IBNUMUNEWOR Telegram 7754
በባህር እየሄደ ለሚያልቀው ወገናችን በተዘዋዋሪም ቢሆን ለሞቱና ለስቃዩ የብዙ አካላት እጅ አለበት።
1- በሃገሩ ሰላም የለም። በስሙ የሚምለው ሁሉ ለጦርነት ነው የሚያጨው። የትናንቱ እልቂት አልበቃ ብሎ የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙ ከዚህም ከዚያም ዛሬም እያየን ነው። ጥቂቶች ሊነግሱ የድሃ ልጅ ማገዶ ይሆናል። ወጣቱ ሞትን ሸሽቶ ሞት ላይ ይወድቃል።

2- በዛሬዋ ኢትዮጵያ በሃገር በቀየ ሰርቶ መለወጥ ቀርቶ የእለት ጉርስ እንኳ መሸፈን የማይወጡት ፈተና እየሆነ ከእለት ወደ እለት እየከፋ ነው። የሰላም መጥፋት፣ ለስራ የማይመች የማያፈናፍን ቢሮክራሲ፣ እዝነት ርህራሄ የሌለው የግብር ሲስተም፣ ማለቂያ የሌለው መዋጮ፣ እሳት የሆነ የኑሮ ውድነት፣ ... ተደማምሮ የወጣቱን በሃገር በቀየው ሰርቶ የመለወጥ ተስፋ አሞሽሾታል።

3- ህገ ወጥ የሚባሉት ጉዞዎች በቀይ ባህር በኩል ወደ የመን - ሳዑዲ፣ በኬንያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ በረሃ በኩል ሜዲትራኒያን ባህር አቋርጦ ወደ ይሮፕ፣ ሁሉም አሰቃቂና ህይወት የሚያስከፍሉ ናቸው። ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ይህንን አስፈሪ አማራጭ የሚወስዱት ወገኖች ስቃይን መርጠው፣ ጀብደኝነት አምሯቸው አይደለም። ህጋዊ የሚባለው መንገድ ''ሽፍታ" ያደፈጠበት ሆኖባቸው እንጂ። ዛሬ የቀበሌ መታወቂያ ለማግኘት ጣጣው ብዙ ነው። በየመንገዱ፣ በየ ቢሮው የምትጠየቀውን መታወቂያ ከምትኖርበት ቀበሌ ለማግኘት ብዙ ደጅ መጥናት ይኖርብሃል። ያውም ከተሳካ። የልደት ካርድ ማውጣትም እንዲሁ ሌላኛው ጣጣ ነው። ፓስፖርትማ ከክፍያው መናር በላይ በየ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤቶች በር ላይ ያለውን ትርምስ ያየ የእውነት ያሳቅቃል። የዜጎችን ኪስ እየበዘበዘ ለወራት፣ አለፍ ሲልም ለአመታት ዜጎችን የሚያንገላታ የማይሻሻል መስሪያ ቤት ማለት ኢሚግሬሽን ቢሮ ነው።
የፓስፖርቱ ጣጣ አልቆ በኤጀንሲዎች በኩል ለመሄድ ደግሞ ሁሉ ሰው የመውጣት እድል አያገኝም። በዚህ የተነሳ አንዳንዱ በራሱ ተፃፅፎ፣ በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ የአየር ትኬት ቆርጦ ለመውጣት ሲሞክር ኤርፖርት ላይ የሚያጋጥሙ ጣጣዎች አሉ። እዚያም ሌላ መሰናክል። እዚያም ሌላ እጅ መንሻ። የቆረጡትን ትኬት ጥለው እንደገና ወደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ ሄደው ከዚያ ሌላ ትኬት ቆርጠው የሚወጡ አሉ።
ህጋዊ የሚባሉት አማራጮች ድህነት ለፈተነው የድሃ ልጅ ኪስ የማይሞከሩ ከሆኑ፣ ህጋዊ የሚባሉት አማራጮች "ህጋዊ" ሌቦች እና ህግን የተደገፉ መሰናክሎች ከበዛባቸው አስኮብላዮችን ማሳደድ እና ህገ ወጥ ደለላዎች እያሉ ማራገብ እንዲሁ በቀዳዳ በርሜል ውሃ መቅዳት ነው የሚሆነው። ይሄ በቀይ ባህር እና በሜድትራኒያን ባህር የውሃ ሲሳይ የሚሆነው፣ ይሄ በሊቢያ በረሃ አሳሩን የሚበላው፣ ይሄ በኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ... በሽፍን መኪና ውስጥ አየር አጥሮት የሚያልቀው፣ ... ይሄ የጅቡቲው መስመር ሲወሳሰብበት በሶማሊያ ቦሳሶ ድረስ ሄዶ የሚባዝነው የስቃይና እንግልት ሱስ ስላለበት አየደለም። ሰርቶ መለወጥ ፈተና ቢሆንበት፣ መንገዱ ሁሉ ቢዘጋጋበት፣ አማራጩ ሁሉ ቢጨልምበት እንጂ። የእውነት የሃገራችን ወጣት ሁኔታ ከልብ የሚያሳዝን ነው። ነገሩ "እባካችሁ በባህር አትሂዱ" እንደማለት ቀላል አይደለም። ብቻ አላህ ፈረጃውን ያምጣልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

tgoop.com/IbnuMunewor/7754
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7754

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Hui said the messages, which included urging the disruption of airport operations, were attempts to incite followers to make use of poisonous, corrosive or flammable substances to vandalize police vehicles, and also called on others to make weapons to harm police. How to build a private or public channel on Telegram? It’s easy to create a Telegram channel via desktop app or mobile app (for Android and iOS): Judge Hui described Ng as inciting others to “commit a massacre” with three posts teaching people to make “toxic chlorine gas bombs,” target police stations, police quarters and the city’s metro stations. This offence was “rather serious,” the court said. In 2018, Telegram’s audience reached 200 million people, with 500,000 new users joining the messenger every day. It was launched for iOS on 14 August 2013 and Android on 20 October 2013.
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American