Telegram Web
Forwarded from Belay mulugeta
ጉባዔ ቤቱ በእሳት ተቃጠለ!

በባሕር ዳር ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተነሳ የእሳት አደጋ ከ2000 በላይ ደቀመዛሙርት የሚማሩበት የአብነት ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ !!!

በባሕር ዳር ሠላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተነሳ የእሳት አደጋ ከ2000 በላይ ደቀመዛሙርት የሚማሩበት የአብነት ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ።

የአደጋውን ሁኔታ አስመልክቶ ከሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም የአቋቋም መምህር የኔታ ፍሬስብሐት አንላይ ጋር ተ.ሚ.ማ ባደረገው ቆይታ በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ አደጋው የተከሰተ ሲሆን ትክክለኛ የአደጋው መንስኤው እየተጣራ የሚገኝ መሆኑና በጉዳቱ የመማሪያ አዳራሾችን ጨምሮ ከ200 በላይ የሚሆኑ የደቀ መዛሙርቱ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ነው የተገለፀው።

በአደጋው ሁለት ተማሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ ትወልዲ ወልደ
ሚካኤል መላክ በክነፍጹራ
መንጦላይተ ደመና ሰወረ
ንጽይት በድንግልና
አልባቲ ሙስና ተወልደ ወልድ እምኔሃ።
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ገብርኤል ማርያምን አበሰራት
ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አላት
ሚካኤል መላክ በክንፉ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንጽይት ናትና በድንግልና
ጥፋት የለባትምና
ወንድ ልጅም ወልዳለችና ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ነፍሴ የወደደችህ እረኛዬ ሆይ! የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥በጎችህን ወዴት እንደምታሰማራ ንገረኝ - መሓ ፩፤፯

“መንጋህን ሁሉ በትከሻህ የምትሸከም መልካሙ እረኛ ሆይ! በጎችህን በወዴት ታሰማራለህ?... የማሰማሪያህን ቦታ እባክህ አሳየኝ፣ የእረፍቱን ውኃ አስታውቀኝ፤ ወደለመለመው መስክ ምራኝ፤ እኔ የአንተ በግ ድምጽህን እሰማ ዘንድ በስሜ ጥራኝ፤ ጥሪህ የዘላለም ሕይወት በጎ ስጦታ ይሆነኝ ዘንድ። … የድህነት መሰማሪያን አገኝ ዘንድ፣ ወደሕይወት የሚገቡ ሁሉ ሊመገቡት ከሚገባው ከሰማያዊው ማዕድም እጠግብ ዘንድ [በጎችህን] የምትመግብበትን [የምታሰማራበትን] ቦታ አሳየኝ”
[ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ የመሓልየ መሓልይ ትርጓሜ]
@Learn_with_John
ለማንኛውም አስተያየት👇
@JohnDPT27
ተወዳጅ ሆይ! ክርስቶስ ኢየሱስ እንዲህ ይልሃል፦

"አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡ የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ፡፡ ...የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡

በቦታው ኹሉ የራቅሁ አይደለሁም፡፡ ትእዛዜን በምትፈጽምበት ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር እኖራለሁና ችግረኞችን የምረዳቸው እኔ ነኝና፤ ለድኾች የምታደርገው ኹሉ ለእኔ ማድረግህ ነው፡፡ እኔም በእርሱ ፈንታ በጎ ዋጋ እከፍልሃለሁና፡፡

በቤትህ ውስጥ እንግዳ በአሳደርክ ጊዜ እነሆ ከእንግዳው ጋር በማደሪያህ አስገባኸኝ፡፡ እንደዚህ ለሚያደርግ ቁጣዬ ከእርሱ ይርቃል፤ ወደ ሕይወት ወደብም አደርሰዋለሁ፡፡ ከክፉ ነገር ኹሉ እጠብቀዋለሁ፡፡ እባርከዋለሁ፡፡ ዘሩንም አበዛለሁ፡፡ ዋጋውንም በሰማይ ባለው በአባቴ ዘንድ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡ ዘለዓለማዊ ዕረፍትንም እሰጠዋለሁ፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

🌹 የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
🌹 የእመቤታችን ጸሎት 🌹
🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
@Learn_with_john
የሚሆነውን እናስተውል!!! ነግ በእኔ ነው እንበል!!! የሚጠበቅብንን እናከናውን !!!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ነገ የሚካሄደው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ ነው ቢልም አስተባባሪ ኮሚቴው መርሐግብሩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል !!!

ሚያዝያ 1 ቀን 2014 (ተሚማ/አዲስ አበባ)

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በደብረ ዕንቁ ቅድስት ልደታ ለማርያም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና በመስቀል ፕሮጀክት አሠሪ ኮሚቴ የተዘጋጀውንና "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል የተባለው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ ነው ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ፡፡

እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል ምክንያት በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል ሲል ከስሷል።

የሩጫ ውድድሩ ማሟላት የሚገባውን ሕጋዊ እውቅና ከሚመለከተው አካል አላገኘም ማለቱ ነው የተገለፀው፡፡

የመስቀል ፕሮጀክት አዘጋጅ ኮሚቴውና የሩጫ አስተባባሪ ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሩጫው እንደሚካሄድ ገልጾ መላው ኦርቶዶክሳውያን ለዚሁ የሩጫ መርሐግብር እንዲዘጋጁ በማለት የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን በተመለከተም ጭምር መግለጫ ሰጥቷል።

ፖሊስ በድንገት የጎዳና ላይ ሩጫ ለማካሄድ የሚደረግ እንቅስቃሴ በከተማው የፀጥታ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥር መሆኑን ህብረተሰቡም ሆነ ሩጫውን አዘጋጅተናል የሚሉ አካላት መገንዘብ ይገባቸዋል ቢልም የሩጫው አስተባባሪዎች አስፈላጊውን ሕጋዊ መንገድ መሄዳቸውን ባወጡት መግለጫ ገልፀዋል ፡፡

#ተዋሕዶ_ሚዲያ_ማዕከል
ሼር ሼር ሼር
@Learn_with_John
የክፋት አለቆች በኅጢአት ምኞት አሳወረውኛል፤ በተንኮላቸውም የልጅነት (የወጣትነት) ውበቴን ነጥቀውኛል። አሁን ንጽሕናዬን ያጣሁ እኔ ምን ላደርግ እችላለሁ? ወደ ክርስቶስ እጮኻለሁ፤ እርሱ ውበቴን ይመልስልኝ ዘንድ - ያን ጊዜ የክፋት ሠራዊት ያፍራሉ። መድኃኒቴም ወደ እኔ ወደ ደቀ መዝሙሩ እንዲህ ብሎ ይመልስልኛል፦ ለመዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደቀደመ ሥፍራህ እመልስሃለሁ፣ ኀጢአትህንም ይቅር እላለሁ። አልተውህም ፈልጌ አግኝቼሃለሁና፤ በገዛ ደሜም ዋጅቼሃለሁና። አንተ ኀጢአተኛ! በሙሉ ኃይልህ በአንደበትህ ሳትሰስት ጩኽ፤ ጌታህ መሐሪ በንስሐ የሚመለሱትንም የሚወድ ነውና። በተመለስህ ጊዜ ወዲያውኑ እርሱ አባትህ ቀድሞ በፊትህ ሊቀበልህ ይወጣል። የሰባውን ፍሪዳ ያርዳል፣ ያማረውን ካባ ያለብስሃል፣ በአንተም ደስ ይለዋል።

[ቅዱስ ኤፍሬም - A Spiritual Psalter 26]
@Learn_with_John
የእለቱ ጥያቄ❀✿❀
"እውነት እውነት እልሀለው፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት ለማየት አይችልም"
ብሉ የተናገረው ለማን ነው?
Anonymous Quiz
28%
ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ
1%
ለቅዱስ ኤልሳዕ
64%
ለቅዱስ ኒቆዲሞስ
7%
ለቅዱስ ጴጥሮስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኑ በብርሀኑ ተመላለሱ
Wolk in the light of God
ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡

ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡

ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡

ዝም እንል ዘንድ የሚቆጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው፡፡

#ንስሐ -
#በቅዱስ_ኤፍሬም
#መቅረዝ_ዘተዋህዶ_ብሎግ



🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
🕊 🕊🕊
🕊
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
h&
🌹 የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
🌹 የእመቤታችን ጸሎት 🌹
🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት
*b& ከሁላችን ጋራ ይሁን 5%
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔርu
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🥀🕊🥀🌹🥀 🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
🕊🕊 🕊 🌹🌹🌹🕊🕊🕊
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
እንኩዋን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

=>ሚያዝያ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
4.እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

=>+"+ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ::
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🕊የእለቱ ቅዱስ ቃል 📜📜

የመጀመሪያው የዘብዴዎስ ልጅ የሐዋርያው የቅዱስ ዩሐንስ መልዕክት
ም፪፤ቁ ፲፱
"ከእኛ ወገን ያልሆኑ ከእኛ ወጥተዋል ፥ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ አብረውን በኖሩ ነበር ፤ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ከእኛ ተለዩ፡፡"
የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን !!!አሜን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአበው ሐይማኖት
የሠማዕታት እምነት
የእለቱ ጥያቄ
"የሽቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ "ብሎ የተናገው ቅዱስ አባት ማነው?
Anonymous Quiz
47%
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
8%
ቅዱስ ጳውሎስ
1%
ቅዱስ እዩብ
44%
የዳዊት ልጅ ሰሎሞን
እልመስጦአግያ+++
የእለቱ ጥያቄ
"የሽቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ "ብሎ የተናገው ቅዱስ አባት ማነው?
እሺ የዚህ ጥያቄ መልስ
የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ነው የተናገረው
መኀልይ መኀልይ ዘሰሎሞን
ምዕራፍ አንድ ቁጥር ሶስት
"ብዙዎች ቢጾሙም የሚከሱ፣ በሕመም የሚጠቁ፣ ውበታቸው የሚደበዝዝ ስለሚመስላቸው፣ ከጾም ይርቃሉ፤ በጾም ምክንያት ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ወተት... ባለመብላታቸውም እንደተጎዱ ያስባሉ፤ የሚፈሰክበትንም ጊዜ እጅግ አድርገው ይናፍቃሉ፤ ለበሽታቸው ኹሉ መድኃኒቱ መብላት ይመስላቸዋል፤ በአብዛኛው አመመኝ፣ አዞረኝ፣ ደከመኝ፣ ቆረጠኝ...በማለት በጾም ጊዜ ይናገራሉ፤ ይኽ ግን ጾሙ የሚፈጥረው ሳይኾን፣ ጾማቸው በዘልማድ ወይም በመጠራጠር ስለሚደረግ ነው፤ የዚኽም መነሻው የእምነት መጉደል ነው፤ ጾምን ያራቀ፣ የናቀ፣ ያቃለለ በጎውን ነገር ኹሉ ከራሱ ያርቃል።"

👉 ('ጾም እና ምጽዋት')
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን

ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
እንደተለመደው ያላችሁን አስተያየት 👇👇👇@JohnDPT27 ላይ አጋሩን 😘
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን

፨፨፨

=>ሚያዝያ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት=
1.እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ
2.ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ (ጻድቃን ነገሥት)
3.ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው)
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)


=>+እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ::
(ዘፍ. 1፥26-31)

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🕊የእለቱ ቅዱስ ቃል 📜📜
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች
ም፲፬ ፤ቁ፳
"በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ፡፡ሁሉ ንፁህ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው፡፡ ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው፡፡"
የቃሉ ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን !!!አሜን
2025/07/06 12:36:26
Back to Top
HTML Embed Code: