Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
መውሊድ በማን ተጀመረ?
~
የመውሊድ ደጋፊዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። ነገር ግን በነዚህ ሺ0ዎች እንደተጀመረ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ማስረጃዎች በጨባጭ አሉ። ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ።
1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):—
በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚይ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡-
“የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውዳመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውዳመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ ﷺ ልደት (#መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ የልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁን)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም የልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436]
መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን ﷺ ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 3/101]
ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው። እያስተዋላችሁ!
2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):—
ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢይ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡-
ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر
“ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ ﷺ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ (ዐለይሃ ሰላም) መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን (ዐለይሂመ ሰላም) መውሊድ እና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው።” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219]
3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲይ (821 ሂ.):—
ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወራ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ ﷺ መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካለ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካል። [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576]
ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው። ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒ'ላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው። ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው። ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ እራሱን ነው የሚያታልለው። ስለዚህ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” ማለት ውሃ አያነሳም።
“ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም። በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው። ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “እሱ ጀማሪ ነው” አላሉም።
መቅሪዚይ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር። [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚ'ላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት። ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ከሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው።
በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው። ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው። አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው። ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም በተጨባጭ አሉ። ያቁት አልሐመዊይን አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው። ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡-
“የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው። እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር። ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚመፀውት ነበር። እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃ .ዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር። በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡-
‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ
በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ
መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ!
ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ።’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138]
ያቁት አልሐመዊይ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው። በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃዲቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም። ከነቢዩ ﷺ ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም። እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 08/2013)
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ስራ ለሰሪው
~
ከማህበራዊ መገናኛዎች ቆይታው ኸይር የሚያተርፍ አለ፣ ወንጀል የሚያተርፍ አለ። እኛ ከየትኛው ነን? ኸይር ለመስራት፣ በኸይር ላይ ለመተባበር፣ ለመማማር ነው የምንጠቀመው? ወይስ ክፋት ለማሰራጨት፣ በየኮመንቱ ለመዘላለፍ፣ ዘርን ከዘር ለማፋጀት፣ የሰዎችን ንግግር እየጠመዘዙ ለመናቆር? የትኛውንም እንስራ ከፊታችን ሒሳብ አለ። ከፊታችን አላህ ፊት መቆም አለ። ሁሉም የዘራውን የሚያጭድበት ከሞት በኋላ ሕይወት አለ። ያኔ ሁሉም የእጁን ውጤት ያገኛል። መቼስ ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጥጠበቅም። ከፋም ለማም ሁሉም ለራሱ ነው። አላህ እንዲህ ይላል :-
{ إِنۡ أَحۡسَنتُمۡ أَحۡسَنتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡۖ وَإِنۡ أَسَأۡتُمۡ فَلَهَاۚ }
"መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡ መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው።" [አልኢስራእ ፡ 7]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-

ለወገን መቆርቆራችን የእውነት ነው ወይ?
~
አንድ የፉላኒ ብሄር ሰው ከኢግቦ ብሄር ሰው ጋር ቢጣላ ብዙ ፉላኒዎች ከፉላኒው፣ ኢግቦዎች ደግሞ ከኢግቦው ወግነው ይነሳሉ። አጥፊው ማነው የሚለውን ሳያጣሩ ማለት ነው። ይሄ ቋንቋና ብሄር እያየ ቆንጨራ የሚያነሳ መንጋ ግን ጎዳና ላይ የወደቀ ወገኑን ቤቱ ወስዶ አያስጠልልም። ለተራበ ወገኑ ቁራሽ አይጥልም። ዶላር እየላከ ታጣቂ የሚያስታጥቀው ዲያስፖራ አስተባብሮ ሰፈሩ ላይ ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋም አይገነባም።
የአብዛኞቻችን ለወገን መቆርቆር ትርጓሜ ጥቃት ሲደርስ ሌላውን ማውገዝ ላይ ያተኮረ ነው። በርግጥ ይሄ የመቆርቆር አንድ ገፅ ነው። ነገር ግን እውነት ለወገን የምንቆረቆር ከሆነ
- በፍርፋሪ እምነቱን የሚቀይረውን እንድረስለት።
- በሺርክና በቢድዐ የተወረረውን እንታደገው።
- በዘረኝነት የሚባላውን ከዚህ ገዳይ በሽታ እንዲድን እንስራ።
- ሁለ ነገሩን እያቃወሰ ካለው የጫት ሱስ እንዲወጣ እንታገል።
- ለዘመድ፣ ለጎረቤት ለችግራቸው እንድረስ።
- ነገ ጤናማ ትውልድ ይሆኑ ዘንድ ለልጆቻችን የተሻለ አስተዳደግ እንስጣቸው።
ሁላችንም ለለውጥ አስተዋፅዖ ማድረግ እንችላለን። ከራሳችን፣ ከቤታችን እንጀምር። እንደ ቤተሰብ ሰውኛ ባህሪ እንዲኖረን እንስራ። ማህበረሰብ የቤተሰብ ድምር ውጤት ነውና አቅልለን አንየው። "ሮም ባንድ ቀን አልተሰራችም።"
በተረፈ እርሱ ቦርጭ ተሸክሞ እየተጓዘ ለተቸገሩ ወገኖቹ መድሃኒት የማይገዛ፣ ሳይቸግረው ወላጅ ቤተሰቡን ዞሮ የማያይ፣ የወገኑ በሺርክ፣ በሱስ መወረር የማይቆረቁረው ሁላ የግለሰቦችን ግጭት ሁሉ ወደ ብሄር እየተረጎመ አቧራ ቢያስነሳ ከሰውነት ተራ መውጣቱን ነው የሚያሳየው። ለፍትህ ቦታ ሳይሰጡ ምድብ እያዩ መሰለፍማ በጫካው ዓለም ያለ የእንስሳት ህግ ነው። ይልቅ ከፍ ብለን እንገኝ። ሰው መሆን ነውንጂ ሰው መምሰልማ ማንን ያቅታል?!

መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም!
{ምስክር እራሳቸው!}
~
ቀደም ባለው ዘመን መውሊድን ደጋፊዎቹ ጭምር ቢድዐ መሆኑን ያምኑ ነበር። ክርክራቸው ቢድዐ ሐሰና (መልካም ቢድዐ) ነው የሚል ነበር። ዛሬስ?አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች እያደረጓቸው ነው። አንዳንዶቹማ ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ ሲንደፋደፉ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] እልህ በሳቸው ላይ እስከሚዋሽ ያደረሰው ሰው ወዮለት!
ለማንኛውም ቀደም ያሉት የመውሊድ #ደጋፊዎች ይሄ ድግስ ከነባሩና ከጥንቱ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ ፈሊጥ እንደሆነ አስረግጠው መስክረዋል። ንግግራቸውን እጠቅሳለሁ፡-
1. አቡ ሻማ፡-
“በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95]
2. ኢብኑ ሐጀር፡-
“የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188]
3. ሰኻዊ፡-
“የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉል ሁዳ ወረሻድ፡ 1/439]
4. ተዝመንቲ፡-
“የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አሲረቱ አሻኒያህ፡ 1/441]
5. አልዒራቂ፡-
“ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136]
6. ሲዩጢ፡-
“የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አልሓዊ፡ 1/189]
(መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ንግግሩን ያጣቀስኩት መውሊድ የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።)
7. ዘርቃኒ፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264]
ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው።
(وَشَهِدَ شَاهِدࣱ مِّنۡ أَهۡلِهَاۤ)
የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው የሆነ ያክል ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ መጤ መሆኑን እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹስ? አይኔን ግንባር ያድርገው ካሉ አይመለሱም።
ብቻ አንባቢ አንድ ቁም-ነገር ይውሰድ። መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (የጋራ ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ የማይታወቅ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የተጠነሰሰ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአኢማዎቹ፣ የነ ቡኻሪ፣ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም። ከዚህ ውጭ ያለ እምነት በኢስላም ስም ቢጠራም፣ "ነባሩ" እያሉ ቢያሽሞነሙኑትም ነባር ሳይሆን ፎርጂድ ነው። ስለዚህ መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለሆነም መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃ.ብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍ .ዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው።
ማምታቻ!
-
መውሊድ ራሳቸው በሚያከብሯቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ መሆኑ ሲነገር ጊዜ እንደ ሐሰን ታጁ ያሉ የዚህ ቢድዐ ደጋፊዎች ሌላ ማምታቻ አምጥተዋል። ይኼውም ቢድዐ የሆነው በኦፊሴል ማክበሩ እንጂ ቀድሞም ነበር የሚል። ይሄ ማምታታት ነው።
1ኛ፦ በቁርኣንም በሐዲሥም የመውሊድ በዓል ፈፅሞ አልተወሳም። ቢወሳ ኖሮ ቀደምቶች በተፍሲራቸውና በሐዲሥ ድርሳኖቻቸው ይገልፁት ነበርና።
2ኛ፦ ከሰለፍ እስከ ኸለፍ አንድ እንኳ ኦፊሴል ባልሆነ መልኩ እንኳ ያከብሩ እንደነበር መረጃ የለም።
3ኛ፦ በቁርኣንና በሐዲሥ የሚገኝ፣ በሰለፎች የተፈፀመ ቢሆን ኖሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ ነው ብለው አይደመድሙም ነበር። አንዳቸውም በኦፊሴል ከመከበሩ በፊት በግል ወይም በማህበረሰብ ደረጃ ይከበር ነበር አላሉም።
=
የቴሌግራም ቻናል ፦

በልብ የመፍታት ኒያ ይዞ ማግባት
~
አንድ ሰው በውስጡ ከሆነ ጊዜ በኋላ ለመፍታት በቁርጥ አስቦ ማግባቱ ሴቷን ማታለል ስለሆነ ሐራም ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"من غشنا فليس منا"
"ያታለለን ከኛ አይደለም።" [ሙስሊም፡ 146]
እንዲህ አይነት ተግባር ዙልም (በደል) ነው። ሰው በእህቱ፣ በልጁ ላይ እንዲፈፀም የማይፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ ሊያደርግ አይገባም። ሴቷንም፣ ቤተሰቧንም የሚጎዳ፣ ማጭበርበር ላይ የተመሰረተ፣ የኢስላምን ገፅታ የሚያጠለሽ፣ ባለ .ጌዎች በኒካሕ ላይ እንዲጫወቱ በር የሚከፍት ፀያፍ ተግባር ነው።
ሙስሊም ማለት ለራሱ የሚወደውን ለሌሎች የሚወድ፣ ለራሱ የሚጠላውን ለሌሎች የሚጠላ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ዙል ቂዕዳህ 04/1444)
=
የቴሌግራም ቻናል፦

ቀለን ከተገኘን ማንም ይወስደናል
~
ማህበራዊ መገናኛዎች ብዙ ሸር እንዳላቸው ግልፅ ነው። ይህንን በማየት የሚያሳድሩትን ጉዳት መዘርዘሩ የረባ ፋይዳ የለውም። የሚሻለው የኸይሩ ተፅእኖ ጎልቶ እንዲገኝ ባጭር ታጥቆ መነሳት ነው። ይሄ ደግሞ በቀዳሚነት የዱዓት ኃላፊነት ነው። ፌስቡክ የጀመረ ሰሞን "አልሐምዱ ሊላሂ ለዚ ጀ0ለኒ ቢልፌስቡኪ ጃሂለን" ብለው ኹጥባ አድርገው ነበር አንድ ሸይኽ። ሰፊውን ህዝብ ከማሰብ አንፃር ካየነው ግን የተሻለው ከመራቅ ይልቅ መጋፈጥ እንደሆነ በተግባር ታይቷል።
"የእ .ብ ^ድ ሰፈር ነው" ስንለው የነበረው ቲክቶክ ለብዙዎች የሂዳያ ሰበብ ሆኗል። ዛሬ ላይ ቆመን ስናየው ትርምሱን ሰምተው ከራቁት ይልቅ በጊዜ ገብተው የሰሩበት ዱዓትቶች የተሻለ ውሳኔ እንደወሰኑ መረዳት ይቻላል። ዛሬ "ቲክቶክ አካውንት የለኝም" ማለት የሚያመፃድቅ ነገር አይደለም። እኔና አንተ ብንሸሸውም ብዙ አይነት የጥፋት አንጃዎች ገብተው እየተርመሰመሱበት ነው። ሌሎች ፕላትፎርሞች ላይ ካለው የበለጠ ህዝብ ደግሞ እዚያ ሰፈር አለ። ያንን ሰፊ ህዝብ ለመታደግ፣ በዚያ በኩል የሚሰነዘረውን አይነተ ብዙ ቀስት ለመመከት መፍትሄው መጋፈጥ ነው። ገብቶ መቅለጥ ሳይሆን ከልብ መጋፈጥ።
ከመሆኑም ጋር ገብቶ ከመመልከት ውጭ የኸይር ተሳትፎ የሌላቸው አካላት ባይገቡ የተሻለ ነው ፣ ራሳቸውን የሚያሸንፉ ከሆነ። ከገቡም ኮተቱ የሚቀንሰው ላይ ቢገደቡ ይሻላል። ለዚህ ደግሞ ቴሌግራም የተሻለ ነው። የፅሁፍም የድምፅም ትምህርቶች በበቂ ሁኔታ አሉ። ንትርኩ በእጅጉ የቀነሰ ነው።
ማህበራዊ ሚዲያ የንባብ ፀር ነው። ጊዜን እንደ እሳት ይበላል። በዚያ ላይ ሱስ ይሆናል። በዚህ የተነሳ ኪታቦችንና መፃህፍትን የሚያነብ ሰው በጣም ቀንሷል። ሌላው ቀርቶ ቁርኣን እንኳ በቅጡ እየቀራን አይደለም። ይህንን ሁኔታ አለመቀየር ያለ ጥርጥር መክሸፍ ነው። ቅንጭብጫቢ ቪዲዮዎችና ድምፆች ቅርፅ ያለውና የተደላደለ ግንዛቤ አያስጨብጡም። በተለይ ለዒልም ፍለጋ አገር አቋርጣችሁ የወጣችሁ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ነጋ ጠባ የምትርመጠመጡ ከሆነ ያለ ጥርጥር ባክናችኋል። መዳን ከፈለጋችሁ በጊዜ አካሄዳችሁን አስተካክሉ።
ሌሎች ዱዓቶችም ቢሆኑ ከሚሰጡት ይልቅ የሚሸምቱት እውቀት የበዛ ሊሆን ይገባል። ያለበለዚያ "ጨው ውሃ ሊቀዳ ሄዶ ሟምቶ ቀረ" እንደተባለው ይሆናል። ሌሎችን እንጠቅማለን ብለን በሌሎች ተፅዕኖ ተሸንፈን ቀልጠን እንዳንቀር። ስለዚህ ጥልቅ የሆነ የንባብ ባህልን ማዳበር ይገባል። ማንበብ ማንበብ አሁንም ማንበብ። ዘመኑ በያቅጣጫው ብዙ አይነት ብዥታ የሚነዛበት ዘመን ስለሆነ ጥልቅ ንባብ የሌለው ግልብ ሰው የሚቋቋመው አይደለም። ብዙ ዱዓት ላይ ደግሞ ይሄ ችግር ጎልቶ ይታያል። ግልብነት፣ ጥራዝ ነጠቅነት፣ ያሉበትን ሃገርና ጊዜ ተጨባጭ አለመረዳት፣ የህዝባችንን ነባራዊ ሁኔታ አለመገንዘብ፣ የጠላትን አሰላለፍና አደረጃጀት ፈፅሞ አለማስተዋል፣ ከዘመን ጋር የመጡ ፈተናዎችንና ተግዳሮቶችን ልክ አለማወቅ፣ ወዘተ .
ይህን ስል ግን ሁላችንም ዜና በዝርዝር አሳዳጅ፣ ሁላችንም የፖለቲካ ተንታኝ፣ ሁላችንም የሴራ ንደፈ ሃሳብ አነፍናፊ እንሁን እያልኩ አይደለም። ዝርዝሩ ብዙ ቢሆንም ባጭሩ ለኃላፊነታችን በሚመጥን መልኩ ራሳችንን እንገንባ ማለቴ ነው። አስተማሪ ከተበላሸ የህዝብ መከራ ይከብዳል።
يا رجال العلم يا ملح البلد
من يُصلِحُ الملحَ إذا الملحُ فسد ؟!
(ኢብኑ ሙነወር ፣ ሶፈር 19/ 1447)

ደግ ማሰብ ይሻላል
~
ሴትዮዋ ለአንዱ ጠበቃ እንዲህ ስትል ጠየቀችው፦
"አንድ ሰው አግብቼ ነበር። ህፃን ልጅ አለው። ህፃኑ ሲወለድ ጊዜ ነው እናቱን በሞት ያጣው። አሁን ላይ እኔ ነፍሰ ጡር ነኝ። ይሄ ህፃን ከልጄ ጋር በጋራ እንዲኖር አልፈልግም። እና አባት ልጁን ወላጆቻቸውን ባጡ ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ እንዲያስገባ የሚያስገድደው የህግ አንቀፅ ይኖራል ወይ?"
ጠበቃው በዚህን ጊዜ እንዲህ አላት፦
"ቆይ አትቸኩይ! ምን ይታወቃል አንቺም በወሊድ ሞተሽ አባት ሁለቱንም ልጆች የምታሳድግ ደግ ሴት ያገባ ይሆናል።... "
ከአንድ 0ረብኛ ፅሁፍ የተመለሰ።

ኢብኑ ተይሚያ ላይ የተሰነዘረ ሃሰተኛ ክስ
~
ኢብኑ በጡጣ (779 ሂ.) የታወቀ ሃገር አሳሽ ነው። በሙስሊሙ ዓለም ሰፊ የሆነ አሰሳ አድርጓል። የአሰሳው ዝርዝርም ሪሕለቱ ኢብኒ በጡጣህ በተሰኘ መድብል ተጠናቅሮ ተቀምጧል። በዚህ ስራ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ አንዱ የደማስቆ ጉብኝቱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ በታዋቂው የደማስቆ መስጂድ (መስጂደል ኡመዊ) ውስጥ "ኢብኑ ተይሚያ ሚንበር ላይ ሆኖ 'አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል፤ ልክ እንደዚህ አወራረዴ' ብሎ አንድ ደረጃ ሲወርድ ተመለከትኩት" የሚል ሰፍሯል። [ሪሕለቱ ኢብኒ በጡጣ፡ 110] ይህንን ውንጀላ የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች በሰፊው ሲቀባበሉት ማየት የተለመደ ነው። ዛሬም ድረስ የሚያነሱት የጥመት አንጃዎች አሉ። አለማው ኢብኑ ተይሚያ አላህን በፍጡር ያመሳስላል ለሚለው ሃሰተኛ ክሳቸው የአይን ምስክር ማቅረብ ነው።
ይሄ ውንጀላ ቅጥፈት እንደሆነ በአምስት መልኩ ማረጋገጥ ይቻላል።
* አንደኛ፦ ኢብኑ በጡጣ ደማስቆ የገባው ረመዳን 9/726 ሂ. እንደሆነ ራሱ መዝግቧል። ኢብኑ ተይሚያ ግን እሱ ደማስቆ ከመድረሱ ከወር በፊት ሸዕባን 6/726 ሂ. እስር ቤት እንደገቡ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲና ኢብኑ ረጀብ መዝግበዋል። ሞተው አስከሬናቸው እስከሚወጣ ድረስም ከወህኒ አልወጡም። ስለዚህ ሰውየው ከነጭራሹ አላያቸውም። "ውሸታም ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ያስፈልገዋል።"
* ሁለተኛ፦ በኢብኑ ተይሚያ ታሪክ ውስጥ የሚታወቀው ወንበር ይዘው የሚያስተምሩ እንደነበሩ እንጂ ሚንበር ላይ ወጥተው ኹጥባ የሚያደርጉ አልነበሩም።
* ሶስተኛ፦ በወቅቱ ኢብኑ ተይሚያ ላይ ብዙ ቅጥፈት የሚለጥፉ ጠላቶች እዚያው ደማስቆ ውስጥ ነበሩ። ግና አንዳቸውም ይህን ክስተት አልገለፁም። የሌለ ፈጥረው የሚወነጅሉ ሰዎች ተጨባጭ ነገር ቢያገኙ ፈፅሞ አያሳልፉም ነበር። እንኳን እንዲህ ዓይነት ከባድ ርእስ አግኝተው በፊቅሃዊ ጉዳይ ልዩነት ወህኒ የሚወረውሩ፣ በዱላ የሚደበድቡ የሚያስደበድቡ ናቸው።
* አራተኛ፦ በኢብኑ ተይሚያ ኪታቦች ውስጥ አንድም ማመሳሰል የለም። ፈጣሪን ከፍጡር የማመሳሰል አቋም ቢኖራቸው ኖሮ በኪታቦቻቸው ላይ በግልፅ ያሰፍሩት ነበር። በህዝብ ፊት ሚንበር ላይ ወጥቶ የሚናገር ሰው አቋሙን በኪታቦቹ ውስጥ ለማስፈር አይሸማቀቅም።
* አምስተኛ:- ይልቁንም በኪታቦቻቸው ውስጥ የምናገኘው ከዚህ ተቃራኒ ነው። አንድ ሁለት ንግግሮቻቸውን ልጥቀስ፦
وَنُزُولُهُ وَاسْتِوَاؤُهُ لَيْسَ كَنُزُولِنَا وَاسْتِوَائِنَا
“የአላህ መውረድና ከላይ መሆን እንደ እኛ መውረድና ከላይ መሆን አይደለም” ብለዋል። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 5/352]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
وصفات الله تعالى لا تماثل صفاتِ العباد، فإنَّ الله تعالى ليس كمثله شيء لا في ذاتـه، ولا صفـاتِه، ولا أفعالِه»
"የላቀው አላህ መገለጫዎች የባሪያዎች መገለጫዎች ጋር አይመሳሰሉም። የላቀው አላህ በዛቱም፣ በመገለጫዎቹም፣ በተግባራቱም ምንም የሚመስለው የለም።" [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 12/65]
ስለዚህ "ኢብኑ ተይሚያ ሚንበር ላይ ሆኖ 'አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል፤ ልክ እንደዚህ አወራረዴ' ብሏል" የሚለው ውንጀላ የለየለት የፈጠራ ክስ ነው ማለት ነው። በነገራችን ላይ አሽዐሪዮች የሐሰት ውንጀላ በመለጠፍ ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው። አቡል ወፋእ ኢብኑ ዐቂል እንዲህ ይላሉ፦ “አሻዒራዎች ከአህሉል ሐዲሥ ጋር በሚያደርጉት ሙግት ላይ ይዋሹባቸው ነበር።” [አረድ ዐለል አሻዒራህ፡ 91]
ባይሆን በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህን መገለጫዎች ማፅደቅ የጀህ -ሚያ ቡድን ተከታዮች ዘንድ ማመሳሰል ተብሎ ነው የሚጠራው። ታላቁ ሰለፍ አቡ ዙርዐ አራዚይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
“አራ .ቋቾች (المعطلة) አላህ በቁርኣኑ እንዲሁም በነብዩ ﷺ አንደበት እራሱን የገለፀባቸውን መገለጫዎች ያስተባብላሉ። ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለ አላህ መገለጫዎች የተላለፉ ትክክለኛ ዘገባዎችን ያስተባብላሉ። ቀድመው ካመኑት ጥመት ጋር በሚስማማ መልኩ የተገለበጡ እይታዎቻቸውን እየተጠቀሙ መልእክታቸውን ያዞራሉ። #ዘጋቢዎቹንም_በማመሳሰል_ይወነጅላሉ። ጌታቸውን እሱ እራሱን በቁርኣኑና በነብዩ ﷺ አንደበት በገለፀበት መልኩ ያለማመሳሰል የሚገልፁ ሰዎችን በማመሳሰል የሚወርፍ ሰው አራቋች ነው። እነዚያን ወደማመሳሰል በማስጠጋታቸው እነሱ አራቋቾች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።” [አልሑጃ ፊ በያኒል መሐጃ፡ 1/187]
ልብ በሉ! አቡ ዙርዐ ረሒመሁላህ ከኢብኑ ተይሚያ 464 አመት ቀድመው በ264 ሂጅራ ነው የሞቱት።
ሌላኛው ሰለፍ አቡ ሓቲም አራዚይም (277 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፦ “የጀህ.ሚያ ምልክት የሱና ሰዎችን #አመሳሳይ ብለው መጥራታቸው ነው።” [ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሓቢል ሐዲሥ፡ 304 - 305]
በዚህ መነሻ መሰረት በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁ ሙስሊሞችን በማመሳሰል ቢወነጅሉ ውንጀላቸው ቡድናዊ ጥላቻ የወለደው ፈጠራ እንጂ እውነታ እንደሌለው መረዳት ይቻላል ማለት ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 24/1445፣ (ሕዳር 28/2016))

ኺላፍ ማስረጃ አይደለም
~
መሠረታዊ የሸሪዐ ማስረጃዎች አራት ናቸው። እነሱም፡ -
1. የተከበረው ቁርኣን፣
2. የነብዩ ﷺ ሱና (ንግግሮቻቸው፣ ተግባሮቻቸው እና ይሁንታዎቻቸው)፣
3. ኢጅማዕ (በአንድ ዘመን ውስጥ ያሉ የዑለማዎች ወጥ ስምምነት) እና
4. ቂያስ (አንድን አዲስ ጉዳይ በሸሪዐ መሰረት ካለው ሌላ ተዛማጅ ጋር በማነፃፀር ብይን መስጠት) ናቸው።
የአንድ ጉዳይ ሑክሙ ከነዚህ ማስረጃዎች በአንዱ ከተረጋገጠ በቂ መረጃ ተገኝቷል። ለምሳሌ አንድ ነገር በሐዲሥ ሐራምነቱ ተጨባጭ መረጃ ከመጣበት "ኢጅማዕ የለበትምና ..." የሚል ክርክር ማንሳት ጤነኛ አይደለም። ኢጅማዕ ከሌለ ቁርኣንና ሐዲሥ ማስረጃ አይሆኑም የሚል ሂሳብ የለም። ምሳሌ ልጥቀስ፦
ሀ - መረጋጋት ወይም ጡመእኒናህ ሶላት ላይ የግድ መገኘት ያለበት ወሳኝ ክፍል እንደሆነ ግልፅ መረጃ መጥቶበታል። ያለ ጡመእኒናህ የሰገደን ሰው ነብዩ ﷺ "አልሰገድክም፣ ተመልሰህ ስገድ" ብለውታል። [ቡኻሪ ፡ 6667] [ሙስሊም ፡ 397] ግልፅ መረጃ ከመምጣቱ ጋር ኺላፍ ያስነሱ አካላት አሉ። ቢሆንም ግልፅ ሐዲሥ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የማንም የተለየ ሃሳብ ዋጋ የለውም።
ለ - በኹፍ ላይ ማበስ የሚፈቀድበት የጊዜ ርዝማኔ በሃገሩ ነዋሪ ለሆነ (ሙቂም) አንድ ቀን ከነ ሌሊቱ፣ ለመንገደኛ ደግሞ ሶስት ቀን ከነ ሌሊቶቹ እንደሆነ ግልፅ ሐዲሥ የመጣ ከመሆኑ ጋር የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቁ አካላት አሉ። ይሄ ኺላፍ ቁም ነገር ሆኖ አይጠቀስም፣ ይጣላል እንጂ።
ሐ - ፂምን መላጨት ሐራም እንደሆነ የአራቱም መዝሀብ አቋም ነው። ጉዳዩ በርካታ ግልፅ ሐዲሦች የመጡበት ከመሆኑ ጋር የተለየ ሃሳብ የሰነዘሩ ስላሉ የኺላፍ ርእስ ነው። ማስረጃው ፍጥጥ ብሎ እየታየ ኺላፍን ደሊል ማድረግ ግን የማያዛልቅ አካሄድ ነው።
መ - ለወንድ ወርቅ እና ሐር መልበስ ኺላፍ ያለበት ርእስ ነው። ጉዳዩ ግን ሐራም እንደሆነ ግልፅ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ከዚህ በኋላ ኺላፍን ደሊል አድርጎ መከራከር ይቻላል? ማንን ለመሸወድ?
ሌሎችም ብዙ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል። ጉዳዩ ነፍሲያ ካልገባበት በስተቀር መረጃ ለሚያከብር ሁሉ ሲበዛ ግልፅ ነው። ከመሆኑም ጋር አንዳንድ ሰዎች የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃ እየቀረበላቸው በጉዳዩ ላይ የተሳሳተ ሃሳብ ያንፀባረቁ አካላትን በማጣቀስ ኺላፍን ደሊል ሲያደርጉ ይታያሉ። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ "ይሄ ነገር የሚከለክል ሐዲሥ ስለመጣበት አይፈቀድም" ሲባሉ "ግን'ኮ እከሌ ፈቅደውታል" የሚሉ አሉ። የነዚህ ሰዎች ችግር ከተነሳው ነጠላ ነገር ሑክም የሚሻገር ስር የሰደደ በሽታ ነው። ችግሩ "የመንሀጀ ተለቂ" መዛባት ነው። ባጭሩ በአንድ ጉዳይ ላይ ኺላፍ ቢያጋጥመን ይሄ በጉዳዩ ላይ ይበልጥ ጥንቃቄ እንድናደርግ እንዲሁም ሚዛን የሚደፋውን ለይተን እንድንወስድ የሚያሳስብ እንጂ የሚያዘናጋ ሰበብ አይደለም።
ኺላፍ ማስረጃ እንደማይሆን ጥቂት የዓሊሞችን ንግግር ልጥቀስ፦
1. ኢብኑ ዐብዲል በር እንዲህ ብለዋል፦
الاختلاف ليس بحجة عند أحد علمته من فقهاء الأمة، إلا من لا بصر له، ولا معرفة عنده، ولا حجة في قوله
“እኔ ከማውቃቸው የኡማው የትኛውም ዓሊም ዘንድ የአስተያየት ልዩነት (ኢኽቲላፍ) በፍጹም ማስረጃ ሊሆን አይችልም። ይህን የሚሉ ደካማ እይታ ያላቸውና እውቀት የሌላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፤ የነሱም ንግግር ማስረጃ ሊሆን አይችልም።” [ጃሚዑ በያኒል ዒልሚ ወፈድሊህ፡ 2/922]
2. አልኸጣቢይ እንዲህ ብለዋል፦
ليس الاختلاف حجة، وبيان السنة حجة على المختلفين
“የአስተያየት ልዩነት ማስረጃ አይደለም። የሱና ግልጽ ሆኖ መምጣቱ ግን በተለያዩት ሰዎች ላይ ሁሉ ማስረጃ ነው።” [አዕላሙል ሐዲሥ፡ 3209]
3. አሻጢቢይ እንዲህ ብለዋል፦
صار الخلاف في المسائل معدودًا في حُجج الإباحة، فربما وقع الإفتاء في المسألة بالمنع، فيقال: لمَ تمنع والمسألة مختلف فيها؟ فيجعل الخلاف حجة في الجواز لمجرد كونها مختلفًا فيها، لا لدليل يدل على صحة مذهب الجواز، ولا لتقليد مَن هو أولى بالتقليد من القائل بالمنع، وهو عين الخطأ على الشريعة؛ حيث جعل ما ليس بمعتمد معتمدًا، وما ليس بحجة حجة
“በጉዳዮች ላይ የሚፈጠር የአስተያየት ልዩነት፣ የተፈቀደ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደ ማስረጃ መቁጠር ተለመደ። በአንድ ጉዳይ ላይ ‘ይህ የተከለከለ ነው’ የሚል ፈትዋ (ብይን) ሲሰጥ፣ ‘ለምን ትከለክላለህ? በጉዳዩ ላይ እኮ ልዩነት አለ!’ የሚል ምላሽ ይሰጣል። በዚህ መልኩ፣ ልዩነቱ መኖሩ ብቻ፣ የተፈቀደ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ሆኖ ይቆጠራል። የተፈቀደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይቀርብ ወይም ከከለከለው ሰው የበለጠ መከተል የሚገባውን ሰው ሳይከተሉ ይህን ማድረግ በሸሪ0 ላይ የተፈጠረ ትልቅ ስህተት ነው። ምክንያቱም መደገፊያ ያልሆነን መደገፊያ፣ ማስረጃ ያልሆነን ማስረጃ አድርገዋልና።” [አልሙዋፈቃት፡ 5/93]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 20/1447)

መኖርህ እዳ አይሁን!
ላንተ ነው! “ቀለም ለገባህ”!
~~
1. አንተ ልዩ አይደለህም
ሙስሊሙ፤ እንደ ማህበረሰብ ሰቅዘው የያዙት ብዙ አይይነት ችግሮች እንዳሉበት ግልፅ ነው። በኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ኢኮኖሚው የደቀቀ፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተናጋ፣ ፖለቲካዊ ስርኣቱና ሚናው የወረደ፣... ብዙ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። ችግሩን ‘ፍሬም’ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ላይ ሃሳቦች ሊለያዩ ቢችሉም ይህን እውነታ በመረዳት አንተ ብቸኛ አይደለህም። እራስህን ከማህበረሰቡ አንዱ እንጂ ልዩ አድርገህ አትሳል። ሙስሊሙ ኡማ ውስጥ የተማረው የቀለለ ከመሆኑ ጋር የተማርከውን የተማሩ፣ የምትረዳውን የሚረዱ ብዙ እንዳሉ አትዘንጋ። ይህንን እውነት ለነፍስህ ሹክ በላት። “ብርቅየ አይደለሽም” በላት። ያኔ እብጠቷ ይተነፍሳል። መንጠራራቷ ይቀንሳል።
2. የደዕዋው ዘርፍ የመፍትሄዎቻችን ሁሉ እናት ነው
ቀዳዳዎቻችን ብዙ ናቸው። በዚያው መጠን ዘርፈ ብዙ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። በሆነች ዘርፍ ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ ስለኖረችህ ለሌሎች በተለይም ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ እይታ አይንሸዋረር። ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ አክብሮት ለኢስላምህ ያለህ አክብሮት ነው። የደዕዋውን ዘርፍ ሳታከብር ለኢስላም አክብሮት ሊኖርህ አይቻልም። ኢስላም ያለ ደዕዋ ምንም ነው። አዎ በደዕዋው ዘርፍ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ። ግና “ችግሩ የሚፈታው በማነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አንተ ለዚህ ብቃቱ አለህ? የተማርከው ትምህርት ለዚህ የሚያበቃህ ነው? የእውነት አካደሚ ስለተማርክ ብቻ ያለውን መሰረታዊ ችግር የምታውቀው ይመስልሃል? እንዴት ሆኖ?!
3. አንጃዎችን መኮነን ከአንጃ ውጭ አያደርግህም
ብዙ የተማሩ ወንድሞች አንጃዎችን ስላወገዙ ብቻ ገለልተኛ የሚሆኑ ይመስላቸዋል። ነገሮችን በዚህ መጠን መረዳት ሲበዛ ግልብነት ነው። በቅድሚያ ገለልተኝነትህ ከሐቅም ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ከልብ መርምር። ጉዳዩን ቀርበው ሳይመረምሩ ሁሉንም በጭፍንና በጅምላ ማውገዝ በስንፍና ውስጥ ማድፈጥ እንጂ ልዩነትን መፀየፍ አይደለም። ይህንን ለማድረግ አቅምና ፍላጎቱ ከሌለህ ዝምታን ማን ያዘብህ? ምላስህንም ብእርህንም ከንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሰብስበህ በምትችለው ሙያ ወገንህን አገልግል። በአደብህ ተከበር። የማትችለውን ገብቼ አቦካለሁ ስትል፣ በምትችለው ዘርፍ ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋፅኦ ታመነምነዋለህ።
ልንገርህ ወዳጄ! የሆኑ የሚፋጩ አካላትን ስላየህ፣ የሚወረወሯቸውን ቃላት ስለሰማህ ብቻ ስለጉዳዩ ያለህን መረዳት በዚያ መጠን አቅልለህ አትመልከት። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ ነው አንዳንዶችን በመሰረታዊ የኢስላም ክፍል ላይ እንዲሳለቁ እየገፋቸው ያለው። ሳይረዱ እንደተረዱ ማሰብ።
እንዲያውም የአንዳንዶቹ ገለልተኝነት ከማስመሰል የዘለለ አይደለም። ክስተቶችን እየጠበቁ ለይተው ሲያጠቁ፣ ለይተው ደግሞ ሲያደንቁ ታገኛቸዋለህ። “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ የሚያሾፍ ሰው፣ “ተው” እና “ሂድ” እያለ በተውሒድ ላይ የሚሳለቅ ሰው በየትኛው ሞራሉ ነው ስለ ገለልተኝነት የሚያደነቁረን? ለኡማው መትረፉ ቀርቶ እራሱን ባዳነ!
4. ይልቅ ለኡማው ሸክም አትሁን!
እራስህን ብቻ ሁን! ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ማኔጅመንት ወይም ፖለቲካ ተምረህ የደዕዋ ስልጠና ካልሰጠሁ አትበል። በዱዓት ላይ መዘባነንህን አቁም። ፖለቲካ ብትደሰኩርም፣ ታሪክ ብትተርክም፣ መድረክ ብታደምቅም ዋጋ የሚኖረው ለተውሒድ በሚኖርህ ክብር ነው። አክብሮቱ ቀርቶ ሸክም የምትሆን ከሆነ የትኛውም ያንተ አበርክቶ ገለባ ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ በተውሒድ ላይ እየተሳለቅክ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በገለልተኝነት ስም ተውሒድንም ሺርክንም እኩል የምታወግዝ ከሆነ እውነቴን ነው የምልህ ከመኖርህ አለመኖርህ የሚሻል ለመባል እንኳን አትመጥንም። እንዲያውም ለሙስሊሙ ኡማ ከጠላት የከፋ እዳ ነህ።
5. ከ“ንቃትህ” ንቃ!
መንቃት ማለት እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት አይደለም። መንቃት ማለት በግምት የታጨቀ የሴራ ፖለቲካ መፈትፈት አይደለም። መንቃት ማለት የራስን እያናናቁ በፈረንጅ ፍልስፍና ላይ መራቀቅ አይደለም። መንቃት እራስን ማወቅ ነው። መንቃት የማህበረሰብን መሰረታዊ ችግር መለየት ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ የወገንህ የሙታን አምልኮ ላይ መነከር የማይቆጠቁጥህ ከሆነ እንኳን ለሰው ልትተርፍ ለራስህ አንቂ ያስፈልግሃል።
ደግሞም እወቅ! ይሄ ሌሎችን ማናናቅና እራስን መቆለል የጀርባ መንሴው ለዘመናዊ ትምህርት ያለህን የተንሸዋረረ እይታ ነው የሚያጋልጠው። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ህዝበ ሙስሊሙ ባለመማሩ የደረሰብት ውስብስብ ችግር እንዳለ የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በልክ አድርገው። የቀለም ትምህርት ከዲን ትምህርት፣ እንግሊዝኛ ከዐረብኛ፣ የነ ዑመር፣ የነ ሙዓዊያ ታሪክ፣ ከነ ሶቅራጠስ ሊነፃፀር አይችልም። በቅድሚያ እራስህን ከአስተሳሰብ ተፅእኖ ነፃ አውጣ! እነ ፍሮይድና ማስሎውን እያደነቅክ ዑለማዎችን የምትንቅ ከሆነ ብሽቅነትህን ብቻ ነው የምታሳየው። “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም” ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [አልኢቅቲዷእ፡ 217]
6. ሚናህን ለይ!
ዱዓት መሃል ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የምታየው ቢያምህ ሰውኛ ስሜት ነው። ሃሳብ ካለህ ዲኑ ያንተም ነውና እርምትና ሃሳብ መስጠት ያባት ነው። ችግር የሚመጣው ያልገባህን እያወራህ የእብድ ገላጋይ ስትሆን ነው። ወይ ዲንህን ተማር! ወይ ሃሳብህ የተመጠነ ይሁን። ባቅምህ ልክ ብቻ አውራ። ቀይ መስመር አትለፍ። ማኔጅመንት ተምረህ ቀዶ ጥገና ህክምና ካላደረግኩ ትላለህ እንዴ? ሳይኮሎጂ ላይ እድሜህን ፈጅተህ ተፍሲር ካላስተማርኩ ይባላል ወይ? ልክ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜህን የቀለም ትምህርት ላይ ስለፈጀህ ብቻ ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጠኸው እምነት ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ካልሆንኩ አይባልም። በቃ አቅምህንና ተሰጥኦህን ለይ! የግድ ስለ ሁሉም ማውራት አይጠበቅብህም።
7. ስለ ዲንህ ተማር
በቀለም ትምህርት ላይ መራቀቅ እንደምትሻው ሁሉ ለዲናዊ ትምህርትም ጊዜ ስጥ። ከምንም በላይ የዚያኛውን አለም ስንቅ ታዘጋጅበታለህ። በመተጓዳኝ የራስህን ጨምሮ የወገንህን ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ትለይበታለህ። በርግጠኝነት ነገሮችን የምትመለከትበት መነፅርም ይቀየራል።
በተለይም ደግሞ መሰረታዊ የእምነትህን ክፍል ተውሒድን ተማር። አካደሚ ስለተማክ ብቻ ከሺርክ የምትርቅ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ወላህ! በአለም ላይ ቁራጥራጭ እንጨቶችን፣ ያሸበረቁ ስዕሎችን፣ ላሞችን፣ አይጦችን፣ በሰው ልጅ ብልት አምሳል የተቀረፁ ሀውልቶችን የሚያመልኩ ህልቆ መሳፍርት ዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች አሉ። የተማሩት ትምህርት፣ የሚቀናጡበት ቴክኖሎጂ፣ የተቆናጠጡት ስልጣን፣ የሚያጋብሱት ሀብት ግኡዛንና እንስሳትን ከማምለክ አላወጣቸውም። ብልህ በሌሎች ይማራል። ሞኝ በራሱ ላይ በሚደርሰው ይማራል። አንተ ከሁለቱም ተራ ወጥተህ ሳይማሩ የተማሩ ከሚመስላቸው አትሁን።

ደግሞም ልንገርህ! አካደሚ እውቀት ቀርቶ ሌሎች የሸሪዐ ዘርፎች እንኳ ዋጋ ይኖራቸው ዘንድ ተውሒድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። ሸምሰዲን አሰፋሪኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ሌሎች የእውቀት ዘርፎች ለተውሒድ እውቀት ቅርንጫፎች ናቸው። ምክንያቱም እሱ ከአምልኮቶች ሁሉ የላቀው፣ ከትእዛዛት ሁሉ በላጩ እንዲሁም እያንዳንዱ አምልኮትና ትእዛዝ፣ ጤናማ ይሆን ዘንድ ብሎም ዋጋ ይኖረው ዘንድ መስፈርቱ ነውና። የክብርና የልቅና ባለቤት የሆነው (ጌታ ምንነት) የሚታወቅበትም ነውና።” [ለዋሚዑል አንዋሪል በሂያ፡ 1/57]
ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!!
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 19/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!!
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 19/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ብለዋል፦
"ወደ አላህ የምትቀርብበት መከራ፣ አላህን ከሚያስረሳህ ጸጋ ይበልጥ ላንተ የተሻለ ነው።"
[ጃሚዑል መሳኢል: 9/387]