የእለቱ ጥያቄ❓❓❓
"እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙ እግዚአብሔር ነው?"ብሎ ከእስራኤል ልጆች ጋር የዘመረውቅዱስ አባት ማነው?

Anonymous Quiz
16%
የዳዊት ልጅ ሶሎሞን
19%
ቅዱስ ሙሴ
51%
ልበ አምላክ ዳዊት
14%
ኢያሱ ወልደ ነነዌ
እሺ ተወዳጆች የዛሬው ጥያቄ መልስ
ኦሪት ዘፀአት ም15፥ቁ 1
"በዚያ ጊዜም ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ ፤" ይላል
ለተሳትፎአቹ እናመሰግናለን በርቱልን😘 ደግሞ እ😉

“ሰው ሆይ ! በዚህ ዓለም መዳተኛ ሆነህ ትኖር ዘንድ እያዘዝኩህ ሳለ፥ አንተ ግን የትውልድ ሀገርህን ጠቅሰህ የምትታበየው ስለ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር ! “ይህ ዓለም ለአንተ እንደማይገባ አስበህ እንድትንቀው ስነግርህ አንተ ግን ስለ ትውልድ ቀዬህ የምትመካው ስለ ምንድን ነው?” እነዚህ ነገሮች ፈጽመው የተናቁ ናቸውና፤ በክርስቲያኖች ዘንድስ ይቅርና በግሪክ ፈላስፎች ዘንድም ቢሆን የተናቁ የተጠቁ ናቸውና፥ “ውጹአን” ተብለውም ይጠራሉ፥ ዝቅ ያለ ግምትም ይሰጣቸዋልና፡፡
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
ተወዳጆች እንደተለመደው ያላችሁን አስተያየት @JohnDPT27 ላይ አድርሱን፡፡በእመቤታችን ፍቅር እንወዳችኀለን❤️😘

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
=>ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ)
3.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ❤️❤️
✨የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቁጥር 22
“ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።”
— ሉቃስ 6፥22

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እህተ መላዕክተ♥♥
A sister to z angels♥♥
A sister to z angels♥♥
በመስቀሉ የተፈጸመው ጋብቻ (በቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ)
ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
“ከእኛ ጌታ በቀር ለእጮኛው ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው ማን ነው? ከቤተ ክርስቲያንስ በቀር የሞተ ሰው ለእርሱዋ ባልዋ ይሆን ዘንድ የምትሻ ሴትስ ማን ናት? ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ደሙን የጥሎሽ ስጦታ አድርጎ ያቀረበ ሰው ማን ነው? በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ ከአንድዬ በቀር ጋብቻውን በሕማሙ ያተመ ሰው ማን ነው ? ከሞተ አካል መጽናናት ታገኝ ዘንድ በእቅፎቹዋ ይዛ በሰርግዋ በዓል ላይ የተገኘች ሙሽራ ከዚህ በፊት ታይታ አትታወቅም ? በየትኛውስ የሰርግ በዓል ላይ ነው የሙሽራውን ሥጋ በመቁረስ በሰርጉ ለታደሙት እንግዶች መብል ይሆን ዘንድ የተሰጠው?
ሚስት በባሏ ሞት ምክንያት ፍቺን ትፈጽማለች ፡፡ ይቺ ሚስት ግን በውድ ባሏ ሞት ምክንያት ከእርሱ ጋር ፍጹም ተዋሕዶን አደረገች፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ራሱን በመሠዋት ቅዱስ የሆነውን ሥጋውን ሁሌም ትመገበው ዘንድ ክብርት ለሆነችው ሙሽራው መብል አድርጎ አቀረበላት ፡፡ ጉኑንም በመወጋት ቅዱስ ደሙን በጽዋው ሞልቶ ሰጣት ፡፡ በዚህም ምክንያት በልቡዋ ያኖረቻቸው ጣዖታት ሁሉ ተወገዱላት ፡፡ በእርሱም ቅዱስ ቅባት ከበረች ፤ እርሱንም በጥምቀት ውኃ ለበሰችው ፤ በሕብስት መልክ ተመገበችው ፤ እንደ ወይንም ጠጣችው ፡፡ በዚህም ምክንያት ሁለቱ በፍጹም ተዋሐዱ አንድ እንደሆኑ ዓለም ሁሉ አወቀ ፡፡
ሙሽሪት ውዱዋ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ በመሞቱ ምክንያት በማንም አለወጠችውም ፡፡ በእርሱ ሞት ሕይወትን አግኝታለችና ለእርሱ ትልቅ ፍቅር አደረባት ፡፡ ባልና ሚስት ለዚህ ምሥጢር ዋነኞቹ ምሳሌዎች ናቸው ፡፡ እነርሱ ለእውነተኛው ጋብቻ እንደ ምሳሌና እንደ ጥላ የሚያገለግሉ ናቸው ፡፡ በእነርሱ መስሎ ሙሴ ይህን ታላቅ ምሥጢር ተናገረ ፡፡ ሙሴ ይህን ምሥጢር በመሸፈኛ ከልሎታልና ተሰውሮን ነበር ፡፡ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ገለጠልን፡፡ ሙሴ “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ”በማለት በምሥጢር የተናገረውን “እኔ ግን ይህን ስለክርስቶስና ስለቤተክርስቲያን ይላለሁ” (ኤፌ.5፡32)በማለት ተረጎመው፡፡” @Learn_with_John

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዘይት ዝንጣፊና የሰሌን ዘንባባ ተሸክሜ ከአርያም የተገኘ መድኃኒት መባል ለአንተ ይገባል እያልኩ ከሕፃናት ጋራ እጮኽ ዘንድ አድለኝ።
የዳዊት ልጅ ሆይ! አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት እንደሆነ ከአንተ ጋር አንድ አድርገኝ።
…
ንጉሣችንና አምላካችን ወደ እኛ መምጣትህ የተባረከች ናት፤ ከጨለማውም ግዛት አድነህ ብርሃንንና ክብርን ወደተመላች መንግስትም አድርሰን።
[የሆሣዕና በዓል በሚደረግባትት ሰንበት ሌሊት የሚነበብ - የዐምዳዊ ስምዖን ድርሳን]
ከዚህ በላይ መድኃኒት የሆነውን ክርስቶስ መቀበል አለ?
@Learn_with_John

"አብረነው ከምንኖረው ሰው የምንወርሳቸው ብዙ ጠባያት አሉ። ይህ አብሮ ከማዋልና ከማደር የሚመጣ መወራረስ ነው። ንግግራችን፣ ሐሳባችን፣ ውሎ አዳራችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆንም እንዲሁ፤ በየዕለቱና በየጊዜው አዳዲስና፣ መልካም ነገሮችን እንወርሳለን። እነዚህም:- ፍቅር፣ ሐሴት ማድረግ፣ ለጋስነት፣ ትሕትና፣ ራስን ለሌሎች መሥዋዕት ማድረግ... የመሳሰሉት ናቸው። ጸሎት የአካልና የመንፈስ ቁስላችንን የሚያክምልን ፍቱን መድኃኒት ነው።"
🔥እናታችን እማሆይ ጣማፍ ኄራኒ🔥
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
እግዚአብሔር ያክብራችሁ እጅግ በጣም ነው የምንወዳችሁ😘 መልካም በዓል ነገ ቅዳሴ እንዳትቀሩ ደሞ😉 በጠዋት ወደ ቅዳሴ 🏃🏃 ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚሄዱ እግሮች የተባረኩ ናቸው፡፡😍

🌿🌿ዮሐንስ 12
13: የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፡ እያሉ ጮኹ።
ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ 🙏💐🌿🌿🌿

"ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ለእናንተ ያለኝ መውደድ፣ ለእናንተ ያለኝ ፍቅር የገለጽኩት መከራ መስቀልን በመቀበልም ነው እንጂ ብዙ ጸጋዎችን በመስጠት ብቻ አይደለም፡፡ ለእናንተ ስል ተተፋብኝ፡፡ ለእናንተ ስል ተገረፍኩኝ፡፡ ለእናንተ ስል አርአያ ገብርን ይዤ፣ ራሴን ባዶ አድርጌ [ክብሬንም እንደ መቀማት ሳልቆጥር] ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ ወደ እናንተ ወደምትጠሉኝ፣ ወደ እናንተ ፊታችሁን ከእኔ ወዳዞራችሁት፣ አዎ! ስም አጠራሬን እንኳን ለመስማት ወደ ተጠየፋችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፡፡
እፈልጋችሁ ዘንድ ከእኔ ርቃችሁ ወደ ኼዳችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፤ አግኝቼ ከራሴ ጋር አዋሕዳችሁ ዘንድም እናንተን ተከትዬ ሮጥሁ፡፡ ፈልጌና አግኝቼም አልቀረሁ ከራሴ ጋር አዋሐድኳችሁ፡፡ ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼ ‘ብሉኝ ጠጡኝም’ አልኳችሁ፡፡ ባሕርያችሁን ከራሴ ጋር አዋሕጄ በዘባነ ኪሩብ ላይ አስቀመጥኩት፡፡ በታች በምድርም በሥጋዬና በደሜ ያዝኳችሁ፡፡ ሌላውስ ይቅርና፥ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እኔን መስላችሁ ለምትነሡት ትንሣኤ ባሕርያችሁን ይዤና በኵር ኾኜ መነሣቴ በቂ አይደለምን? ይህ እናንተን ደስ ለማሰኘት በቂ አይደለምን? ከሰማየ ሰማያት የወረድኩት ግን ባሕርያችሁን በመዋሐድ ብቻ ለማክበር አይደለም፤ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን በመስጠት ከእናንተ ጋር ለማዋሐድም ጭምር ነው እንጂ፡፡ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
አዎ! የተፈተትኩት የተቆረስኩት የእኔና የእናንተ ትስስር፣ ውሕደትና አንድነት ይበልጥ ጽኑዕና ፍጹም እንዲኾን ለማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ነገሮች ቢዋሐዱ ተዋሕዶአቸው ጽኑዕ ስላልኾነ ሚጠት አለበት፡፡ እኔ ግን ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት እንደዚህ እንዲኾን አይደለም፡፡ ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት፣ አንድ ያደረግኩት ተዋሕዶአችን ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ነው፡፡”
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚ከኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ከሚለው መጽሐፍ
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
እሺ የክርስቶስ ተወዳጆች በርቱ እግዚአብሔር ያበርታችሁ ያጠንክራችሁ አሜን በእመቤታችን ፍቅር ሁላችሁንም እንወዳችኀለን♥♥ እናመሰግናለን
@Learn_With_John

ክርስቲያኖች_ሁላችሁ_ኑ_እናፅናናት
"ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። የተወደደ ልጇ በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር እንባን አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"

በመስቀል ላይ ሳለህ ራስህን ዘንበል (ዘለስ) ያደረግህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ ምስጋናን አሳርግ ዘንድ ለሞተውና ላዳነኝ ምስጋና ይሁን እያለች ነፍሴ በአምላካዊ በገና ታመሰግን ዘንድ የነፍሴን ራስ ከፍ ከፍ አድርግ ።
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በመስቀል ላይ የሞትክ በሞትህም ሞት ድል የሆነ አንተ እንደ አባትህ ሕያው ስትሆን በሥጋ ሞትን የምትቀበል ሁነሃልና ።
ሞትንም የምታጠፋው አንት ነህና አንተስ መቼም መች አንተ ነህ አንተም የሕይወት አካል ነህ ።
ለሞት ተሳብክ በአንተም ሞት ሞት ጠፋ ሕይወትነትህንም በአሳወቅኸው ጊዜ አይቶህ ሞት ጠፋ ድምፅህንም ሰምቶ ሞት ጠፋ ።
ሙታንም በአወቁህ ጊዜ ዳኑ ሕያው አንተ የሞትን ልብስ ለብሰህ ሙታን ወዳሉበት ወርደሃልና ።
ነፍስህ የሕይወትን መዐዛ እፍ ባለችባቸው ጊዜ ዳኑ ።
(የዓምዳዊ ስምዖን ጸሎት)

“እንደ ተናገረ ተነሥቷልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።” — ማቴ ፳፰፡፮ (28፡6)
"ትላንት ከእርሱጋ ተሰቅዬ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ እከብራለሁ ትላንት ከእርሱጋ ሞቼ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ ህያው እሆናለሁ ትላንት ከእርሱ ጋ ተቀብሬ ነበር ዛሬ ከእርሱ ጋር እነሳለሁ"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ)
"ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ሞተ ወኪዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሐበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ"
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘለዓለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ"
ስርዓተ ቅዳሴ ፻፸፫ (173)
ዛሬ ደፋሩ ሞት የተሻረበት ቀን ዛሬ በብሉይ ኪዳን ሞትን ፈርተን እንኖር ነበር የትንሳኤው በኩር መድኃኒታችን ሞትን በሞቱ ሲያጠፋው ግን ሞትሆይ በጌታ ሞት ድል ተነስተሀልና የሚፈራህ አጣህ ወደ ጌታችን ጋር መዳረሻ ድልድይ ሆንከን ስንሞትም በማልቀስ ፋንታ ድል አድራጊዋ ቤተክርስቲያን መዘመር ጀመረች።
ዛሬ የናዝሬቱ ፀሐይ ኢየሱስ ንጉሣችን በሞ ትላይ ነገሠ ሞትን አሳፈረው ጌታ ሰዱቃውያንን በትንሳኤው አሳፈራቸው ምክንያትም አሳጣቸው።
የነብያትን ተስፋ፣ የአበውን ናፍቆት፣ ዛሬ ትንቢትን ሁሉ ፈፀመ ትምህርታቸውን በተግባር አሳያቸው የክርስቲያኖችም መመኪያ ሆነ።
ዛሬ ጌታችን እርሱ ምርኩዝ መደገፊያ ሆኖን ሞትን፤ ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን እንቀጠቅጠው ዘንድ ረዳን በትንሳኤው ብርሃን ተስፋችንን እውን አደረገው አከበረንም።
ዛሬ የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ባህርያችንን አከበረው ቀደሰው ድኅነታችንን ፈፀመ በትንሳኤው ብርሃን ለእኛ ሰላምን አደረገ ሕይወትም ሆነን ድል አድርጉ ብሎ ፈለጉን አሳየን።
ዛሬ በዳግማዊው አዳም ትንሳኤ ቀዳማዊው አዳም ተደሰተ ምክንያቱም በትንሳኤው ብርሃን ብሉይነቱን አድሶለታልና ቀዳማዊት ሔዋንም በዳግማዊት ሔዋን ልጅ ድኅነት ሆኖላታል ከፍሬዋ ከፃድቁ አቤል ሞት ከሐዘን በቀር የጠቀማት ነገር ባይኖርም በልጅ ልጇ በተወዳጅ መድኅኗ ሞት ግን ተጠቅማለች ድኅነት ሆኖላት ወደነበረችበት ወደ ናፈቀችው ገነት ተመልሳለች።
ቀድሞ ከድንግሊቱ ማኅፀን እንደተወለደ ዛሬም ደግሞ ማንም ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር ፍቅር ተስፋን እውነተኛ ሰላምን ይዞ ከመቃብር ተነሳ
ቤተክርስቲያን በትንሳኤው ትደሰታለች ሙሽራዋ ሞቶ አልቀረምና ዘወትር ትንሳኤውን ትሰብካለች ከበዓላት ሁሉ በላይ ነውና ዘውትር በቅዳሴዋ ታስባለች ታከብረዋለችም እርሱ ባይነሳ ኖሮ ትምህርቷ ሁሉ ከንቱ ይሆን ነበርና
ትንሳኤው ለእኔ መንፈሳዊ ኩራቴ ሕይወቴ ተስፋዬ እምነቴ መዝሙሬ አርማዬ ጠንካራ ያረገኝ ሕይወቴ ነው የዚህ ድል አድራጊ ንጉሥ ልጅ በመሆኔ ደስታ ይሰማኛል።
መልካም በዓል አካሌ በዓሉን በመንፈሳዊ ቅናት ሆነን እናክብር እርሱ ሲነሳ እኛ አንሙት😢 ይልቅ ግን ከእርሱ ጋ አብረን ዕንነሣ
✍️አሸናፊ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እኔ በህይወት ዘመኔ እነዚህ አባቶች የሚያገለግሉትን የሚያመልኩትን መድኃኒት የሆነውን አምላክ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለማመልክ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ ካህናት የፀጋ ፀጋ የተሰጣቸው ልዩ የእግዚአብሔር አገልጋዩች ናቸው፡፡ ሌትም ቀንም ስለ እኛ በፀሎት የሚተጉ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ልዩ ስጦታችን ናቸው፡፡ ጌታችን አሁንም እድሜ ፀጋ በረከት ጤና ፀጋ በቃ ሁሉ ነገር ይስጣቸው፡፡ አሜን አሜን አሜን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን
@Learn_with_John
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን
@Learn_with_John
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
" ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፤"
"በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን ፤"
" አሰሮ ለሰይጣን ፤"
" አግዐዞ ለአዳም ፤"
" ሰላም ፤"
" እም ይእዜሰ ፤"
" ኮነ ፤"
" ፍሥሐ ወሰላም ።"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
#ሰኞ (ማዕዶት)፦
ማዕዶት ማለት (መሻገሪያ፣ መሻገር) ማለት ነው። ቀድሞ እስራኤላውያን ባሕረ ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል። ምሳሌነቱም ፈርዖን የዲያብሎስ፣ ሠራዊቱ የሠራዊተ ዲያብሎስ፣ ግብፅ የሲዖል፣ ባሕረ ኤርትራ የባሕረ ሲዖል፣ እስራኤል የምእመናን፣ ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር፣ በትረ ሙሴ የመስቀል ምሳሌ ሲሆን እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት ተሻግረው ምድረ ርስት እንደገቡ ነፍሳትም በክርስቶስ መሪነት ባሕረ ሲዖልን ተሻግረው ገነት የመግባታቸው ምሳሌ ነው። ስለዚህ ትንቢቱ ምሳሌው መድረሱን ለማጠየቅ ዕለቷ ማዕዶት ተብላለች።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
=>ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ