tgoop.com/learn_with_John/743
Create:
Last Update:
Last Update:
✍ኹለት ዓይነት ኃጢአተኞች አሉ✍
🔥🍂🔥🍂🔥🍂🔥🍂🔥
#የመጀመሪያዎቹ በውሳጤያቸው፥ ከፍ ያለና ሥር የሰደደ ኃጢአትን የመሥራት ፍላጎት ያላቸው ናቸው፡፡ ልባቸውና ሕሊናቸው ኹሉ በኃጢአት የተሞላ ነው፡፡ ኃጢአትን ከፍ ባለ ደረጃ ስለሚፈጽሙአት የለመዱትን ኃጢአት ሳይሠሩ መኖር የሚቻል አይመስላቸውም፡፡ ይህ ዓይነቱ ኃጢአት እጅግ አደገኛና መንፈሳዊ በሽታ ነው፡፡ እነዚህ ኃጥአን ከዚህ በሽታቸው ሊታከሙ የሚችሉት ከፍ ያለ ርኅራኄ በመስጠትና አንድ በጽኑ የታመመ የሥጋ ሕመምተኛን በምናክምበት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነው፡፡ እንደዚህ ካላደረግን ይህ ሰው ይባስኑ ሊጠፋ ይችላልና፡፡
#ኹለተኛዎቹ ደግሞ ከስንፍናቸውና ከሐኬተኝነታቸው የተነሣ ኃጢአት የሚሠሩ ናቸው፡፡ ኃጢአት ላለመሥራት ዓቅሙ ቢኖራቸውም ቅሉ ከስንፍናቸው የተነሣ ግን ኃጢአት ይሠራሉ፡፡ ፈተና ሲመጣ ፈተናውን ለመቋቋም ይሰንፋሉ፡፡ በደመ ነፍስ እንደሚመራ እንስሳ ኾነው ሰንፈው ምኞታቸውን ይከተላሉ፡፡ እነዚህን ኃጥአን ከዚህ በሽታቸው ለማከም ጠበቅ ያለና በዓቅማቸው ሊያስደነግጣቸው የሚችል ቀኖናን በመስጠት ነው፡፡
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚 አምስቱ የንስሐ መንገዶች
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/743