tgoop.com/learn_with_John/744
Last Update:
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር እንጂ እርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም እርሱ አንተን ሲሰማህ ችግሮችህ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለህ፡፡
ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ “አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡
ስለዚህ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው ቢበላሽ ራስህን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት እውነት እልሀለው እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡
የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልሀለው፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ ጋር፣ … ትገናኛለህ፡፡
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተህ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራህ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተህ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ ይዘኅ ቀረኽ፡፡
ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡
🥀ወደ ፈጠረ መምጣትህ ጅማሬህ ነው፤
🥀 ከርሱ ጋር ያለው ቆይታህ ዕድገትህ ነው፤
እርሱን አምነህ እንደኖርህ አምነህ ስትሞትም ሕይወትህ ነው፡፡
እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልህ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ”
📖/ መዝ.118፡144/፡፡
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ
ይቆየን!!!
@Learn_with_john
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/744