Telegram Web
ኢዜማን እንደገና!

ምን ማለታችን ነው?

ፓርቲያችን ኢዜማ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ካሉት የሰላማዊ ፖለቲካ አራማጅ ፓርቲዎች በይዘትም በተደራሽነትም ከግንባር ቀደም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ የመጀመሪያው ነው። ይህ ፓርቲ በብዙ እህቶችና ወንድሞች የጋራ መስዋዕትነት የተመሰረተ እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የፀና ነው። ሚሊየኖች ተስፋቸውን የጣሉበት የፖለቲካ ስብስብ የተጣለበትን እምነት ይበልጥ ለማጠናከርና ታዓማኝነቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደገና ተጠንቶ: ጊዜውን የዋጄ መሆን አለበት።

ይህን ሰፊ የህዝባዊ ተቀባይነት ወደ የሚታይ የለውጥ ፋና ወጊነት ለማድረስ ትናንት የተነሳበትንና ዛሬ ያለበትን በመገምገም እራሱን ለነገ ማብቃት ይገባዋል። መላው ኢዜማዊያን በነቂስ ወጥተው የኢትዮጵያ ተስፋ የሆነውን ፓርቲ የውስጥ ግምገማና ምዘና በማድረግ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትልና ተቋማዊነት ለማረጋገጥ ተተኪዎችን ማፍራት ይገባዋል። የነበረውንና በሰፊው ህዝብ አመነታ ያገኘበትን የፖለቲካ አቋም: የተነሳበትን ህዝባዊ ጥያቄ ምላሽ ከምን እንደደረሰ የሚያጠናና በቀጣይ ለሚደረጉ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች ራሱን ያዘጋጀ የነገው ትውልድ አደራ ተቀባይ መሆን የሚችል ተቋም ሊገነባ ይገባል። እስከዛሬ የመጣበትን የኋሊት እያየ የወደፊት መድረሻውን ከተለዋዋጭ የፖለቲካ ኹናቴ ጋር እያስተያየ በየጊዜው ራሱን ማደስ የሚችል ተራማጅ ሀይል መሆን አለበት።

i, የውስጥ ግምገማ

ዋና ዋና የፖለቲካ መርሆቻችን ላይ እስከዛሬ ድረስ እንዴት እንደተጓዝን: በየትኞቹ ጎልተን ወጥተን በህዝብ ይሁንታ እንዳገኘን: የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች በጋራ በመቀመጥ ከትናንት እስከዛሬ የተጓዝንበት የአብሮነት መንገድ በነፃነት መተንተን መገምገምና ጥንካሬዎቻችንና ድክመቶቻችን መለየት አለባቸው። ይህ የውስጥ ተሃድሶ የፖለቲካ ፓርቲ ሥራዎቻችን በማጥራት በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሊሰፍን የሚችለውን የፖለቲካ ሂዴትና ተለዋዋጭነት መቋቋም የሚችል እንዲሆን አቅሙን ማሳደግ ይጠበቅበታል።

የውስጥ ግምገማችን መሠረታዊያን:

ሀ/ የመመሪያዎችና ደንቦችን

የተሻሻለው የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ በተግባር ሲፈተሽ ምን ዓይነት የአሠራር ለውጥ አምጥቷል? የመተዳዳሪያ ደንቡ ተግባራዊነት ምዘና ተደርጎበት በውስጡ የጎደለውን ክፍተት በመሙላት አሰሪ እና ገዢ በሆኑ መንገዶች መቃኘት ይገባዋል። የመተዳደሪያ ህገ ደንብ: የአሠራር መመሪያዎች: የስነ ስርዓት ደንቦች እና ሌሎች የጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔዎች በማይጣረሱ መልኩ ወደ ተግባር ሊለወጡ የሚገባቸው ስለሆነ በግልፀኝነትና በነፃነት ውይይት በማድረግ አቃፊ አሳታፊና ተፈፃሚ እንዲሆኑ መስራት

ለ/ በመደራጀታችንና በህብረት ፖለቲካ በመስራታችን እንደአንድ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ በሀገራችን በተነሱ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ የነበረንን: ያለንና የሚኖረንን ሚና በዝርዝር ትንታኔ በመለየት በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያለንን የማሳካት: የማሻሻልና የማስፈፀም አቅማችን በመዘርዘር የተግባር ግምገማ ሊናደርግ ይገባል

ሐ/ የግብረ መልስ ትንታኔ

እንደአንድ መሪ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ከምስረታችን ዕለት ጀምሮ ከነባር የፖለቲካ ታጋዮች እስከ አዳዲስ የፖለቲካ ትውልድ ገፆች: ደጋፊም አባላትም አመራርም ከነበሩ አካላት የትግል ምልከታ ግብረ መልሶችን ከልብ በመቀበል እራስን ወደውስጥ መፈተሽ ይጠበቅብናል። ከፓርቲያችን ውጪ ያሉ በተመሳሳይ የአንድነትና የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄ ከሚሰሩ ተቋማትና ደጋፊዎች: ከገዢውና ከተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዋናነት ደግሞ ከሰፊው መራጩ ህዝብ የሚሰጡንን ግብረ መልሶችን በመቀበል ኢዜማን እንደገና መስራት ይጠበቅብናል።

2, የመዋቅር ኹናቴ

ኢዜማን ከሌሎች የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለየው የአደረጃጀት መሠረቱን ከምርጫ ክልል መጀመሩ ነው። ይህ ፓርቲው ህዝባዊ መሠረት እንዲኖሩት ካደረጉት የኢዜማ አምዶች መካከል አንዱ ነው። ፓርቲያችን በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሄድ ከተፈለገ የማያቋርጥ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትል ያስፈልገዋል። የማህበራዊ መሠረቱን ተደራሽነትና ስፋት እንደገና በማጥናት እንደየአስፈላጊነቱ የመዋቅር ማሻሻያም ሊያደርግ ይገባል። የኢዜማ ተቋማዊ መሰረት ከዋና ቢሮው በተጨማሪ ሌሎች ጽ/ቤቶችም ክረምት በጋ የሚሰሩ 24/7 ለአባሎቻችን ክፍት የሆኑ የፖለቲካ ስራ የሚሰራባቸው ተቋማዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት።

3, ተተኪ ማፍራት

ለቀጣዩ ትውልድ የምናቀበለው የማህበራዊ ፍትህ የማስፈን ጥያቄን በሚታይ በሚጨበጥና በሚቆጠር የተተኪ ትውልድ ላይ መስራት አለበት። የኢዜማ አዲሱ ትውልድ የዘመኑን ፖለቲካ የተረዳ የኋላ ታሪኩን የማይዘነጋ ስለነገ የሚሰራ አዲስ የፖለቲካ ትውልድ ለመፍጠር በቁርጠኝነት መስራት አለበት። ፓርቲው በቀጣይ አንግቦት የተነሳውን ጥያቄዎችን የሚያስቀጥሉለት ስንት አባላት አሉት? ስንት አመራሮችን አብቅቷል? ይህ በወረቀትና በምዕናብ የሚቀርብ ብቻ ሳይሆን የሚታይና የሚጨበጥ መሆን አለበት።

እኚህ ከላይ የቀረቡትን የአማራጭ ሀሳቦች ላይ በመምከር ሁላችን የምንወደውንና ዋጋ የከፈልለትን ፓርቲያችን እንደገና በማደራጀት: በማደስ: ወደ ልህቀት መምራት እንችላለን።

ኢዜማ አጠቃላይ ሂደቱንና ጉዞውን ከመነሻው ሀሳብ ጋር በማነፃፀር እንደገና ራሱን ለመጭው የፖለቲካ ጉዞ ማዘጋጀት ስላለበት ይህ የፓርቲያችን የአብላጫው አባላት ጥያቄ መሆኑን ለማስገንዘብ ከጎኔ በመሆን ድጋፍ እንድታደርጉልኝና በቀጣይም ብቁ ተገዳዳሪ የሀገራዊ ፓርቲ ስብስብ እንድንሆን እንደገና መስራት ይጠበቅብናል።

ዶ/ር ካሳሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ
ኢዜማን እንደገና!
ለሊቀመንበርነት ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ይመኑ

ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በትምህርት ዝግጅቴ በሕክምና የዶክትሬት ዲግሪ አለኝ፤ የማኅበረሰብ ጤና አጠባባቅ ስፔሻሊስትም ነኝ፡፡ በተጨማሪም በቪዥዋል/ፐርፎርሚንግ ጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪ አለኝ፡፡ ከኢዜማ ምሥረታ በፊት በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ የድጋፍ ማኅበር ኮሚቴ ኾኜ ካናዳ ውስጥ የፖለቲካ መድረኮችን በማዘጋጀት ተሳትፍያለሁ፡፡ በ 2011 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ኢዜማን ለመመሥረት በነበረው ሂደት በጤና እና ትምህርት ፖሊሲ ዝግጅት ቡድን ውስጥ እንዲሁም የምርጫ ክልል 24 አባል ኾኜ ለኢዜማ ምሥረታ ጉባኤ ምርጫ ክልሉን ወክዬ ተሳትፊያለሁ፡፡ በምርጫ 2013 ኢዜማን ወክዬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተወዳድሪያለሁ፡፡

ከኢዜማ ምሥረታ ጀምሮ በተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ እንዲሁም ሰኔ 2014 ዓ.ም በተካሄደው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመኾን አገልግያለሁ፡፡ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ አስፈጻሚ አባልነት፣ በዓለም አቀፍ የድጋፍ ማኅበር ተወካይነት፤ ቀጥሎም የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ኃላፊ በመኾን እስከአሁን ድረስ ፓርቲያችንን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡

ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በመልካም ሥነምግባሬ፣ በትምህርትና ሥራ ተሞክሮዬ እንዲሁም ለሀገሬ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር እታወቃለሁ፡፡ በኪነጥበቡ ዘርፍ የግጥም ወዳጅ ሲኾን፤ ሦስት የግጥም ስብስበችን አሳትሜ ለሕዝብ አቅርብያለሁ፡፡ ዘንድሮ በሚካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም ለሊቀመንበርነት ለመወዳደር ዕጩ በመሆን አልፊያለሁ፡፡

ለምክትል ሊቀመንበርነት ማዕረጉ ግርማ ኃይሉ

በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በመሠረታዊ የጋዜጠኝነት ሙያ በተለያዩ ተቋማት ከሦስት በላይ ሰርትፊኬቶች ያለኝ ሲሆን፤ በሕግ ሙያ በኢንሹራንስ ኩባንያ ውስጥ በነገረ ፈጅነት፣ በግል ድርጅት ውስጥ በሕግ አማካሪነት እንዲሁም ካለፉት 4 ዓመታት ጀምሮ በሕግ አማካሪና ጠበቃነት እየሠራሁ እገኛለሁ።

በፖለቲካው ዘርፍ ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪነቴ ጀምሮ ህወሓት መራሹን ኢሕአዴግ በመቃወም በ1988 ዓ.ም የተደረገው ደማቅ የዐድዋ 100ኛ የድል በዓል አከባበርን በዋናነት በአዲስ አበባ እንዲከበር በሚጠይቀው ሰላማዊ ሰልፍ ከመሳተፍ ጀምሮ በመአሕድ/መኢአድ የወጣቶች እንቅስቃሴ ውስጥ በወጣት አመራርነት፣ በቅስቀሳ ቡድንና በኪነት መሪነት በመላው ሀገራችን በቀስቃሽነትና አደራጅነት፣ ፓርቲው በሚያዘጋጀው ጋዜጣ የወጣቶች አምድ ፀሐፊነትና የአሥራት ጋዜጣ ም/አዘጋጅ በመኾን አገልግያለሁ፡፡

በተጨማሪም፤ በፓርቲው ላእላይ ምክር ቤት አባልነት፣ በ1997 ዓ.ም በነበረው የቅንጅት ፓርቲ እንቅስቃሴ ውስጥ በዋና መሥሪያ ቤት በምርጫ ዘመቻ የምዕራብ ኢትዮጵያ ዴስክ አስተባባሪነትና ከምርጫው በኋላ በነበረው የምርጫ ማጣራት ሥራ ቅንጅትን በመወከል በደቡብ ኦሞ ዞን በፓናሊስትነት ተሳትፍያለሁ፡፡

በወቅቱ ከተነሳው ግርግር ጋር ተያይዞ በደረሰባቸው እስርና ድብደባ ለከፍተኛ ሕመም በመዳረጋቸው ምክንያት አካላቸውን እስከማጣት በመድረስ ለዓይነስውርነት ተዳርግያለሁ፡፡

በ 2011 ዓ.ም ኢዜማ ሲመሠረት ባለኝ አቅም ጠብታ አስተዋፅዎ ላበርክት በማለት በኢዜማ ውስጥ በምርጫ ክልል 12/13 በአባልነት፣ በወረዳው የሕገ ደንብ ተርጓሚና ዲስፕሊን ኮሚቴ አባልነት፣ በ 2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ ኢዜማን ከሌሎች በተለየ መልኩ አካታችና እውነተኛ የኹሉም ዜጎች ፓርቲ መኾኑን ያሳየበትንና እስከዛሬም ድረስ ብቸኛ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለዓይነስውራን በብሬል ያሳተመ ፓርቲ እንዲኾን ጉልህ አስተዋፅዎ አድርጊያለሁ፡፡

ኢዜማ በመስከረም 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ባሻሻለው መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ባስቀመጠው መሠረት የአካል ጉዳተኞች መምሪያ በሥራ አስፈፃሚ አባልነት እንዲካተት በተወሰነው መሠረት ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ የመምሪያው ኃላፊ በመኾን፣ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ አባልነት፣ በ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ በአባልነትና የጉባኤው ም/ሰብሳቢ በመሆን፣ በ2016 ዓ.ም በተደረገው ኮንፈረንስ የአዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ፤ እንዲሁም ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡

በሥራ ትጋቴ፣ በዓላማ ጽናቴ፣ ባካበትኩት የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ተሞክሮ የምታወቅ ሀገር ወዳድ ዜጋ ነኝ፡፡ ዘንድሮ በሚካሔደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም በምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር ዕጩ በመሆን አልፊያለሁ።

#ኢዜማን_በልኩ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታዬ ሽመልስ

እጩ የኢዜማ ፋይናንስ ተወዳዳሪ
አሰፉ ተረፈ ውቤ እባላለሁ የትምሕርት ዝግጅቴ በአካውንቲነግ የመጀመሪያ ዲግሪ እና በቢዝነስ ማኔጅመንት ማስተርስ አለኝ።

በሥራ ዓለም በግል ድርጅቶች ውስጥ በአካውንታንትነትና በፋይናንስ ማናጀርነት ከ12 ዓመታት በላይ አገልግያለሁ፤ በግሌ ንግድ በመጀመርም ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ።

በተለያዩ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ።

ከኢዜማ ከምሥረታ ጀምሮ የምርጫ ወረዳዎችን በማዋቀር፣ በአዲስ አበባ ምርጫ ወረዳ 15 በሥራ አስፈጻሚነት እስከ 2014 ድረስ አገልግያለሁ። በተጨማሪም የብሔራዊ ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ እና ብሔራዊ የሴቶች መምሪያ ቋሚ ኮሚቴዎች ውሰጥ ተሳትፎ በማድረግ ለፓርቲው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ምርጫ ወረዳ 15ን በመወከል የኢዜማ ጉባኤ ተሳታፊ በመኾንም ለፓርቲው ይጠቅማል ያልኩትን ሀሳብ አካፍያለሁ፤ ውሳኔዎች ላይም አሻራዬን አሳርፊያለው።

በ 2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ወረዳ 15 የክፍለ ከተማ ምርጫ ታዛቢ፣ በ 2014 በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የብሔራዊ ክዋኔ እና ፋይናስ ኦዲት ዕጩ ኾኜ በመወዳደር በአንደኛ ደረጃ በጠቅላላ ጉባኤ ለመመረጥ በቅቼያለሁ።

እኔ አሰፉ ተረፈ ድርጅታችን ኢዜማን በዕውቀቴ፣ በጊዜዬ እና ጉልበቴ ኹሉ በማገልገል አብሬያቸው የሠራኃቸው ሁሉ ይመስክሩልኛል።

በማኅበራዊ ሕይወቴ ተግባቢና ሀገር ወዳድ ንቁ ዜጋ ነኝ። በአሁኑ ወቅትም  የኢዜማ ብሔራዊ ክዋኔ እና ፋይናንስ ኦዲት ሰብሳቢ ኾኜ በማገልገል ላይ ነኝ።

በዘንድሮው የኢዜማ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለፋይናንስ ኃላፊነት (ትሬዠረር) ለመወዳደር ዕጩ በመኾን አልፊያለሁ።
#ኢዜማ_ምን_ያስፈልገዋል ?

👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት

#ኢዜማን_በልኩ !!

ኢዜማ በአማራጭ ኃይልነት ጠንካራ ቁመና ያለው ፓርቲ ሆኖ እንዲወጣ አሁን ላይ “ምን ያስፈልገዋል?” ካልን ተራማጅ አስተሳሰብ ያለው የአዲሱ ትውልድ አካል የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ ቆራጥ እና ትጉህ አመራር ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን።

አሁን የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ኃላፊነትን የሚረከብበት ጊዜ ነው። ይህ ደግሞ ላለፉት 50 ዓመት ደጋግመን በሞከርነው እና ተፈትኖ በወደቀ የፖለቲካ ባሕል ውስጥ ተዘፍቆ ሊሳካ የሚችል አይደለም። አሁናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአዲስ መንፈስ አዲስ ትግል ይፈልጋል። አዲሱ የፖለቲካ ትግል የአዲሱ ትውልድ ኃላፊነት እና መብትም ጭምር ነው። በተለመደው መንገድ ባረጀ አስተሳሰብ ሄደን የተለየ ቦታ መድረስ ካለመቻላችንም በላይ የምንመኘውን ውጤት አናመጣም።

ይህ የኢዜማ አዲሱ ትውልድ ድምፅ ነው። ይህ ድምፅ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተዘጋጀ፣ ፖለቲካን ተስፋ አስቆራጭ በኾነ ዝግታ አልያም በስሜት እየቸኮለም የማይጋልብ “ኢዜማን በልኩ!” ብሎ የተነሳ ቁርጠኛ አመራር ነው። ላለፉት ስድስት ዓመታት ሀገራችን የነበረችበትን አስጊ የጸጥታ ሁኔታ እና የመበተን ስጋት በቅጡ በመረዳት ኢዜማ በእርጋታ እና በስክነት ሲሠራ እንደቆየ የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ በሀገራችን ያሉትን ተለዋዋጭ ክስተቶች በጥልቀት በመገንዘብ እና በተለይም ሀገራዊ ምክክሩን እና 7 ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ከግምት በማስገባት በተግባር ኢዜማ በልኩ፣ በራሱ መንገድ፣ የራሱን ጉዞ ለማድረግ ተነስቷል።

ይህ ጉዞ ከኹሉም የፖለቲካ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግን ሀቀኛ ትብብር የሚፈልግ እንደኾነ አያጠያይቅም። እኛ እንደምናስበው ኢዜማ በዚህ ሰዓት ጠንካራ መዋቅር መዘርጋት እና ተልዕኮውን መሸከም እና መፈጸም የሚችል ቆራጥ ድርጅታዊ አመራር ያስፈልገዋል። ይህ አመራር የጠራ አረዳድ ያለው፣ እርስ በእርስ የማይጓተት፣ ስለ ዓለምአቀፍ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ እንዲሁም ውስጣዊ ድርጅታዊ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ያለው መኾን አለበት። ኢዜማ የጋራ ግብና ዓላማ ሰንቆ የሚሠራ፣ ኹሌም ለመማር ዝግጁ የኾነ፣ ዘመኑን የሚዋጅ እውነተኛ የአዲሱ ትውልድ አመራር ለመኾን ቆርጦ የተነሳ አመራር ያስፈልገዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም እኛ አራታችን (ሊቀመንበር፣ ም ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና ፋይናንስ) ተግባብተን ለመመረጥ እየሠራን እንገኛለን።


👉 ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇

https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk
2025/06/26 02:01:11
Back to Top
HTML Embed Code: