Telegram Web
🌹🌹🌹🌹🌹

መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ለበረከት)

በስመ እግዚአብሔር

የአምልኮት ፍቅሩ ሐቅለ ሕሊና በሚያቃጥል በእሳታዊ እግዚአብሔር ስምና፤ ይህን ከንቱ ሰነፍ ዓለም በአማላጅነት ድንቅ ጥበቡ በምትፈውስ በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን አምላክን በወለደች በድንግል ማርያም ስም ጽልመተ አበሳን የምታስወግድ የብርሃን መቅረዝ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ቸርነትህን እመሰክር ዘንድ አዋጅ ነጋሪ ቅዱስ አንደበትህ በአየረ ሰማይ በልዕልና ጎልቶ ይሰማ። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! አዋጅ ነጋሪ በኾነ በቅዱስ አንደበትህ የንስሓ ትምህርተ ስብከት ከሰዎች ላይ የኃጢአት ሸክምን እንዳስወገድክ ከእኔም ከአገልጋይህ ላይ የሚያሰቃየኝን ጽኑእ የኃጢአት ክምር አስወግድልኝ።

ሰላም ለኩልያቲከ

ከአምላክ ልቡና ጋር ለሚስማማ ኵላሊትህና ሳይቅበዘበዝ በፀጥታ ለሚኖር ሕሊናህ ሰላምታ ይገባል። ዓለምን የናቅህ ንጹሐ ግብር ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በተጋድሎ የሥቃይ ግብረ ሕማም አንተን የሚመስለው የሰማዕታት ሹም ተርቢኖስ የተባለው ከመንፈስ ወንድምህ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋራ እኔን በቅድስት ተዋሕዶ እምነቴ እንድጸና በአማላጅነታችሁ ትረዱኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

🌹🌹🌹🌹🌹
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
"ልብኪ የዋህ ዘኢየአምር ተበቊሎ ለኃጥእ እምተኃጒሎ፡፡ ተሣሀልኒ ድንግል ዘልማድኪ ተሣህሎ ምንተ እነግረኪ ዉስተ ልብየ ዘሀሎ፡፡ እስመ አንቲ ተአምሪ ኀዘንየ ኩሎ፡፡"

እመቤቴ ማርያም ሆይ ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ ስለዚህም ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡

መልክአ ኤዶም
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"


*"የህይወት ስንቅ"*


አንድ ወጣት አንድን ታላቅ አባት ጥሩ
ሰው የሚባለው ምን የሚያደርግ ነው ብሎ ቢጠይቃቸው፤
:
*እኚህ ትልቅ አባትም መልሰው ይኸውልህ ልጄ አንተም ብትሆን ጥሩ ሰው ለመሆን ከፈለግክ ሊኖሩህ የሚገቡ ጉዳዮችን ላስቀምጥልህ ልብ ብለህ አድምጠኝ!!*
:
:::---::::---::::---::::---::::
1. "ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ጥሩ ሰው ማለት ፡-
:
~►ዘወትር ለኃጢአቱ የሚጨነቅና ይቅርታ የሚጠይቅ፤

~►ዘወትር በሥራና በትጋት የተጠመደ፤

~►ከመናገር ዝምታን ገንዘብ
የሚያደርግ፤

~►የፈጣሪን ትእዛዛቱን የሚጠብቅና እራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው በማለት መለሱለት፡፡
:
ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከመንፈሳዊ ሕይወቱ ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡

ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ
ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም በንስሐ ቶሎ ሲመለስ ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል፤

ስለዚህ ንስሐን እንደ ቀላል ነገር አትቁጠረው፤

2 ." መልካምነት ውደድ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ከተሰወረ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ፣ ከጠላት መልካም ሐሳብ የወዳጅ ክፉ ምክር፣ ከራቀ ወንድም የቀረበ ወዳጅ ሳይሻል እንደማይቀር አትዘንጋ፤

መልካም ሞት የመልካም ኑሮ ውጤት ነው፤

አንደበተ ትልቅ ውስጠ ቀላል እንዳትሆን ተጠንቀቅ

3. "በፈጣሪ እንጂ በደጋፊዎች አትተማመን!"
:::---::::---::::---::::---::::

በደጋፊዎች ከተማመንክ ከሰባራ ወንበር ላይ እንደተቀመጥክ ቁጠረው፤

የሰይጣን ደህና ባይኖረውም፣ ብቻውን ካለ ሰይጣን ይልቅ በሰው ላይ ባደረ ሰይጣን ተጠንቀቅ፣ በሰው ላይ ያደረ ሰይጣን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስትለው ከሰውየው ጋር ተጣብቆ ያስቸግራልና፡፡

4 ."ካለፈው ስህተትህ ተማርበት እንጂ አትማረርበት!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰዎች በአንተ ላይ ምንም እንዳያወሩ ሥልጣን የለህምና፤ የሚሉህን እየሰማህ ስህተትህን አስተካክል፤
:
5 ."አስፍቶ መረዳትን አዳብር!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሌሎች እንዴት ማጥቃት እንዳለብህ
የሚነግርህን ሰው ሌላ ጊዜ እሱ ሲያጠቃህ እንዴት መካለከል እንዳለብህ እየነገረህ እንደሆነ ተረዳው።
:
ሌሎችን ቀርበህ እንዴት እንደምትወድ የሚነግርህን ሰው ግን ለፍቅር እድል ስጠው።
:
6 ." ለመታመን ማመን አለብህ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ሰውን ማመን ቀብሮ ነው የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው።
:
ለማመን ሰው መቅበር ካስፈለገ
የተቀበረን ለማመንም መቀበር ሊያስፈልግ ነው።
:
ሰውን የማምነው ቀብሬ ከሆነ ሌሎችም እኔን የሚያምኑኝ ቀብረውኝ ነው።
:
መኖር ግዴታ በሆነበት ህይወት ውስጥ ሞት መብት አይሆንም።
:
ማንኛውም ሰው ራሱን በህይወት ማቆየት እንጂ ለመሞት ራሱን መግደል አይችልም።
:
ነገር ግን ራስን ለመግደል ቀላል ዘዴ አለ። :
►መጀመሪያ ማሳብ ማቆም።
:
►ቀጥሎ ማሰብ ያቆምከውን አሳብ መኖር።
:
7. "ለማድረግ ተዘጋጅ!"
:::---::::---::::---::::---::::
:
ለማድረግ ስታስብ እጥፍ አድርገህ አስብ!"
:
ያሰብከውን ስትተገብር በቁመትህ ልክ አድርግ።
:
ከፍ ባልክ ቁጥር ከፍታህ ቋሚ መድረሻህ አለመሆኑን እወቅ።
:
ወደ ላይ ከፍ ስትል ወደ ታች ተመልከት።
:
በከፍታህ ወቅት ወደታች መመልከትህ ስትወድቅ የምታርፍበትን ምቹ ቦታ እንድትለይ ያደርግሀል።
:
8. "ለችግር የተሸነፍክ አትሁን !"
:::---:::::---::::---::::---:::::
:
በህይወትህ ችግር ሲያጋጥምህ ችግሩን መለየት የመፍትሄ መጀመሪያ መሆኑን ተረዳ።
:
ችግሩን የመለየት መጀመሪያው ደግሞ አንተ ራስህ በራስህ ችግር አለመሆንህ ለይቶ ማረጋገጥ ነው።
:
ሳያልፍ የመጣ ክፉ ነገር የለምና እስኪያልፍ ታገሥ፤

9 ."ትንሽ ለመስጠት አትፍራ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የስጦታ ዋጋ በተቀባዩ ስሜት እንጂ በስጦታው ይዘት አይወሰንም።
:
ለሰጪው ትንሽ የሆነ ለተቀባዩ ትልቅ ዋጋ አለው።
:
10. "ክብርህን ከምግባርህ እንጂ ከሰው አትጠብቅ !"
:::---::::---::::---::::---::::
:
የምትቀበለው አንተ አስቀድመህ በሰጠኸው ልክ ነውና!
:
ለመከበር ፤ ለመወደድ ፤ ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት አንተ አስቀድመህ ሌሎቹን አክብር ፤ ውደድ ፤ጥሩ ጓደኛም ሁንላቸው ምክንያቱም መልካምነት ለራስ ነውና!
:
በህይወታችን ለሰዎች ከክፋት የነጻ
በፍጹም ንጹሕ ልቦና መልካምና ቅን ሆነን እንኖር ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!
/// አሜን 3x ///
እናቱ እናቴ - ልደትሽ ልደቴ !

+ + +
ለእናትነት ክብር - እርሱ ከመረጠሽ
በዮሐንስ በኩል - ለእኔ ከተሰጠሽ
እኔም እርሱን ጌታ - ብዬ ከተቀበልሁ
ማዳኑን አምኜ - በሕጉ ስር ከዋልሁ
እናቱን እናቴ - ብየ ለመቀበል...
ጥያቄ ልደርድር? ለምን? እንዴት? ልበል?
+ + +
ልጅሽ በምድር ላይ - ሥጋሽን በመልበስ
አዳምን ሊያድነው - ለእኛም ጽድቅን ሊያወርስ
የረገጠው መሬት - የቆመበት ቦታ
ከቤተልሄም ዋሻ - እስከ ጎለጎታ
ቅዱስ ከተባለ - ውሎ ያደረበት
ልዩ ክብር ካለው - የተሰቀለበት...
አንችማ እናቱ - ማህፀን ዓለሙ
የሰውነት ልኩ - ሥጋውና ደሙ
እንዴት አትከብሪ!? እንዴት አትቀደሽ!?
እንዴት አትወደጅ!? እንዴት አትወደሽ!?
+ + +
እንኳንስ ለእኔና...
ለእርሱም ለጌታችን - ፈጣሪ ለሆነ
እናቱ መባልሽ - ይህ እውነት ከሆነ
እናቴ መሆንሽ - እንዴት አልታመነ???
+ + +
በሥጋ ያይደለ - በረቀቀ መንፈስ
እናቴ ሆነሽኝ - ያንችን ክብር ብወርስ
ይሄንን መታደል - እንዴት እገፋለሁ?
እናቱ እናቴ ነሽ! - ተቀብየሻለሁ!!!
+ + +
ፈጣሪን ልትወልጅው - አምላክን ልታ’ዥው
ሰማይና ምድር የማይወስኑትን - በእቅፍሽ ልትይዥው
ከድንግልና ጡት - ወተት ልታጠቢው
የዓለሙን መጋቢ...
ከደኃ ማጀትሽ - ሲራብ ልትመግቢው
እናት አባትሽን - ከእስር ልታስፈቺ
የክፋትን አባት - በፍቅር ልትረቺ
ከሀና ከኢያቄም - የተወለድሽ አንቺ
እናትና ድንግል - ንግሥትና አገልጋይ
ሰማየ ሰማያት - ጽርሐ አርያም ሆይ!
የአንቺ ግሩም ልደት - ለእኔም ነው ልደቴ
የጥምቀት መሥራቹ - ልጅሽ ነው አባቴ
ዳግም የተወለድሁ - ከውኃና መንፈስ
ባንቺ መወለድ ነው - የአዳም ተስፋው ሲደርስ
ሕይወት የሆነልን - የልጅሽ ሥጋና ደም
ከአንቺው ነው የነሳው - ከላይ አልወረደም
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እና ነሽ - ልደትሽ ልደቴ
+ + +
+
ቅድስተ ቅዱሳን - ንጽሒተ ንጹሐን
ማሕጸኑ ለጽድቅ - እናቱ ለብርሃን
ሰማየ ሰማያት - ታናሽ ብላቴና
ከእያቄም ወሀና - ተወለደሻልና
ዓለም ብርሃን አየ - ውስጥሽ ባለው ፀሐይ
አዳም ቀና አለ - ተስፋ ብርሃኑን ሊያይ
ፍጥረታት በሙሉ - ከሰማይ ከምድር
በደስታ ተመሉ - ልደትሽ ሲነገር
ተወለደሻልና - የፀሐይ እናቱ
ጽርሃሐ-አርያም ሆንሽ - ብላቴናይቱ !
+ + +
+
(፡›አበው ስለክብርሽ - ቃላት አጠራቸው
ስለ ደም ግባትሽ - ምሳሌ ጠፋቸው
እኔ ግን ደፋሩ - እዘባርቃለሁ
ባልበሰለ ብዕር - ቃላት እመርጣለሁ
በተንሸዋረረ ዓይን - ክብርሽን አያለሁ
ምልጃሽን እያሰብሁ - በተስፋ እኖራለሁ‹፡)
+ + +
የብርሃን እናቱ - የፀሐይ ምሥራቁ
የአዳም ሙሉ ተስፋ - የሰይጣን መብረቁ
ስለ አንቺ መወለድ - ዓለም ተፈጠረ
ስለ አንቺ መወለድ - የሰው ልጅ ከበረ
አዳምና ዘሩ - በኃጢአት ቢረክሱ
በአንቺ መወለድ - ግን በክብር ነገሡ
በአንቺ ልዩ ልደት - አዳም አምላክ ሆነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ክብራችን ገነነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ዲያብሎስ ታሰረ
በአንቺ ልዩ ልደት - ባሪያ መሆን ቀረ
እኔም ደፋር ሆንኩኝ - ፍርሃት ተሰወረ
ባዶው አዕምሮዬ - ክብርሽን ነገረ፡፡
+ + +
ሰማይና ምድር - ልደትሽን ሲያከብሩ
ሊቃውንት ሲቀኙ - መላእክት ሲዘምሩ
ክብርሽን ተማምነው - በምልጃሽ ያደሩ
በምህረት ቃል ኪዳን - ለክብር ሲጠሩ
እንደልጅነቴ ለእኔም - እንዲደርሰኝ
እንባሽን አስታውሶ - ልጅሽ እንዲምረኝ
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
የአንቺ መወለድ ነው - የጽድቅ መሠረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እናቴ ነሽ - ልደትሽ ልደቴ፡፡


ተጻፈ በተክለ ስላሴ
10-6-2020
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"


► ይቅር ስትል በትክክል መኖር ትጀምራለህ፤
► ይቅር ማለት የደካማዎች አይደለም፤
► የበደሉህን ይቅር ማለት የመንፈስ
ጥንካሬ እና በራስ የመተማመን ምልክት
ነው፤
► ይቅር ስትል ታድጋለህ፤
► ይቅር ስትል ልብህ ይሽራል፤
► ይቅር ስትል ቀጥ ብለህ ትቆማለህ፤
► ይቅር ስትል አይኖችህ ንፁህ ይሆናሉ
ከዚያም ፊት ለፊትህ ያለውን መንገድ
በግልፅ ታየዋለህ። ብስጩነት የመንፈስ
ህመም ነው፤
► ይቅር ስትል በትክክል መኖር
ትጀምራለህ!!!

እግዚአብሔር ይቅርታ የሚጠይቅ አንደበትን ይቅር የሚል ልብን ያድለን።
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰውረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
​​የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜

የሉቃስ ወንጌል 24:6-7

"​​የሰው ልጅ በኃጢያተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ። "

ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን አሜን!!
"ሰይጣን ክፉ ነው፡፡ ቢሆንም ደካማ ነው፡፡ እርሱ ጋር ካለው ኃይል እኛ ጋር ያለው ጸጋ እግዚአብሔር ይበልጣልና፡፡ እኛው ራሳችን በፍቃዳችን ከረድኤተ እግዚአብሔር እያራቅን በሄድን ቁጥር ግን እርሱ እየፈራ እየተንቀጠቀጠም ቢሆን እየቀረበ ይመጣል፡፡ ቤቱ ዘበኛ ከሌለው አልያም እንዲሁ ክፍት ከሆነ ሌባ እየፈራም ቢሆን እንደሚገባ፡፡ ለቀዳማይቱ ሔዋን ያደረገውም እንደዚህ በቀስታ ነበር፡፡ አስቀድሞ በኀልዮ (በሐሳብ) ይሞክራል፡፡ በጣም መንቻካ ከመሆኑ የተነሣም ይህን ደግሞ ደጋግሞ ያደርገዋል፡፡ ሐሳቡን ለመቀበል ዝግጁዎች እንደሆንን ሲረዳም ሐሳቡን ፈጥነን ወደ ገቢር (ተግባር) እንድንለውጠው ሹክ ይለናል፡፡ ይህም እንደ ሐሳቡ ደጋግሞ ያደርጓል፡፡ በተለይ ምቹ.ሁኔታዎችን ሲመለከት ይህን ደጋግሞ ይሞክራል፡፡ እንደ ተዘጋጀን ሲያውቅም ክፉ መርዙን እፍ ይልብናል፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጠረናል፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ ከወደቅን በኋላ የመጀመርያው ከሳሻችን እርሱ መሆኑ ነው፡፡ “አሁን አንተ መንፈሳዊ ነኝ ትላለህ፤ ሆኖም ደግሞ እንዲህ በመሰለ ርካሽ ኀጢአት ትወድቃለህ” እያለ ሰላም ያሳጣናል፡፡ ለሁሉም ግን ወደ እግዚአብሔር መመለሱ ይሻላል፡፡ በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት “የሰነፍ አእምሮ የሰይጣን ቤተ ሙከራ ነው” ነፍሳችንን ቃለ እግዚአብሔርን አናስርባት፡፡ በየጊዜው ምክርን ከሐኪሞቻችን (ከንስሐ አባቶቻችን) እንሻ፡፡"

🌹ቃለ ሕይወት ያሰማን 🌹

🌿የእግዚአብሔር ቸርነት🌿
🌷የእመቤታችን ምልጃ 🌷
🌳የቅዱስ ሚካኤል ጠባቂነት🌳
🌹የቅዱሳን ሁሉ በረከት🌹
ከሁላችን ጋር ይሁን

🕊የሰላም ሌሊት
🕊
🍀🌹🌹🍀
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
📖መዝሙረ ዳዊት
ምዕራፍ146:1-3
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ።
በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ።

ስለቃሉ የቃሉ ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ እና ስሙ ከፍ ከፍ ያለ ይሁን አሜን
“ዘአነ” ከተባለ መጽሐፍ ይጠንቀቁ፡፡

- “ዘአነ” የተሰኘ በግዕዝ ቋንቋ ርእሱን ያደረገ መጽሐፍ ወልደ ሰማዕት በተባለ ተጽፎ በስንዱ (እህተ ማርያም) “መድኃኔ ዓለም እና ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር” ታትሞና ተዘጋጅቶ በቅርቡ ተመርቋል፡፡ ይህን መጽሐፍ በነጻ ይታደላል፡፡ በማንኛውም መንገድ መጽሐፉን ለማሰራጨት ጥረት ስለሚያደርጉና የተሳሳተ ትምህርት ሊኖረው ስለሚችል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን ምዕመናን እንዳትጭበረበሩ ለማለት እንፈልጋለን፡ በተለይ ለሕጻናት ልጆቻችሁ ማሰብ በጣም ተገቢ ነው፡፡ የእነ ስንዱ ማኅበር እንደፈለጉ የሚፈነጩበት የራሳቸው ዘመን አቆጣጠር (Calendar) እንደሚጠቀሙ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡ዲ/ን ዮሴፍ ፍስሐ
ስሞዖን ወአቅሌስያ ዘነበሩ በንሒሳ በኃጢአ ዉሉድ በከዩ
መጠነ ዓመታት ሠላሳ። ሥሉስ ቅዱስ ሶበ ነፍኁ በዉስተ
ከርሣ። ተወልደ እምኔሆሙ ቀናዬ አናብስት ስሳ ። በኀይለ
አምላኩ ዘይሠሪ አበሳ። አብ በዘባኑ ወልድ በዘበኑ መንፈስ
ቅዱስ በዘበኑ ዘሐዘልዎ በኪዳኑ ። ገብረ መንፈስ ቅድስ
ሠለስተ ገፃተ ዘይዜኑ ። አዋክየ አዋክየ አዋክየ ሥኑ ።
በኢትዮጵያ ዘተቀብረ በድኑ። ኦ አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ዕቀበኒ ወአድኀነኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለሕዝበ ክርስቲያን
አሁን አንድ አባት እደነገሩኝ በስልክ

ጠቅላይ ቤተክህነት በፌደራል ፖሊስ ተከቧል። መውጣትም ሆነ መግባት እንደማይቻል ተገልጿል።

ከአባቶች ጋር ለመወያየት የመጡ የአቃቂ ቃሊቲ ማኅበራት ኅብረት ወጣቶችም እንደታሰሩ ምንጮች ገልጸዋል።

ምን አይነት ፈተና እደመጣብን አላወቅም እግዚአብሔር ሁሉንም ሰላም ያድርግልን

@KeAbawandebet
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"


✞ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ክፉውን ነገር ተጸየፉት ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ !! በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ !!!

📢 ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ በመከራ ታገሡ በጸሎት ጽኑ !!!

📢 ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ፤ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

👉 ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ የትዕቢትን ነገር አታስቡ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ፤ ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።

✞ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ !!!

💒 ሮሜ ሰዎች ም/12 : 9 .. ...💒



🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
🕊 🕊🕊
🕊
ቃለ ሕይወትን ያሰማን

🌹 የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
🌹 የእመቤታችን ጸሎት 🌹
🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን

የፍቅር ዘመን፤ የቸርነት ፤የይቅርታ፤የምህረት አመት ያድርግልን፤

🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🥀🕊🥀🌹🥀 🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
🕊🕊 🕊 🌹🌹🌹🕊🕊🕊
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

=>ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1. ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል)
2. ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት)
3. አባ ሚካኤል ገዳማዊ
4. አባ ይስሐቅ ግብጻዊ

=>ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
“እርሱ ብቻ #የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል *ብርሃን_ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ #አላየውም #ሊያይም_አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16
የቃሉ ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱ5ስ ክርስቶስ ስሙ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን አሜን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእስራቴ አላፍርም
እኔ የማርያም ነኝ 🙏💐
ከእመቤቴ ፍቅር የሚለየኝ ምንድነው መከራ ነው ወይስ ችግር ወይስ እስራት ነው?
በእስራቴ አላፍርም በፀሀይ እናት ደስ ይለናል ❤️
ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን አባታችን እንግዳወርቅ በመዝሙሮችህ አሳድገኸናል እግዚአብሔር እድሜ እና ፀጋ ይስጥልን
አሜን አሜን አሜን
2025/07/04 11:01:34
Back to Top
HTML Embed Code: