Telegram Web
የእለቱ ጥያቄ
"እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ሰውነቴም ድና ቀረች"ብሎ የቦታውን ስም #ጵንኤል ብሎ የሰየመው ቅዱስ አባት ማነው?
Anonymous Quiz
36%
ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ሙሴ
33%
የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ
23%
ነብዩ ኤልያስ
8%
አባታችን አብርሀም
እሺ ሰዎች የዛሬው ጥያቄ #መልስ
ዘፍ ም፴፪ ቁ ፴
የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ ነው የተናገረው
እግዚአብሔር ያክብርልን
ወዮ! በእናንተ ፈንታ ኾኜ እኔ በጎ ምግባራችሁን ብሠራላችሁና እናንተም የእነዚህን ምግባራት ሽልማት መቀበል የምትችሉ ቢኾን እንዴት ደስ ባለኝ?! እንዲህ ቢኾን ኖሮስ እንደዚህ አድርጉ እያልሁ ብዙ ባላስቸገርኳችሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን እንዴት ማድረግ ይቻለኛል? ይህ በጭራሽ የማይቻል ነውና፤ እግዚአብሔር ለኹሉም ሰው ዋጋዉን የሚያስረክበው እንደ ሥራው ነውና፡፡ እናት የታመመ ልጇን ስታይ፣ ከትንታና በቃጠሎ (Inflammation) ከመንገብገብ የተነሣ ያገኘውንም ሥቃይ ስትመለከት አብዝታ ታለቅሳለች፤ ልጇንም፡- “ልጄ! እኔ ልንደድልህ፤ እኔ ልንገብገብልህ” ትለዋለች፡፡

እኔም፡- “ወዮ! እኔ በደከምኩላችሁ፤ ለኹላችሁም የሚኾን በጎ ምግባርም እኔ በሠራሁላችሁ” እላለሁ! ግን ምን ያደርጋል፤ ይህን ማድረግ አልችልማ! እያንዳንዱ ሰው በፍርድ ወንበር ፊት የሚቀርበው የየራሱን ሥራ ይዞ ነውና፤ አንዱም ስለ ሌላው ሰው የዘለዓለም ኩነኔውን ሊቀበልለት አይቻለውምና፡፡ ስለዚሁ ምክንያት ታምሚያለሁ፤ በዚያች ቀን ላይ ለፍርድ በተጠራችሁ ጊዜ ምንም ልረዳችሁ አልችልምና ጥልቅ የሆነ ኀዘን ይዞኛል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
እንግዲህ ❤️ቤተሰቦቻችን እንደተለመደው ያላችሁን አስተያየት በ @JohnDPT27 ላይ አድርሱን እንወዳችዋለን 😘😘
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

=>ሚያዝያ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት=
1.እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ
2.ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
3.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ (ክፉ ላለመናገር ዲንጋይ ጐርሶ የኖረ አባት)
4.ቅድስት ታኦድራ
5.ቅዱስ አርሳኒ
6.ቅዱስ ያሬድ ካህን (ልደቱ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ (አባ ገብረ ሕይወት)
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

💐ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💐
🕊 የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
የመጀመርያይቱ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት
ምዕራፍ 4ቁጥር 17
"ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?”
የቃሉ ባለቤት ጌታችነ መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገ ይሁን!!! አሜን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የእለቱ ጥያቄ ??
ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ " እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?" ብሎ እስከ ምፅአቱ ድረስ መኖሩን ያመለከተለት ቅዱስ አባት ማነው?
Anonymous Quiz
16%
ቅዱስ ጳውሎስ
76%
ቅዱስ ዩሐንስ
2%
ለቅዱስ ያዕቆብ
6%
ለሁሉም
እሺ የዛሬው መልስ
ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ??›››ዮሐ 21፡20 ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን
አሜን አሜን አሜን
ስለተሳትፎዋቹ እናመሰግናተን ተወዳጆች 😘😘😍በርቱልን
አቤቱ አምላኬ የሕይወቴ ጌታ ሆይ
የስንፍናን መንፈስ፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ስልጣን መሻትንና ከንቱ ወሬን ከእኔ አርቅልኝ
ነገር ግን በምትኩ የንጽሕናን፣ የትሕትናን፣ የትዕግስትንና የፍቅርን መንፈስ ለእኔ ለባሪያህ አድለኝ
አዎን፣ ጌታና ንጉሥ ሆይ የራሴን መተላለፍ እንድመለከት እንጂ በወንድሜ ላይ እንዳልፈርድ አድርገኝ
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ምስጉን ነህና፤ አሜን
[ቅ. ኤፍሬም ሶርያዊ]

O Lord and Master of my life,
Take from me a spirit of sloth, despair, lust of power, and idle talk;
But give rather the spirit of chastity, humility, patience, and love to Thy servant.
Yea, O Lord and King, grant me to see my own transgressions and not to condemn my brother
For blessed art Thou unto ages of ages. Amen.
[St. Ephrem The Syrian]
@Learn_With_John
"ሰማያዊውን ነገር ብቻ የምናስብ ከሆነና ከዓይናችን ፊት ካስቀመጥነው፤ ከራስ ወዳድነት ቀፎ ወስጥ ወጥተን ሁሉን የሰው ልጅ መውደድ እንጀምራለን። እግዚአብሔርን አብልጠን በወደድን ቁጥር አብልጠን እንመጸውታለን። አብዝተን ስንሰጥ ደግሞ፥ በግለኝነታችን ዓይን ሳይሆን በመንፈሳዊ (በእግዚአብሔር) ዓይን ማየት እንጀምራለን። በእርሱ ውስጥም በእኛ አድሮ የሚሠራውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እናያለን።"

🔥ቅዱስ ይስሐቅ ዘነነዌ🔥
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን 🙏

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን
እንግዲህ የአልመስጦአግያ ቤተሰቦች በሙሉ እንደተለመደው ያላችሁን አስተያየት👇👇 @JohnDPT27 ላይ አድርሱን እንዳትረሱ ደሞ በእመቤታችን ፍቅር እንደምንወዳችሁ😍😍😘😘
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን💐
=>ሚያዝያ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አዳምና ሔዋን (የዕረፍታቸው መታሠቢያ)
2.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት (ልደቱ)
3.አባታችን ቅዱስ ኖኅ (ልደቱ)
4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (የጌታችንን ጐኑን የዳሰሰበት)
5.ቅድስት ማርያም ግብፃዊት (ከኃጢአት ሕይወት ተመልሳ በፍፁም ቅድስናዋ የተመሠከረላት እናት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.እናታችን ሐይከል
3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
4.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
5.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
6.ቅድስት ሰሎሜ
7.አባ አርከ ሥሉስ
8.አባ ጽጌ ድንግል
9.ቅድስት አርሴማ ድንግል

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ዕብራውያን፡፡
ምዕራፍ 13 ቁጥር 5
"አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለመውደድ ይሁን ያላችሁም ይብቃችሁ፤እርሱ ራሱ፦አለቅህም ከቶም አልተውህም ብሏልና፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን፡፡ "
የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን አሜን!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጥፋቴ ይቺህ ቀን ድንበር ትሁነኝ😭😢
የእለቱ ጥያቄ
"መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለጠጋ ነህ የሰይጣን ማህበር ናቸው እንጂ.......ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ፡፡" ብሎ ጌታችን ወደ የትኛው ቤተክርስቲያን ላከ?
Anonymous Quiz
21%
በሰምርኔስ ወዳለው ቤተክርስቲያን
25%
በፊልድልፍያ ወዳለው ቤተክርስቲያን
37%
በኤፌሶን ወዳለው ቤተክርስቲያን
17%
በጴርጋሞን ወዳለው ቤተክርስቲያን
“These three things God requires of all the baptized: right faith in the heart, truth on the tongue, temperance in the body” [Gregory The Theologian]

ቅዱስ ጎርጎርዮስ እንደመከረን እግዚአብሔር በጥምቀት ልጅነትን ካገኘንባት ጊዜ ጀምሮ እነዚህን ሦስት ነገሮች ከእኛ ይሻል፦ በፍጹም እምነት የተሞላ ልብን፣ እውነትን ብቻ የሚናገር አንደበትን፣ ራስን በመግዛት የተሸለመ ሰውነትን። እነዚህን ፍሬዎች ለወይኑ ቦታ ጌታ እያፈራንለት ይሆን?
@Learn_with_John
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

ስንክሳር 🌳

=>ሚያዝያ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኢያቄም (የድንግል ማርያም አባት)
2.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
3.ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
4.ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች
"ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፡፡ ክፉውን ነገር ተፀየፉት ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ተዋደዱ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ፤ ለስራ ከመትጋት አትለግሙ፤በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ለጌታ ተገዙ፤በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሱ፤በፀሎት ፅኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ::"
ስለቃሉ የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን!!! አሜን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
2025/07/05 13:48:24
Back to Top
HTML Embed Code: