኽ ሙሓመድ መኪን
24,ኡሱሉ ሱና ሊል ሑመይዲ
25,ኣልከሊማቱ ሒሳን ፊ በያኒ ዑሉዊ ራሕማን
26,ዓቂደቱ ጠሓዊያ
27,ዓቂደቱል ዋሲጥያ ብሸኽ ሙሓመድ መኪን

📚ሓዲስ
1,ዒሽሩን ሓዲስ
2,ኣረበዒኑ ነወውያ
3,ሙኽተሰር ቡኻሪ

📚ፊቕህ
1,ኣሕካሙል ሓይዲ ወኒፋሳ
2,ሹሩጡ ሰላት ወኣርካኒሃ ወዋጂባቲሃ
3,ሙኽተሰሩ ሲያም ሚን ፊቅሂል ሙየሰር
4,ኣኽጣኡ ለዚ የቀዑ ፊ ባዕዲ ሳኢሚነ ወሳኢማት
5,መትኑ ቓየቱ ወተቅሪብ (ኣቢ ሱጃዕ)
6,መትኑ ቓየቱ ወተቅሪብ (ኣቢ ሱጃዕ) ብሸኽ ሙሓመድ መኪን
7,ዱሩሱል ሙሂማ

📚ኣዳብ
1,ሲፈቱ ዘዉጀቱ ሳሊሓ
2,ተጥሪዙል ወሳኢሉል ሙፊዳ ሊልሓያቲ ሰዒዳ

📚ኡሱሉል ፊቅህ
1,መትኑ ወረቃት
2,ኣል ኡሱል ሚን ዒልሚል ኡሱል

📚ተጅዊድ
1,ተይሲር ፊ ኣሕካሚ ተጅዊድ

➷➴➷ ናይ ቴሌግራም ቻናል:-
https://www.tgoop.com/Alikhlasderstat
በ ቅርብ ቀን  ገበያ ላይ የሚውል አዲስ ኪታብ

የ ኡስታዝ  ኸድር አዲሱ ኪታብ የ ኪታቡ ከቨር  ይህንን ይመስላል

በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)

https://www.tgoop.com/UstazKedirAhmed/8749
https://www.tgoop.com/UstazKedirAhmed/8749
ወንድማችን ሙርሰል ሰዒድ ከእገታው ተለቋል። አልሐምዱ ሊላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ሶላት የዲን ምሰሶ፣ ሁለተኛዋ የኢስላም ማእዘን ነች። ሶላት የዱንያ የኣኺራ ኑር ነች። ሶላት በዱንያ የአይን ማረፊያ፣ በኣኺራ ከመከራ መትረፊያ ነች።
ከዚች ውድ ዒባዳ ከሶላት አንፃር ራሳችንን ብቻ ሳይሆን ልጆቻችንን መከታተል ይገባል። ልጆችን በሶላት ጉዳይ ፈፅሞ ችላ ማለት አይገባም። እንደ እድሜያቸው በሶላት ማዘዝ፣ መቆጣት፣ መቅጣት ያስፈልጋል። ካደጉበት፣ ከኖሩበት ይቀላቸዋል። ካልሆነ ግን ውጤቱ ተቃራኒው ነው የሚሆነው። ይሄ ከመሆኑ በፊት በጊዜ መከታተልና ማስለመድ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
በባህር እየሄደ ለሚያልቀው ወገናችን በተዘዋዋሪም ቢሆን ለሞቱና ለስቃዩ የብዙ አካላት እጅ አለበት።
1- በሃገሩ ሰላም የለም። በስሙ የሚምለው ሁሉ ለጦርነት ነው የሚያጨው። የትናንቱ እልቂት አልበቃ ብሎ የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙ ከዚህም ከዚያም ዛሬም እያየን ነው። ጥቂቶች ሊነግሱ የድሃ ልጅ ማገዶ ይሆናል። ወጣቱ ሞትን ሸሽቶ ሞት ላይ ይወድቃል።

2- በዛሬዋ ኢትዮጵያ በሃገር በቀየ ሰርቶ መለወጥ ቀርቶ የእለት ጉርስ እንኳ መሸፈን የማይወጡት ፈተና እየሆነ ከእለት ወደ እለት እየከፋ ነው። የሰላም መጥፋት፣ ለስራ የማይመች የማያፈናፍን ቢሮክራሲ፣ እዝነት ርህራሄ የሌለው የግብር ሲስተም፣ ማለቂያ የሌለው መዋጮ፣ እሳት የሆነ የኑሮ ውድነት፣ ... ተደማምሮ የወጣቱን በሃገር በቀየው ሰርቶ የመለወጥ ተስፋ አሞሽሾታል።

3- ህገ ወጥ የሚባሉት ጉዞዎች በቀይ ባህር በኩል ወደ የመን - ሳዑዲ፣ በኬንያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ በረሃ በኩል ሜዲትራኒያን ባህር አቋርጦ ወደ ይሮፕ፣ ሁሉም አሰቃቂና ህይወት የሚያስከፍሉ ናቸው። ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ይህንን አስፈሪ አማራጭ የሚወስዱት ወገኖች ስቃይን መርጠው፣ ጀብደኝነት አምሯቸው አይደለም። ህጋዊ የሚባለው መንገድ ''ሽፍታ" ያደፈጠበት ሆኖባቸው እንጂ። ዛሬ የቀበሌ መታወቂያ ለማግኘት ጣጣው ብዙ ነው። በየመንገዱ፣ በየ ቢሮው የምትጠየቀውን መታወቂያ ከምትኖርበት ቀበሌ ለማግኘት ብዙ ደጅ መጥናት ይኖርብሃል። ያውም ከተሳካ። የልደት ካርድ ማውጣትም እንዲሁ ሌላኛው ጣጣ ነው። ፓስፖርትማ ከክፍያው መናር በላይ በየ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤቶች በር ላይ ያለውን ትርምስ ያየ የእውነት ያሳቅቃል። የዜጎችን ኪስ እየበዘበዘ ለወራት፣ አለፍ ሲልም ለአመታት ዜጎችን የሚያንገላታ የማይሻሻል መስሪያ ቤት ማለት ኢሚግሬሽን ቢሮ ነው።
የፓስፖርቱ ጣጣ አልቆ በኤጀንሲዎች በኩል ለመሄድ ደግሞ ሁሉ ሰው የመውጣት እድል አያገኝም። በዚህ የተነሳ አንዳንዱ በራሱ ተፃፅፎ፣ በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ የአየር ትኬት ቆርጦ ለመውጣት ሲሞክር ኤርፖርት ላይ የሚያጋጥሙ ጣጣዎች አሉ። እዚያም ሌላ መሰናክል። እዚያም ሌላ እጅ መንሻ። የቆረጡትን ትኬት ጥለው እንደገና ወደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ ሄደው ከዚያ ሌላ ትኬት ቆርጠው የሚወጡ አሉ።
ህጋዊ የሚባሉት አማራጮች ድህነት ለፈተነው የድሃ ልጅ ኪስ የማይሞከሩ ከሆኑ፣ ህጋዊ የሚባሉት አማራጮች "ህጋዊ" ሌቦች እና ህግን የተደገፉ መሰናክሎች ከበዛባቸው አስኮብላዮችን ማሳደድ እና ህገ ወጥ ደለላዎች እያሉ ማራገብ እንዲሁ በቀዳዳ በርሜል ውሃ መቅዳት ነው የሚሆነው። ይሄ በቀይ ባህር እና በሜድትራኒያን ባህር የውሃ ሲሳይ የሚሆነው፣ ይሄ በሊቢያ በረሃ አሳሩን የሚበላው፣ ይሄ በኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ... በሽፍን መኪና ውስጥ አየር አጥሮት የሚያልቀው፣ ... ይሄ የጅቡቲው መስመር ሲወሳሰብበት በሶማሊያ ቦሳሶ ድረስ ሄዶ የሚባዝነው የስቃይና እንግልት ሱስ ስላለበት አየደለም። ሰርቶ መለወጥ ፈተና ቢሆንበት፣ መንገዱ ሁሉ ቢዘጋጋበት፣ አማራጩ ሁሉ ቢጨልምበት እንጂ። የእውነት የሃገራችን ወጣት ሁኔታ ከልብ የሚያሳዝን ነው። ነገሩ "እባካችሁ በባህር አትሂዱ" እንደማለት ቀላል አይደለም። ብቻ አላህ ፈረጃውን ያምጣልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ለማን ነው የምትሞተው?
~
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎም አሁንም ትግል ትግል የሚሉ አሉ፣ ከግንድ ያታግላቸውና። ወጣት ሆይ! ይሄንን በህዝብ፣ በብሄር ስም እየማለ ወደ ጦርነት የሚጠራህን፣ ለእልቂት የሚጋብዝህን የደም ነጋዴ አትስማ። ለእናትህ ኑር። እናትህ አንተን አጥታ የምትሆነውን መሆን በአይነ ህሊናህ ተመልከታት። አታሳዝንም ወይ? ለራስህ ኑር። ለቤተሰብህ ኑር። ለማን ነው የምትሞተው? ያገራችን ፖለቲከኛ ተቆርቋሪ መስሎ እየሰበከ ህዝብን ከህዝብ እያጋጨ ለራሱ ስልጣንና ጥቅም አንተን ቤዛ የሚያደርግ መ ~ ሰ ~ ሪ ፍጡር ነው። ካንተ በፊት ካለቁት ትምህርት ውሰድ። ዛሬ ማን የሚያስታውሳቸው አለ? ቤተሰቦቻቸውን ማን ዞሮ ያያቸዋል? ከጦርነቱ መጨረሻ ላይ ሲማግድህ የነበረው አካል የስልጣን ወንበር ላይ ሲቀመጥ አንተ ምናልባት ከተረፍክ የሆነ መያድ ጋር ተነጋግሮ ዊልቸር እና ክራንች ነው የሚስሰጥህ። ለኣኺራህ አትፀድቅ፣ ለዱንያህ አያልፍልህ። ለማን ነው የምትሞተው ታዲያ?
ይልቅ ዞር ዞር ብለህ ሰርተህ ለመልለወጥ ጣር። ኑሮህን አሸንፍ። ራስህን ቻል። ቤተሰብህን አግዝ። ለራስህ፣ ለቤተሰብህ ስትል እወቅበት። ለገዛ ወገኑ የሞት ድግስ እየደገሰ የሚጋብዝ የማንም ጣ.ሳ ራ ስ መጫወቻ አትሁን። በቃ በለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ትዝታ!
~
አንድ ቤተሰቤ ነው፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ስለሺርክና ተውሒድ፣ ህዝባችን ስላለበት ሁኔታ እያወራን ሳለን የራሱን የኋላ ታሪክ ያወራኝን አስታወስኩና የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት የሚገልፅ ስለመሰለኝ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ከገጠር ተነስቶ ወደ ጂቡቲ ሊሄድ ይነሳል፡፡ “መንገዱ ይቀናኛል ወይ?” የሚለውን ለማወቅ ጠንቋይ ዘንድ ሄድኩኝ አለ፡፡ ጠንቋዩ ጥንቆላውን ከነገረኝ በኋላ የተለመደውን የተወሰኑ ብሮች ሰጠሁት፡፡ የማይረሳኝ ግን ስግብግብነቱ ነው፡፡ የሰጠሁት ብር ሳይበቃው ትከሻዬ ላይ ጣል ያደረግኩትን አዲስ ሽርጥ ጠየቀኝ፡፡ ሰጠሁት፡፡ መንገዱ ቀኝ እንደሆነ እያባሸረ ነገረኝ፡፡ ጂቡቲ ስደርስም ወር ባልሞላ ጊዜ ስራ እንደማገኝ አበሰረኝ፡፡ ተስፋ በተስፋ!

እንዲያውም በጊዜው በዋናው የጂቡቲ መንገድ ላይ ያለውን ኬላ ሽሽት የሚደረገውን ተለዋጭ ጉዞ ትቼ በዋናው መስመር እንድሄድ አበክሮ ነገረኝ፡፡ መንገድ ገባሁ፡፡ በዋናው መስመር ለመሄድ ግን ትንሽ በሰውየው ላይ ካለኝ ኢማን ይልቅ ስለመንገዱ አደጋ የምሰማው አደላብኝና ሌላ መስመር ያዝኩ፡፡ የሚገርመው ግን በሌላኛው መስመር እየተጓዝኩ ሳለሁ ተያዝኩ፡፡ “አይ የነገረኝን አልቀበል ብየ ነው ይሄ የመጣብኝ” አልኩ፡፡ ይሄ ይበልጥ በሰውየው ላይ እንዳምን አደረገኝ፡፡ የተወሰነ ብር ከፍየ ተለቀቅኩ፡፡ ብቻ እንደምንም ጂቡቲ ገባሁ፡፡

እንደገባሁ ሁለት እህቶቼ ከነሱ ጋር እንድመጣ ቢጠይቁኝ ፈቃደኛ አልሆንኩም፡፡ ቢለምኑኝ ቢያስለምኑኝ አሻፈረኝ አልኩኝ፡፡ ምክንያቱም ባጭር ጊዜ ውስጥ ስራ እንደማገኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ግና ምኞት ሆኖ ቀረ፡፡ ስራ ሳላገኝ ወር፣ ሁለት ወር፣ … ስድስት ወር፣ … እያለ አመት ደፈንኩ፡፡ ኧረ እንዴት ነው ነገሩ?!

ከእለታት አንድ ቀን ለሶላት መስጂድ ውስጥ በገባሁበት ከሶላት በኋላ በኦሮምኛ ደዕዋ ይደረጋል፡፡ ብዙውን ሀሳብ ብረዳውም እኔ ከማውቀው የወሎ ኦሮምኛ የተወሰነ በመለየቱ ሀሳቦች ሳልረዳቸው ያልፉኛል፡፡ እጅ ላይ፣ አንገት፣ ወዘተ ስለሚታሰሩ ህርዞች (ክታቦች) አደገኝነት ሺርክ እንደሆኑ ሲተነትን ስሰማው በጣም ደነገጥኩ፡፡ ምክንያቱም በሰዓቱ ክንዴ ላይ ያሰርኩት ህርዝ አለኝ፡፡ (ይሄ ህርዝ ያ ጠንቋይ የሰራለት እንደሆነ የነገረኝ መሰለኝ፡፡ ወሬውን ከነገረኝ አራት አመት ስለሆነ እርግጠኛ አልሆንኩም፡፡) ብቻ ያንን ክንዴ ላይ ያለ ህርዝ ደዕዋው እስከሚያልቅ ድረስ ማቆየት እራሱ አስጨነቀኝ፡፡ በዚያ ላይ እራሴን አላመንኩትም፡፡ አሁን ላይ የጋለው ስሜቴ ላይ እያለሁ ቆርጬ ካልጣልኩ ኋላ ላይ ሀሳብ ቀይሬ መጣል እንደሌለብኝ ሁሉ ላምን እችላለሁ፡፡ በ “አዋቂዎች” ላይ ያለኝ እመነት ጫን ያለ ስለሆነ ብዙም እራሴን አላመንኩትም፡፡ ደዕዋው ሳይጠናቀቅ ከመስጂድ ወጣ ብየ ከእጄ ላይ ከበጠስኩት በኋላ እንዲርቅልኝ ድንጋይ ጋር አድርጌ ፌስታል ውስጥ አስገብቼ ከጠቀለልኩት በኋላ የምችለውን ያክል አርቄ ወረወርኩት፡፡ ኦህህህህ! አልሐምዱ ሊላህ! ሰላም!

ተመልሼ ደዕዋውን መከታተል ይዣለሁ፡፡ በጣም ደስ በሎኛል፡፡ ሲጠናቀቅ ዳዒውን ይዤ አናገርኩት፡፡ አስሬው የነበረውን ህርዝና ያደረግኩትን አጫወትኩት፡፡ አያይዤም ብዙ መማር እንደምፈልግ ነገር ግን የማውቀው ኦሮምኛ ትንሽ ስለሚለይ የተወሰነ ሀሳብ እንደሚያልፈኝ ነገርኩት፡፡ የከሚሴ ሰው ጋር አገናኘኝ፡፡ ከሱ ጋር ረጅም ጊዜ በመቆየት ተጠቀምኩኝ፡፡

ከረጅም ጊዜ በኋላ በባህር አድርጌ ወደ ሳዑዲ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ ብዙ ሆነን ጀልባ ላይ ተሳፈርን፡፡ ጉዞው እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ ማዕበሉ ልክ እንደተራራ ሆኖ ከርቀት ይመጣል፡፡ ያ የማዕበል ተራራ ሲያልፍ ጀልባዋ ከሰማይ መሬት ነው የምትፈጠፈጠው፡፡ የተበታተነች ይመስላል፡፡ በጣም አስጨናቂ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን ምንም ሳይመስላቸው ከሴቶቹ ጭን ላይ ተኝተው እያፏጩ የሚሄዱ ጎረምሳዎች አሉ፡፡ አሳፋሪ! አንድ ማዕበል ሲያልፍ ሌላ እየተተካ ጉዟችን ቀጠለ፡፡ አንዷ ተሳፋሪ ወልይ ብላ የምታስባቸውን ሙታኖች እየጠራች ትማፀናለች፡፡ “እከሌ ድረሱልን፡፡” “እከሌ እንዲህ በሉን፡፡” “የዛሬን” እያለች ትማፀናለች፡፡ እሷ በምትፈፅመው ሺርክ እዚሁ ሰምጠን እንዳንቀር የበለጠ ተጨነቅኩ፡፡ የምትጣራው አላህን አይደለም፡፡ እሷ በተጣራች ቁጥር እኔ ጭንቀቴ ጨመረ፡፡ ከዚያ “ዝም በይ!” ብዬ አምባረቅኩባት፡፡ “ካልሆነ ግን ከዚህ ውሃ ውስጥ ነው አንስቼ የምጥልሽ” አልኳት፡፡ የተወሰነ ዝም አለች፡፡ አስፈሪው ጉዞ እንደቀጠለ ነው፡፡ ትንሽ ቆይታ እየደጋገመች “በርደን ወሰላመን ዐላ ኢብራሂም” “በርደን ወሰላመን ዐላ ኢብራሂም” ማለት ያዘች፡፡ አንዱ ቀና ብሎ “እባክህ ይሄንንኳ ተዋት” አለኝ፡፡ በሁኔታዋ ላፍታም ቢሆን ሳቄ መጣ፡፡

… ጉዞው ተጠናቆ፣ የመን ላይ ብዙ ተንገላቶ ሳዑዲ ገብቶ በአሁኑ ሰዓት ቁርኣን ሓፊዝ ሆኗል፡፡ ታሪኩ ህዝባችን ያለበትን በስሱ ያሳያል በሚል ነው ያሰፈርኩት፡፡ በየቤቱ ስንት ተመሳሳይ ጉድ አለ?!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tgoop.com//IbnuMunewor
http://www.tgoop.com//IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ዐምር ብኑል ዓስ - ታላቁ ባለ ውለታችን
~
ስለ ታላቁ የኢስላም ባለ ውለታ ስለ ዐምር ብኑል ዓስ - ረዲየላሁ ዐንህ - እፅፋለሁ። የሺ0 ፈረስ በሆኑ የታሪክ አተላዎች ክብሩ እየተጎደፈ ስላለው ጀግናው የነብዩ ﷺ ሶሐቢይ እፅፋለሁ። የሶሐባ ጠላት የሆኑ እር-ጉም ሺዐዎችን እያወደሱ፣ በሶሐባ ክብር ላይ የሚረማመዱ ልባቸው በተሸይዩዕ መግል የተበከሉ ፍጥረቶችን እያየን ዝም ልንል አይገባም።

1 - ዐምር ብኑል ዓስ - ረዲየላሁ ዐንህ - ከነብዩ ﷺ ሶሐቦች ውስጥ አንዱ ናቸው። ሶሐባነት ተራ ማእረግ አይደለም። ይህን የሚረዳው የሶሐባን ደረጃ የሚያውቅ ነው። ዐምር ከመካ በድል መከፈት በፊት ነው የሰለሙት። ይህም የሆነው ከኻሊድ ብኑል ወሊድና ከዑሥማን ብኑ ጦልሐ ጋር ወደ ነብዩ ﷺ ዘንድ በመምጣት ነው። ዐምር አምነው ወደ መዲና ከተሰደዱት ሙሃጂሮች፣ በአላህ መንገድ ላይ ከተፋለሙት አማኞች ውስጥ ናቸው። እነዚህን አስመልክቶ አላህ ምን ብሏል?
{إِنَّ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِینَ هَاجَرُوا۟ وَجَـٰهَدُوا۟ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ یَرۡجُونَ رَحۡمَتَ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ}
"እነዚያ ያመኑትና እነዚያም (ከአገራቸው) የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ፡፡ አላህም እጅግ መሃሪ አዛኝ ነው።" [አልበቀራህ፡ 218]

2 - ዐምር ከነብዩ ﷺ እና ከኸሊፋዎቻቸው ዘንድ ታማኝ ነበሩ። ለዚያ ነበር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሲመርጧቸው የነበረው። የዛቱ ሰላሲል ዘመቻ ላይ በነብዩ ﷺ ሰንደቅ ተሰጥቷቸው አዋግተዋል። መካ የተከፈተች አመት የሁዘይል ጎሳ ወደሚያመልኩት የሱዋዕ ጣዖት ተልከው አፈራርሰው ተመልሰዋል። በዑመር፣ በዑሥማን እና በሙዓዊያ ተሹመው አገልግለዋል።

3 - ዐምር ለተለያዩ ሃገራት መከፈት፣ ለብዙ ህዝቦች ሂዳያ ሰበብ የሆነ ታላቅ ባለ ውለታ ናቸው። በነብያችን ﷺ የዖማንን ህዝብ ወደ ኢስላም እንዲጣሩ ተልከዋል። የሳቸውን ህልፈት ሲሰሙ ጊዜ ወደ መዲና ተመልሰዋል። [ጦበቃቱ ኢብኑ ሰዕድ፡ 7/493] በኸሊፋው አቡበክር ሻምን በመክፈት ሂደት ላይ ከተሾሙ አሚሮች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ በየርሙክ ዘመቻ ከሮማውያን ጋር ተፋልመዋል። በኺላፋው ዑመር ብኑል ኸጧብም ፊለስጢንና አካባቢዋ ላይ የተሾሙ ሲሆን ኋላም ተሻግረው ግብፅን እንዲያቀኑ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ግብፅን በድል የከፈቱ ጀግና ናቸው። እስኪ በሺዐና በፈረሶቻቸው የተከፈተ አንድ ስንዝር መሬት ጥቀሱ።

4 - ዐምር አርባ አካባቢ ሐዲሦችን ከነብዩ ﷺ ያስተላለፉልን ታላቅ ባለ ውለታችን ናቸው።

5 - ዐምር ብኑል ዓስ "ሰዎች ሰለሙ። ዐምር ብኑል ዓስ ግን አመነ" ብለው ነብዩ ﷺ የመሰከሩላቸው ናቸው። [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 3020] በተጨማሪም "የአልዓስ ልጆች ዓምር እና ሂሻም ሙእሚኖች ናቸው" ብለው መስክረውላቸዋል። [ሙስነድ አሕመድ፡ 8042]

6 - ዐምር ብኑል ዓስ ለነብዩ ﷺ ጥልቅ የሆነ ውዴታ ነበራቸው። ዐምር እንዲህ ይላሉ፦ "እኔ ዘንድ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ በላይ የተወደደ፣ አይኔ ላይ የተከበረ የለም። እሳቸውን ከማክበሬ የተነሳ በሙሉ አይኔ አይቻቸው ስለማላውቅ መልካቸውን ልግለፅ ብል ልገልፃቸው አልችልም።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 121] ታያለህ አይደል ከነብዩ ጋር ኖረው መልካቸውን መግለፅ አልችልም ሲሉ? አክብሮታቸው በዚህ ልክ ነበር! ሱብሓነላህ!!

ፍፃሜ!

ህመማቸው ሲጠናባቸው ጊዜ ጠባቂያቸውን ታላላቅ ጓዶችህን አስገባልኝ አሉት። ሲገቡ ጊዜ ተመለከቷቸው።
* "ያው እንግዲህ እዚህ ሁኔታ ላይ ደርሻለሁ። ያለሁበትን (ፈተና) መልሱልኝ" አሏቸው።
- "ያንተ አምሳያ ይህን ይላል ወይ አለቃ? ይሄ'ኮ ማንም የማይመልሰው የአላህ ውሳኔ ነው!" አሉ።
* "በሚገባ አውቃለሁ። እንድትገሰፁ ስለወደድኩ ነው ይህን ማለቴ" ካሉ በኋላ ደጋግመው "ላ ኢላሀ ኢለላህ!" እያሉ ሞቱ። [ታሪኹ ዲመሽቅ፣ ኢብኑ ዐሳኪር፡ 46/198]

ሞታቸው በ43 ዓመተ ሂጅራ የዒደል ፊጥር ሌሊት ነበር። ለዒድ ሶላት የታደመው ህዝብ ሶላተል ጀናዛ ሰግዶባቸው በግብፅ ካይሮ ከተማ አልሙቀጦም አካባቢ ተቀብረዋል። ሲሞቱ 90 አመታቸው ነበር። ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዷህ።

ከባድ ቅጥፈት በባለውለታችን ላይ!
-
የዑሥማንን በግፈኞች መገደል ተከትሎ በኸሊፋው ዐሊይ እና በሙዓዊያ (ረዲየላሁ ዐንሁም) መካከል እስከ ደም መፋሰስ የደረሰ አለመግባባት እንደተከሰተ ይታወቃል። በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሚጠቀሰው የዐምር ብኑል ዓስ እና የአቡ ሙሳ አልአሽዐሪ የሽምግልና ሂደት ነው።

ከዚህ ሽምግልና ጋር በተያያዘ አንድ እውነተኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ዐምር ብኑል ዓስን በሴራ እና ቃል በማፍረስ የሚወነጅል ትርክት አለ። ይሄ ሃሰተኛ ውንጀላ በሰፊው በመሰራጨቱ የተነሳ ብዙ ሙስሊሞች ለዐምር ብኑል ዓስ ጥላቻ አርግዘዋል። ይሄ መስተካከል ያለበት ፀያፍ ጥፋት ነው። ታሪኩ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነው:-

ከሲፊን ጦርነት በኋላ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይን፣ ሙዓዊያ ደግሞ ዐምር ብኑል ዓስን ለሽምግልና ይመርጣሉ። ሁለቱ ሽማግሌዎችም ዐሊይንም ሙዓዊያንም ከሃላፊነታቸው ሊያወርዱ ይስማማሉ። ከዚያም አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ ሚንበር ላይ በመውጣት "እኔ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ" ብለው ቀለበታቸውን ያወልቃሉ። ዐምር ብኑል ዓስ በተራቸው ተነሱና "እኔም እንዲሁ አቡ ሙሳ እንዳደረገውና ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ። ሙዓዊያን ደግሞ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማፀናው አፀናዋለሁ" አሉ። ይህንን ተከትሎ ጫጫታ በዛ። አቡ ሙሳ ተቆጥተው ወጡ። ወደ ዐሊይ ዘንድ ወደ ኩፋ ሳይሆን ወደ መካ ሄዱ። ዐምር ብኑል ዓስ ደግሞ ወደ ሻም ሙዓዊያ ዘንድ ሄዱ።
=
ይሄ ታሪክ:-

1ኛ፦ ከማስረጃ የተራቆተ ወፍ ዘራሽ የፈጠራ ወሬ (መውዱዕ) ነው። በዘገባው ውስጥ አቡ ሚኽነፍ የተሰኘ ውሸታም ሰው አለበት። ያለ ተጨባጭ መረጃ ደግሞ ሶሐባን ቀርቶ ተራ ሙስሊምም አይወነጀልም። ሐራም ነው። ለተጨማሪ መረጃ እነዚህን ምንጮች ተመልከቱ፦ [አኑስሑ ወልኢርሻድ ኢላ ተርኪ ቂሶሲን ላ የሲሑ ለሃ ኢስናድ: 61] [አልመሽሁር ሚነ ዶዒፍ ወማ ዩግኒ ዐንሃ፡ 409]

2ኛ፦ ዐሊይ ኸሊፋ ናቸው። ኸሊፋ ደግሞ እንዲህ እንደዋዛ በአንድና በሁለት ሰው ፍላጎት ከስልጣኑ አይነሳም። ኺላፋ እንዲህ ቀልድ ነው ወይ? ያ ሁሉ ቃል ኪዳን የተገባለት ሰው በሁለት ሰዎች ውሳኔ የሚወርድበት አሰራር የለም።

3ኛ፦ ደግሞም ሙዓዊያ ረዲየላሁ ዐንሁ በጊዜው ፈፅሞ "ኸሊፋ ነኝ" አላሉም። ከዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ጋር ያጣላቸውም ኸሊፋነቱ ይገባኛል ብለው አይደለም። ይልቁንም ሙዓዊያ የዑሥማን ገዳዮች ተላልፈው ካልተሰጧቸው ለ0ሊይ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀራሉ። ዐሊይ ደግሞ ሙዓዊያን ከሻም አስተዳዳሪነታቸው ሊያነሷቸው ይፈልጋሉ። መረጃ ልጥቀስ።
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አቡ ሙስሊም አልኸውላኒይ ረሒመሁላህ ሙዓዊያ ዘንድ ገብቼ "አንተ ግን ዐሊይን በኸሊፋነቱ ላይ እየተቀናቀንከው ነው ወይ? አንተ የሱ አቻ ነህ'ንዴ?" ብዬ ጠየቅኩት ይላሉ። "በጭራሽ ወላሂ! እኔ ዐሊይ በላጭና በጉዳዩም (በኸሊፋነቱ) ላይ የተገባ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን ዑሥማን በግፍ እንደተገደለ አታውቁም? እኔኮ የአጎቱ ልጅ ነኝ። ስለዚህ የሱን ደም ነው የምጠይቀው። ስለዚህ ዐሊይ ዘንድ ሂዱና የዑሥማንን ገዳዮች አሳልፎ እንዲሰጠኝ ንገሩት። ከዚያ በኋላ ለነገሮች እጅ እሰጥለታለሁ" አለ። ከዚያ ዐሊይ ዘንድ ሄደው ሲያናግሩ ገዳዮቹን አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። [ታሪኹል ኢስላም፡ 540]

ስለዚህ ሙዓዊያ "ኸሊፋ ነኝ" ብለው ባልሞገቱበት እንዴት ነው "ዐምር ብኑል ዓስ፡ የሙዓዊያን ኸሊፋነት አፅንቻለሁ" የሚሉት?!
ወደ ነጥቡ ስመለስ ዐምር ብኑል ዓስ በሴራ ዐሊይን ለማስወገድና ሙዓዊያን ለማንገስ ሰርተዋል የሚለው ወሬ የፈጠራ ታሪክ ነው። እንደ ፀሐይ ፍንትው ያለ መረጃ ሳንይዝ ሶሐቦችን ቀርቶ ከነሱ በኋላ የመጡ ትውልዶችን እንኳ ልንወነጅል አይገባም። ሌላው ቀርቶ ተጨባጭ ጥፋት ቢገኝ እንኳ ምላሳችንንም እጃችንንም ልንሰበስብ ግድ ይለናል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ሶሐቦቼን የተሳደበ የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁንበት” ብለዋልና። [አሶሒሐህ: 5/446] ደግሞስ ለስንቱ ጠማማ ወግኖ የሚሟገት ትውልድ በየትኛው ሞራሉ ነው በውዱ ነብይ ﷺ ውድ ባልደረቦች ላይ አፉን የሚከፍተው?! እኮ ማነህ አንተ?!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 25/2016)
=
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ሶሐቢዩ ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦

"ተቅዋ ማለት እራስህን ከማንም በላይ አድርገህ ላታይ ነው።"

[ተፍሲሩል በገዊይ: 1/60]

አላህ የሰጠን ኒዕማዎች ለምሳሌ የሸሪዐም ይሁን የዱንያ እውቀት፣ ዒባዳ፣ ኢስላማዊ ሸዓኢርን ማንፀባረቅ፣ ዝና፣ ስልጣን፣ ቤተሰባዊ ደረጃ፣ ሃብት፣ መልክ፣ ንቃት፣ ወዘተ. ልባችንን እንዳያሳብጡብን፣ ራሳችንን ልዩ አድርገን ማየት ላይ እንዳይጥሉን፣ ሌሎችን ዝቅ አድርጎ የመናቅ በሽታ እንዳያመጡብን መጠንቀቅ ይገባል። ብልጥ ማለት ራሱን እየተከታተለ ነፍሲያውን ረግጦ የሚይዝ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ቡኻሪ ላይ እንዳትፈልገው"
~
የ ኢስላም ማስረጃ ውስጥ ከሌለ ከየት ነው የመጣው ታዲያ?

* ይህንን አጭር የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ እርምት ይመልከቱ።
* የቴሌግራም ቻናሉን በዚህ ሊንክ ጆይን ብታደርጉ ትጠቀማላችሁ ኢንሻ አላህ፦
https://www.tgoop.com/Muhammedsirage
እየተረሳ የመጣ ሱና
~
የአላህ መልእክተኛ ﷺ "ስጦታ ተሰጣጡ፣ ትዋደዳላችሁና" ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ ፡ 3004]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
እየተስተዋለ!
~
ላይክ አጅርም ወንጀልም ይኖርበታል። የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን እያስተዋልን። ወንጀልን፣ ጥፋትን ፣ ክፋትን በላይክ፣ በኮመንት መደገፍና ማሰራጨት በስራ መዝገባችን ላይ ወንጀል ማስመዝገብ ነው። ጥፋት በማስራጨት፣ ዲንን በመጉዳት፣ ሹቡሃ በመንዛት፣ አጥፊዎችን በማስተዋወቅ ላይ የተሰማሩ አካላትን ፎሎው፣ ላይክ፣ ሰብስክራይብ፣ ጆይን፣ ... ማድረግ ለጥፋታቸው እገዛ መስጠት ነው። ስለዚህ ከንዲህ አይነት ገፆች ወይም አካላት ዛሬ ነገ ሳንል በጊዜ እንራቅ።

በሌላ በኩል የዲንም ይሁን የዱንያ ጠቃሚ ትምህርቶችን ስናገኝ በላይክ፣ በኮመንት፣ በማሰራጨት እናግዝ። ይህንን ማድረግ አጅር እንዳለው አይረሳ። ሶደቃ መልኩ ብዙ ነው። ላይክና ሼር ምን ያህል ነው ወጪው? አምስት ሳንቲም ላናወጣበት አጉል እንሰስታለንዴ? ብንሰስት እኛው ነን የሚቀርብን። ኸይር በማሰራጨትና በመደገፍ የሚገኘው አጅር ነው የሚያልፈን። ስለዚህ በምንገኝባቸው ፕላትፎርሞች ሁሉ ወገናቸውን ለመጥቀም ደፋ ቀና እያሉ ያሉ አካላትን ስራቸውን እንደግፍ። እዚህ ግባ የሚባል ቁም ነገር የሌላቸው እንቶ ፈንቶዎች በሺ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ላይክና ቪው እያገኙ የቁም ነገር ስራዎች የተመልካች ድርቅ ሲመታቸው ማየት አሳፋሪ ነው።

ብቻ ለራሳችን ለነጋችን ስንል እንወቅበት። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል :-

{ فَمَن یَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةٍ خَیۡرࣰا یَرَهُۥ (7) وَمَن یَعۡمَلۡ مِثۡقَالَ ذَرَّةࣲ شَرࣰّا یَرَهُۥ (8) }
"የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል።" [አዘልዘለህ: 7-8]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
በአካልም ይሁን በማህበራዊ መገናኛዎች ጓደኞቻችንን መምረጥና መለየት ይገባል። በጓደኛ ሰበብ የተጠቀመ፣ የተለወጠ እንዳለ ሁሉ፤ በጓደኛ ሰበብ መንገድ የሳተ፣ በጓደኛ የልብ ድርቀት የተጋባበት ፣ በጓደኛ ከኸይር የራቀ፣ ጥፋት የተላመደ፣ ሐያኡን ያጣ ፣ ... ብዙ አለ።
ስለዚህ ራሳችንንም ልጆቻችንንም ከመጥፎ ጓደኝነት እንጠብቅ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ነብዩን ﷺ የሚጠላ አንድ ሙስሊም የለም። እሳቸውን ጠልቶ ሙስሊም መሆን አይቻልም። የነዚህ ሰዎች ንግግር አንድምታ መውሊድን የሚቃወም ሁሉ ሙስሊም አይደለም የሚል ነው የሚሰጠው።
ይሄ የሰውየው ንግግር ሀሰተኛ፣ ፅንፈኛ እና ነውረኛ ንግግር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ብዙ ሴቶች እርቃናቸውን በሚሄዱበት በዚህ ዘመን ኒቃብ መልበስ እየፈለጉ በችግር ምክንያት መልበስ ያልቻሉ እህቶች መኖራቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን !?

ጂልባብ እና ኒቃብ የሚለብሱ እህቶች እንደ ባይተዋር በሚታዩበት ሀገር ውስጥ መልበስ ፈልገው በእጅ ማጠር ምክኒያት ያለበሱ ወይም የለበሱትን መቀየር ያልቻሉ እህቶችን መመልከት ልብ ይሰብራል። ለዚህም ሲባል ይሄ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚልን በሙሉ አካታች የሆነ ሰፊ ሀሳብ ይዘንላችሁ መተናል።

ሀሳቡም :- የኒቃብ ባንክ መክፈት ነው።  ይህም ማለት ስራዉን በሚሰሩ  ወይም  በሚመለከታቸዉ  እህቶች  ስም የባንክ  አካውንት  የተከፈተ  ሲሆን  ገንዘብ  በማሰባሰብ  ኒቃብና  ጅልባብ መግዛት::  ቅያሪ  ኒቃብና  ጅልባብ  ኖሯቸዉ መስጠት ለሚፈልጉ  እህቶች  ያሉበት ሰፈር ድረስ ሄዶ  በመቀበል  ለተቸገሩ  እህቶቻችን  ማድረስ  ናቸው።

የኒቃብን ግዴታነት አውቀውና   ተረድተው በችግር ምክንያት መልበስ ላልቻሉ እህቶች እንድረስላቸው።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ➛ 1000588690486
Hikma and/or Ahlam and/or Muhiba

ለየትኛውም  ሀሳብ ፣ አስተያየት ፣ ጥቆማና ጥያቄ  እነዚህን አማራጮች  መጠቀም ትችላላቹ 

እህቶች በዚህ👇
@AhluYeWereilua
@nikab_new_wbetea 

ወንድሞች በዚህ👇
@FuadBezu
@red_one1212

ስልክ 0913666695
         0910863508

የቴሌግራም  ቻናላችን👇
www.tgoop.com/NikabJilbab

የቴሌግራም  ግሩፓችን 👇
www.tgoop.com/nikab_jilbab_group
አሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ ወበረካቱህ

ውድ ተከታታዮቻችን በሙሉ፥ እነሆ! የፊታችን ማክሰኞ 06/12/2017 ዓ.ል ፎሎው የማድረግ ቻሌንጅ 2ኛ ሳምንት እንዲሁም በተወዳጅ ኡሥታዞቻችን የሙሐደራህ መርኃ ግብር በቲክቶክ ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም አሰናድተናል። በእለቱም በኡሥታዞች በሚሰጡ ዳዕዋዎች በርካታ ትምህርቶች የምንቀስም ሲሆን፤ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

ፕሮግራም አቅራቢዎች
❶ ኡሥታዝ ሙሐመድ አብደላህ ባቲ
➋ ኡሥታዝ ናሲር ሙሐመድ (አቡል ዓባስ)
➌ ኡሥታዝ አብዱረዛቅ ባጂ
ሌሎችም ኡሥታዞች ይኖራሉ

ቀን :- እለተ ማክሰኞ 06/12/2017
ሰዓት :- ከምሽቱ 03:00
ቦታ :- በዳዕወቱል አንቢያ የቲክቶክ አካውንት

⭕️ማሳሰቢያ⭕️
ቲክቶክ ለማትጠቀሙ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙ በቴሌግራም ቻናላችን ይተላለፋል :- https://www.tgoop.com/daio_TG07

#Dawatul_Anbiya
#የነቢያት_ጥሪ_በሁሉም_ቦታ_ጊዜ_እና_ሁኔታ
ቀጣዩ የትምህርት አመት እየተቃረበ ነው። ብዙ ደብተርና ዩኒፎርም ማሟላት የማይችሉ ወገኖች በያካባቢው አሉና ተወላጆችን እያስተባበርን ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት ላይ ብንሰራ መልካም ነው። በወረዳ ወይም በቀበሌ ደረጃ ሰዎች ኃላፊነት እየወሰዱ ቢሰሩበት ጥሩ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
2025/09/14 07:00:50
Back to Top
HTML Embed Code: