ማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ያስገነባቸውን አራት አብያተክርስቲያናት ሊያስመርቅ ነው!!!
በማኅበረቅዱሳን አስተባባሪነት በደቡብ ኦሞ ሀገረስብከት ግንባታቸው የተጠናቀቁ የአራት አብያተክርስቲያናት ሕንጻ ቡራኬና ቅዳሴ ቤት ከግንቦት 26-29 ቀን ዓ.ም ይከናወናል።
1. ከግንቦት 26-27 ቀን 2014ዓ.ም (ዓርብና ቅዳሜ) በበናጸማይ ወረዳ የይርጋ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሕንጻ
2. ከግንቦት 27-28 ቀን 2014ዓ.ም (ቅዳሜና እሑድ) በበናጸማይ ወረዳ የጎልድያ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሕንጻ
3. ከግንቦት 27-28 ቀን 2014ዓ.ም (ቅዳሜና እሑድ) በማሌ ወረዳ የአጆ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሕንጻ
4. ከግንቦት 28-29 ቀን 2014ዓ.ም (እሑድና ሰኞ)በዳሰነች ወረዳ የካፑሲያ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሕንጻ
እርስዎም በተጠቀሱት ዕለታት ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመገኘት በበዓሉ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
የለብንም ስተት ካወራን በዋላ ሁሉም ነገር በትክክል እሄደ ነው ለዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ከልብ አመሰግናለሁ
ወደፊትም አንድ ላይ ተጠናክረን እንቀጥላለን

''እስመ በትህትና ትትረከብ ልዕልና''
"ኦ ትሕትና ዘመጠነ ዝ ትሕትና::
†††
"ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው::
(ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ)
+++++
ብፁዕ አቡነ አብርሃም (የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) እና
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)
ለሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በጠቅላይ ሥራ አስኪጅነትና በቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊነት ለመምራት ተመርጠው፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ማርያም ሲቀበሉ፤

ሰውነታችሁን_ለሰይጣን_ምቹ_አታደርጉ!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥 ተወዳጆች ሆይ የብዙዎቻችን ሰውነት ለሰይጣን ምቹ ነው፡፡ ለሰይጣን ምቹ ሰውነት ማለት ንስሐ ያልገባ በኃጢአት ግራ የሚጋባ ሰውነት ነው፡፡ ለሰይጣን ምቹ የሆነ ሰውነት ማለት በሐሜት፣ በቧልት፣ በምቀኝነት፣ በክፋት፣ በዝሙት፣ በስኳር፣ በአድመኝነት፣ በዘረኝነት ወዘተ የረከሰ ሰውነት ማለት ነው፡፡
🔥 ለሰይጣን ምቹ ሰውነት ማለት ለፈጣሪ የማይንበረከክ፣ ሰማያዊ አምልኮት የማያቀርብ፣ የማይሰግድ፣ የማይጸልይ፣ የማይጾም፣ ቅዱስ ቁርባን የማይቀበል ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ሰውነት ለምጽዋት የተዘረጋ ነው፡፡ ነገር ግን በዝሙት የረከሰ ነው፡፡ ይህ ለሰይጣን ምቹ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ጸሎተኛ ነን፡፡ በጸሎተኝነታችን ልክ እጅግ ሐሜተኛ እና ቅናተኛ ነን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
🔥 አንዳንዶቻችን እጅግ አማኝ እና ሰርክ ለኪዳን፣ ለቅዳሴ እና ለጉባኤ ከቤተ ክርስትያን የማንርቅ ነን፡፡ ነገር ግን ሲበዛ ቂመኛ እና ይቅርታ የለሾች ጨካኝ ነን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡ አንዳንዶቻችን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን አንደበታችንን በመዓዛ መለኮት ማጣፈጥ እየቻልን ‹‹እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝና›› እያልን አንደበታችን በሐሜት የመረረ ነው፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
አንዳንዶቻችን በመንፈሳዊ እውቀታችን ሰዎችን መክረን፣ አስተምረን ከኃጢአት መልሰን ለንስሐ እናበቃለን እኛ ግን ተመክረን የማንሰማ፣ ከኃጢአታችን መመለስ ያቀተን፣ ንስሐ የማንገባ ለቅዱስ ቁርባን የማንበቃ ነን፡፡ በዚህ ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
🔥 አንዳንዶቻችን የወሲብ ፊልም ማየት፣ ግለ ወሲብ መፈጸም ኃጢአት እንደሆነ ለሰው እንናገራለን እናስተምራለን በዚህም እነዛ ሰዎች ከዚህ ሰይጣናዊ ሱስ ተላቀው ንስሐ ይገባሉ ልማደ ሰይጣንንም ይተዋሉ፤ እኛ ግን ሰው ባላየ እግዚአብሔር ባየ የወሲብ ፊልም እናያለን ግለ ወሲብ እንፈጽማለን፡፡ በዚህም ለሰይጣን እንመቻለን፡፡
አንዳንዶቻችን መጽውቱ ብለን ሰዎች እንዲመጸውቱ፣ ድሆችን እንዲረዱ እናደርጋለን፡፡ የእኛ እጅ ግን በታንክ ፍሬን ተይዟል፣ መመጽወትም እንቢ ብሎናል፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
🔥 አንዳንዶቻችን ሰዎች ሲያማቸው እንዲጸልዩ፣ ጸበል እንዲጠመቁና በዚህም እንደሚድኑ መክረን እነዛ ሰዎች በምክራችን ተጠቅመው ጸልየው ተጠምቀው ይድናሉ፡፡ እኛ ስንታመም ግን እምነት አጥተን በየሆስፒታሉ እንንከራተታለን፡፡ በዚህ ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
ወዳጆቼ በየትኛውም ጉድለታችን ሰይጣን ወደ ሕይወታችን ይገባል፡፡ ሰይጣን ትንሿን ስህተታችንን፣ የኃጢአት ፍላጎታችንን አይቶ ወደ እኛ ጎራ ይልና ትንሿን ስህተት ትልቅ፣ ኃጢአትን ደግሞ ጽድቅ አድርጎ የእሱ መጫወቻ ያደርገናል፡፡
🔥 ሰይጣን አንዴ በዝሙት ከጣለን ስሜታችን ደግሞ ደጋግሞ ይጥለናል፡፡ ሰይጣን በመርፌ ቀዳዳ ስህተት ይገባና እኛ ግን ከስህተታችን በሰፊው በር መውጣት ያቅተናል፡፡
ዛሬ ሥጋዊ ፍላጎታችን፣ ዓላማችን፣ እውቀታችን፣ ትምህርታችን፣ ርእዮተ ዓለማችን፣ አመለካከታችን በራሱ ለሰይጣን ምቹ ስለሚሆን ልናስተውል እና ልንነቃ ይገባናል፡፡ ዛሬ ከላይ እስከታች፣ ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት፣ ከዓለማዊው እስከ መንፈሳዊው፣ ከምሁሩ እስከ ፊደል ነውሩ፣ ከወጣቱ እስከ አዛውንቱ ያለነው ሰውነታችን ለሰይጣን ምቹ ስለሆነ ሕይወታችን በፈተና፣ በስቃይ፣ በመንፈሳዊ ባዶነት የተመላ ነው፡፡
እግዚአብሔር ‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፣ ሰውነታችሁን ቀድሱ፣ ቅዱሳንም ሁኑ›› ብሎ አዞናል፡፡
🔥 ነገር ግን ሰውነታችንን በኃጢአት አረከስን፣ ሕገ እግዚአብሔርንም አፈረስን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ሆንን፡፡ ሰይጣን ለራሱ ምቹ በሆነ ሰው እና ሰውነት ላይ እንደፈለገ ይሆናል፣ የፈለገውን ዓላማ ይፈጽማል፣ ለሚፈልገው ዓላማ መጠቀሚያ ያደርገዋል፡፡ /ዘሌ 11÷44/
ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኃለሁ›› በማለት የልመና ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ /ሮሜ 12÷1/
በእውነት ሰውነታችን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው? ሰውነታችን ቅዱስ እና መሥዋዕት ነው? ሰውነት በኃጢአት ሲረክስ ነፍስም ትረክሳለች፡፡
🔥 ልብ በሉ ቆሻሻ ነገር ላይ እና ቆሻሻ ስፍራ ላይ ዝንቦች ይሰፍራሉ፡፡ በኃጢአት የቆሸሸ እና የተበላሸ ሰውነት ላይ አጋንንት ይሰፍራሉ፡፡ በቆሻሻ ነገር እና በቆሻሻ ስፍራ ላይ ዝንቦች ለሰው ጎጂ የሆኑ በሽታዎችን ያከማቻሉ፡፡
በኃጢአት በቆሸሸ ሰውነት ላይም አጋንንት መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያጠለሽ፣ ነፍሳችንን የሚያቆሽሽ ክፉ መርዙን ይረጫል፣ ጎጂ የሆነ ኃጢአትንም ያጠራቅማል፣ የሥጋ እና የነፍስ በሽታ ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር በዘሌ 11÷43 ላይ ‹‹በእነርሱ እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱ›› ብሎናል ‹‹በእነርሱ እንዳትረክሱ›› ያለው አንድም በሰይጣን ክፉ ምሪት እና ተግባራት ሰውነታችንን፣ ነፍሳችንን እንዳናረክስ ነው፡፡
🔥 ስለዚህ ሰውነታችሁን ለንስሐ፣ ለጽድቅ፣ ለጾም፣ ለጸሎት፣ ለስግደት እና ለቅዱስ ቁርባን ምቹ አድርጉ እንጂ በፍጹም ለሰይጣን ምቹ አታድርጉ፡፡
✍በቀሲስ ሄኖክ ወልደ- ማርያም

ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ሰኔ_20_እና_21
👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።
ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።
ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ።
ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።
ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!

🥀 ዛሬ በለጥከኝ🥀
አንድ የበቁ አባት ደቀመዝሙራቸው እየተፈተነ እንደሆነ በጸሎታቸው ወቅት ተረዱ። ስለዚህ ደቀመዝሙራቸውን ጠርተው "ከሚፈትንህ ጾር ትላቀቅ ዘንድ እግዚአብሔርን እንድጠይቅልህ ትወዳለህን?" ብለው ጠየቁት።
እርሱም "አባቴ እየተፈተንኩ እንደሆነ አውቃለሁ ነገር ግን መፈተኔ ፍሬ እንዳፈራ ያደርገኛልና ፈተናውን የምታገስበት ኃይል ይሰጠኝ ዘንድ ለምኑልኝ" አላቸው በዚያ ጊዜ ልጄ ብዙ ሳስተምርህ ብኖርም ዛሬ በለጥከኝ ብለው መለሱለት።
በክርስትና ሕይወት የሚያጋጥመን ፈተና ለጥፋት የሚመጣብን የሚመስለን እንኖር ይሆናል።
ነገር ግን ፈተናውን እንወጣና የእግዚአብሔርን በረከት እንቀበል ዘንድ ነውና እንደ ደቀመዝሙሩ ትእግስቱንና፣ ድል ማድረጉን እንዲሰጠን መለመን ይኖርብናል።
ጌታችንም ሲያስተምር "በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ" ዮሐ 16፣33 በማለት ከእርሱ ጋር ከሆንን የሚገጥሙንን ፈተናዎች ሁሉ እንደምናሸንፍ የነገረን ለዚህ ነው።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
📖ሮሜ 8፣31

Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (Yordi Addise)
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም

✍ኹለት ዓይነት ኃጢአተኞች አሉ✍
🔥🍂🔥🍂🔥🍂🔥🍂🔥
#የመጀመሪያዎቹ በውሳጤያቸው፥ ከፍ ያለና ሥር የሰደደ ኃጢአትን የመሥራት ፍላጎት ያላቸው ናቸው፡፡ ልባቸውና ሕሊናቸው ኹሉ በኃጢአት የተሞላ ነው፡፡ ኃጢአትን ከፍ ባለ ደረጃ ስለሚፈጽሙአት የለመዱትን ኃጢአት ሳይሠሩ መኖር የሚቻል አይመስላቸውም፡፡ ይህ ዓይነቱ ኃጢአት እጅግ አደገኛና መንፈሳዊ በሽታ ነው፡፡ እነዚህ ኃጥአን ከዚህ በሽታቸው ሊታከሙ የሚችሉት ከፍ ያለ ርኅራኄ በመስጠትና አንድ በጽኑ የታመመ የሥጋ ሕመምተኛን በምናክምበት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነው፡፡ እንደዚህ ካላደረግን ይህ ሰው ይባስኑ ሊጠፋ ይችላልና፡፡
#ኹለተኛዎቹ ደግሞ ከስንፍናቸውና ከሐኬተኝነታቸው የተነሣ ኃጢአት የሚሠሩ ናቸው፡፡ ኃጢአት ላለመሥራት ዓቅሙ ቢኖራቸውም ቅሉ ከስንፍናቸው የተነሣ ግን ኃጢአት ይሠራሉ፡፡ ፈተና ሲመጣ ፈተናውን ለመቋቋም ይሰንፋሉ፡፡ በደመ ነፍስ እንደሚመራ እንስሳ ኾነው ሰንፈው ምኞታቸውን ይከተላሉ፡፡ እነዚህን ኃጥአን ከዚህ በሽታቸው ለማከም ጠበቅ ያለና በዓቅማቸው ሊያስደነግጣቸው የሚችል ቀኖናን በመስጠት ነው፡፡
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚 አምስቱ የንስሐ መንገዶች

አስተካክለኝና ትክክል ልኹን
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር እንጂ እርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም እርሱ አንተን ሲሰማህ ችግሮችህ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለህ፡፡
ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ “አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡
ስለዚህ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው ቢበላሽ ራስህን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት እውነት እልሀለው እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡
የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልሀለው፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ ጋር፣ … ትገናኛለህ፡፡
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተህ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራህ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተህ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ ይዘኅ ቀረኽ፡፡
ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡
🥀ወደ ፈጠረ መምጣትህ ጅማሬህ ነው፤
🥀 ከርሱ ጋር ያለው ቆይታህ ዕድገትህ ነው፤
እርሱን አምነህ እንደኖርህ አምነህ ስትሞትም ሕይወትህ ነው፡፡
እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልህ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ”
📖/ መዝ.118፡144/፡፡
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ
ይቆየን!!!
@Learn_with_john

#ስምዐ #ጽድቅ
ስለዚህም ተክለሃይማኖት ሆይ የእውነት ምስክር ሆንክ። "ወበእንተዝ ተሰመይከ ተሰመይከ ተክለ ሃይማኖት። ስምዐ ጽድቅ ኮንከ ስምዐ ጽድቅ ኮንከ ተክለሃይማኖት"። ዋሽቶ ከመኖር እውነትን ተናግሮ መሞት ይበልጣል። ዋሽቶ ከመከበር እውነትን ተናግሮ መጠላትና መሰደብ ይሻላል።
።
ታላቁ ቅዱስ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ዘመኑን ሁሉ ቅዱስ እግዚአብሔር የገለጠውን እውነት በአንደበቱ በመስበክ በሕይወቱ በመተግበር ኖሯል። በእርግጥ የመኖር ፍሬ ነገርም ለእውነት እስከ ሞት ድረስ ታምኖ መኖር ነው። ቅዱስ አባታችን በዛሬው እለት ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም አርፎ ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት የተሸጋገረባት ቀን ናት። ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ። የጻድቃን ሞታቸው ሕይወታቸው ነው። ቅዱሳን እውነትን በመያዛቸው በሐሰተኞች ቢሳደዱም መከራ ቢደርስባቸውም ሁልጊዜም ደስተኞች ነበሩ። የደስታቸው ምንጭ እግዚአብሔር ነውና። ለዚያምኮ ነው ቅዱስ ዳዊት ንዑ ንትፈሣሕ በእግዚአብሔር ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ያለው።
።
እንኳን አደረሳችሁ።🌱🌱🌱🌹🌹

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለፀአተ ነፍስከ በስብሐት አዕላፍ እንግልጋ። ለዓለም ዛቲ እምግብርናቲሃ ወጹጋ። ተክለ ሃይማኖት ቶማስ ለመርዓስ ዐቃቤ ሕጋ። ለእለ ገብሩ ተዝካረከ እንዘ ሀለው በሥጋ። ሀቦሙ እግዚእየ ሞገስ ወጸጋ። ትርጉም፦ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከዚች ዓለም የፈተናና የመከራ ቂም በቀል ኑሮ በመላእክት አጃቢነት በክቡር ለተለየችው ፀአተ ነፍስ ሰላም እላለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ የመራስ ዓቃቤ ሕግ ቶማስ የተባልክ አንተ ተክለ ሃይማኖት ነህና በሕይወተ ሥጋ ሳሉ መታሰቢያህን ላደረጉ ሁሉ ጌታዬ ሆይ ክብርና ሞገስን አጎናጽፋቸው። መልክአ አቡነ ተክለ ሃይማኖት።

ትሑት እና ትዕግሥተኛ ሁን
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል
/ ዘኁ 12:3/
ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር
ሐዋርያው " ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ ..ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ..." /ሮሜ 12*17-19/ብሏልና ። እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ " ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ " / ሮሜ 12*21/ በማለት ይጠይቀናል ።
በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው ። ለዚህ ነው ሐዋርያውም " እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል ። " / ሮሜ 15*1/ ያለው።
ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ ። ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል ። ወቅቶችን ዝናባማ ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል ።
ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ ።
ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም ። ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው ። ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው ። ከንነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው ። ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው ።
✍አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

... ዲያብሎስ የነገሠ ቢመስልም ለጊዜው ነው፤
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
አማራጭ አሳጥቶ በህልውናችን ሳይቀር አስጨንቆ፣ ኦርቶዶክሳውያንን ከቤተ መቅደስ ያወጣቸው ዘንድ ይታገላል፤ ...
. 'ማመን' እንደ ኋላ ቀርነት፣ 'ክሕደት' እንደ መሠልጠን ተቆጥሯል፤
. 'ሥርዐት መጠበቅ' ዐላዋቂነት፣ 'አጉራ ዘላይነት' ደግሞ ዐዋቂነት ኾኗል፤
. ሥርዐት እይዛለኁ የሚሉት ይገፋሉ፤ 'ዓለም ' ማለፊያ፣ ማግደሚያ ታሳጣቸዋለች፤ ...
. ሥልጣን እና ገንዘብ ኹሉን ያዙበታል፤
. እኲይ እየበዛ ሲሔድ፣ ጽድቅ እና ኀጢአት ለውድድር ይቀርባል፤
ዓለም 'መዳኛውን' መሞቻ ይመስለዋል፤
. 'መሞቻው' የቀና መንገድ ይመስለዋል፤...
. ለዚህ ኹሉ መድኃኒቱ ግን በመጨረሻ 'ጽድቅ' ታሸንፋለች፤ ዓለምም እንደ መጋረጃ ትጠቀለላለች፤ ...
. ርሱን [ሰይጣንን] ፊታዉራሪ አድርገው፣ ቤተ ክርሲቲያንን ሲያስጨንቁ የነበሩ ኹሉ ያን ጊዜ፣ ኀፍረትን ይጎናጸፋሉ፤ ...
. ያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን አክሊሏን ክርስቶስን ተቀዳጅታ በጽድቅ አደባባይ ትመላለሳለች፤ ...
.ዓለማዊነት እና ኦርቶዶክሳዊነት እኩል ተካክለው በመንገድ ይቆማሉ፤ ...
👉 አላውያን ንገሥታት እና ቀናይያን አባቶች በፊታችን አሉ፤
🤔. እንደ አጋንንት መለያየት፣ እንደ መላእክት አንድ መኾንን መምረጥ ድርሻዉ የእኛ ነው፤ ...
👀. አኹን እነ ሄሮድስ የመሰሉ በአንድ ጎራ፥ እነ [መጥምቁ] ዮሐንስ በአንድ ጎራ የተሰለፉበት ዘመን ነው፤
. እንደ እውነቱ ከኾነ፣ የሄሮድስ መንገድ የኾነው የበላይነት እና ዓለማዊነት፣ ሐኬት እና ዝሙት፣ ስግብግብነት እና ደም አፍሳሽነት ለጊዜው እያዩሉ ይመስላሉ፤
👉. ነገር ግን ፍጻሜው ጽድቅ ያሸንፋል ነዉና ወገኖቼ አስተዉሉ! ከደመቀው እንዳትዘፍኑ ተጠንቀቁ፤
. ኹለት ነገሥታት ተቀምጠዋል፤ ምድራዊው ሄሮድስ እና ገባሬ ሰማያት ወምድር ክርስቶስ፤
. ኹለት መንገድ ጠራጊዎች አሉ፦
☝️- የሄሮድስ መንገድ ጠራጊ፦ ሥልጣን ገንዘብ፣ ወይን፣ ዘፈን እና ዝሙት፤
✌️- የቅዱስ ቃል ክርስቶስ መልእክተኛ፦ ጽዱል ኮከብ ዮሐንስ፤ ...

ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። ስለዚህም በመጽሐፍ _"አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው "ተብሎአል። [መዝ 136*8_9] የባቢሎን ልጅ [የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። [1ቆሮ 10*4] ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።
✍አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@Learn_with_John
✍አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@Learn_with_John
ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡
ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡
🌻ቃለ ህይወት ያሰማን❤️
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!
🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂
🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17
ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።
ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።
✍ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ