tgoop.com/ethzema/4691
Create:
Last Update:
Last Update:
👉 #የምርጫ_ቅስቀሳ_ሰዓት
#ኢዜማን_በልኩ !!
የዳበረ ተቋማዊ ባሕል
ተቋማዊ ባሕል በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ አባላት የሚኖራቸው የጋራ አረዳድ፣ ከሌሎች ድርጅቶች አባላት የሚለያቸው እሴት እና ስለተቋማዊ ጉዳዮች የሚኖራቸው ተቀራራቢ አመለካከትን የሚያካትት ነው። ተቋማዊ ባሕል የአንድ ድርጅት አባላት ውሳኔ የመስጠት አቅማቸው፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር ያላቸውን ነፃነት፣ ድርጅታዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የመመልከት ብቃታቸውን፣ ሂደትና ውጤት እንዲተሳሰሩ የማድረግ ችሎታቸውን፣ በጋራ ተናብበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኛነት እንዲሁም ለድርጅቱና ለሥራቸው ያላቸውን ተአማኒነትን የሚመለከት ጉዳይ ነው።
ከዚህ አንፃር ኢዜማ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከተለመደው የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀትና አሠራር የተለዩ ባሕሎችን ተግባራዊ አድርጓል። ኢዜማ ከሌሎች ድርጅቶች የሚለይባቸውን ባሕሎች ለመትከል ተንቀሳቅሷል። ይኹን እንጂ፤ የተጀመሩ በጎ ባሕሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና አዳዲስ ድርጅታዊ ባሕሎችን ለመትከል የሚያስችል ጠንካራ አመራር አልተፈጠረም። በሊቀመንበር ደረጃ የሚመራው የኢዜማ የድርጅት ክንፍ በሚጠበቀው ልክ ለመምራት አለመቻሉ ጅምር ተቋማዊ ባሕሎች በአባላት ዘንድ እንዳይሰርፁ እንዲሁም አዳዲስ የአሠራር ሂደቶች ስላልተፈጠሩ አባላት እምቅ አቅማቸውን አውጥተው እንዳይጠቀሙ ኾኗል። በመኾኑም፤ ተቋማዊ ባሕል ለኢዜማ ውጤታማነት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ እና የአባላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም ያለውን ጠቃሚነት በመገንዘብ፤ አባላት ድምጽ ሰጥተው የሚመርጡን ከኾነ ከተቋማዊ ባሕል አንፃር የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እናደርጋለን።
ሙሉውን ሰነድ ለማንበብ ከታች የተያያዘውን ማሥፈንጠሪያ ይጫኑ 👇
https://drive.google.com/file/d/1prqfUjj2PzXojUVGNCVYyviZ5Qb-lS6Y/view?usp=drivesdk
BY የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ethzema/4691