Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📖 قال الله تعالى:
﴿ وَاعْتَصِمُواْ بِحَبْلِ اللّهِ جَمِيعًا وَلاَ تَفَرَّقُواْ ﴾.

🎙 الشيخ الوالد/ ربيع بن هادي المدخلي - رحمه الله -.
==

የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የደዕዋ ጥሪ ለሁሉም ሙስሊሞች
~
የፊታችን ጁሙዐ ምሸት 3፡00 ላይ ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል ኢንሻአላህ።

ተጋባዥ : - የተከበሩ ሸይኽ 0ሊይ ብኑ አሕመድ አራዚሒይ
فضيلة الشيخ علي بن أحمد الرازحي

* ሸይኹ በርካታ ኪታቦችን ያዘጋጁ እና ብዙ ዱሩሶች ያሏቸው ታዋቂ የየመን ዓሊም ናቸው።

* ዐረብኛ ለማይችሉ ከትርጉም ጋር አብሮ ይቀርባል።
* የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል ይሄ ነው፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

* ማስታወቂያውን በማሰራጨት የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ።


دعوة لحضور محاضرة للشيخ علي بن أحمد الرازحي - حفظه الله تعالى- من علماء اليمن السلفيين
يوم الجمعة تاريخ 11-7-2025 م  الساعة التاسعة مساء بتوقيت مكة المكرمة 🇸🇦  الثالثة مساء بتوقيت إثيوبيا 🇪🇹
يلقيها إلى إخوانه في بلاد الحبشة عبر الإنترنت والدعوة عامة لطلاب العلم والمسلمين أجمعين ويوجد ترجمة لمن لا يفهم اللغة العربية وذلك على قناة ابن منور بالتليجرام من خلال الرابط التالي:

https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

أسأل الله أن ينفع بهذه المحاضرة ويجزي الشيخ و الإخوة المشرفين والمترجمين خير الجزاء إنه ولي ذلك والقادر عليه.
~ሁላችንም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው፣ ከታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዓሊይ ብኑ አሕመድ አራዚሒይ የሚተላለፈው የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ቀርተውታል።

https://www.tgoop.com/IbnuMunewor?livestream=9b5f6234af43db499a
Live stream finished (1 hour)
Forwarded from Fuad Mohammed (فؤاد محمد)
ስለ ትናንቱ የኦንላይን ደዕዋ
~
በቅድሚያ አላህ ስላገራውም ስላደለንም አልሐምዱ ሊላህ። በመቀጠል ጊዜያቸውን ሰጥተው ውድ ምክሮችን ያካፈሉንን ሸይኽ ዐሊይ አራዚሒይን ከልብ እናመሰግናለን። እንዲሁም ለሃሳቡ መነሻ የሆኑ ወንድሞችን ዐብዱልፈታሕ ሙሐመድዘይን (የመን በዒልም ፍለጋ ላይ ያለ ወንድማችን ነው)፣ አሕመድኑር ኸዲር ከወሎ ወረባቦ፣ ደዕዋውን በመተርጎም ላይ ያገዙ አቡል 0ባስ ናሲር፣ ዐብዱረዛቅ ባጂ፣ አቡ ሱፍያን እና የመን ከሸይኽ ዐሊይ ጋር ያለ ሌላ የሃገራችን ልጅ (ኻሊድ?) ሁላችሁንም ጀዛኩሙላሁ ኸይረን።

ለታዳሚዎች ባጠቃላይ ለተፈጠረው የኔትዎርክ ችግር - ከኛ ቁጥጥር ውጭ ቢሆንም - ይቅርታ እየጠየቅን ፕሮግራሙን ስለታደማችሁ በጣም ደስ ብሎናል። አላህ በሰማችሁት የምትጠቀሙ ያድርጋችሁ። ለወደፊቱም በአላህ ፈቃድ ከሌሎች መሻይኾች ጋርም በመነጋገር ተመሳሳይ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ሃሳቡ አለን። እንደዚሁም በሃገር ውስጥ መሻይኾች እና ኡስታዞችም ለማስተላለፍ የምናስብበት ይሆናል ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ለህፃን ሙሐመድ እንድረስለት። ጉዳቱ የከፋ ነው። ለውጭ ህክምና የተደረገው የድጋፍ መጠን ስላልምላለ በምንችለው ብናግዘው መልካም ነው። ዱዓም እናድርግለትለት።


✔️የባንክ አካውንቶች፦
Account Name: Ziyad Nuredin

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦1000525385373
ዳሽን ባንክ: 2933592396721
አዋሽ ባንክ: 01425898257700
አቢሲንያ ባንክ:  29173998 
ኦሮሚያ ባንክ:  1756167200001
ቴሌብር: 0912844116


(ለበለጠ መረጃ):
+251912844116 (ዚያድ )   አባት
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ቅድሚያ ለቁርኣን
~
በዚህ ዘመን ያለው የሙሉ ቀን የትምህርት ፕሮግራም ልጆች በስርአት ቁርኣን እንዳይቀሩ እንቅፋት ሆኗል። ልጆች ለቁርኣን በቂ ጊዜ እያገኙ አይደለም። የተሻለ ሰፊ ጊዜ ያለው ትምህርት የሚዘጋበት የክረምቱ ክፍለ ጊዜ ነው። ቁርኣንን የማስተማር ሲስተማችን ደካማ በመሆኑ ልጆች ለማጠናቀቅ አመታት ይወስድባቸዋል። ያም ሆኖ አጥርተው መቅራት የማይችሉት ብዙ ናቸው።
ችግሩን ለመቅረፍ የችግሩን መንስኤ መረዳት ይገባል።

1- በቂ አስተማሪ መመደብ፣

አንድ ኡስታዝ ብዙ ተማሪዎችን በስሩ የሚይዝ ከሆነ ልጆች በቂ ትኩረትና እድል አያገኙም። የሚያቀራቸው፣ የሚያርማቸው፣ የሚያዳምጣቸው ፣ ... ካላገኙ ልፋታቸው እንዲሁ መመላለስ ይሆናል።

2- ለአስተማሪዎቹ የተሻሉ የማስተማር ስልቶችንና የልጆች አያይዝ ስልጠና መስጠት፣

ቀለል ያለ የአቀራር ሲስተም እንዲከተሉ ማሳየት፣ ኢኽላስን ማሳሰብ፣ ልጆች እንዳይሰለቹ አድርጎ መያዝ፣ ሞራላቸውን መገንባት፣ ደካሞችን ትኩረት እንዳይነፍጉ መጠቆም፣ ልክ ያለፈ እና የሚያስበረግግ ቅጣት እንዳይኖር ማሳሰብ፣ ወዘተ .

3- ሰፊውን ጊዜ ለቁርኣን ማድረግ

ይህንን ማስታወሻ ለመፃፍ የተነሳሁት በዚህኛው ነጥብ ምክንያት ነው። በብዙ ሰፈሮች የክረምቱን ጊዜ ቁርኣን በቅጡ መቅራት የማይችሉ ልጆች የክረምት ኮርስ እየተባለ ከልጆቹ አቅም ጋር በማይሄድ ርእስ መጥመድ እየተለመደ መጥቷል። ቁርአን ያልቀሩ ልጆችን ሙቱኖችን ማስሐፈዝ፣ ሐዲሥ ማስሐፈዝ፣ አቅማቸውን ያላገናዘበ ሲራ፣ ፊቅህ፣ ... ማስተማር ቅደም ተከተል ያልጠበቀ አካሄድ ነው። በቅድሚያ ሙስተዋቸውን እንለይ። አቅማቸውን እናገናዝብ። ቅደም ተከተሎችን እንጠብቅ። ቁርኣን ላልቀሩ ልጆች ትርጉማቸውን የማያውቋቸውን የተጅዊድ፣ የተውሒድ፣ የሲራ መንዙማዎችን በማስሐፈዝ ከምንጠምዳቸው ቀለል ባለ መልኩ ባጭሩ የውዱእ አደራረግ፣ የሶላት አስጋገድ፣ አርካኑል ኢማንና አርካኑል ኢስላም፣ ወላጅን ማክበር፣ የመሳሰሉ ትምህርቶችን በጣም ባጭሩ እየደጋገሙ በመጠቆም ሰፊውን ጊዜ ቁርኣን ንባብ እንዲለዩ፣ አጥርተው እንዲቀሩ ማገዝ ይገባል።
ቁርኣን የጨረሱትን ደግሞ እንዳቅማቸው እየለዩ ማስተማር ነው። ዋናው ትኩረቴ ልጆች በሚገባ ቁርኣን የሚቀሩበትን ጊዜ ባግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ለአስተማሪዎች ወይም ለአስተባባሪዎች ማስታወስ ነው።

.
* በአሁኑ ጊዜ ልጆች በሰፊው የሚማሩባትን የአልቃዒደቱ ኑራኒያህ አፕ የፈለገ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.zoomat.noorania

* ሌሎችም በቁርኣን አቀራር ላይ የተሻሉ የምትሏቸው አፖች ፣ መማሪያዎች፣ ምክሮች ካሉ ብትጠቁሙ ለሌሎችም ይጠቅማሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Forwarded from ABU MUSLIM A-DUROOS
دورة الإمام المزني

📢ታላቅ የኮርስ እና የዳዕዋ ፕሮግራም
➡️ በሚዛን አማን ከተማ በኑር መስጂድ

ተጋባዥ እንግዶች

ኡስታዝ አቡ ሙስሊም አል-ዓሩሲ
ኡስታዝ  አብዱረዛቅ  አል ባጂ
ኡሰታዝ አቡል ዐባስ አል-በከዊ
دورات
- شرح السنة للمزني
- منظومة في السير إلى الله ..
- آداب معلم القران ومتعلمه

المحاضرات
- الهمة في طلب العلم
- السنة و البدعة
- الاستقامة على دين الله
- الحقوق العشرة

ኮርሱ በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል⬇️
https://www.tgoop.com/AbumuslimAlarsi
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካምን ይናገር፣ ካልሆነ ዝም ይበል።" [ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ስለ ጤናዬ ሁኔታ ብዙዎች እየጠየቃችሁ ነው። አልሐምዱ ሊላህ ደህና ነኝ። ህመሙ ቀድሞ ከነበረው በጣም ቀንሶልኛል። ለጊዜው ጉዳቱ ለውጥ መኖሩን ማወቅ አልችልም። MRI ወይም CT Scan ይፈልጋል። የ 3 ወር ቀጠሮ ስለተሰጠኝ ያኔ ይታወቃል። ኢንሻአላህ ለውጥ እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ወር ከ15 ቀን አካባቢ ሆኖኛል።

ያሰባችሁ የተጨነቃችሁልኝ ሁሉ እጅግ ከልብ አመሰግናለሁ። አላህ በዱንያም በአኺራም አብዝቶ ይመንዳችሁ። ስልክ እየደወላችሁ ያላነሳሁላችሁ ወይም 'ሜሴጅ' ልካችሁ ያልመለስኩላችሁ ብዙ አላችሁ። ባለመመለሴ ይቅርታ አድርጉልኝ። በድጋሜ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
... ወንድማለም ግን የያዝከው ተውሒድ የሚያስገድል ከሆነ እኛም ደስ እያለን ለመሞት ወላሒ ዝግጁወች ነን።

አንተ ጀግና ወጣት ነህ ስንቶቹ ሲሽለጠለጡ በተውሒድህ ፀንተህ ተፋልመሀል
(እንደዛ ነው የምናስብህ ሀቂቃ) አሏህ ማረፊያህን ጀነት ያድርገው ጀግናዬ‼️

ብዙ ፕሮግራሞች አውጥተን
ብዙ ነገር አስበን ተማክረን ነበር ብዙ ቦታ ሔደን ትብብራችንን አጠንክረን ስንት አስበን ቀደር ቀደመ የአሏህ ውሳኔ ተፈፀመ አሏህ ይዘንልህ ጀግናዬ።

ለቤተሰቦችህ አሏህ ፅናቱን ይስጣቸው
እንኳን የወለደህ የወደደህና የተጎዳኘህም ሀዘንህ ከብዶታል አሏህ ይዘንልህ

በተቻለ መጠን በዛ አካባቢ ያላችሁ የሱና ወንድሞች ጥንቃቄ አድርጉ አሏህ ይጠብቃችሁ።

http://www.tgoop.com/nuredinal_arebi
http://www.tgoop.com/nuredinal_arebi
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች፦

ችግር በበረታበት በዚህ ወቅት ለኸይር ስራም ቢሆን " ይህንን አድርጉ ፣ ለዚህ አዋጡ " ማለት የሚከብድም የሚያሳፍርም ሆኗል !

የዛሬውን አይነት ጥያቄ ይዞ መቅረብ ግን ያኮራልና የሚከተለውን ልንል ወደድን ...

በቆቦ እና በአካባቢዋ ቀኝ ግራውን ሳይፈራ ለተውሒድ ሲታገል የነበረ ወንድማችን ነው በግፍ የተገደለው !
ወንድማችን
ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የተወሰነ እዳም ጥሎ ነው የሄደው የተከበረው ጀግና ወንድማች ....

እንረባረብ - አሏህ ዘንድ አጅሩን እናገኛለን !


1000685224325

ሙሐመድ

ሰይድ

አልይ

https://www.tgoop.com/Muhammedsirage
2025/09/14 20:58:21
Back to Top
HTML Embed Code: