tgoop.com/learn_with_John/692
Last Update:
"ሰይጣን ክፉ ነው፡፡ ቢሆንም ደካማ ነው፡፡ እርሱ ጋር ካለው ኃይል እኛ ጋር ያለው ጸጋ እግዚአብሔር ይበልጣልና፡፡ እኛው ራሳችን በፍቃዳችን ከረድኤተ እግዚአብሔር እያራቅን በሄድን ቁጥር ግን እርሱ እየፈራ እየተንቀጠቀጠም ቢሆን እየቀረበ ይመጣል፡፡ ቤቱ ዘበኛ ከሌለው አልያም እንዲሁ ክፍት ከሆነ ሌባ እየፈራም ቢሆን እንደሚገባ፡፡ ለቀዳማይቱ ሔዋን ያደረገውም እንደዚህ በቀስታ ነበር፡፡ አስቀድሞ በኀልዮ (በሐሳብ) ይሞክራል፡፡ በጣም መንቻካ ከመሆኑ የተነሣም ይህን ደግሞ ደጋግሞ ያደርገዋል፡፡ ሐሳቡን ለመቀበል ዝግጁዎች እንደሆንን ሲረዳም ሐሳቡን ፈጥነን ወደ ገቢር (ተግባር) እንድንለውጠው ሹክ ይለናል፡፡ ይህም እንደ ሐሳቡ ደጋግሞ ያደርጓል፡፡ በተለይ ምቹ.ሁኔታዎችን ሲመለከት ይህን ደጋግሞ ይሞክራል፡፡ እንደ ተዘጋጀን ሲያውቅም ክፉ መርዙን እፍ ይልብናል፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጠረናል፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ ከወደቅን በኋላ የመጀመርያው ከሳሻችን እርሱ መሆኑ ነው፡፡ “አሁን አንተ መንፈሳዊ ነኝ ትላለህ፤ ሆኖም ደግሞ እንዲህ በመሰለ ርካሽ ኀጢአት ትወድቃለህ” እያለ ሰላም ያሳጣናል፡፡ ለሁሉም ግን ወደ እግዚአብሔር መመለሱ ይሻላል፡፡ በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት “የሰነፍ አእምሮ የሰይጣን ቤተ ሙከራ ነው” ነፍሳችንን ቃለ እግዚአብሔርን አናስርባት፡፡ በየጊዜው ምክርን ከሐኪሞቻችን (ከንስሐ አባቶቻችን) እንሻ፡፡"
🌹ቃለ ሕይወት ያሰማን 🌹
🌿የእግዚአብሔር ቸርነት🌿
🌷የእመቤታችን ምልጃ 🌷
🌳የቅዱስ ሚካኤል ጠባቂነት🌳
🌹የቅዱሳን ሁሉ በረከት🌹
ከሁላችን ጋር ይሁን
🕊የሰላም ሌሊት
🕊
✟🍀🌹🌹🍀✟
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/692