Telegram Web
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “እናትነት እና የአእምሮ ጤና” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን ዶ/ር ፌቤን ፋንጮ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/mZ98Rv8ctr1Tin819

የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ https://www.tgoop.com/mhaddisababa

The monthly Mental Health Addis’ event has come and it will be held on May 11, 2024 at Adore Addis Hotel (near Atlas) in the afternoon at 10:00 local time.

This time the topic is “Motherhood and Mental Health”

Our guest speaker is Dr Feben Fancho.

To attend please register by filling this Google form:-
https://forms.gle/mZ98Rv8ctr1Tin819

To get a reminder and get direction please join our Telegram Channel: https://www.tgoop.com/mhaddisababa

#mentalhealth #AdoreAddis
#mentalhealthawareness
#talkmentalhealth
#mentalhealthmatters
ሰለስተ
***
ኣብ ተመኩሮ ወዲ ሰብ ሰለስተ መሰረታዊ ድልየታት ንጉዕዞ ህይወትና ይቐርፅዎ። ሓይሊ(will to Power) ዕግበትን (gratification) ትርጉምን (meaning ) እዮም። ስልጣን ምቁፅፃር ጥራይ ዘይኮነስ ብድሆታት ንምስጋርን ንምፅዋርን ወሳኒ ተራ ይፃወት እዩ። ዕግበት ኪኖ ደስታ ዝኸይድ ኮይኑ ምድላይ ክብርን ፍትሕን ዘጠቓልል እዩ።

ትርጉም (meaning) ድማ ካብ ምሕሳብ ጥራይ ርሒቑ ኣብቲ ዝፀልመተ ህሞታትና እውን እንተኾነ ዕላማን ፅንዓትን ንምርካብ ዝግበር ዓሚቝ ምድላይ እዩ። እዞም ባእታታት እዚኣቶም ኣብቲ ዝተሓላለኸ ኩነታት ህይወትና ተሓዋዊሶም ንተመኩሮታትና ይቐርፁን ንውሳነታትና ይፀልዉን እዮም።

(Will to power ) ስልጣን ብቕንዕናን ርህራሀን ምስ እንጥቀመሉ ኣንፃር በደል ደው ክንብልን ንመሰላት ካልኦት ክንጣበቕን ሓይሊ ይህበና ንኣወንታዊ ለውጢ ዝኸውን ሓይሊ እውን ይኸውን። ኣብ ዝተሓላለኸ ህላወታት ክንጓዓዝ ከለና ሓቀኛ ምልኣት ኣብ ምድላይ ስልጣን፣ ዕግበት ወይ ትርጉም ጥራይ ዘይኮነስ ኣብ ስኒት ውህደት ሰለስቲኡ ምዃኑ ምርዳእ ይደሊ። ፅንዓት ከነማዕብል ሓቀኛ ምትእስሳር ክንደሊ ንፅባቐ ናይቲ ብዕላማን ዕላማን ዝተነብረ ህይወት ክነዋሃህድን ክንሓቁፍን ንፅዕር።

ዋላ እኳ እዞም ሰለስተ ነገራት ብጣዕሚ ሰፈሕቲ ዛዕባታት እንተኾኑ ብሓፂሩ እየ ክገልፆ ፈቲነ።

ዳንኤል ገብረህይወት
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት, MSc
ንዴትን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
======================
ተናዶ የማያውቅ ሰው አሳዩኝ እና አምጣ የወለደች በቅሎ አሳያችኀለሁ፡፡ ሁላችንም የሆነ አጋጣሚ ላይ እንናደዳለን፡፡ ልዩነቱ ንዴትን የምንቆጣጠርበት መጠን ነው፡፡ ተናደን የምንወስናቸው ውሳኔዎች ጊዜ ሲያልፍ ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡ ዋጋው፦ ጊዜ ማባከን፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው መቆራረጥ፣ መታሰር...ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡

ንዴትን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች እነሆ፦

1. መናደዳችንን መቀበል-

እንዳልተናደድን ለማስመሰል መሞከር ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የሚያናድደንን ሁኔታ እንዴት እንደምንለውጥ እንዳናስብ ከማድረግ አልፎ ለአእምሮ ጤንነታችን፣ ለጨጓራችን እንዲሁም ለደም ግፊታችን ጥሩ አይደለም፡፡ መናደዳችንን ስንቀበል ራሳችንን ማረጋጋት እንችላለን፡፡ ( "የማናውቀውንና የማንቀበለውን ችግር መለወጥ አንችልም፡፡" የሚለው አባባል በግልባጩም ትክክል ነው፡፡)

2. ዘርዝሮ መመልከት-

መናደዳችንን ከተቀበልን በኃላ ለምን እንደተናደድን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ቢቻል የተፈጠረውን ነገር ብንፅፈው የበለጠ ግልፅ ይሆናል፡፡ መፍትሄውም እንደዚያው፡፡ ስንዘረዝረው አንዳንዶቹን ችላ ብለን ማለፍ ያለብን ሌሎቹ ደግሞ ከመርሀችን ጋር ስለሚጋጩ ለመለወጥ የሆነ ነገር ማድረግ ያለብን እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ ሁለቱን እንዳናቀያይር በዝርዝር ማየቱ ጥሩ ነው፡፡ ( ታክሲ ግፊያ ላይ አንድ ሰው ቸኩሎ ረግጦን ታክሲ ውስጥ ሲገባና ሞባይላችንን ለመውሰድ ኪሳችን ውስጥ ሲገባ የምናደርጋቸው ነገሮች ይለያያሉ፡፡)

3. እንቅስቃሴ ማድረግ-

ንዴት አእምሯዊ ስሜት የሆነውን ያክል አካላዊ መገለጫዎችም አሉት፡፡ እጃችን ይጨበጣል፤ ሰውነታችን ይወጣጠራል፡፡ ይህንን አካላዊ ውጥረት ለማርገብ አካላዊ እንቅስቃሴ ፍቱን ነው፡፡ ቢቻል ቢቻል ሣኮ መደብደብ፤ ካልሆነ የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ፤ ቢያንስ ግን ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ ጥሩ ነው፡፡

4. የሚያናድዱን ነገሮች መመዝገብ-

የሚያናድዱንን ነገሮች ብንመዘግብና ብናሰላስላቸው የሆነ አይነት ድግግሞሽ እየታየን ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ ራሳችንን የበለጠ እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ ራሳችንን ስናውቅ የምንሄድበትን መንገድ እና እንዴት እንደምንደርስ ግልፅ ስለሚሆንልን የተረጋጋና ንዴትን መቆጣጠር የሚችል ሰው እንሆናለን፡፡

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
ዶ/ር ለበዓል አልፈታም ???  ሲያገባ ይተወዋል !!!
====================================
ብዙ ጊዜ  ወደ ህክምና  እሚመጡበት  ምክንያት ታስረው ወይም በፖሊስ ታጅበው ስለሆነ ይሁን ፤ ከነሱ ፍቃድ ውጪ ህክምና  እየተደረገላቸው ስላለ፤ አሊያም እውን የመታሰር ስሜት እየተሰማቸው ብቻ እኔ ሙሉ ለሙሉ ባልተረዳሁት ግን እነሱ በሚሰማቸው ስሜት ምክንያት  አንድ አንድ ታካሚዎች " ዶ/ር መቼ ነው እምንወጣው/ህክምና እምጨርሰው ? ሳይሆን  "ዶ/ር መቼ ነው እምፈታው " ነው እሚሉኝ ፡፡ ስራ ከመጀመሬ በፊት ጊቢው በመቶዎች  እሚቆጠሩ ታካሚዎች ስላሉት  ጊቢውን ዞር ዞር እያሉክ ታካሚዎችን ስመለከት አንድ ታካሚ "ዶ/ር ለበአል አልፈታም " እያለ  አብሮኝ  ይራመድ  ጀመር ፡፡ቢሮ ጋር እንዲጠብቀኝ  ነግሬው ቅኝቴን ቀጠልኩ …..
ወደ ታካሚ ምርመራ እምናደርግበት  ክፍል ስመለስ ዛሬ ህክምናቸውን ጨርሰው ወደ ቤት እሚሄዱ ታካሚዎች በተርታ ተደርድረው  አይናቸውን ቁልጭ ቁልጭ እያደረጉ የእኔን መምጣት ይጠባበቃሉ፡፡ይህ ጉጉታቸው  ያን የድሮውን ጊዜ ትዝ አስባለኝ፡፡ያን የወረቀት ዘመን !!   ድሮ ድሮ የፋይናል ፈተና ውጤት ለማየት  የነበረ ጉጉት …. የኢንተራነስ ውጤት ተለጥፎ የማየት ጉጉት ….. የኳሊ ፈተና  ውጤት የማየት ጉጉት   
የመጀመሪያው ታካሚ አናግሬ ስጨርስ  ከቤተሰብ ጋር ስለታሰበው  ነገር  ለመነጋገር  እንዲገቡ የአ/ቶ እከሌ ቤተሰብ ብለን ጠርተን አስገባን፡፡ ታካሚው ለመጀመሪያ ጊዜ የተኝቶ ህክምና በመድረጉ ከፍተኛ ለውጥ እዳዩ  በውጤቱም ደስተኛ እንደሆኑ  ነገረውን ሲስተሮቹንም እንድሁም እኛንም  አመስገኑ ፡፡ ወደ ፊት ክትትል እንደሚያስፈልግ ፤ መዳሀኒቱ  ከሀኪም ትእዛዝ ውጪ እንዳይቆም እንዲሁም የእርሻውን ስራ መቀጠል እንደሚችል … እናም ሌሎች ነገሮችን እንዳወራን የእነሱን ሀሳብ እና ጥያቄ  እየመለስኩ እናቱ በመሃል አቋረጠችኝ እና "የልጄ ችግር ሚስት ነው አሁን እንደወጣ አድረዋለው ፡፡ ጥሩ ልጅ አዘጋጅተናል ቤቱ ሁሉ ሙሉ ነው …….ሲያገባ ይተወዋል" ፡፡  አስቡት ለአነድ ወር ከአስር ቀን ከቤተሰብ  ተለይቶ የነበረን አንድ ሰው ልክ እንደወታጣ ትዳር እሚባል  ትልቅ ሃላፊነት ላይ መጣል  ?? ከቤተሰቡ አንዲሁም ከታካሚው ጋር በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን የትዳር ጉዳይ አሁን ባለበት ሁኔታ አንገብጋቢ  እነዳልሆነ ተስማማን ለቀጣይ ቀጠሮ ቀን ወስደው ተለያየን፡፡ ትዳር መያዝ (ተቃራኒ ጾታ ግንኙነት መጀመር ) የአእምሮ ህመምን ይፈውሳል የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በምስራቁ ማህበረሰብ አንዲሁም ህንድ አና መሰል አገሮች ላይ ይታያል፡፡
  ይህ አጋጣሚ ማህበረሰብ ውስጥ ስለ አዕምሮ ህመም  በጉልህ  ተንሰራፍተው ያሉ እንደ አውነት ተደርገው እሚወሰዱ የተሳሳቱ ግንዘቤዎች አንድ ሁለት አንድላቹ አስገደደኝ ፡፡
  የአዕምሮ ህመም ያለበትን ሰው ማወቅ/መለየት  ቀላል ነው ፡፡ አንግዲያውስ  ዙሪያህ ካሉ አራት ሰዎች አንዱ የአዕምሮ ህመም ተጠቂ እንደሆነ አገራችን ላይ ያለ ጥናት ያሳያል ፡፡ ማነው ከአራታቹ  የአዕምሮ ህመም ተጠቂ አንተ ትሆን  ወይስ  መለየት ከበደህ ?
  የአእምሮ ህመም ጠንካራ አማኝ ካለመሆን እሚከሰት ነው ፡፡  ታዲያ ለምን ሼኮችን ፣ ቄሶች እንዲሁም የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች  የህመሙ ተጠቂ ሆኑ  ….ወይስ  እነሱ ታመው አልገጠሙህም እንግዲውስ  እነሱም በዚህ ተጠቅተው ህክምና ያደርጋሉ፡፡
  የአዕምሮ ህመም  ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ለማህበረሰብ ስጋት ናቸው ፤ ማህበረሰብ ላይ  ከፍተኛ አካለዊ እንዲሁም ቃላዊ ጥቃቶችን ያደርሳሉ፡፡ ምንም እንኳን  አንዳነድ ያልታከሙ ከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ የገጠማቸው ሰዎች  በህመሙ ማገረሽት ምክንያት ቁጡነት ቢታይቸውም   እንድ አጠቃላይ ሲጣይ ህሙማኑ በአካለዊ እና ፆታዊ ጥቃቶች ተጎጂ እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 
  የአዕምሮ ህሙማን ውጤታማ ሰራተኞች አይደሉም /የቤተሰብ ሸክሞች ናቸው፡፡ በአግባቡ ህክምና ያገኙ ሕሙማን እሚገባውን ሀላፊነት ሊወጡ እሚችሉ እንዲሁም አንዳነድ ሕሙማን ከማሕበረሱብ ላቅ ባለ ሁኔታ ችሎታቸውን ሲያሳዩ እናያለን ፡፡ ከአገር ውስጥ እነ ደራሲ አውግቼው ተረፈ እንዲሁም ከውጪ እነ ጆን ናሽ(ኖቤል ፕራዝ የሸነፈ ታዋቂ ኢኮኖሚሰት) እነ ጂም ኬሪ   እነ ፊዮዶር  ዶስቶቭሰኪ መጥቀስ ይቻላል፡፡ታዋቂው የባርሴሎና የማሀል ሜዳ ማሽን አነድሬ ኢኔሰታ በድባቴ ህመም ይሰቃ እንደነበር ያውቃሉ ??
  አዕምሮ ታማሚ ይሻለዋል እንጂ አይድንም ፡፡ የስኳር ፣የግፊት ታማሚ ወይም የኤችአይቪ ተጠቂ ይድናል ……. ታዲያ እነሱን ለምን ማህበረሰቡ ተወ፡፡   የአእምሮ ህመሞችን  አንድ አይነታቸው ቢለያዩም ሶሲው የአእምሮ ህመም ህክምናቸውን ከጨረሱ ብኋላ  ሙሉ ለሙሉ ከህመማቸው ሲድኑ አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች ግን ልክ እንደ ስኳር እና ግፊት ዘላቂያው ህክምና ተደርጎ ውጤታማ ህይወትን ይቀጥላሉ፡፡
  እነ እከሌ አምልኮ ስላለባቸው ነው መገበር፤  ስላቆሙ  ወደ ልጆቻቸው  ዛሩ የወረደው፡፡   አንዳንድ የአዕምሮ ህመሞች በዘር ሀረግ የመተላለፍ እድላቸው ከፍ ስለሚል  እርስ በእርስ ጋብቻ የሚዘወተርበት ቤሄሮች እንዲሁም የአንድ ቤተሰብ ሀረግ ላይ በዝቶ ታይ ይችላል፡፡

የአዕምሮ ህክምናን ለእርሶም ሆነ ለቤተሰቦ እምትሹ የድሬደዋ  እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በስልክ ቁጥር በ0254119722/0251130996/98  በመደወል ቀጠሮ በማስያዝ በኢፍቱ፣ በዴልት ሆስፒታል  እና በሴንተራል ሲቲ ሆስፒታል   እንዲሁም በሣቢያን ጠቅላላ ሆስታፒል ቢመጡ ግልጋሎቱን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር ያገኛሉ::
ድሬደዋ, ኢትዮጲያ
ዶ/ር ቶፊቅ አብደላ(የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)  
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ሠላም ዶር ዮኒ! መጽሐፉን ጨርሸዉ በስተመጨረሻ ያለኝን ሃሳብ ላካፍል ብዬ ነው

ቀላሉን ነገር አታካብድ መጽሐፍ ላይ የግሌ ዕይታ

ቀላሉን ነገር አካበድክ አትበሉኝና😁…ይህ መጽሐፍ አጠገባችን ያሉትን ትናንሽ የሚመስሉ ግን ሲተገበሩ ትላልቅ አዎንታዊ ዉጤቶችን የሚያመጡ መርሆችን በማወቅ እንዴት ህይወተችንን ቀለል አድርገን በደስታ መሙላት፤ ስኬታማ እና ዘና ያለ ሠላማዊ ህይወት መኖር እንደምንችል የሚያሳየን ተግባር ተኮር መጽሐፍ ሆኖ አገኝቸዋለሁ። ሃሳቦቹም አስተማሪ ምሳሌዎች እና ታሪኮችን ባካተቱ እና በጣም በቀላል አቀራረብ በቀረቡ ከ1 እስከ 100 በተዘረዘሩ መርሆች ዉስጥ የተካተቱ ናቸዉ።

አሁን ባለንበት ዓለም ቀላል የመረጃ ፍሰት መኖሩ ብቻዉን የምናየዉን፣ የምንሰማዉን፣ የሚያስደስተንን እና የሚያስከፋን-የሚያበግነንን ነገር አብዝቶታል። ብቻ በዚህም ሆነ በአጠቃላይ ህይወታችን የሚያስፈልገንን እንዴት መለየት እንደምንችል እና በምንፈልገዉ ነገር ላይ ብቻ እንዴት ማተኮር እንደምንችል እና ያለዉን ፋይዳ ይህ መጽሐፍ ያስረዳናል። ጥቂት ሃሳቦችን ለማየት ያክል ምስጋናና ትዕግስት ያላቸዉን ሀይል እና ጠቀሜታ ያሳያል ፤ ምርጫችንን እንዴት ለአዎንታዊ ፋይዳ እንደምንጠቀም ያስረዳናል ፤ የጊዜ አረዳድን እና አጠቃቀምን ያብራራል ፤ እራስን እንዴት እና ለምን መቀበል እንዳለብን በምክንያት ያስረዳል ፤ የጊዜያዊ ስሜት ዉጣ ወረድን እንደምንችል ያስተምረናል ወዘተ። በአጭሩ ሆደ ሰፊነት ለዘላቂ ዉስጣዊ ሠላም የሚል ይመስላል።

በሁሉም ረገድ መጽሐፉ የዘነጋነዉን እያስተወሰን ፤ ዋጋ የነሳናቸዉን ጉዳዮች ዋጋ እያሳየን ፤ ያላወቅነዉን እያስተማረን በሆደ ሰፊነት ወደ ደስተኛ፣ ቅን፣ የዋህ እና ሠላማዊ ማንነት የሚመራ ድንቅ መጽሐፍ ሆኖ አገኝቸዋለሁ። ቀላሉን የማናካብድ ከባዱን ነገር የማያንኳስስ በሳል ማንነት እንዲኖረን ያለን ደግሞ ዋጋዉን እንድንረዳ የሚያደርግ አስተማሪ የአሁኑ እና የመጪዉ ትዉልድ መጽሐፍ ይመስለኛል። ተደጋግሞ ሊነበብ የሚገባ ነዉ። የተጠቀሱ ልምምዶች ደግሞ ተደጋግሞ ቢተገበሩ ትልቁን ዉጤት የሚያስገኙ ናቸዉ።

ስለሁሉም ዶር ዮናስ ላቀዉ ከምትሰራቸዉ ግሩም ስራዎች ጎን ለጎን ይህን ድንቅ መጽሐፍ ተርጉመህ ስላቀረብክልን ከልብ አመሰግናለሁ።

ምስጋናዉ ገ/ሚካኤል
ስምዒታዊ ንቕሓት ወይ ግንዛበ ንሰብ ሞያ ሳይኮሎጂ
(ስነ- ልቦና)
Emotional Awareness For Psychologists

ስምዒታዊ ንቕሓት ንሰብ ሞያ ስነ-ልቦና ቁልፊ ኣካል ሞያዊ ምዕባለ እዩ። ናይ ገዛእ ርእስና ስምዒታት ምርዳእን ምምሕዳርን ብብዙሕ ምኽንያታት ኣዝዩ ኣገዳሲ እዩ። ንኣብነት እስከ እዞም ስዒቦም ዘለው ነጥብታት ንርኣዮም።

1. ምክልኻል ሕዱር ፀቕጢ:-
ስምዒታዊ ንቕሓት ምልክታት ፀቕጥን ድኻምን ብኣግኡ ከነለሊ ስለዘኽእለና ህይወትና ብዝሓሽ ንምምሕዳር ኣድላዪ ስጉምትታት ክንወስድ የኽእለና። እዚ ርእሰ-ሓልዮት እዚ ጥዕናና ንምዕቃብን ንዓማዊልና ብኣድማዒ መንገዲ ናይ ምድጋፍን ዓቕምና ንምቕፃልን ኣገዳሲ እዩ።

2. ዝተዓፃፀፈ ፍወሳዊ ዝምድናታት:-
ምስ ስምዒታትና ክንሰማማዕ ከለና ዝዓበየ ርህራሄን ምርድዳእን ከነርኢ ንኽእል። እዚ ድማ ምስ ዓማዊል (Client, Patients) ምትእምማንን ርክብን ንምህናፅ ይሕግዝ፣ ንዕብየቶምን ንሕውየቶምን ምቹ ዝኾነ ውሑስን ደጋፍን ሃዋህው ይፈጥር።

3. ዕላማዊ ውሳነ:-
ንቕሓት ናይ ገዛእ ርእስና ስምዒታዊ ምላሽ ንውሳነና ክፅልዉ ዝኽእሉ ወገናውነት ንምልላይን ንምቁፅፃርን ይሕግዘና። እዚ ድማ ዕላማ ዘለዎ ኮይኑ ከም እንቕፅልን ዝለዓለ ደረጃ ክንክን ከም እንህብን ንዓማዊልና ዝጠቅም ውሳነታት ከም እንወስድን የረጋግፅ።

4. ውልቃውን ሞያውን ዕብየት:-
ስምዒታዊ ንቕሓት ምምዕባል ቀፃሊ መስርሕ ኮይኑ ቀፃሊ ርእሰ-ኣስተንትኖን ትምህርትን ዘተባብዕ እዩ። ከም ኣእምሮኣዊ ምትእስሳር ክትትልን ውልቃዊ ፍወሳን ዝኣመሰሉ ሜላታት ኣብዚ ምዕባለ ክሕግዙ ይኽእሉ እዮም። እዚ ድማ ከም ልምምዳውያን ንዝተመሓየሸ ክእለትን ብቕዓትን ኣበርክቶ ይህብ።

5. ምምሕያሽ ናይ ርክብ ክእለት:-
ናይ ስምዒት ንቕሓት ምውናና ንኣድማዒ መንገዲ ናይ ምዝርራብ ዓቕምና የዕብዮ። ንዓማዊል ብግቡእ ርህራሄን ምርድዳእን መልሲ ክንህብ የኽእለና፣ ዝሓሸ ውፅኢት ሕክምና የመቻችው እዩ።

6. ህንፀት ተፃዋርነት:-
ስምዒታትና ምርዳእን ምምሕዳርን ተፃዋርነት ይሃንፅ ንብድሆታት ሞያና ብዝበለፀ ንኽንመርሕ ይሕግዘና። እዚ ተፃዋርነት እዚ ኣብ ሞያና ንነዊሕ እዋን ዝፀንሕ ኣድማዕነትን ዕግበትን ንምዕቃብ ወሳኒ እዩ። ከም ሰብ ሞያ ስነ-ልቦና መጠን ስምዒታዊ ንቕሓትና ንምዕባይ ቃል ምእታው ንሞያዊ ምዕባለና ኣገዳሲ እዩ።

ስምዒታዊ ጥዕናና ቀዳምነት ብምሃብ ናይ ገዛእ ርእስና ፅቡቕ ህይወት ነማሓይሽ ጥራይ ዘይኮነስ ንዓማዊልና ናይ ምድጋፍ ዓቕምና እውን ነዕቢ። እዚ ንርእሰ-ንቕሓትን ዕብየትን ዝግበር ተወፋይነት ኣብ መወዳእታ ነቶም እነገልግሎም ሰባት ዝሓሸ ውፅኢትን ዝያዳ ዕግበት ዘለዎ ሞያዊ ጉዕዞን የስዕብ።

ዳንኤል ገብረህይወት
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት, MSc
2024/05/23 19:22:36
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243