😭 ዜና ዕረፍት የደብረ ነጎድጓድ ታላቁ ዋርካ ዐረፉ።
😭 "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬንም ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖቴንም ጠብቄአለሁ። እንግዲህስ የጽድቅ አክሊል ይቆየኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በዚያ ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም"። 2ኛ ጢሞ 4፥7-8።
😭 የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና የመካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የረጅም ዓመታት አገልጋይ የነበሩት ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ሞት ዐረፉ።
😭 ቀብርራቸው በትውልድ ከተማቸው በዓድዋ ይፈጸማል። በደቡሩ ዛሬ መጋቢት 28 2015 ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ላይ የሽኝት መርሐ ግብር ይደረጋል። ምንጭ፦ ፍቅረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት።
😭 እግዚአብሔር አምላክ የቆሞስ አባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አገልጋዮቹ አጠገብ ያሳርፍልን። በረከታቸው ይደርብን።

Forwarded from መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።
አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።
ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።
አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++
©ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)

አለምን የሰራ ሲሆን፥
ከእኛ እንዳንዱ ቢሆን።
እንደ በደለኛ ቆጥረነው፥
በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀልነው።
++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
ከእኛ እንዳንዱ ቢሆን።
እንደ በደለኛ ቆጥረነው፥
በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀልነው።
++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
አንድ ጊዜ ጅማ ዩንቨርስቲ ዋናው ግቢ ጉባኤ ግእዝ ቋንቋ ስንማር የተፈተናት ፈተና ትዝ አለችኝ። ፈተናው
"ብየ አክሊል ዲበ ርእስየ
መዓልተ እውዕል ታኅተ ሰብእ
ወሶበ በጽሐ ጊዜሁ ለምሴት አኀድር ላዕለ ሰብእ
መኑ አነ"
የሚል ነበር። "በራሴ ላይ አክሊል አለኝ፣ ቀን ቀን ከሰው በታች እውላለሁ፣ በምሽት ጊዜ ደግሞ ከሰው በላይ አድራለሁ። እኔ ማን ነኝ" የሚል እንቆቅልሽ ተጠይቆ። አንዱ ጓደኛችን ሲመልስ "ሱሪ" ነው አለ። ገረመንና አክሊሉ ምንድን ነዋ? ስንለው "ቀበቶው ነዋ" ብሎን አረፈ። ነገር ግን መልሱ አውራ ዶሮ ነበር። ዶሮ ቆጥ ላይ ስለሚያድር ማታ ከሰው በላይ ያድራል።
።
በይሁዳ ራስ ስለዞረው ዶሮ የሚናገር እና በጸሎተ ኃሙስ ስለታረደው ዶሮ የሚናገር መጽሐፍ መጽሐፈ ዶርሆ የሚባል አለ። ነገር ግን ያንን ሳነበው ፲፪ቱ ብልት የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ የሚል አላገኘሁም። ብቻ ያው ዶሮ ወጥ በፍስክ ሲበሉት ደስ ይላል። እንቁላልም ገንቢ ምግብ እንደሆነ ሐኪሞች ይነግሩናል። ከዚህ ውጭ የማውቀው ነገር እንደሌለኝ ስነግራችሁ በደስታ ነው።
።
© መጋቤ ዶርሆ ወእንቁላል

የቤተክርስቲያን ያልሆነን ትምህርት የቤተክርስቲያን እያስመሰሉ ማቅረብ ይቅር። ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ከወርቅ የጠራ ነው። በነቢያት የተነገረ፣ በሐዋርያት የተሰበከ፣ በሊቃውንት የተመሠጠረ ትምህርት አላት። ከዚያ ውጭ የራስን ግላዊ እይታ አስተምህሮዋ አስመስሎ ማቅረብ አይገባም። አርዮስ በመሰለኝ በካደ ጊዜ ሊቃውንቱ "ከመጽሐፍ አላገኘኽው፣ ከመምህር አልተማርከው እባክህ ይቅርብህ። አስብኽው ከሆነ አትናገረው፣ ተናግረኽው ከሆነ አትድገመው" ብለውት ነበር። እርሱ ግን ስላልሰማቸው ራሱን ጎዳ። በክፋት እና በስሕተት ጎዳና ያለ ሰው መጀመሪያ የሚጎዳው ራሱን ነው። በሰው ጭብጫቦ ሰክሮ እውነትን መጨቆን አይገባም። የሰውን ጩኽት ፈርቶም እውነትን መደበቅ አይገባም። ሰው መዋቲ ነው። ፈራሽ በስባሽ የሆነ ሰውን መፍራት አይገባም። ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ እንኳ ንጉሡ ዖዝያንን ፈርቶ እውነትን ቢሸሻት ለምጻም ሆኗል። በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ብሎ ራሱ ያመጣዋል። ያ የምትፈራው የምታፍረው ንጉሥ ሞተ ለማለት። የማይሞተው አምላክን መፍራት እንደሚገባው ለማመልከትም ቀጥሎ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዊኅ ብሎ ያመጣዋል።
።
ሰው ቤተክርስቲያንን ሊከተል ይገባዋል። አስተምህሮዋን መጠንቀቅ ይገባዋል። እውነት በአጨብጫቢ ብዛት አትለካም። የእውነት ልኳ ራሱ ክርስቶስ ነው። በምጽአት ጊዜ ለሁሉ በአደባባይ ትገለጣለች። እስከዚያው ግን ኃጥአን ጻድቃን መስለው ሊኖሩ ይችላሉ። ጻድቃንም ኃጥአን ተብለው ሊኖሩ ይችላሉ። ያች የእውነት ቀን ስትመጣ ሁሉ ይገለጣል። እርሱ ሞቶ እኛን ያዳነን መድኃኔዓለምን እናስበው። ፍቅርን በተግባር አሳየን። እውነት እርሱ ነው። እርሱን እንከተል።

_የመበለት ዱላ_
መበለት ማለት አሮጊት ሴት ማለት ነው። የኔታ ቡሩክ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የነበሩ የመጽሐፍና የቅኔ መምህር ነበሩ። እና አንድ ቀን "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለ" ብለው ይናገራሉ። ይህን የሰሙ መበለቶች ዱላቸውን ይዘው የኔታን ሊደባደቡ ግርርርርር ይላሉ። ይህንን የተመለከቱ አንድ ሸምገል ያሉ ሰውየ "ቆይ እስኪ ከዱላው በፊት እንጠይቀው" ይሉና። ሄደው አንተን ብሎ መምህር ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለ ብለሃል አሉ እውነት ነው ይሏቸዋል። የኔታም "አዎ እውነት ነው ለእግዚአብሔርኮ የሚሳነው ነገር አለ" ብለው ይደግሙታል። የሰው ብስጭት ጨመረና "ምንድን ነው እግዚአብሔርን የሚሳነው?" ይሏቸዋል። የኔታም ሲመልሱ "ውሸት ነዋ" ብለው መለሱ። እግዚአብሔር ጻድቅነት የባሕርይው ነው ካልን ውሸት ይሳነዋል ማለት ነው ብለው ሲናገሩ ዱላ ይዞ የመጣው መበለት ሁሉ አፍሮ ወደየቤቱ ሄደ ብሎ አንድ የኔታን በቅርበት የሚያውቃቸው ሰው ነግሮኛል።
።
እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ያለ ምሉዕ ነው፣ ጻድቅ ነው፣ ኃያል ነው ወዘተ ካልን ይህ የባሕርይው ስለሆነ አይለወጥም ማለት ነው። ምክንያቱም የባሕርይ ማለት የማይለወጥ የራስ የሆነ ነገር ማለት ነው። እግዚአብሔር አይለወጥም። እንደማይለወጥም በትን. ሚል. ፫፣፮ እንዲሁም መዝ. ፩፻፩፣፳፯ ተገልጿል። እግዚአብሔር ምሉዕነት የባሕርይው ከሆነ ምሉዕነቱን መተው አይችልም ማለት ነው። እግዚአብሔር ኃያልነት የባሕርይው ነው ካልን ኃያልነቱን አይተውም ማለት ነው። ነገረ ሥጋዌን ስንናገር እንኳ ቃል ቃልነቱን ሳይለቅ ሥጋን ሆነ ሥጋም ሥጋነቱን ሳይለቅ ቃልን ሆነ ነው የምንለው። ኃያሉ ኃያልነቱን ሳይለቅ ድኩም ሥጋን ተዋሐደ። የማይሞተው የማይሞትነትን ሳይለቅ የሚሞት ሥጋን ገንዘቡ አደረገ። ይህንም ተዐቅቦ በተዋሕዶ እንለዋለን። የአንድን ሰው ሐሳብ ምክንያቱን እና የሐሳቡን መነሻ ሳይረዱ በግምት መናገር አይገባም። ዱላን ከማንሳት መጠየቅ ይቀድማል። በተለይ ሴት ልጅ ጭምት ዝም ያለች በትሕትና የምትኖር መሆን አለባት። ፈጠን ፈጠን የምትል ቀባጣሪ መሆን የለባትም።

Forwarded from ♱ ባሕራን ♱
†
[ ግንቦት ላይ የታሰበው ምንድን ነው ! ]
ግንቦት ላይ በሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ላይ በቤተክርስቲያን ጠላቶች እንዲፈጸም የታሰበውና የሚፈለገው ዕቅድ ምንድን ነው ? !
አገዛዙ ፣ ጽንፈኛ አህዛብ ፣ መናፍቃን ፣ ዘረኛ ቡድኖች ፣ የውጪ ኃይሎች ለቤተ ክርስቲያን የደገሱትን የጥፋት ድግስና በሚዲያዎቻቸው የጀመሩትን ዘመቻ መላው ኦርቶዶክሳዊ በአትኩሮት ሊከታተለው ይገባል።
ዓይናችንን በቤተክርስቲያናችን ላይ !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

+ ስንናደድ ለምን እንጮሃለን? +
🔥🍂🔥🍂🔥🔥🍂🔥🍂🔥
አንድ ብልህ አረጋዊ አባት በገዳም የሚኖሩ ደቀ መዛሙርትን ሰብስበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው :-
"ስንናደድ ለምን እንጮሃለን?
ሰዎች ሲበሳጩ ስለምን እርስ በእርሳቸው ይጯጯሀሉ?"
ደቀ መዛሙርቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ብለው ካሰቡ በኋላ ከመካከላቸው አንዱ ተነስቶ እንዲህ ሲል መለሰ :-
"ስንናደድ መረጋጋት ስለሚያቅተን እንጮሀለን።"
አረጋዊው አባትም ቀጠል አድርገው
"አብሮህ ያለው ሰው ከአጠገብህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ስለምን ትጮህበታለህ?
በለሰለሰ ድምፅ መነጋገር የማይቻል ነገር ነውን?
ስትበሳጭ ስለምን ሌላኛው ሰው ላይ ትጮሀለህ?"
ደቀ መዛሙርቱ በየተራ እየተነሱ የመሰላቸውን ኹሉ መለሱ ።
ነገር ግን የአንዱም ደቀ መዝሙር ምላሽ እኚህን ብልህ አረጋዊ አባት ስላላረካቸው የራሳቸውን ጥያቄ እንዲህ ሲሉ መለሱ:-
"ሁለት ሰዎች በሚበሳጩበት ሰዓት ልባቸው እጅግ ይራራቃል።
ይህን ርቀት ለመቀነስ እና ለመደማመጥ ደግሞ የግድ መጮህ አለባቸው!
አምርረው በተቆጡ መጠን በመካከላቸው ሰፊ መራራቅ ስለሚፈጠር ለመደማመጥ ይበልጡን መጮህ ግድ ይላቸዋል።
ቀጠሉና አረጋዊው አባት ሌላ ጥያቄ አስከተሉ :-
"ሁለት ሰዎች ሲዋደዱስ ምን ይፈጠራል?
ከመጯጯህ ይልቅ በለሰለሰ ድምፅ ያነጋገራሉ።
ለምን ካላችሁኝ ምክንያቱ ልባቸው በጣም ስለሚቀራረብ ነው! በመካከላቸው ያለው ርቀት ጥቂት ስለሚሆን እጅጉን እየተዋደዱ በመጡ ቁጥር ቃል ማውጣቱንም ትተው በሹክሹክታ ያወራሉ።
በመጨረሻም መንሾካሾክም ሳያስፈልጋቸው ዓይን ለዓይን በመተያየት ብቻ ይግባባሉ።
እንዲህ ነው ሁለት የሚዋደዱ ሰዎች የሚቀራረቡት ።"
"በምትከራከሩ ጊዜ ልባችሁ እንዲራራቅ አትፍቀዱለት፣ይበልጥ የሚያራርቃችሁንም ቃላት አትጠቀሙ! ምክንያቱም አንድ ቀን በመካከላችሁ ያለው ርቀት እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ዞሮ መመለሻው መንገድ ይጠፋባችኋል!"
"ፍቅር ልብን የተረጋጋ እና ሕይወትን የሚሰጥ ሲያደርገው በአንጻሩ ጥላቻ ደግሞ የተረበሸ ያደርገዋል በዚህም ሌላውን የሚጠሉ ራሳቸውን ያሰቃያሉ! ከፍቅር በላይ ምን ጣፋጭ ነገር አለ?"
"ለእኛ ያለህ የማይቋረጥ ፍቅርህ ከአባትም፣ ከእናትም ፣ ከሚስት እና ከባልም የሚበልጥ አቤቱ ፍቅር የሌለን ባሪያዎችህን ማረን አሜን!!!"
ምንጭ :- አባ ዮሐንስ ክሮንስታት የተባሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባት እንደጻፉት
ትርጉም :- ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ

"መንገዴ ነህ"
ተስፋዬ አደረኩህ፥ ሞተህ ስላኖርከኝ፤
በራሴ ላይ ሾምኩህ፥ አዳኝ ስለሆንከኝ።
መሄጃዬ አንተ፥ መደምደሚያ ሆንከኝ፤
ህይወትህን ሰተህ፥ ሞትን አሻገርከኝ።
፥
በመንገዶች ላይ፥ እንቅፋት ኖሮበት፤
ወድቄ እንድቀር፥ጠጠር ዘርተውበት።
እንድመለስ ሽቶ፥ ሆኖ ሁሉ ከንቱ፤
እኔን መጣል ነበር፥ ጠላቴ ምኞቱ ።
፥
በመንገዶችቼ ላይ ፥ አቋራጭ ቢኖርም፤
እኔ አንተን አለቅም፥ እኔ ያላንተ አልኖርም።
አውቀዋለሁ፥ ለኔ አይጠቅምም፤
ትግስቴ እስኪያልቅ፥ ብፈተንም።
አምናለው በእግዚአብሔር፥ አልፋለው ሁሉንም።
፥
ተነሽ በርቺ ፥አይዞሽ ልጄ፤
እኔ ይዤሻለው፥ በበረከት እጄ።
ይለኛል ዘወትር፥ ጠላት እንዳልፈራ፤
አይበቅልም ከርሻዬ ፥እንክርዳድ ቢዘራ፤
እግዚአብሔር አለ፥ የሰማዩ ጌታ፤
ስወድቅ የሚያነሳ፥ ልቤን ያበረታ።
የረታኝን ጠላት፥ በመስቀል የረታ፤
ህይወቴን ፈጠረ፥ በትንፋሹ እፍታ
፥
መንገዴን ጠራጊ፥ የአባቶቼ አምላክ፤
በፈተና እንዳልወድቅ፥ እኔን የጠበክ።
ለአንተ ለዘላለም፥ ይንበርከክ ጉልበቴ፤
አንተን ብቻ እናምልክ፥ እኔና ያ ቤቴ።
፥
ሰቶኝ የማይቀማ፥ታማኝ አምላክ አለኝ፤
ጥሎኝ የማይተኛ፥ጠባቂ ጌታ አለኝ።
ታድያ በዚህ አለም፥ እኔ ምን ጎድሎኛል?
በእርሱ ህያው መንገድ፥ ሁሌም ያኖረኛል።
፥
አሜን ክብር ይሁን፥ መንገዴን ላፀዳ፤
አሜን ምስጋና ይሁን፥ ልጁን ለሚረዳ።
አሜን አምልኮ ይሁን፥ ህይወቴን ለሰራ፤
በልቦናዬ እርሻ፥ የማያልቅ ፍቅሩን ሳይሰስት ለዘራ።
ምስጋና ይድረሰው፥ ክብር ይግባው ጌታዬ፤
መንገዴ ህይወቴ፥ ባለውለታዬ።
+++++++
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
ተስፋዬ አደረኩህ፥ ሞተህ ስላኖርከኝ፤
በራሴ ላይ ሾምኩህ፥ አዳኝ ስለሆንከኝ።
መሄጃዬ አንተ፥ መደምደሚያ ሆንከኝ፤
ህይወትህን ሰተህ፥ ሞትን አሻገርከኝ።
፥
በመንገዶች ላይ፥ እንቅፋት ኖሮበት፤
ወድቄ እንድቀር፥ጠጠር ዘርተውበት።
እንድመለስ ሽቶ፥ ሆኖ ሁሉ ከንቱ፤
እኔን መጣል ነበር፥ ጠላቴ ምኞቱ ።
፥
በመንገዶችቼ ላይ ፥ አቋራጭ ቢኖርም፤
እኔ አንተን አለቅም፥ እኔ ያላንተ አልኖርም።
አውቀዋለሁ፥ ለኔ አይጠቅምም፤
ትግስቴ እስኪያልቅ፥ ብፈተንም።
አምናለው በእግዚአብሔር፥ አልፋለው ሁሉንም።
፥
ተነሽ በርቺ ፥አይዞሽ ልጄ፤
እኔ ይዤሻለው፥ በበረከት እጄ።
ይለኛል ዘወትር፥ ጠላት እንዳልፈራ፤
አይበቅልም ከርሻዬ ፥እንክርዳድ ቢዘራ፤
እግዚአብሔር አለ፥ የሰማዩ ጌታ፤
ስወድቅ የሚያነሳ፥ ልቤን ያበረታ።
የረታኝን ጠላት፥ በመስቀል የረታ፤
ህይወቴን ፈጠረ፥ በትንፋሹ እፍታ
፥
መንገዴን ጠራጊ፥ የአባቶቼ አምላክ፤
በፈተና እንዳልወድቅ፥ እኔን የጠበክ።
ለአንተ ለዘላለም፥ ይንበርከክ ጉልበቴ፤
አንተን ብቻ እናምልክ፥ እኔና ያ ቤቴ።
፥
ሰቶኝ የማይቀማ፥ታማኝ አምላክ አለኝ፤
ጥሎኝ የማይተኛ፥ጠባቂ ጌታ አለኝ።
ታድያ በዚህ አለም፥ እኔ ምን ጎድሎኛል?
በእርሱ ህያው መንገድ፥ ሁሌም ያኖረኛል።
፥
አሜን ክብር ይሁን፥ መንገዴን ላፀዳ፤
አሜን ምስጋና ይሁን፥ ልጁን ለሚረዳ።
አሜን አምልኮ ይሁን፥ ህይወቴን ለሰራ፤
በልቦናዬ እርሻ፥ የማያልቅ ፍቅሩን ሳይሰስት ለዘራ።
ምስጋና ይድረሰው፥ ክብር ይግባው ጌታዬ፤
መንገዴ ህይወቴ፥ ባለውለታዬ።
+++++++
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
Forwarded from Tazena /ታዜና/
"ድህንነት' ነሽ"
የለብን አበሳ፥ የለብን መርገም፤
ቀድሶናልና፥ የክርስቶስ ደም።
አንቺ የኖህ ርግብ፥ አማን በአማን፤
የጥፋቱ ውሀ፥ ጎደለ አሜን፤
አንቺ የዘርዓ ያዕቆብ፥ የዳዊት ሙሽራ፤
ከደረትሽ ያለው፥ መስቀልሽ አበራ።
፡
ባንቺ በናታችን፥ በእመቤታችን፤
ህፃኑ ተሰጠን፥ ዳንን ሁላችን፤
አዳም የተከለው፥ የዘራው ጸደቀ፤
መሬትሽ ነውና፥ በጣም የታወቀ።
፡
የድህነት' አዝመራ፥ ካንቺ እንለቅማለን፤
በመዳኛ ልጅሽ፥ በእርሱ እንድናለን፤
ከእንግዲህ ህመማችን፥ ጭንቃችን አይጥና፤
ክርስቶስ በደሙ፥ ቀድሶናልና።
ድልድዩ ይሰራ ጠማማውም ይቅና።
፡
ተለያይቶ መኖር፥ አጉድሎናልና፥ በድሎናልና።
ጠማማውን መንገድ የቀና አድርገን፤
ጋራ ሸንተረሩን አስተካክለን ፥ሰርተን፤
ሀይማኖት ከምግባር፥ አስተባብረን ይዘን፤
ከድንግል ማርያም ጋር፥ አብረናት ተጉዘን፤
መላ አካላችንን፥ ከሐጥያት አንፅተን፤
የድህንነት' ሰብል፥ እንሰብስብ በርትተን።
++++++
ድህነት' ጠብቆ ይነበብ/መዳን፣መፈወስ/
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
የለብን አበሳ፥ የለብን መርገም፤
ቀድሶናልና፥ የክርስቶስ ደም።
አንቺ የኖህ ርግብ፥ አማን በአማን፤
የጥፋቱ ውሀ፥ ጎደለ አሜን፤
አንቺ የዘርዓ ያዕቆብ፥ የዳዊት ሙሽራ፤
ከደረትሽ ያለው፥ መስቀልሽ አበራ።
፡
ባንቺ በናታችን፥ በእመቤታችን፤
ህፃኑ ተሰጠን፥ ዳንን ሁላችን፤
አዳም የተከለው፥ የዘራው ጸደቀ፤
መሬትሽ ነውና፥ በጣም የታወቀ።
፡
የድህነት' አዝመራ፥ ካንቺ እንለቅማለን፤
በመዳኛ ልጅሽ፥ በእርሱ እንድናለን፤
ከእንግዲህ ህመማችን፥ ጭንቃችን አይጥና፤
ክርስቶስ በደሙ፥ ቀድሶናልና።
ድልድዩ ይሰራ ጠማማውም ይቅና።
፡
ተለያይቶ መኖር፥ አጉድሎናልና፥ በድሎናልና።
ጠማማውን መንገድ የቀና አድርገን፤
ጋራ ሸንተረሩን አስተካክለን ፥ሰርተን፤
ሀይማኖት ከምግባር፥ አስተባብረን ይዘን፤
ከድንግል ማርያም ጋር፥ አብረናት ተጉዘን፤
መላ አካላችንን፥ ከሐጥያት አንፅተን፤
የድህንነት' ሰብል፥ እንሰብስብ በርትተን።
++++++
ድህነት' ጠብቆ ይነበብ/መዳን፣መፈወስ/
©ምህረት/Mihert/
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
Forwarded from ♱ ባሕራን ♱
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
†
" አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም " [ መዝ. ፳፭ ፥ ፫ ]
" እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ፥ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።" [ መዝ.፳፯ ፥ ፲፬ ]
በሌላ ስፍራም ፦
" እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ ፤ አበረታሃለሁ ፥ እረዳህማለሁ " [ ኢሳ.፵፩ ፥፲ ]
† † †
💖 🕊 💖