Telegram Web
ከሁለቱ መፃህፍት የበለጠ የወደዳችሁት የትኛውን ነው?
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
የጤና ባለሞያ መንደድ (Health Care Burnout)
================================
አንዳንድ ጊዜ ትሰራ ትሰራና ድክም ይልሀል። አሁንም መስራት ከቀጠልክ ትዝላለህ። አካልህም ስሜትህም ሲዝል መንደድ (Burn out) ይከተላል። የጤና ባለሞያዎች መንደድ በአለማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጠው ነው።

የጤና ባለሞያው ከመዛል አልፎ መንደድ ላይ ሲደርስ ከፍተኛ ሀዘን ይሰማዋል፣ እንቅልፍ አይኖረውም፣ ከቤተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ይሻክራል፣ የተለያዩ መድሀኒቶች መጠቀም ሊጀምር ወይም ራሱን ሊያጠፋ ይችላል። (በሚያሳዝን ሁኔታ በሀገራችንም ራሳቸውን ያጠፉ የጤና ባለሞያዎች አሉ።) ተፅእኖው ባለሞያው ላይ ብቻ ተወስኖ አይቀርም። ታካሚዎች በሙሉ ልብ የሚያዳምጣቸው አይኖርም፣ የሚያገኙት ህክምና ጥራቱ ይቀንሳል። የጤና ተቋሙም ቢሆን ውጤታማነቱ ይወርዳል። ዝውውር የሚጠይቁ፣ ስራ የሚቀሩ እና የሚለቁ ሰዎች ስለሚበዙ ወጥነት ያለው አገልግሎት መስጠት አይችልም።

መንስኤው ምንድነው?
መንደድ እንዳይከሰት የሚከላከሉት ሁለት ነገሮች ናቸው። የግለሰቡ ጥንካሬና (Individual resilience) የተቋም ቅልጥፍና (Organizational efficiency)። የግለሰብ ጥንካሬ ለማዳበር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በቂ እንቅልፍ...ወዘተ አስፈላጊ ናቸው። ሆኖም የእነዚህ ሚና ከ20 ከመቶ አይበልጥም። ዋናው የተቋም ቅልጥፍና ነው።

ለምሳሌ አንድ ሀኪም በጥራት በአንድ ቀን ውስጥ ማየት ያለበት አስር ታካሚ ቢሆንና ለስራው ደግሞ የኩላሊትና የጉበት ምርመራ የሚያስፈልገው ቢሆን የሚሰራበትን ሆስፒታል አስተዳደር የተበላሸውን የኩላሊትና የጉበት ላብራቶሪ እንዲያሰራ ነግሯል እንበል። ዛሬ ነገ እየተባለ ለወራት አልተሰራም። ለሊት ተረኛ ሆኖ እንቅልፍ ሳይተኛ አድሮ የቀን ስራው ላይ ተገኝቷል። "የግዴታ ሰላሳ ታካሚ ነው ማየት ያለብህ!" ተብሎ ሰላሳ ካርድ ሲመጣለት አስቡት። "ብዙ የተመረቁ ሀኪሞች አሉ፤ እኔ ሰላሳ ታካሚ ላጥላጥ እያደረግሁ ከማክም ሁለት ተጨማሪ ሀኪም ተቀጥሮ ታካሚዎቹ በደንብ ቢታዩ ጥሩ ነበር።" ብሎ ማሰቡ አይቀርም። ለታካሚዎቹ ብቻ ሳይሆን ለራሱም በማሰብ። ቀጥሎ የኩላሊት ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችን እየደበረው "ውጭ አሰሩ" እያለ ይልካል። ታካሚዎቹም "እሺ" እያሉ ለማሰራት ይሄዳሉ። አንድ በእድሜ አባቱ የሚሆኑ ታካሚ ግን "ምንም ብር የለኝም ልጄ። እዚሁ እናንተ ጋ አሰራልኝ ተባበረኝ" ይሉታል። "እኛ ጋ የለም" ብሎ ሲያያቸው ያሳዝኑትና "በቃ በዚች አሰሩ" ብሎ ከሚያገኛት እጅግ አነስተኛ ደሞዝ ለታካሚው የላብራቶሪ ማሰሪያ የተወሰነ ብር ይሰጣቸዋል። ይህ እሽክርክሪት በተለያየ ቀን በተለያየ መልክ ሲደጋገም አስቡት።

በጣም የደከማቸው የጤና ባለሞያዎች አሉ። ለእነሱም ለሚያክሙትም ሰው ስንል ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

Physician, first heal thyself. መፅሀፍ ቅዱስ ሉቃስ 4:23 ላይም "...ባለ መድሀኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ..." ይላል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
በዩቲዩብ ተቀላቀሉ https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የለውጥ ሂደቶች

▪️ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች ያልፋሉ:: ለውጥ በአንድ ጀምበር አይመጣም:: ሂደት ነው:: ብዙ መውደደቅና መነሳቶች: ብዙ ተስፋ ሰጪና ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያቶች ታልፈው ነው ስኬት ላይ የሚደረሰው:: ምናልባት አንዳንዶቹ እድል: ብርታት ወይንም ብልጠት በታከለበት ሁኔታ ነገሮች ቶሎ ተፈጽመውላቸው ይሆናል::

▪️እንደ Prochaska እና DiClemente እይታ ከሆነ: መለወጥ በሽክርክሪት ይመሰላል::

▪️ ለዛሬ ለዚህ ጽንሰ ሃሳብ አስረጅ እንዲሆነን: ሱስ የማቆም ሂደትን እንመለከታለን

▶️ Pre-contemplation/ቅድመ ውጥን:-

▫️ በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለችግሮቻቸው ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ነው::

▫️ብዙ ሱስ አስያዥ እጾችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች: ሱሱ በሚታይ ሁኔታ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው ቢሆን እንኳን: ችግሩን አምኖ ከመቀበል ይልቅ: ምንም ችግር እንዳልተከሰተባቸው በመካድ (denial) እና ሱሰኛ እንዳልሆኑና ማቆም ከፈለጉ በየትኛውም ጊዜ ማቆም እንደሚችሉ ሲናገሩ ይስተዋላል:: በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና እነዚህን ጉዳቶች እንዲያስተውሏቸው (impact assessment): እጽ ተጠቃሚ መሆናቸው የጠቀማቸውንና የጎዳቸውን ነገር (pros and cons) እንዲዘረዝሩ በማድረግ ነገሮችን እንዲያሰላስሉ መፍቀድ ይሆናል::

▶️ Contemplation/ውጥን-

▫️በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለ ችግሩ እውቅና ይኖራቸዋል:: ንግግሮቻቸው በመለወጥና ባለመለወጥ ሃሳቦች መሃል ይዋልላሉ::

▫️ 'እጹን መጠቀሜ ከባለቤቴ ጋር እንዳጋጨኝ አውቃለሁ: ግን ደሞ ጓደኞቼን ሳገኝ መጠቀሜ አይቀርም: የክፋ ቀን ወዳጆቼን ማጣት ደሞ አልፈልግም' አይነት ንግግሮች ይስተዋላሉ::

▫️ብዙዎቹ የዕጽ ተጠቃሚዎች እዚህኛው ደረጃ ሲደርሱ ወደ ባለሙያ እርዳታን ለማግኘት የማቅናት እድላቸው ይጨምራል::

▫️በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና ወደ መለወጥ ሃሳቦች እንዲዘነብሉ ማበረታታት ይሆናል::

▫️ የችግሩን ግዝፈት እንዲረዱ እና ለውጥ ለማምጣት ብቁ እንደሆኑ እንዲገነዘቡ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሻገር ይቻላል::

▶️ Preparation/ የዝግጅት ምዕራፍ

▫️በዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የመለወጥ ውጥናቸው ሚዛን መድፋት ይጀምራል::

▶️ Action/ ተግባራዊ የመለወጥ ስራዎች

▫️የለውጥ ስራዎቻቸው መታየት ይጀምራሉ:: የሚጠቀሙትን ሱስ መጠን ሲቀንሱ: ከፍ ሲልም ሲያቆሙት ይስተዋላል::

▫️በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉ ሰዎች: የለውጥ ሂደቱን የሚያሳልጡ መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ ይደረጋል::

▶️ Maintenance/ ለውጥን ማስቀጠል

▫️በዚህ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች: የቀድሞ ባህርያቸው እንዳያገረሽ ስራን ይፈልጋል::

▶️ Relapse/ ወደ ቀደመ ባህርይ መመለስ

▫️ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደቀደመ ባህርያቸው ሊመለሱ ይችላሉ:: እነዚህ ምክንያቶችን መለየትና መስራት መቋቋምያ መንገዶችን መፈለግ ያሻል::

▪️የሱስ ማቆም ህክምናዎች እነዚህ የለውጥ ሂደቶቾን መሰረት አድርገው ይካሄዳሉ::
▪️በግል ወይንም በቡድን ሊሰጡ ይችላሉ::
▪️የሱስ ማቆም ህክምናን ለማግኘት የተለያዩ የህክምና ተቋም አማራጮች በመዲናችን ይገኛሉ::
▪️በቀጣይ ስለ ህክምና አማራጮቹ እንቃኛለን::

Reference
- Curriculum based motivational group by Ann Fields and Internet

ቸር ይግጠመን!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
Hakim
ትውስታ እና የህግ ምስክርነት
===================
ትውስታ ባይኖር ህይወታችን የተለየ መልክ ይኖረው ነበር። ለምሳሌ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ትውስታ ባይኖረን ቤት ውስጥ የምናገኘውን ሰው "ምን እያደረግህ ነው፣ ከየት ነው የመጣኸው፤ እና በዋናነት ደግሞ ማነህ?" ልንል እንችላለን። ትውስታ ትናንት እና ነገአችንን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። ትውስታ ባይኖር ጓደኝነት አይታሰብም።

ትውስታችን የሚያጋጥመንን ነገር ሁሉ 'ሴቭ' ቢያደርግ ቦታ ስለሚሞላ ወይም ለመለየት አስቸጋሪ ስለሚሆን ስሜት ያልተጫነባቸውን ክስተቶች ላሽ ይላቸዋል። አምስተኛ ክፍል እያለን አንድ አርብ ክለባችን አየር ሀይል ምድር ባቡር ከተባለው ሌላ ክለብ ጋር ተጫውቶ ዋንጫ በልቶ ነበር። ጨዋታው ላይ በረኛችን አንድ ኳስ ተወርውሮ ሲይዝ እንዲሁም ነውጠኛው የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ተቀይሮ ሲገባ ቁልጭ ብሎ አሁንም ትዝ ይለኛል። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሀሙስ እለት በትምህርት ብቻ ነበር ያለፈው። ማን እንዳስተማረን፣ ምን እንደተማርን የማስታውሰው ዜሮ ነው።

የአይን ምስክር ተብለው ፍርድ ቤት ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ሳያውቁ በስህተት፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አውቀው በድፍረት ትውስታቸው የተሳሳተ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። በቀጣይ ምሳሌዎችን አቀርባለሁ። ለዛሬው ግን ሮጀር ሚላ የኮርና እንጨቷ ጋር ሄዶ በአንድ እጁ ወገቡን ይዞ እንደ ያንቡሌ የጨፈረውን እናስታውሳለን። ጎሏን የምናስታውስ ስንቶች እንሆን። በተመሳሳይ ረሺድ ያኪኒ መረቡን ይዞ ያለቀሰ ጊዜ ኳሱን ያቀበለው ማን ነበረ?

በዩቲዩብ ተቀላቀሉ https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የሃገር ፍቅር የኪነጥበብና ቲያትር ቡድን የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአማኑኤል ሆስፒታል በመገኘት ለሰራተኞችና ለህሙማን ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት አቅርበዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይም የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃዎችንና አስተማሪ የሆኑ ጭውውቶችን/ድራማ ለታዳሚዎቹ በማቅረብ የኪነጥበብ ስራዎቻቸውን አካፍለዋል፡፡
እናመሰግናለን።
የታካሚዎችን Privacy ለመጠበቅ ታካሚዎች ያሉባቸውን ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ማንነታቸው እንዳይለይ አደብዝዞ (Blurr አድርጎ) መልቀቅ ወይም የታካሚዎቹ ፈቃድ ያስፈልጋል።

በዩቲዩብ ተቀላቀሉ https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የወንድማማች ፉክክርን በብልሀት የያዙ እናት
===========================
ስብሀት ለአብ ገብረእግዚአብሄር በአስር አመቱ ከወላጆቹ ተለይቶ ከርባ-ገረድ ወደ አዲስአበባ ቢመጣም በልጅነቱ ጥሩ ፍቅር ስለተሰጠው ለመልመድ እንዳልተቸገረ ይናገራል። በተለይ ለእናቱ ወ/ሮ መአዛ ተወልደ መድህንን ያለው ፍቅር ከፍተኛ ነው። እናቱን በስማቸው ሳይሆን "ወለላይ" እያለ ነው የሚጠራቸው።

ከዚህ በፊት የእትማማቾች (የወንድማማቾች) ፉክክር የልጆች ስነልቦና ላይ የሚያሳድረውን ዘላቂ አሉታዊ ተፅእኖ አይተናል። የነ ስብሀት እናት ወለላይ ግን በብልሀት ነበር ልጆቻቸውን ያሳደጉት። "ስብሀት ገ/ሄር ህይወትና ክህሎት" የሚለው የአለማየሁ ገላጋይ መፅሀፍ ገፅ 37 ላይ ስብሀት የሚከተለውን ይላል፦

"ለተቃና ስነ ልቦና ደግሞ የእናቴ ድርሻ ከፍተኛ ነው። በጣም ነበር የምትወደኝ። እኔ የራሴን ሳስታውስ እናታችን እኔን ከሁሉ አስበልጣ የምትወደኝ ነበር የሚመስለኝ፣ ትንሽ ካደግን በኋላ ተወልደ (ታናሽ ወንድም) ስጠይቀው "እኔን ከሁሉ አስበልጣ የምትወደኝ ይመስለኝ ነበር" አለኝ።ዮሴፍም (የታናሽ ታናሽ ወንድም) እንደዚሁ። ስለዚህ ጥበብ ነው ያ። እናቴ የጥሩ ተፅዕኖ ገድ ሆነችኝ። በመልካም ተፅእኖ በሩን ከፈተችልኝ።"

የወንድማማች (የእህትማማች) ፉክክርን ወላጆች በብልሀት ሲይዙት ይህንን ይመስላል።

በዩቲዩብ ተቀላቀሉን https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
2024/06/16 10:42:34
Back to Top
HTML Embed Code: