Telegram Web
የሕግ የበላይነት ተከብሮ አባላቸን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን!!!

የኢዜማ አባል የሆኑት ሲኒየር ፋርማሲስት ኃይለማርያም ብርሃኑ የድሪም ኬር አጠቃላይ ሆስፒታል የፉርማሲ ክፍል ኃላፊ፣ የኢዜማ የባህርዳር ከተማ የስራ አስፈፃሚ፣ በፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የስራ አስፈፃሚ፣ ፓርቲውን በመወከል የ2013 ዓ.ም የክልሉ ምክርቤት እጩ ተወዳዳሪ እንዲሁም በአማራ ክልል በነበረው ሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ በሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ያሉ ቆራጥ፣ ሀገር እና ወገንን ቀን ከሌት በማገልገል የሚተጉ ዜጋ ናቸው።

አባላችን ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም ምሽት በ2፡00 ሰዓት በፓሊሶች ከቤታቸው ተወስደው በባህርዳር ከተማ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያለምንም ክስ የታሰሩ ሲሆን ፤ በግንቦት 4 ቀን አካልን ነፃ የማውጣት ክስ ተመስርቶ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም የባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ከነበሩበት ቦታ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው የት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም፡፡

መንግስት አንድን ዜጋ ከሕግ በላይ ሆኖ አስሮ ማንገላታቱ ሳያንስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አለማክበር ሲጨመርበት ተስፋ አስቆራጭ ነው! በመሆኑም የሕግ የበላይነት ተከብሮ አባላቸን በአስቸኳይ እንዲፈቱ በአፅንኦት እንጠይቃለን!!!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ
የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 13/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኅዘን መግለጫ

*
#ኢዜማ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር መምሪያ ቋሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ መስፍን አበበ ግንቦት 26/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 27/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ 8:00 ሰዓት በሽሮሜዳ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

የፓርቲው አመራሮች እና አባላት በአባላችን በአቶ መስፍን አበበ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ኅዘን እየገለጽን ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1446ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) አደረሳችሁ!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) የፓርቲው ከፍተኛ አካል የሆነውን ጠቅላላ ጉባኤ በያዝነው ወር ሰኔ 28 እና 29/ 2017 ዓ.ም. ለማድረግ ዝግጅቱን የጨረሰ ሲሆን በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የከፍተኛ አመራሮችን የሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ የዋና ጸሐፊ እና ፋይናንስ /ትሬዠረር/ ኃላፊ ምርጫ ይገኝበታል።

በዚሁ መሠረት ባለፉት ወራት የእጩዎች ልየታ የተደረገ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ሰኔ 02/2017 ዓ.ም. ለኃላፊነት የሚፎካከሩ ተወዳዳሪዎች የፓርቲውን የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ተጠቅመው የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያካሒዱበትን ዕጣ አውጥተዋል፤ በተጨማሪም የውድድር እና የምረጡኝ ቅስቀሳ የስነ- ምግባር ደንብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ከሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያካሂዱ አስመራጭ ኮሚቴው ለማሳወቅ ይወዳል።
ኢዜማን እንደገና!

ዶ/ር ካሳሁን ደለነ

ዕጩ ዋና ፀሐፊ

እኔ የኢዜማ የሙያና የሠራተኛ ማህበራት መምሪያ ሃላፊ ዶ/ር ካሳሁን ከዚህ ቀደም በፓርቲያችን ኢዜማ ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች ያገለገልኩ ሲሆን ፓርቲው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለመታከትና ያለማቋረጥ በቅንነትና በመሰጠት እያገለገልኩ እገኛለሁ። በኢዜማ ላስካ መደበኛ ምርጫ ክልል በአባልነት የጀመርኩት የፖለቲካ ትግል ጉዞ በምርጫ 2013 ላይ የምርጫ ክልሌን በመወከል ለኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢዜማ ዕጩ ሆኜ መቅረቤ ይታወቃል። በኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባልነት በቅንነት ከማገልገል ጀምሬ በፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባልነት: የደቡብ ክልል የኢዜማ አደረጃጀቶች አስተባባሪ በመሆን አገልግያለሁ። በመቀጠልም የድርጅት ጉዳይ መምሪያን በምክትል ሃላፊነት በማገልገል የፓርቲውን መዋቅሮች የማጠናከርና የማስቀጠል ትልቅ ሀላፊነቶችን ተወጥቻለሁ።

እኔ ፓርቲያችን በመወከል የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ በአመራርነት አገልግያለሁ። በኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዘርፍን በአስተባባሪነት በመምራት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የጋራ ምክር ቤቶች ወደ ሰላማዊና ጤናማ የፖለቲካ ሥራ እንዲሰሩ የበኩሌን አስተዋፅዖ ተወጥቻለሁ።

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በአመራርነት እያገለገልኩ ከዚህ ቀደም ምክር ቤቱን ወክዬ በአውሮፓ ህብረት የውጭ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ኮሚሽን የወጣቶች አማካሪ ቦርድ አባላነት በዕጩነት ተወዳድርያለሁ።

ከሀገር አቀፍ ፖለቲካ በተጨማሪ በመላው አፍሪካዊያን አንድነት ትግል ውስጥ በንቃት የተሳተፍኩ ስሆን ከዚህ ቀደም Global Pan Africanism Network-GPAN የተሰኘ ንቅናቄን በምክትል ፕረዚዳንትነት የመራሁና በአፍሪካ ህብረት በወጣቶች ቋሚ መልዕክተኛ ቢሮም አገልግያለሁ። በአሁኑ ሰዓትም የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የወጣቶች ድምፅ ውስጥ በአባልነት እየተሳተፍኩ እገኛለሁ። የ Model African Union Ethiopia የተሰኘ የሲቪክ ማህበር መስራች አባል በመሆን ከሌሎች ፓን አፍሪካዊ ወጣቶች ጋር በቀጣይ የአህጉራዊ አንድነት ላይ ከሚሰሩ አካላት ጋርም በንቃትና በቁርጠኝነት እያገለገልኩ ነው።

በሙያዬም በታታሪነት የተመሰከረልኝና በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ውስጥ እየሰራው ነው። በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የማህበረሰብ ሳይንስና ፖለቲካ ትምህርት ክፍል ውስጥ Comparative Politics በሁለተኛ ድግሪ ደረጃ ተከታትያለሁ። በጥናታቸውም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትን በማነፃፀር ተመልክቻለሁ።

በዚህ የኢዜማ የከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ውድድር ላይ በዋና ፀሐፊነት ለማገልገል በዕጩነት ቀርብያለሁ። የዜግነት ፖለቲካና ማህበራዊ ፍትህ በተሰናሰለ መልኩ ለመጪዋ ኢትዮጵያ ለማስረፅ ድጋፍ እንድትሰጡኝና እንድትመርጡኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ ሁሉንም አስፈላጊ ግብዓቶች አሟልቶ የተመረቀው የ #ኢዜማ አካዳሚ በአዲስ አበባ ለሚገኙ አመራሮቹ አምስት ቀን የፈጀ አጭር ስልጠና

1.Critical Thinking

2.What Constitutes a Good Society and the International Crisis

3.Impact of Global Trends on Modern Ethiopian Politics

4.Current Ethiopian Politics and political Leadership

5.EZEMA's Direction and Principles

በሚሉ ርዕሶች ላይ በመስጠት ይፋዊ ስልጠናውን በመስጠት ጀምሯል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታዬ ሽመልስ

እጩ የኢዜማ ፋይናንስ ተወዳዳሪ
2025/06/26 15:48:53
Back to Top
HTML Embed Code: