tgoop.com/learn_with_John/613
Last Update:
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"
🥀🥀🥀 ፍቅር ቊስል ነው 🥀🥀🥀
🍃🍃🍃🍃🍃
🌹 ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።
🌹 "አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ!" ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው።
🌹 በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና
ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።
🌹 ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቈስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን ፣ አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
✍ Fr Haralambos Libyos
Papadopoulos
ተርጓሚ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
@Learn_with_John
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/613