tgoop.com/IbnuMunewor/7759
Last Update:
አቡ ሙስሊም አልኸውላኒይ ረሒመሁላህ ሙዓዊያ ዘንድ ገብቼ "አንተ ግን ዐሊይን በኸሊፋነቱ ላይ እየተቀናቀንከው ነው ወይ? አንተ የሱ አቻ ነህ'ንዴ?" ብዬ ጠየቅኩት ይላሉ። "በጭራሽ ወላሂ! እኔ ዐሊይ በላጭና በጉዳዩም (በኸሊፋነቱ) ላይ የተገባ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን ዑሥማን በግፍ እንደተገደለ አታውቁም? እኔኮ የአጎቱ ልጅ ነኝ። ስለዚህ የሱን ደም ነው የምጠይቀው። ስለዚህ ዐሊይ ዘንድ ሂዱና የዑሥማንን ገዳዮች አሳልፎ እንዲሰጠኝ ንገሩት። ከዚያ በኋላ ለነገሮች እጅ እሰጥለታለሁ" አለ። ከዚያ ዐሊይ ዘንድ ሄደው ሲያናግሩ ገዳዮቹን አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። [ታሪኹል ኢስላም፡ 540]
ስለዚህ ሙዓዊያ "ኸሊፋ ነኝ" ብለው ባልሞገቱበት እንዴት ነው "ዐምር ብኑል ዓስ፡ የሙዓዊያን ኸሊፋነት አፅንቻለሁ" የሚሉት?!
ወደ ነጥቡ ስመለስ ዐምር ብኑል ዓስ በሴራ ዐሊይን ለማስወገድና ሙዓዊያን ለማንገስ ሰርተዋል የሚለው ወሬ የፈጠራ ታሪክ ነው። እንደ ፀሐይ ፍንትው ያለ መረጃ ሳንይዝ ሶሐቦችን ቀርቶ ከነሱ በኋላ የመጡ ትውልዶችን እንኳ ልንወነጅል አይገባም። ሌላው ቀርቶ ተጨባጭ ጥፋት ቢገኝ እንኳ ምላሳችንንም እጃችንንም ልንሰበስብ ግድ ይለናል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ሶሐቦቼን የተሳደበ የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁንበት” ብለዋልና። [አሶሒሐህ: 5/446] ደግሞስ ለስንቱ ጠማማ ወግኖ የሚሟገት ትውልድ በየትኛው ሞራሉ ነው በውዱ ነብይ ﷺ ውድ ባልደረቦች ላይ አፉን የሚከፍተው?! እኮ ማነህ አንተ?!
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 25/2016)
=
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7759