Telegram Web
የመዋቅርና የጽ/ቤቶቻችን ኹናቴ

የተወደዳችሁ የኢዜማ አባላትና የጉባዔ ተሳታፊዎች

ኢዜማን እንደገና በሚለው መሪ ቃላችን ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የመዋቅርና የምርጫ ክልሎቻችን አሁናዊ ገፅታ አንዱ ማሳያ ነው። ይህን ከሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ያደረገንን ከታች ወደ ላይ የተዘረጋውን መዋቅራዊ አደረጃጀታችን ወደ ምንፈልገው ተቋማዊ ማንነት ማድረስ እንደምንችል አምነንበት ነው። ፓርቲያችን ወደ መራጩ ህዝብ ለመድረስ መዋቅራዊ ይዘቱን ተቋማዊ ቅርፅ ማስያዝ ነው። ይህን ፓርቲ ከህዝባዊ ድጋፍ በተጨማሪ የተቋም ባለቤት ልናደርገው ይገባል። መላው ኢትዮጵያዊያን በየምርጫ ክልላቸው በጋራ በመግባባት ዘመናዊ ፖለቲካ የሚሰሩትን ኹናቴ ማመቻቸት ተቀዳሚ ተልዕኳችን ይሆናል።

ፓርቲያችን ኢዜማን ከሌሎች የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለየው የአደረጃጀት መሠረቱን ከምርጫ ክልል መጀመሩ ነው። ይህ ፓርቲው ህዝባዊ መሠረት እንዲኖሩት ካደረጉት የኢዜማ አምዶች መካከል አንዱ ነው። ፓርቲያችን በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሄድ ከተፈለገ የማያቋርጥ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትል ያስፈልገዋል። የማህበራዊ መሠረቱን ተደራሽነትና ስፋት እንደገና በማጥናት እንደየአስፈላጊነቱ የመዋቅር ማሻሻያም ሊያደርግ ይገባል። የኢዜማ ተቋማዊ መሰረት ከዋና ቢሮው በተጨማሪ ሌሎች ክረምት በጋ የሚሰሩ 24/7 ለአባሎቻችን ክፍት የሆኑ የፖለቲካ ስራ የሚሰራባቸው ተቋማዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት።

በቀጣይ ለ3 ዓመታት በእናንተ ይሁንታ የፓርቲያችን ዋና ፀሐፊ ከሆንኩ በየመዋቅሩ የሚገኙ የምርጫ ክልሎችን ከመጎብኘት ባለፈ የእያንዳንዱ ጽ/ቤት ጉዳይ የዋና ቢሮው ጉዳይ ሆኖ ህግና አሰራር በሚፈቅደው መልኩ ሁሉም የምርጫ ክልሎች የተጠናከረ ተቋም እንዲኖራቸው ያለመታከት እሰራለሁ። የጠቅላላ ጉባዔው በሚሰጠኝና በቀጣይም የሚደራጀው የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ አቅጣጫ የኢዜማን ተቋማዊነት ከዋና ቢሮ ባሻገር ወደ መራጩ ህዝብ ልብ እንዲዘልቅ እሰራለሁ!

ኢዜማን እንደገና!

ዶ/ር ካሣሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ
2025/06/26 10:58:20
Back to Top
HTML Embed Code: