tgoop.com/learn_with_John/602
Last Update:
"ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ለእናንተ ያለኝ መውደድ፣ ለእናንተ ያለኝ ፍቅር የገለጽኩት መከራ መስቀልን በመቀበልም ነው እንጂ ብዙ ጸጋዎችን በመስጠት ብቻ አይደለም፡፡ ለእናንተ ስል ተተፋብኝ፡፡ ለእናንተ ስል ተገረፍኩኝ፡፡ ለእናንተ ስል አርአያ ገብርን ይዤ፣ ራሴን ባዶ አድርጌ [ክብሬንም እንደ መቀማት ሳልቆጥር] ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ ወደ እናንተ ወደምትጠሉኝ፣ ወደ እናንተ ፊታችሁን ከእኔ ወዳዞራችሁት፣ አዎ! ስም አጠራሬን እንኳን ለመስማት ወደ ተጠየፋችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፡፡
እፈልጋችሁ ዘንድ ከእኔ ርቃችሁ ወደ ኼዳችሁት ወደ እናንተ መጣሁ፤ አግኝቼ ከራሴ ጋር አዋሕዳችሁ ዘንድም እናንተን ተከትዬ ሮጥሁ፡፡ ፈልጌና አግኝቼም አልቀረሁ ከራሴ ጋር አዋሐድኳችሁ፡፡ ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼ ‘ብሉኝ ጠጡኝም’ አልኳችሁ፡፡ ባሕርያችሁን ከራሴ ጋር አዋሕጄ በዘባነ ኪሩብ ላይ አስቀመጥኩት፡፡ በታች በምድርም በሥጋዬና በደሜ ያዝኳችሁ፡፡ ሌላውስ ይቅርና፥ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እኔን መስላችሁ ለምትነሡት ትንሣኤ ባሕርያችሁን ይዤና በኵር ኾኜ መነሣቴ በቂ አይደለምን? ይህ እናንተን ደስ ለማሰኘት በቂ አይደለምን? ከሰማየ ሰማያት የወረድኩት ግን ባሕርያችሁን በመዋሐድ ብቻ ለማክበር አይደለም፤ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን በመስጠት ከእናንተ ጋር ለማዋሐድም ጭምር ነው እንጂ፡፡ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
አዎ! የተፈተትኩት የተቆረስኩት የእኔና የእናንተ ትስስር፣ ውሕደትና አንድነት ይበልጥ ጽኑዕና ፍጹም እንዲኾን ለማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ነገሮች ቢዋሐዱ ተዋሕዶአቸው ጽኑዕ ስላልኾነ ሚጠት አለበት፡፡ እኔ ግን ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት እንደዚህ እንዲኾን አይደለም፡፡ ራሴን ከእናንተ ጋር ያዋሐድኩት፣ አንድ ያደረግኩት ተዋሕዶአችን ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ነው፡፡”
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚ከኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ከሚለው መጽሐፍ
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
እሺ የክርስቶስ ተወዳጆች በርቱ እግዚአብሔር ያበርታችሁ ያጠንክራችሁ አሜን በእመቤታችን ፍቅር ሁላችሁንም እንወዳችኀለን♥♥ እናመሰግናለን
@Learn_With_John
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/602