Telegram Web
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
መጀመርያው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ም፱ ፥ቁ ፩፱
"እኔ ከሁሉ ይልቅ ነፃ ስሆን ብዙዎችን ወደ ሐይማኖት እሰበስባቸው ዘንድ እንደ ባርያ እራሴን ለሁሉ አስገዛው፡፡"
የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን!!!
አሜን አሜን አሜን🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿💐💐💐💐💐💐💐
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልቦናዬ ያውጣውዳሴ ለክብርሽ
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"


🥀🥀🥀 ፍቅር ቊስል ነው 🥀🥀🥀
🍃🍃🍃🍃🍃


🌹 ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።

🌹 "አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ!" ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው።


🌹 በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና
ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።

🌹 ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቈስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን ፣ አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።


Fr Haralambos Libyos
Papadopoulos

ተርጓሚ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
@Learn_with_John
ቅዱስ አልዓዛር

👉ከትንሳኤው ሳምንት ይህች ዕለተ ረቡዕ "አልዓዛር" ትባላለች:: ጌታችን ከሙታን ስላስነሳው ዕለቷ የሐዋርያው መታሰቢያ ሆናለች::
ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ. 11)
ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል::

ለስም አጠራሩ ስግደት ክብር ጌትነት ይድረሰውና
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ
"አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ
እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)

ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

የጌታችን ቸርነቱ የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

ጌታ ኢየሱስም ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ::
የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም ፍቱትና ይሂድ ተውት አላቸው:: (ዮሐ. 11:40-44)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Learn_with_John
@Learn_with_John
ይቀላቀሉ ሌሎችም ለማግኘት
#share
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
መኀልይ መኀልይ ዘሰለሞን
ም፩ ፥ቁ፯
"ነፍሴ የወደደችህ እረኛዬ ሆይ! የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥በጎችህን ወዴት እንደምታሰማራ ንገረኝ"
ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን !! አሜን አሜን አሜን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተነስቷል ተነስቷል ተነስቷል እንደተናገረው💐💐💐💐
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"

እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡

ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰውረን

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
🌹🌹🌹
በዚህ መንፈሳዊ ግሩፕ ውስጥ ያላችሁ ወንድምና እህቶቻችን በክርስቶስ ፍቅር እንወዳችኀለን 😍 የክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን
አሜን💐
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፳
=>ሚያዝያ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ በብኑዳ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ቄርሎስ : ሚስቱና 12 ልጆቹ ሰማዕታት (ከቅዱስ በብኑዳ ጋር የተገደሉ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
የማቴዎስ ወንጌል
ም፮ ፥ ቁ ፵፬
“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”
የቃሉ ባለቤት አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረና የተመሰገነ ይሁን !!
አሜን🌿🌿
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትንሳኤው ጌታ 💐🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🌿
አሳዛኝ ዜና
አሁን በዚህ ሰዓት የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንን ጽንፈኞች ወደ አካባቢው ማንም እንዳይቀርብ በማስፈራራት ጉልላቱን በማውረድ ካፈረሱ በኋላ እያቃጠሉት የሚገኝ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንም ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ምንጭ፡-ማህበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
Forwarded from መርጌታ ፍስሀ የባህል ህክምና (Bini Girmachew)
አሁን በደረሰኝ መረጃ ደሞ

ሥልጤ ዞን ውስጥ የምትገኘዋን ቂልጦ ማርያም ለማቃጠል እየሔዱ ነው። አሁንም የክልሉ ልዩ ኃይል ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሥልጤ ዞን ላይ ያለውን ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲያስቆም እንጠይቃለን።

በሁሉም ቦታ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያንንና ምእመኑን ተደራጅታችሁ ከጥቃት ተከላከሉ።

ለማንኛውም ሁሉ ዜናዎችን እዚህ ላይ መከታተል ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/+rsfbT9cY-iA4YmZk
https://www.tgoop.com/+rsfbT9cY-iA4YmZk
https://www.tgoop.com/+rsfbT9cY-iA4YmZk
Forwarded from መርጌታ ሰናይ የባህል መድሃኒት ቀማሚ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንድ ቤተሰብን የሚረብሹ መረጃዎች መልቀቅ አልፈለኩም ለዛ ነው

🟢@yeemariyaam21🟢
🟡@yeemariyaam21🟡
🔴@yeemariyaam21🔴
ድጋሚ አሳዛኝ ሰበር ዜና
የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ ሙስሊሞች መቃጠሉ ተገለፀ !!!

የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ ሙስሊሞች መቃጠሉ ተገለፀ።

የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶ አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ ከሶላት በተመለሱ ሙስሊሞች የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ገልጾ በተመሳሳይም የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ ኃይሎች መቃጠሉ ገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስታት እየተፈጠረ ያለውን ችግር በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

በዞኑ ኦርቶዶክሳውያንና አብያተ ክርስቲያናት በጫና ውስጥ መሆናቸውን የገለፀው ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግ ጠይቋል።

ይህንን እኩይ ተግባር የፈፀሙ ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀርቡና ፍትሕ እንዲሰፍን እንዲደረግ ጭምር ነው የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የጠየቀው።
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
@Learn_with_John
ለሌሎች ያጋሩ 👍
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

† ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፳፩ †

=>ሚያዝያ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ (ፍቁረ እግዚእ)
2.ቅዱሳት አንስት (ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ)
3.'500' ቅዱሳን ባልንጀሮች (በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ)
4.ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
5.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
6.ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
7.አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ (ኢትዮዽያዊ)
8.ቅዱስ አካክሪስ
9.ቅዱስ ይወራስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🌿የእለቱ ቅዱስ ቃል📜📜
የመጀመርያይቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ም፲፪ ፥፯-፲፩🌿 "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል::"
የቃሉ ባለቤት ጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን !!!
አሜን አሜን አሜን💐💐💐
2025/07/04 18:36:31
Back to Top
HTML Embed Code: