tgoop.com/IbnuMunewor/7753
Create:
Last Update:
Last Update:
ሶላት የዲን ምሰሶ፣ ሁለተኛዋ የኢስላም ማእዘን ነች። ሶላት የዱንያ የኣኺራ ኑር ነች። ሶላት በዱንያ የአይን ማረፊያ፣ በኣኺራ ከመከራ መትረፊያ ነች።
ከዚች ውድ ዒባዳ ከሶላት አንፃር ራሳችንን ብቻ ሳይሆን ልጆቻችንን መከታተል ይገባል። ልጆችን በሶላት ጉዳይ ፈፅሞ ችላ ማለት አይገባም። እንደ እድሜያቸው በሶላት ማዘዝ፣ መቆጣት፣ መቅጣት ያስፈልጋል። ካደጉበት፣ ከኖሩበት ይቀላቸዋል። ካልሆነ ግን ውጤቱ ተቃራኒው ነው የሚሆነው። ይሄ ከመሆኑ በፊት በጊዜ መከታተልና ማስለመድ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7753