tgoop.com/learn_with_John/606
Last Update:
“እንደ ተናገረ ተነሥቷልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።” — ማቴ ፳፰፡፮ (28፡6)
"ትላንት ከእርሱጋ ተሰቅዬ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ እከብራለሁ ትላንት ከእርሱጋ ሞቼ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ ህያው እሆናለሁ ትላንት ከእርሱ ጋ ተቀብሬ ነበር ዛሬ ከእርሱ ጋር እነሳለሁ"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ)
"ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ሞተ ወኪዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሐበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ"
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘለዓለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ"
ስርዓተ ቅዳሴ ፻፸፫ (173)
ዛሬ ደፋሩ ሞት የተሻረበት ቀን ዛሬ በብሉይ ኪዳን ሞትን ፈርተን እንኖር ነበር የትንሳኤው በኩር መድኃኒታችን ሞትን በሞቱ ሲያጠፋው ግን ሞትሆይ በጌታ ሞት ድል ተነስተሀልና የሚፈራህ አጣህ ወደ ጌታችን ጋር መዳረሻ ድልድይ ሆንከን ስንሞትም በማልቀስ ፋንታ ድል አድራጊዋ ቤተክርስቲያን መዘመር ጀመረች።
ዛሬ የናዝሬቱ ፀሐይ ኢየሱስ ንጉሣችን በሞ ትላይ ነገሠ ሞትን አሳፈረው ጌታ ሰዱቃውያንን በትንሳኤው አሳፈራቸው ምክንያትም አሳጣቸው።
የነብያትን ተስፋ፣ የአበውን ናፍቆት፣ ዛሬ ትንቢትን ሁሉ ፈፀመ ትምህርታቸውን በተግባር አሳያቸው የክርስቲያኖችም መመኪያ ሆነ።
ዛሬ ጌታችን እርሱ ምርኩዝ መደገፊያ ሆኖን ሞትን፤ ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን እንቀጠቅጠው ዘንድ ረዳን በትንሳኤው ብርሃን ተስፋችንን እውን አደረገው አከበረንም።
ዛሬ የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ባህርያችንን አከበረው ቀደሰው ድኅነታችንን ፈፀመ በትንሳኤው ብርሃን ለእኛ ሰላምን አደረገ ሕይወትም ሆነን ድል አድርጉ ብሎ ፈለጉን አሳየን።
ዛሬ በዳግማዊው አዳም ትንሳኤ ቀዳማዊው አዳም ተደሰተ ምክንያቱም በትንሳኤው ብርሃን ብሉይነቱን አድሶለታልና ቀዳማዊት ሔዋንም በዳግማዊት ሔዋን ልጅ ድኅነት ሆኖላታል ከፍሬዋ ከፃድቁ አቤል ሞት ከሐዘን በቀር የጠቀማት ነገር ባይኖርም በልጅ ልጇ በተወዳጅ መድኅኗ ሞት ግን ተጠቅማለች ድኅነት ሆኖላት ወደነበረችበት ወደ ናፈቀችው ገነት ተመልሳለች።
ቀድሞ ከድንግሊቱ ማኅፀን እንደተወለደ ዛሬም ደግሞ ማንም ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር ፍቅር ተስፋን እውነተኛ ሰላምን ይዞ ከመቃብር ተነሳ
ቤተክርስቲያን በትንሳኤው ትደሰታለች ሙሽራዋ ሞቶ አልቀረምና ዘወትር ትንሳኤውን ትሰብካለች ከበዓላት ሁሉ በላይ ነውና ዘውትር በቅዳሴዋ ታስባለች ታከብረዋለችም እርሱ ባይነሳ ኖሮ ትምህርቷ ሁሉ ከንቱ ይሆን ነበርና
ትንሳኤው ለእኔ መንፈሳዊ ኩራቴ ሕይወቴ ተስፋዬ እምነቴ መዝሙሬ አርማዬ ጠንካራ ያረገኝ ሕይወቴ ነው የዚህ ድል አድራጊ ንጉሥ ልጅ በመሆኔ ደስታ ይሰማኛል።
መልካም በዓል አካሌ በዓሉን በመንፈሳዊ ቅናት ሆነን እናክብር እርሱ ሲነሳ እኛ አንሙት😢 ይልቅ ግን ከእርሱ ጋ አብረን ዕንነሣ
✍️አሸናፊ
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/606