IBNUMUNEWOR Telegram 7758
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ዐምር ብኑል ዓስ - ታላቁ ባለ ውለታችን
~
ስለ ታላቁ የኢስላም ባለ ውለታ ስለ ዐምር ብኑል ዓስ - ረዲየላሁ ዐንህ - እፅፋለሁ። የሺ0 ፈረስ በሆኑ የታሪክ አተላዎች ክብሩ እየተጎደፈ ስላለው ጀግናው የነብዩ ﷺ ሶሐቢይ እፅፋለሁ። የሶሐባ ጠላት የሆኑ እር-ጉም ሺዐዎችን እያወደሱ፣ በሶሐባ ክብር ላይ የሚረማመዱ ልባቸው በተሸይዩዕ መግል የተበከሉ ፍጥረቶችን እያየን ዝም ልንል አይገባም።

1 - ዐምር ብኑል ዓስ - ረዲየላሁ ዐንህ - ከነብዩ ﷺ ሶሐቦች ውስጥ አንዱ ናቸው። ሶሐባነት ተራ ማእረግ አይደለም። ይህን የሚረዳው የሶሐባን ደረጃ የሚያውቅ ነው። ዐምር ከመካ በድል መከፈት በፊት ነው የሰለሙት። ይህም የሆነው ከኻሊድ ብኑል ወሊድና ከዑሥማን ብኑ ጦልሐ ጋር ወደ ነብዩ ﷺ ዘንድ በመምጣት ነው። ዐምር አምነው ወደ መዲና ከተሰደዱት ሙሃጂሮች፣ በአላህ መንገድ ላይ ከተፋለሙት አማኞች ውስጥ ናቸው። እነዚህን አስመልክቶ አላህ ምን ብሏል?
{إِنَّ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِینَ هَاجَرُوا۟ وَجَـٰهَدُوا۟ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ یَرۡجُونَ رَحۡمَتَ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ}
"እነዚያ ያመኑትና እነዚያም (ከአገራቸው) የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ፡፡ አላህም እጅግ መሃሪ አዛኝ ነው።" [አልበቀራህ፡ 218]

2 - ዐምር ከነብዩ ﷺ እና ከኸሊፋዎቻቸው ዘንድ ታማኝ ነበሩ። ለዚያ ነበር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሲመርጧቸው የነበረው። የዛቱ ሰላሲል ዘመቻ ላይ በነብዩ ﷺ ሰንደቅ ተሰጥቷቸው አዋግተዋል። መካ የተከፈተች አመት የሁዘይል ጎሳ ወደሚያመልኩት የሱዋዕ ጣዖት ተልከው አፈራርሰው ተመልሰዋል። በዑመር፣ በዑሥማን እና በሙዓዊያ ተሹመው አገልግለዋል።

3 - ዐምር ለተለያዩ ሃገራት መከፈት፣ ለብዙ ህዝቦች ሂዳያ ሰበብ የሆነ ታላቅ ባለ ውለታ ናቸው። በነብያችን ﷺ የዖማንን ህዝብ ወደ ኢስላም እንዲጣሩ ተልከዋል። የሳቸውን ህልፈት ሲሰሙ ጊዜ ወደ መዲና ተመልሰዋል። [ጦበቃቱ ኢብኑ ሰዕድ፡ 7/493] በኸሊፋው አቡበክር ሻምን በመክፈት ሂደት ላይ ከተሾሙ አሚሮች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ በየርሙክ ዘመቻ ከሮማውያን ጋር ተፋልመዋል። በኺላፋው ዑመር ብኑል ኸጧብም ፊለስጢንና አካባቢዋ ላይ የተሾሙ ሲሆን ኋላም ተሻግረው ግብፅን እንዲያቀኑ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ግብፅን በድል የከፈቱ ጀግና ናቸው። እስኪ በሺዐና በፈረሶቻቸው የተከፈተ አንድ ስንዝር መሬት ጥቀሱ።

4 - ዐምር አርባ አካባቢ ሐዲሦችን ከነብዩ ﷺ ያስተላለፉልን ታላቅ ባለ ውለታችን ናቸው።

5 - ዐምር ብኑል ዓስ "ሰዎች ሰለሙ። ዐምር ብኑል ዓስ ግን አመነ" ብለው ነብዩ ﷺ የመሰከሩላቸው ናቸው። [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 3020] በተጨማሪም "የአልዓስ ልጆች ዓምር እና ሂሻም ሙእሚኖች ናቸው" ብለው መስክረውላቸዋል። [ሙስነድ አሕመድ፡ 8042]

6 - ዐምር ብኑል ዓስ ለነብዩ ﷺ ጥልቅ የሆነ ውዴታ ነበራቸው። ዐምር እንዲህ ይላሉ፦ "እኔ ዘንድ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ በላይ የተወደደ፣ አይኔ ላይ የተከበረ የለም። እሳቸውን ከማክበሬ የተነሳ በሙሉ አይኔ አይቻቸው ስለማላውቅ መልካቸውን ልግለፅ ብል ልገልፃቸው አልችልም።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 121] ታያለህ አይደል ከነብዩ ጋር ኖረው መልካቸውን መግለፅ አልችልም ሲሉ? አክብሮታቸው በዚህ ልክ ነበር! ሱብሓነላህ!!

ፍፃሜ!

ህመማቸው ሲጠናባቸው ጊዜ ጠባቂያቸውን ታላላቅ ጓዶችህን አስገባልኝ አሉት። ሲገቡ ጊዜ ተመለከቷቸው።
* "ያው እንግዲህ እዚህ ሁኔታ ላይ ደርሻለሁ። ያለሁበትን (ፈተና) መልሱልኝ" አሏቸው።
- "ያንተ አምሳያ ይህን ይላል ወይ አለቃ? ይሄ'ኮ ማንም የማይመልሰው የአላህ ውሳኔ ነው!" አሉ።
* "በሚገባ አውቃለሁ። እንድትገሰፁ ስለወደድኩ ነው ይህን ማለቴ" ካሉ በኋላ ደጋግመው "ላ ኢላሀ ኢለላህ!" እያሉ ሞቱ። [ታሪኹ ዲመሽቅ፣ ኢብኑ ዐሳኪር፡ 46/198]

ሞታቸው በ43 ዓመተ ሂጅራ የዒደል ፊጥር ሌሊት ነበር። ለዒድ ሶላት የታደመው ህዝብ ሶላተል ጀናዛ ሰግዶባቸው በግብፅ ካይሮ ከተማ አልሙቀጦም አካባቢ ተቀብረዋል። ሲሞቱ 90 አመታቸው ነበር። ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዷህ።

ከባድ ቅጥፈት በባለውለታችን ላይ!
-
የዑሥማንን በግፈኞች መገደል ተከትሎ በኸሊፋው ዐሊይ እና በሙዓዊያ (ረዲየላሁ ዐንሁም) መካከል እስከ ደም መፋሰስ የደረሰ አለመግባባት እንደተከሰተ ይታወቃል። በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሚጠቀሰው የዐምር ብኑል ዓስ እና የአቡ ሙሳ አልአሽዐሪ የሽምግልና ሂደት ነው።

ከዚህ ሽምግልና ጋር በተያያዘ አንድ እውነተኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ዐምር ብኑል ዓስን በሴራ እና ቃል በማፍረስ የሚወነጅል ትርክት አለ። ይሄ ሃሰተኛ ውንጀላ በሰፊው በመሰራጨቱ የተነሳ ብዙ ሙስሊሞች ለዐምር ብኑል ዓስ ጥላቻ አርግዘዋል። ይሄ መስተካከል ያለበት ፀያፍ ጥፋት ነው። ታሪኩ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነው:-

ከሲፊን ጦርነት በኋላ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይን፣ ሙዓዊያ ደግሞ ዐምር ብኑል ዓስን ለሽምግልና ይመርጣሉ። ሁለቱ ሽማግሌዎችም ዐሊይንም ሙዓዊያንም ከሃላፊነታቸው ሊያወርዱ ይስማማሉ። ከዚያም አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ ሚንበር ላይ በመውጣት "እኔ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ" ብለው ቀለበታቸውን ያወልቃሉ። ዐምር ብኑል ዓስ በተራቸው ተነሱና "እኔም እንዲሁ አቡ ሙሳ እንዳደረገውና ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ። ሙዓዊያን ደግሞ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማፀናው አፀናዋለሁ" አሉ። ይህንን ተከትሎ ጫጫታ በዛ። አቡ ሙሳ ተቆጥተው ወጡ። ወደ ዐሊይ ዘንድ ወደ ኩፋ ሳይሆን ወደ መካ ሄዱ። ዐምር ብኑል ዓስ ደግሞ ወደ ሻም ሙዓዊያ ዘንድ ሄዱ።
=
ይሄ ታሪክ:-

1ኛ፦ ከማስረጃ የተራቆተ ወፍ ዘራሽ የፈጠራ ወሬ (መውዱዕ) ነው። በዘገባው ውስጥ አቡ ሚኽነፍ የተሰኘ ውሸታም ሰው አለበት። ያለ ተጨባጭ መረጃ ደግሞ ሶሐባን ቀርቶ ተራ ሙስሊምም አይወነጀልም። ሐራም ነው። ለተጨማሪ መረጃ እነዚህን ምንጮች ተመልከቱ፦ [አኑስሑ ወልኢርሻድ ኢላ ተርኪ ቂሶሲን ላ የሲሑ ለሃ ኢስናድ: 61] [አልመሽሁር ሚነ ዶዒፍ ወማ ዩግኒ ዐንሃ፡ 409]

2ኛ፦ ዐሊይ ኸሊፋ ናቸው። ኸሊፋ ደግሞ እንዲህ እንደዋዛ በአንድና በሁለት ሰው ፍላጎት ከስልጣኑ አይነሳም። ኺላፋ እንዲህ ቀልድ ነው ወይ? ያ ሁሉ ቃል ኪዳን የተገባለት ሰው በሁለት ሰዎች ውሳኔ የሚወርድበት አሰራር የለም።

3ኛ፦ ደግሞም ሙዓዊያ ረዲየላሁ ዐንሁ በጊዜው ፈፅሞ "ኸሊፋ ነኝ" አላሉም። ከዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ጋር ያጣላቸውም ኸሊፋነቱ ይገባኛል ብለው አይደለም። ይልቁንም ሙዓዊያ የዑሥማን ገዳዮች ተላልፈው ካልተሰጧቸው ለ0ሊይ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀራሉ። ዐሊይ ደግሞ ሙዓዊያን ከሻም አስተዳዳሪነታቸው ሊያነሷቸው ይፈልጋሉ። መረጃ ልጥቀስ።

tgoop.com/IbnuMunewor/7758
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7758

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Administrators Add up to 50 administrators To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon. Commenting about the court's concerns about the spread of false information related to the elections, Minister Fachin noted Brazil is "facing circumstances that could put Brazil's democracy at risk." During the meeting, the information technology secretary at the TSE, Julio Valente, put forward a list of requests the court believes will disinformation. But a Telegram statement also said: "Any requests related to political censorship or limiting human rights such as the rights to free speech or assembly are not and will not be considered."
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American