ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡
ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡
🌻ቃለ ህይወት ያሰማን❤️
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!
🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂
🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂🥀🍂
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17
ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።
ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።
✍ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

#ንብ_የምትሞተው_መቼ_ነው?
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
የብልህ ሰው መገለጫው ይሄ ነውና ሁልጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ። ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም። ሁል ጊዜ አመስግኑ: ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል። ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ "የእግዚአብሄር ስም የተባረከ ይሁን" እያላችሁ አመስግኑ።(ኢዮ.1:21)
እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? በሽታ ነውን? ታዲያ ይሄ'ኮ አዲስ ነገር አይደለም። ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና። ሃብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን? ታዲያ ይሄ'ኮ ማግኘት የሚቻል ነው: ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው።
ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ክስ ነውን? ታዲያ ተጎጂዎቹ'ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚከሱን ሰዎች እንጂ እኛው አይደለንም። "ኃጢአት የምትሰራ ነፍስ ትሞታለች" እንዲል ተጎጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሰሩት እንጂ እኛው አይደለንም (ሕዝ.18:4)። ተጎጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው። ስለዚህ በዚህ ምውት በሆነ ሰው ልትቆጡ አይገባም: ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል እንጂ።
ንብ የምትሞተው መቼ ነው? ሌላውን ስትናደፍ ነው። እግዚአብሄር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቆጣ እንደማይገባን ያስተምረናል። የምንቆጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን። ስንቆጣቸው የጎዳናቸው ይመስለን ይሆናል ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጎጂዎቹ እኛው ነን።
#ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች
#የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስብከቶች
🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ
📖 መዝሙር 64/65፤11
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🥀🌻🌻
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
🕊 🕊🕊 🕊🕊🕊🕊🕊🕊
🕊 🕊🕊🕊🕊
ቃለ ሕይወትን ያሰማን

ወዳጄ ምንም አይነት የኃጢአት አዘቅት ውስጥ ብትሆን በእግዚአብሔር ሁሉ ይቻልሀል።ተስፋ አትቁረጥ.......
ማርያም ግብፃዊት
ከልጅነቷ ጀምራ ዘማዊት ነበረች።ነገር ግን በኃላ ዘመን ንስሓ ገብታ በገዳመ ዮርዳኖስ በምናኔ ኑሮዋን አሳለፈች።ያች ዘማዊት ሴት የጾም ፣የተጋድሎ ሰው ሆነች።መጀመሪያ ራሷን በኃላም ዲያቢሎስን አሸነፈች።
የቅድስት እናታችን በረከት ይደርብን አሜን።
@Learn_with_John ይቀላቀሉን።

1ኛ ዮሐንስ 5:18-21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው #እናውቃለን።
¹⁹ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ #እናውቃለን።
²⁰ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ #ልቡናን #እንደ_ሰጠን #እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው። #እርሱ_እውነተኛ_አምላክና_የዘላለም_ሕይወት_ነው።
²¹ ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን #ጠብቁ።

#ድንግሊቱ ስለሚያገባት ሙሽራ ማጥናት አያሻትም፤ልታለል እችላለሁ ብላም አትሰጋም። #ሙሽራዋ #እግዚአብሔር #እንጂ #ሰው አይደለምና፤ጌታ እንጂ እርሷን የሚመስል ገብር #አይደለምና።በሙሽሮቹ መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነውና።ከጋብቻቸው ማሰሪያ አንፃርም ስንመለከታቸው የሙሽራው ስጦታዎች ቀለበት፣ ቁራጭ መሬትእና ብዙ መክሊት ወርቅ አይደሉም
#መንግስተ ሰማያትና በዚያ ያሉ በጎ በጎ ነገሮች እንጂ በተጨማሪም ያገቡ ሴቶች በሌሎች ብዙ ምክንያቶች መካከል ከትዳር አጋራቸው ሲለያቸው እንደሚችል አስበው ሞትን ይፈራሉ ድንግሊቱ ግን ሙሽራዋን ፊት ለፊት ማየት ፈልጋና ያንን ክብር ሽታ #ሞትን #ትናፍቀዋለች፤በሕይዎት መቆየትንም ትጨነቃለች።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#በእንተ #ድንግልና #ከሚለው #መፅሀፍ #የተወሰደ።

Forwarded from እልመስጦአግያ+++ (mihret j)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገብረ መንፈስ ቅዱስ♥♥♥
Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (...typing)
❗️ አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ❗️
ከዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም
-------------------------------
ምሥራቅ ሐረርጌ ,ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ ፩ ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም
የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም "በታጠቁ ኃይሎች" እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ማምሻው የታጠቁ ኃይሎት በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባት መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል ፡፡ ሚዲያችን የሚመለከታቸውን አካላት ቦታው ድረስ በመደወል እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት እንዲህ በማለት ገልጸዋል "ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀዋል፣ ገዳሙን በሁሉም አቅጣጫ በመግባት እያስጨነቁ ይገኛሉ ሦስት አገልጋዮችን አግተዋቸዋል ድረሱል ድረሱል" የሚል ድምፅን አሰምተዋል፡፡ የወረዳ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
የሚመለከተው የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በአስቸኳይ የመነኮሳትን እንግልትና የድረሱልን ድምጽ በመስማት አስፈላጊው የፀጥታ ኃይል ወደ ቦታው እንዲልክና ለሀገር የሚጸልዩ መነኮሳትንና ደቀመዛሙርት እንዲታደግ እንጠይቃለን ሲል የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት ሚዲያ ገልጿል።

+ ተአምረ ማርያምና አንዳንድ ጉዳዮች +
(ክፍል አንድ)
ተአምረ ማርያምን በተመለከተ ሲነሡ የነበሩ ጉዳዮችን መቼም ሁሉም ሰው ያውቃቸዋል፡፡ ከመቅድሙ ጀምሮ ‘እንዴት ድንግል ማርያም ከዓለም አስቀድሞ ታስባ ትኖር ነበር ይባላል?’ ‘እንዴት ተአምርዋን የሰማ ሥጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይባላል?’ ‘ለሥዕልዋ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ የሚል እርግማን እንዴት በሐዲስ ኪዳን ይነገራል?’ ‘የድንግል ማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም እንጂ 16ቱን ትእዛዛት በመጠበቅ አይደለም እንዴት ይባላል?’ የሚሉ ጥያቄዎች ከፕሮቴስታንቶች አንዳንዶቹ ሲያነሡ አይተናል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተነሡትን አንዳንድ ጥያቄዎች እንደመግቢያ እንመልከታቸውና በጉዳዩ ላይ ያለውን ዝርዝር ጉዳይና ዘላቂ መፍትሔ ደግሞ አስከትለን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
‘‘እንዴት ድንግል ማርያም ከዓለም አስቀድሞ ታስባ ትኖር ነበር ይባላል?’’ የሚለው ጥያቄ ማንም ቢያነሣው ላያስደንቅ ይችላል፡፡ ‘ጸጋ ብቻ’ /Sola gratia/ በሚል አስተምህሮ እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰናቸው ሰዎች ብቻ እንደሚድኑ የሚያምነውን አስተምህሮ /Predestinationን/ እንደ መሠረተ እምነቱ የሚያስተምር ፕሮቴስታንቲዝምን የሚከተሉ የካልቪን ተከታይ የሆኑ ሰዎች /በእርግጥ አንዳንዶቹ አሁን አንቀበለውም እያሉ ነው/ እንዴት ቀድማ ታስባ ትኖራለች የሚል ጥያቄ ሲያነሡ መስማት ትንሽ ያስገርማል፡፡ እኛ ባናምንበትም እንዲያው ድንግል ማርያም ሌላው ቢቀር እነርሱ የሚያምኑበት ‘የPredestination አካል’ የምትሆንበትን ዕድል እንኳን ሊኖር እንደሚችል ቢያስቡ ጥሩ ነበር፡፡
ምክንያቱም የመጀመሪያዋ ክርስቲያን እንደመሆንዋ የተመረጡ /elect/ ከሚሏቸው ውስጥ በመቆጠር እድልዋ ቀዳሚ ናትና ከዓለም አስቀድማ ልትታሰብ ትችል ነበር፡፡
በመሠረቱ እንኳንስ ድንግል ማርያም ማንኛውም ፍጡር በአምላክ ሕሊና ታስቦ ይኖር ነበረ፡፡ ይህም ከፍጡሩ ማንነት አንጻር ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ሁሉን አስቀድሞ ማወቅ ጋር የተያያዘ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ እንኳን ድንግል ማርያም እኛ ለሁላችን እንኳን ‘ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን ፤ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን’’ ተብሎ ተነግሮልናል፡፡ ኤፌ. 1፡4
የድንግል ማርያም ጎልቶ የሚነገረው ስለ አንድ ምክንያት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ የሰው ልጅን መውደቅ የሚያውቅ እንደመሆኑ የሰውን ልጅም እንዴት እንደሚያድነው ያውቃል፡፡ እንዴት እንደሚያድነው ከዓለም አስቀድሞ ካወቀ ደግሞ በማዳኑ ሥራ ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆነችውን ድንግል ማርያምንም ከዓለም አስቀድሞ ያውቃታል ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ። ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ’ ብሎ ክርስቶስ በደሙ የሚያደርገው ቤዛነት ከዓለም መፈጠር በፊት እንደታወቀ ተናግሯል፡፡ 1ጴጥ. 1፡20 የክርስቶስ በከበረ ደሙ እኛን ማዳኑ ዓለም ሳይፈጠር ከታወቀ ከእርስዋ ሥጋና ደምን ነሥቶ የሚወለድባት ድንግል ማርያም በአምላክ ሕሊና የማትታሰብበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡
በጉባኤ ኒቅያ ‘ጥበብ ጌታ ፈጠረኝ እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ’ የሚለውን አርዮስ የካደበት ምሳ. 8፡23 ላይ ያለው ቃል የተብራራው ‘ፈጠረኝ የሚለው ቃል የተዋሐደውን ሥጋ የሚያጠይቅ ነው’ (ወጥበብኒ ዘትብል ፈጠረኒ እግዚእ ያኤምር በእንተ ዘፈጠረ ለርእሱ ሥጋ በከርሰ ማርያም) ተብሎ ነው፡፡ /ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ 76፡15/ ጥበብ ፈጠረኝ ማለትዋ ቅድመ ዓለም ሥጋን ስለመልበሱ የታወቀ መሆኑን የሚያስረዳ መሆኑ በኒቅያ ጉባኤ እንደ ማስረጃ ከቀረበ ድንግል ማርያም ከዓለም አስቀድሞ በአምላክ ሕሊና ታስባ ለመኖርዋም ትልቁ ማስረጃ ይኼው ጥቅስ ይሆናል፡፡ (ለዝርዝሩ ‘የብርሃን እናት’ ገጽ 324ን ይመልከቱ)
ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያሳተመው የብዙ ምሁራን የነገረ ማርያም ጥናቶች ስብስብ መጽሐፍ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይላል፡፡ ‘Mariology is a new creation or, perhaps, a new way of looking at creation. For this reason, the idea arose quite logically that Mary was chosen in eternity to be the Mother of God, and She is associated with Wisdom, who says in Proverbs 8:23 : Ages ago I was set up, at first, before the beginning of the earth’ ‘ነገረ ማርያም አዲስ ፍጥረት ወይም (ምናልባት) ሥነ ፍጥረትን በአዲስ መንገድ መመልከቻ መነጽር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ቅድመ ዓለም የተመረጠች የመሆንዋ ሃሳብ ከበቂ አመክንዮ ጋር ይነሣል፡፡ እርስዋም ‘የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ ፤ ምድርን ሳይፈጥር አስቀድሞ ከዓለም በፊት ሠራኝ’ ከምትለው ጥበብ ጋር ተያይዛ ትነሣለች’ /The Oxford Handbook of Mary, Oxford University, UK 2019 Press 2/
ሁለተኛው ጥያቄ ‘ተአምርዋን የሰማ ሥጋ ወደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል’ የሚለውን ቃል በመጥቀስ ‘እንዴት የክርስቶስ ሥጋና ደም ከተአምረ ማርያም ጋር ሊተካከል ይችላል?’ የሚል ጥያቄ ነው፡፡ ይህም ጥያቄ ከፕሮቴስታንት አቅጣጫ መነሣቱ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ እኔ መረጃ አጥሮኝ ካልሆነ በቀር ከመቼ ወዲህ ነው አንድ ፕሮቴስታንት የሥጋ ወደሙ ተቆርቋሪ የሆነው? የአስተምህሮ ለውጥ ተደርጎ እንደሆነ አላውቅም፡፡ በብዙ ለዘመናት ጸንቶ እንደተቃወመው ግን ፕሮቴስታንቲዝም በክርስቶስ ሥጋና ደም አማናዊነት ጨርሶ አያምንም፡፡ ጌታችን ‘ይህ ሥጋዬ ነው ይህ ደሜ’ ነው ብሎ የሠጠውን ምሥጢረ ቁርባንም ‘አብሮ ከሚበላ የመታሰቢያ ማዕድነት ያለፈ ፋይዳ የለውም’ በሚል አቋም የፕሮቴስታንቱ ዓለም ከካቶሊክና ኦርቶዶክሱ ዓለም ጋር ሲሟገት የአምስት መቶ ዓመት ዕድሜውን እንዳሳለፈ ሁላችን የምንስማማባቸው የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ሥጋ ወደሙ ተራ የመታሰቢያ ማዕድ ከሆነ ደግሞ እውነትም ከመብላት መስማት የተሻለ ጥቅም አለውና ይህንን ቃል ሊቃወሙ የሚችሉበት መሠረት አይኖራቸውም፡፡
የተአምረ ማርያም መቅድም ግን ጉዳዩን የሚጀምረው ተአምርዋን መስማት ምንኛ ከሥጋ ወደሙ ያነሠ መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡ ሰው ‘ሥጋውንና ደሙን ይቀበል ፤ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የሚከለክል የታወቀ ምክንያት ከገጠመው ግን ተአምርዋን ሰምቶ ይሒድ’ የሚለው ንግግር ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የማይችል ሰው ተአምርዋን መስማት እንደሚችል ያስረዳል፡፡ ተአምረ ማርያም ከሥጋ ወደሙ እኩል ቢሆን ኖሮ ሰውዬውን ሥጋ ወደሙን ከመቀበል የከለከለው ምክንያት ተአምርዋንም ከመስማት ይከለክለው ነበር፡፡ ለምሳሌ ‘በአካል መጥተህ እንድታገኘኝ ነገር ግን በአካል ለመምጣት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ባትችል ቢያንስ በስልክ ደውልልኝ ፤ ከደወልህልኝ እንደ መጣህ እቆጥረዋለሁ’ ብለህ ለወዳጅህ ነገርኸው፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር በአካል መምጣትና በስልክ መደወልን እኩል ያደርጋል ማለት አይደለም፡፡

በአጭሩ ዓረፍተ ነገሩ ሥጋ ወደሙን ዘወትር በመቀበል ሕይወት የሚኖርን ክርስቲያን የሚመለከት ቃል ነው፡፡ ይህ ክርስቲያን ፍጹም መንፈሳዊ ሕይወትን እየኖረ እንዳለ ምስክር የሚሆነው ሥጋ ወደሙን ከመቀበል የሚከለክለው ደዌ ወይም የታወቀ ምክንያት እንጂ አልቆርብም የሚል የኃጢአት ሰበብ አይደለም፡፡ እንዲህ ላለው ትጉሕ ቆራቢ ሰው ሁልጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየገሠገሠ መቁረብ ልማዱ ነውና አስቀድሶ አለመቁረብም ኀዘን ይሆንበታል፡፡ ለዚህ ሰው መቅድመ ተአምረ ማርያም ያጽናናዋል፡፡ ‘የታወቀ ምክንያት ወይም ሕመም ስለከለከለህ ባለመቁረብህ አትዘን ቢያንስ ተአምርዋን ሰምተህ ሒድ ፤ በዚያ ዕለት ልትቆርብ ተመኝተሃልና ሰምተህ በመሔድህ ያን ቀን ብትቆርብ የምታገኘውን በረከት አላስቀርብህም’ ነው፡፡ ይህ ግን ንስሓ አልገባም አልቆርብም ተአምርዋን ሰምቼ ይበቃኛል የሚል ብልጣ ብልጥ ትዕቢተኛ ሰው የሚሠራ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህንን ዓይነቱን ሰው ከመቁረብ የሚከለክለው ‘የታወቀ ምክንያት ወይም ደዌ ሳይሆን’ የኃጢአት ፍቅር ነው፡፡
ሦስተኛው ጥያቄ ‘ለሥዕልዋ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ የሚል እርግማን እንዴት በሐዲስ ኪዳን ይነገራል?’ ነው፡፡ ‘ለሥዕልዋ ስገዱ’ ማለት ለድንግል ማርያም ስገዱ ማለት ነው እንጂ እርስዋና ሥዕልዋን ነጣጥሎ ለማየት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ በእንተ ሥዕላት አምላካዊያት (On the Divine Images) ላይ ደጋግሞ እንደገለጸው በሥዕላት ፊት የሚደረግ ማንኛውም አክብሮትና ስግደት ለሥዕሉ ሳይሆን ለሥዕሉ ባለቤት ነው፡፡ ድርሳነ ሚካኤልም ‘ወሶበ ንሰግድ ቅድመ ሥዕላት አምላካዊያት አኮ ዘንሰግድ ለረቅ ወለቀለም ወለግብረ ዕድ’ ‘በእግዚአብሔር ሥዕል በተሳሉ በአምላካዊያት ሥዕላት ፊት ስንሰግድ የምንሰግደው ለወረቀቱ ለቀለሙ ወይንም ለሰው የእጅ ሥራ አይደለም’ ስግደትና ሥዕላትን በሚመለከት እነዚህን ቀደምት ጽሑፎች ይመልከቱ፡፡
‘በሐዲስ ኪዳን እንዴት እርግማን እንሰማለን’ የሚለው ተቃውሞ ‘እንዲህ የሚያደርግ መንፈስ የተወጋ ይሁን’ ‘ወግቼዋለሁ’ ሲሉ ከሚውሉ ሰዎች አቅጣጫ መነሣቱ አሁንም አስደናቂ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ጉዳዩ የሚረገመው አካልና እርግማኑ ተገቢነት ላይ እንወያይ እንጂ ሐዲስ ኪዳን ላይ ጨርሶ የግዝት ቃል ሥራ አቁሞአል ማለት አይቻልም፡፡ ጌታ በለስዋን ‘ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ ብሏታል’ /ማቴ. 21፡19/ ሐዋርያት ‘ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን’ ‘ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን’ ብለዋል፡፡ /ገላ.1፡8፣9/ እግዚአብሔር አያሰማን እንጂ በዕለተ ምጽአትም ‘እናንተ ርጉማን’ የሚለው ቃል የመጨረሻው ቃል ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ቃል ተራ እርግማን ሳይሆን በድርጊቱ የተገኙትን ከክርስትና ኅብረት የሚለይ በምድር ያሰረችው በሰማይ የታሰረ የሚሆንላት ቤተ ክርስቲያን የምትናገረው ቃለ ውግዘት (በግሪኩ Anathema) ነው፡፡ ይህም በተስፋ የምንጠብቃት መንግሥተ ሰማያት እስክትመጣና ‘ከእንግዲህ ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም፡፡ የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል ባሪያዎቹም ያመልኩታል ፊቱንም ያያሉ’ የሚለው ቃል እስከሚፈጸምልን ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ (ራእ. 22፡3)
የመጨረሻው ነጥብ ‘የድንግል ማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም እንጂ 16ቱን ትእዛዛት በመጠበቅ አይደለም እንዴት ይባላል?’ የሚለው ነው፡፡ መደጋገም ይሆንብኛል እንጂ አሁንም ጥያቄው ከእነርሱ መነሣቱ ያስደንቀኛል፡፡ ፕሮቴስታንቲዝም የትእዛዛት ተቆርቋሪ መሆን የጀመረው ከመቼ ወዲህ ነው? በማመን እንጂ ትእዛዝ በመጠበቅ አይዳንም በሚለው ትምህርት ምክንያት ስንት ውዝግብ አልተነሣም? ጳውሎስ የመገረዝን ሕግ ሥራ ለአሕዛብ ጽድቅ የግድ አስፈላጊ አይደለም ብሎ ያስተማረበትን ሮሜና ገላትያ ያለ አገባቡ በአጠቃላይ በጎ ሥራ አያፈልግም እንዳለ አድርገው በያዙት የተሳሳተ መረዳት ምክንያት በሰማይ በክብር አብረው የሚዘምሩትን ጳውሎስና ያዕቆብን ሳይጣሉ ያጣሏቸው እነርሱ አይደሉምን? አሁን ደግሞ ተአምረ ማርያምን ጎዳን ብለው እንዴት ትእዛዝ መፈጸም አያስፈልግም ትላላችሁ? ብለው ሲመጡ ማየት ምንኛ አስገራሚ ነው?
በመሠረቱ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እነሱ እንደሚሉት ሥራ ብቻውን ያጸድቃል ብላ አምና አታውቅም፡፡ ልጆችዋንም እኔ በጎ ሥራ አለኝ በእርሱ እጸድቃለሁ ብለው እንዳያስቡ ታስጠነቅቃለች፡፡ ጸሎትዋም መዝሙርዋም ‘ምግባር የለኝም’ ነው፡፡ ‘እንበለ ምግባር ተራድእኒ ፍጡነ ፤ ምግባርየሰ ኃጢአተ ኮነ’ ‘እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤ ቦኑ በከንቱ ኪዳንኪ ኮነ’ ‘በምን ምግባሬ ፊትሽን አየዋለሁ’ ‘እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኜያለሁ’ ወዘተ የሚሉት እልፍ ምስጋናዎች ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋ በምግባሬ እጸድቃለሁ ብለው ተስፋ እንዳያደርጉና በክርስቶስ በማመናቸው (በሥጋ እንደመጣና ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ማመንን ይጨምራል) እና በእግዚአብሔር ጸጋ ወይም ቸርነት እንደሚጸድቁ (እምነት + ሥራ + ጸጋ) ታስተምራለች፡፡
የድንግል ማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም መባሉ የሚያበሳጨው ካለ መጽሐፍ ቅዱስ ‘ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ’ ይላል፡፡ ገላ. 5፡13 እንኳንስ ለአምላክ እናት አጠገብህ ላለው ወንድምህም በፍቅር ባሪያ ብትሆን ትጠቀማለህ እንጂ አትጎዳም፡፡ ለድንግል ማርያም ባሪያዋና ታዛዥዋ ብትሆን ግን ብዙ ትጠቀማለህ፡፡ ክርስቲያኖች ሆይ ልንገራችሁ ሁሉን ትታችሁ ለድንግል ማርያም ብቻ ታዘዙ፡፡ የእርስዋ ትእዛዝ አንድ ነው ‘የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ’ ዮሐ. 2፡5
+ ተአምራትን እንዴት እናያቸዋለን? +
መጽሐፍ ቅዱስ ‘የሐዋርያት ሥራ’ን የመሰሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል የሠሩትን ሥራ የሚተርኩ መጻሕፍት ያለበት መጽሐፍ ነው፡፡ ‘የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው’ በማለት ሕያዋን መጽሐፍት ወይም ተንቀሳቃሽ መጽሐፍ ቅዱስ /Living bible or moving bible/ ተብለው የሚጠሩትን የቅዱሳንን ሕይወት እንድናጠና እና በኑሮአቸው እንድንመስላቸው ያሳስበናል፡፡ (ዕብ. 13፡7) ቅዱስ ጳውሎስ ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ’ ብሎ እንደነገረን ክርስቶስን ለመምሰል የጳውሎስን የሕይወት ታሪክ ማጥናት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ (1ቆሮ. 11፡1) ራሱ ጳውሎስም ከእርሱ የቀደሙ የእምነት አርበኞችን አስደናቂ ታሪክ ከዘረዘረ በኋላ ‘ሁሉን እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል’ ብሏል፡፡ (ዕብ. 11፡32) ጳውሎስ የቅዱሳኑን ታሪክ ለመተረክ ያጠረው ጊዜ እንጂ ፍቅር አልነበረም፡፡
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ አድሮ ያደረገውን መስማትም የቅዱሳን ታሪክ አካል ነው፡፡ ‘በሐዋርያት እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ’ ‘እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር’ እንደሚል እግዚአብሔር በባሪያዎቹ እጅ ታላላቅ ተአምራት ያደርጋል፡፡ (ሐዋ. 2፡42 ፣ 19፡11) የእስራኤል ንጉሥ ‘ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምር እስቲ ንገረኝ’ እያለ ግያዝን እየጠየቀ በደስታ ይሰማ እንደነበረ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያደረጉትን ተአምር መስማት ለምናምን ሰዎች እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ (2ነገሥ. 8፡4)

እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነውና እሱ ያደረገው ተአምር ምንም ቢሆን ከከሃሊነቱ አንጻር የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡ ለደካማው የሰው ልጅ ኃይል ሠጥቶ የሚሠራውን ነገር ስንሰማ ግን ኃይሉ በሰው ድካም ሲገለጥ ስናይ የበለጠ እናደንቃለን፡፡ የቅዱሳን ተአምር መቼም ቢደረግ በእግዚአብሔር እጅ የተደረገ ነው፡፡ ‘ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳችስ እንኳን ያለ እርሱ አልሆነም’ እንደሚል ድንግል ማርያም ያደረገችው ተአምር ሁሉ በእርሱ የተደረገ ነው፡፡ ተአምረ ማርያምም ራሱ ተአምረ ኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ተአምር ይሠራል ፤ ያለ ድንግል ማርያምም ተአምር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ድንግል ማርያም ግን ያለ እግዚአብሔር አንዳች ተአምር ልትሠራ አትችልም፡፡ ክርስቶስ ‘ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም’ ያለው ለዚህ ነው፡፡ (ዮሐ. 15፡5)
ኦርቶዶክሳዊያን ስለ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክዋን ፣ ዘለዓለማዊ ድንግልዋን ፣ መቼም መች መርገም ያልደረሰባት ንጽሕት መሆንዋ ፣ አማላጅነትዋን እናምናለን ፤ ከዚህ ፈቀቅ ሊያደርገን የሚሻ ቢኖርም እነዚህ የነገረ ማርያም መሠረተ እምነቶቻችን ናቸውና እስከ ሰማዕትነት ድረስ እንጸናለን፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል’ ‘የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም’ ብሎ ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. 12፡14 ፤ ማቴ. 17፡20) ስለዚህ ‘ያመነች ብፅዕት’ የተባለችው ድንግል ማርያም (ሉቃ. 1፡45) በልጅዋ አነጋገር ክርስቶስ የሚያደርገውን ተአምር ታደርጋለች ፣ ከዚያም የሚበልጥ ታደርጋለች ፣ የሚሳናትም የለም፡፡
ተአምራትን የሚያነብ ሰው በእምነት ካላነበበው ብዙ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ እውነት ለመናገር ይህ ከክህደት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊነት ደረጃችን ዝቅ በማለታችን የተነሣ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ በተአምራት መጻሕፍት ላይ ተደረጉ የሚባሉ ተአምራትን በእርግጠኝነት የሚያምን ልብ ቢኖረን ኖሮ ተአምራቱን እኛ ራሳችን ልንፈጽማቸው በቻልን ነበር፡፡ እኛ ግን እንኳንስ ተአምራቱን ልንፈጽማቸው ቀርቶ ተፈጽመዋል ብለን አምነን ለመቀበልም እንኳን ገና ነን፡፡ በዚህ የተነሣ የቅዱሳን ተአምራት ሲነበቡ ልባችን በጥርጣሬ ይናወጻል፡፡ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች ደግሞ ተአምራት ሲሰሙ ‘አቤት ተረት’ ለማለት ተነቦ እስከሚያልቅ ድረስ አይጠብቁም፡፡
በገድላትና ድርሳናት ላይ ያሉ ታሪኮችንና ተአምራትን ተረታ ተረት ናቸው ብሎ ለመደምደም ከቸኮልክ መጽሐፍ ቅዱስንም ማመንህ አስገራሚ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ? አንድ አባት ‘ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?’ ተብለው ሲጠየቁ ‘የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ’ ብለዋል፡፡ ‘አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው’ ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? ‘እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)
ወደ ተአምረ ማርያም እንመለስና ለመሆኑ ተአምረ ማርያምን ማን ጻፈው? ከየት መጣ? ተአምረ ማርያም ላይ የሚነሡ ብዙ ጥያቄዎች ሁሉም የተሳሳቱ ናቸው ሊባል ይችላል? ብፁዓን አባቶች "ተአምረ ማርያም ላይ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው" ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? በቤተ ክርስቲያንዋ በኩልስ በአዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ የሚነሡ ጉዳዮች የሉም? ሌሎች የሚያሳዩት ንቀትና ስድብ እንዳለ ሆኖ በአዋልድ በቤተ ክርስቲያንዋ እይታስ ምን እየተሠራ ነው? የዚህ ጽሑፍ ቀጣይ ክፍል ትኩረት ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት - ይቀጥላል
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 12 2015 ዓ.ም.
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

(ክፍል ሁለት)
መጋቤ ሐዲስ የኔታ እሸቱ በአንድ ወቅት ‘ልጅ አባቱን ሳይመስል ከቀረ በዲኤንኤ ይመረመራል፡፡ አዋልድ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ናቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲኤናኤ የሚገኘው አዋልድ መጻሕፍት ላይ ነው’ ብለው ነበር፡፡ ሰሞኑን በነበሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መድረኮች ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ሌሎችም አባቶች ያደረጓቸውን ንግግሮች አስተውሎ ለሰማ ሰው ሊያስተውለው የሚችለው ይህንኑ ቁም ነገር ነው፡፡
ከሰሞነኛው ውዥንብር በፊትም በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ይህንኑ ሃሳብ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ በገድላትና ድርሳናት ላይ የተደረጉ የመቀሰጥ ሥራዎች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘላቂ መፍትሔ ለመሥጠት እየተሠራች መሆኑን ያሳያል፡፡ አዋልድ መጻሕፍት አባታቸውን መጽሐፍ ቅዱስንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረተ እምነት የማይመስሉ ሆነው እንዳይገኙና ቤተ ክርስቲያን በማትቀበለው ይዘት የታተሙና የተሰራጩትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ አሠራር መፍትሔ እንደሚያገኙ አባቶች በአንድ ቃልና በአንድ ልብ ተናግረዋል፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና ከማስከበር ጋር በዘላቂነት መፍትሔ የሚሠጥ መንገድ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስም ካሉበት አስተዳደራዊ ጫናዎች ጋር እንደ መጀመሪያው የሐዋርያት ሲኖዶስ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ አይደለም’ ብሎ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጥራት ፣ ሃይማኖትን ማቅናቱ የኖረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልማድ ነው፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከቀናት በፊት እንዲህ አሉ፦
‘በገድሎቻችን ፣ በተአምረ ማርያም ፣ በተአምረ ኢየሱስ እየተሠራ ያለውን [ደባ?] በዚህ አጋጣሚ ሳንጠቁም አናልፍም፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ ብዙ ሓላፊነት አለበት፡፡ ወደፊት ሥራዬ ብሎ የሚሠራው ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ልዩ ትኩረት ሠጥቶ የሚያሠራው ይሆናል፡፡ በየመንደሩ ማተሚያ ቤቶች አሉ፡፡ በየመንደሩ ያለ ምንም ፈቃድ የጸሎት መጻሕፍት በጸሎት ስም ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷ ስማቸውን የማታውቃቸውን መጻሕፍት ሳይቀር ሲፈልጉ ግርማ ሞገስ ይሉታል ፣ ሲፈልጉ ሌላም ሌላም ይሉታል፡፡ ይሄንን ብትገዙ ይህንን ብታነቡ ፣ ይሄንን በአንገታችሁ ብታሥሩ ፣ በትራሳችሁ ብታደርጉት የሚሉ ብዙ ማደናገሪያ ፣ ማወናበጃዎች ኅትመቶችም አሉ፡፡
በገድሎቻችንም ውስጥ ደግሞ አዳዲስ ... ትናንትና በዘመናቸው የተጻፉ ገድላትን በታላላቅ ገዳማትና አድባራት ውስጥ በየሙዝየሙ በየቤተ መዘክሩ ገብተን ብናነጻጽራቸው ምንም ግንኙነት ፣ ዝምድና የሌላቸውን ደራስያን እየደረሱ ፣ ሥርዋጽ እያስገቡ ‘ይሄ ነው እንግዲህ’ ብለው ስም የሚያጠፉበትም አስቀድመው የሠሩትም ሥራ መኖሩን ሳንጠቁም አናልፍም፡፡ በተፈለገው ገድል ላይ ፣ ተአምረ ማርያም ላይ ፣ ተአምረ ኢየሱስ ላይ ብዙ የምንጠቅሰው ስላለን ነው፡፡ ምክንያቱም ተቆጣጣሪ የለም፡፡ እኛ ያለንበትንም [ሁኔታ] ‘አካሔዱን አይቶ ስንቁን ይቀሙታል’ እንደሚባለው [ነው] የእኛ አካሔድ ጊዜያዊ ነገር ላይ ተጠምደናል፡፡ ሹመት ላይ ፣ ሥልጣን ላይ ፣ ጥቅማ ጥቅም ፍለጋ ላይ ፣ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ላይ ፣ በጎጡ በጎሣው ወዘተ እንደተጠመድን ስላዩን እነርሱ ሥራቸውን እየሠሩ ፣ ከንጹሑ ስንዴ ላይ እንክርዳድ እየዘሩ እያበቀሉ ያንን ደግሞ ለደፋሮች ፣ ኀፊረ ገጽ የሌላቸው ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ማንነት ለማያውቁ በድፍረት እንዲናገሩ ጋባዦች መኖራቸውን ሳንጠቁም አናልፍም፡፡
እነዚህ ሁሉ ዓይናማ ሊቃውንት ያሏት ቤተ ክርስቲያን የትኛው ገድል ፣ የትኛው ተአምር ፣ የትኛው ድርሳን ፣ የትኛው ተአምረ ማርያም በዚህ ዘመን በየትኛው ማተሚያ ቤት ተጨመረ ፣ ተቀነሰ የሚለው ራሱን የቻለ ጥናት ይካሔድበታል’
ይህንን የብፁዓን አበው ንግግር ይዘው ላለፉት ጥቂት ዐሠርት ዓመታት ከቤተ ክርስቲያን በተቃራኒ የቆሙ አንዳንዶች ሰዎች ‘ቃላችን ተሰማ’ በሚል ስድባቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ከማሰብ የመጣ እንደነበር አድርገው ለመሣል ሲሯሯጡ ታይቶአል፡፡ ግዴለም ክሬዲቱን ይውሰዱ ፣ ሟች ሲባል ‘አቤት’ ገዳይ ሲባል ‘አቤት’ ግን መቼም የሚያስተዛዝብ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ገድላትንና ተአምራትን በተመለከተ ስለሚሠሩ የሊቃውንት ጉባኤ ሥራዎች ሲናገር ግን የሰሞኑ የመጀመሪያ አይደለም፡፡
በቤተ ክርስቲያንዋ አዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ ላይ በሊቃውንት ጉባኤ መሪነት ሥራዎች እንዲሠሩ ተደጋጋሚ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቶአል፡፡ የመጨረሻውን እንኳን ብንጠቅስ ግንቦት 2009 ዓ.ም. በተደረገው ርክበ ካህናት በተአምረ ማርያም ፣ በፍትሐ ነገሥት ፣ በስንክሳርና በራእየ ማርያም መጻሕፍት ላይ የተወያየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡-
‘‘በግል አታሚዎች እየታተሙ በሚወጡ የአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ፣ ወቅት እየጠበቁ ኾነ ተብለው በግለሰቦች ተጨምረዋል፤ የተባሉ ተኣምራትና የሕዝቦች ስያሜዎች የመሳሰሉት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን የማይወክሉና ከዕውቅናዋ ውጭ የወጡ ኅትመቶች (unauthorized versions) እንደኾኑ በምልአተ ጉባኤው ተመክሮበታል፡፡ የቀድሞዎቹን ትክክለኛ ቅጅዎች (authoritative texts) የሚያፋልስና አስተምህሮዋን የሚፃረር ይዘት በግል አታሚዎቹ ተጨማምሮባቸዋል ከተባሉት ውስጥ፥ የራእየ ማርያም እና የተኣምረ ማርያም መጻሕፍት በምሳሌነት የተጠቀሱ ሲኾን፤ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስንና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን በማካተት የታተመ ‘ተኣምረ ማርያም’ በአስረጅነት ቀርቧል፡፡
በበላይ ሕጓ እንደተደነገገው፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ከጥንት ጀምሮ በሊቃውንት ልጆችዋ አማካይነት እየጻፈች፣ እየተረጎመችና እያዘጋጀች ስትገለገልባቸው፣ ስትጠብቃቸውና ስታስተምራቸው የኖሩትን መጻሕፍት ኹሉ፣ ዛሬም በያሉበት በባለቤትነት የመጠበቅና የማስጠበቅ መብት ያላት በመኾኑ፣ በዚኽም በኩል፥ ስግብግብ አታሚዎችን በማስቆምና የትክክለኛ ቅዱሳት መጻሕፍቷን ኅትመትና ሥርጭት በመቆጣጠር አስፈላጊው ኹሉ እንዲፈጸም፣ ምልአተ ጉባኤው ትእዛዝ ሰጥቷል’’ /ሐራ ተዋሕዶ ፤ ግንቦት 5 2009 ዓ.ም./
ገድላትን ፣ ድርሳናትና ተአምራት እርማት ሊደረግባቸው ይችላል ሲባል ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትዋን /ዶግማዋን/ እየከለሰች የሚመስለው የዋህ ሰው ይኖራል፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን ካለመረዳት የሚመነጭ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ አዋልድ መጻሕፍትን ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትንም መጻሕፍት ከብዙ መጻሕፍት መካከል መርጣ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ይሁን ብላ በጉባኤ የወሰነች መሆንዋን የመጽሐፍ ቅዱስን ቀኖና ታሪክ (The History of the Canonaization of the Bible) የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ‘ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ሠጠችን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አልሠጠንም’ እንደሚባለው ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን እንኳን በዕድሜ ትቀድመዋለች፡፡ ስለዚህ እንኳንስ አዋልድ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ አራት መቶ ዓመታትን በፈጀ ማጣራትና ድካም በቀኖና ተደንግጎ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ መጽሐፍ ነው እንጂ ጥንቅቅ ብሎ ከነማውጫውና ከነኅዳግ ማስታወሻው ከሰማይ የዘነበ መጽሐፍ አይደለም፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ቀኖና እንኳን ቅዱስ አትናቴዎስ በትንሣኤ ዕለት በተነበበው አባታዊ መልእክቱ 367 ዓ.ም.

የሠጠው ዝርዝር እስካሁን ድረስ ዓለም የሚጠቀምበት የእስክንድርያ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ እንኳን አዋልድ መጻሕፍትን ቀርቶ የመጽሐፍ ቅዱስንም ቁጥር የወሰነችና ‘ይህ ይውጣ ይህ ይግባ’ የማለት ሥልጣን ያላት የእግዚአብሔር መንግሥት እንደራሴ ናት፡፡ በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስን ስታጣራ ያልተቆጣች ቤተ ክርስቲያን ገድላት ድርሳናትንና ተአምራትን ለማረም ልትቸገር አትችልም፡፡
ገድላት ድርሳናትና ተአምራትን ለማረምና ለማቅናት የምትችለው ግን ራስዋ ቤተ ክርስቲያንዋ እንጂ በጋራ በምንቀበላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ከእኛ ጋር መስማማት ባልቻሉ ሰዎች አይደለም፡፡ በልጁ መወለድ ከማይስማማ ሰው ጋር ስለ ልጁ አስተዳደግ መነጋገር እንደማይቻል በአዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት ከማያምን ሰው ጋር ስለ አዋልድ መጻሕፍት ይዘት መነጋገርም አይቻልም፡፡
ወንጌል የክርስትና ትምህርት መጽሐፍ ሲሆን ገድላት ደግሞ የወንጌሉ ሥዕላዊ መግለጫዎች /Iconography of the bible/ ተግባራዊ ክርስትና መማሪያዎች ናቸው፡፡ ገድላት ፣ ድርሳናትና ተአምራት ሲነሡ ‘ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌላ መጽሐፍ አንፈልግም’ ብለው የሚተቹ አካላት መጽሐፍ መሸጫ መደብሮቻቸው ጎራ ብትሉ ‘ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ አይሸጥም’ አይሏችሁም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩ የትርጉም መጽሐፎች ፣ ‘የሚስዮናውያን ታሪኮች’ ፣ ‘ሲኦል ደርሶ የመጣው ሰው ምስክርነት’ ፣ ‘የወንጌላዊው እገሌ የአገልግሎት ሕይወት ግለ ታሪክ’ ወዘተ የሚሉ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው? አዋልድ መጻሕፍት ማለትም ይሄ ነው፡፡ ለእነርሱ ሲሆን ተፈቅዶ ለእኛ ሲሆን ከተከለከለ double standard theory ይሆናል፡፡ እኛ ግን የምናምነውን እስካወቅን ድረስ እምነታችንን አክብረን እንከተላለን እንጂ በሌሎች ሚዛን አናስመዝንም፡፡ ገድላት ድርሳናትና ተአምራት ምንም እንከን ባይኖራቸውም እንኳን የማይቀበሏቸው ሰዎች በይዘታቸው ላይ የሚሠጡት አስተያየት ዋጋ ሊሠጠው አይገባም፡፡
በገድላት ፣ ድርሳናትና ተአምራት ላይ የሚኖሩ የታሪክ ፣ የነገረ ሃይማኖት ፣ የትርጉም ወዘተ ልዩነቶችን ለማረም ያመነ ሰው መሆን ብቻም በቂ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ሆዱ ላይ ድንገት ስለት ቢሰካበት ይሄንን ሰው ለመርዳት ማንኛውም ተራ ሰው የሚመጣለት መፍትሔ የተሰካውን ቢላ እጀታ ይዞ ስለቱን ማውጣት ነው፡፡ ይሄንን ሲያደርግ ግን የሰውዬውን ሆድ እቃ ዘርግፎ ሊገድለው ይችላል፡፡ የቀዶ ሕክምና ባለ ሙያዎች ግን በጥንቃቄ ስለቱን ከሰውዬው አካል ለይተው በማውጣት ሌላው አካል ሳይጎዳ ማዳን ይችላሉ፡፡
በአዋልድ መጻሕፍት ላይ የሚኖሩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣትም ማንኛውም አንባቢ አይችልም፡፡ ‘ተረት ነው’ ብሎ ለማጣጣል ምንም እውቀት ስለማይጠይቅ ማንም ሊሠራው ይችላል፡፡ አዋልድ መጻሕፍቱን አጥርቶ ለአገልግሎት ለማዋል ግን አገባብ የሚያውቁ የቅኔ መምህራን ፣ ጥንታዊ ድርሳናትን መመርመርና መመዘን የሚችሉ የሥነ ድርሳናት ባለሙያዎች /ፊሎሎጂስቶች/ ፣ የመጻሕፍት መምህራን ፣ አዋልድ መጻሕፍቱን ከታሪክ አንጻር መተንተን የሚችሉ የታሪክ ምሁራን ፣ ሥነ ጽሑፋዊ ዳራውን መቃኘት የሚችሉ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ወዘተ ለሺህ ዓመታት የተከማቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱ የመጻሕፍት ሀብት ማደራጀትና በጥራት ለትውልዱ በሚመጥን መንገድ የማቅረብ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ በሊቃውንት ጉባኤ እየታዩ ካሉና የብዙ ቀሳጢያን እጅ በየዘመኑ ካረፈባቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ተአምረ ማርያም ነው፡፡
ከሁሉም በፊት ተአምረ ማርያምን በተመለከተ የሚሠራውን ሥራ ታላቅነት ለመረዳት የተአምረ ማርያምን ግዝፈት በማሳየት ልጀምር፡፡
ብዙ ሰው ተአምረ ማርያም ሲባል ስለ አንድ መጽሐፍ ብቻ እየተነገረ ስለሚመስለው በተአምረ ማርያም ላይ የሚነሡ ጥያቄዎች ስለ አንድ መጽሐፍ ብቻ የሚነገሩ ሊመስለው ይችላል፡፡ እውነት ለመናገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አድባራትና ገዳማት የሚገኙ የተአምረ ማርያም የብራና ቅጂዎችና የታተሙ መጻሕፍትን አንድ ጊዜ ገልጠን በጋራ እናንብብ ቢባል ሁሉም መጻሕፍት በገፅ ብዛት ፣ በያዙት ተአምራት ቁጥር ፣ በተአምራቱ ቅደም ተከተል ፣ በተአምራቱ ውስጥ ባሉ ታሪኮች ዝርዝር ሁኔታ ብዙ ልዩነቶች አሏቸው፡፡ ስለዚህ ‘ተአምረ ማርያም ላይ እንዲህ ይላል ወይ?’ ለሚል ጥያቄ የአዋቂ ሰው መልስ የሚሆነው ‘የትኛው ቅጂ ላይ?’ የሚል ጥያቄ ነው፡፡
+ የተአምረ ማርያም የትመጣ (Origin) +
ወላዲተ አምላክን የሚመለከቱ መጻሕፍት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መነበብ የጀመሩት ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ መሆኑ የታመነ ነው፡፡ በ300 ዓ.ም. በግብፅ በዐረቢኛ ተጽፎ በ600 ዓ.ም. ወደ ግእዝ የተተረጎመው ‘መጽሐፈ ስደታ ለማርያም’ ወይንም ‘ነገረ ማርያም’ ከተአምረ ማርያም በፊት ከተተረጎሙ የነገረ ማርያም መጻሕፍት መካከል ተጠቃሹ ነው፡፡ የPEMM researcher የሆኑት መሐሪ ወርቁ በ2022 ባጠኑት ጥናት እንደገለጹት ይህ የነገረ ማርያም መጽሐፍ Early Christian Infancy Gospelን በምንጭነት የተጠቀመ ሲሆን የግእዙ ትርጉም ከዐረቢኛው ይልቅ ድንግል ማርያምን በታሪኩ ማእከልነት የሚያስቀምጥ ነው፡፡ የመጽሐፈ ስደታ ለማርያም ሁለት ቅጂዎች በBritish Library የሚገኙ ሲሆን አንደኛው ለአፄ በካፋ እናት ለማርያማዊት (1720 ዓ.ም.) የተሠጠ ሌላኛው ለአፄ ኢያሱ ካልዕ (1730 ዓ.ም.) የተጻፈ ነው፡፡
ተአምረ ማርያም ራሱን ችሎ በመጽሐፍ ደረጃ መጻፍ የጀመረው ግን ከ13ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ያጠኑ ምሁራን ይስማማሉ፡፡ ተአምረ ማርያም ከ13ኛው እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የቆየ መጽሐፍ ቢሆንም በእነዚህ ሁሉ ዘመናት ቀስ በቀስ እየጨመረ እያደገ የመጣ አንድ ትልቅ የመጽሐፍ ዋርካ እንጂ እንደ አንድ መጽሐፍ ተጽፎ ተጠናቅቆ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ዛሬ የደረሰ አይደለም፡፡ በየስፍራው ያሉት የተአምረ ማርያም ቅጂዎች ሲመሳከሩ ትንሹ 3 ተአምራትን ብቻ የያዘ ሲሆን ትልቁ እስከ 390 ተአምራትን የያዘ ነው፡፡ በአጠቃላይ በተለያዩ መጻሕፍት ተበታትነው ያሉት ደግሞ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱ ተአምራትን ይሆናሉ፡፡ Princeton Ethiopian Eritrian and Egyptian Miracles of Mary (PEMM) በ2018 ይፋ ባደረገው ጥናት በየገዳማቱ ያሉት የተአምረ ማርያም የብራና ቅጂዎችም ከ560 እስከ 643 ይደርሳሉ፡፡
በ1300 ዓ.ም. ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዐረቢኛ ወደ ግእዝ የተተረጎመው የመጀመሪያው የተአምረ ማርያም ቅጂ ስምንት ተአምራትን ብቻ የያዘ ነበር፡፡ ከዚያም በ1400 በአፄ ዳዊት ዘመን የተጻፈው የተአምረ ማርያም ቅጂ ደግሞ ከዐረቢኛ የተተረጎሙ 75 ተአምራትን የያዘ ሲሆን በወርቅ ቀለም ያጌጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ሥዕላት ያሉበትና ንጉሡም ከድንግል ማርያም እግር ሥር ሲወድቁ የተሣለበት ነበረ፡፡ (EMML 9002) [ይህ ቅጂ በግሸን ማርያም ዕቃ ቤት ይገኛል /1967 Diana Spencer] ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በኋላ በ1525 ዓ.ም. የተጻፈው ተአምረ ማርያም ደግሞ 350 ተአምራትን የያዘ ነበር፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ሌላ ቅጂ ደግሞ 33 ተአምራትን ብቻ የያዘ ሲሆን ‘አኮኑ ብእሲ’ የሚል ርእስ ያላቸው አርኬዎች የተካተቱበት ነው፡፡

ተአምረ ማርያም ከዋናነት የመጣው ከግብፅ እንደመሆኑ የተተረጎመው ከዐረቢኛ ወደ ግእዝ ነው፡፡ የዐረቢኛው ትርጉም ደግሞ ከላቲን የተተረጎሙ ተአምራትን የሚያካትት ነው፡፡ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፉት ተአምራትም ለምሳሌ የ1525 ቅጂ ላይ ብንመለከት 71 ተአምራት የተፈጸሙት በግብፅ ፣ 60ው በአውሮጳ ፣ 16ቱ በመካከለኛው ምሥራቅ ፣ 57ቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙ ናቸው፡፡ ጌታቸው ኃይሌ (ፕሮፌሰር) በ2013 ዓ.ም. በጻፉት አንድ ጥናት ላይ ደግሞ በደብረ ዘመዳ ማርያም የተገኘው በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጻፈ ብራና 55 በሀገር ውስጥ ብቻ የተፈጸሙ ተአምራትን የያዘ ነው፡፡ (EMML 6835)
ኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮጲካም የተአምረ ማርያም ተአምራትን መቼት ሲዘረዝር የሚበዙት ተአምራት የተፈጸሙት በስፔን ፣ ጣሊያን ፣ ፈረንሳይ ፣ ሶርያ ፣ ፍልስጤም ፣ ግብፅ /ቀልሞን (ፋዩም) ፣ ዳይራል አል ሙሃረቅ (ቁስቋም) አል ማግታስ (ደብረ ምጥማቅ)/ መሆኑን ይገልጻል፡፡ [Encyclopedia Ethiopica Vol. 4 789] ከዚህ በተጨማሪ ተአምረ ማርያም ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙ ተአምራትም በየጊዜው ተጨምረው ተካትተውበታል፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ተአምረ ማርያም አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ያመጣው መጽሐፍ አይደለም፡፡ በየዘመናቱ ነገሥታቱ አፄ ዳዊት ፣ አፄ በካፋ ፣ አፄ ልብነ ድንግል ፣ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፣ አፄ ቴዎድሮስ (ተአምረ ማርያም ዘቅዱስ መድኃኔ ዓለም መቅደላ ) የተአምረ ማርያምን ነባር ቅጂዎች በማስጻፍና ለትውልድ በማሻገር ፣ አዳዲስ ተአምራትን በማስጨመር ፣ ሥዕላትን በተአምራቱ ላይ በማሣል ፣ በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲኖርና እንዲነበብ በማድረግ ክፍለ ዘመናትን በተሻገረው የተአምረ ማርያም ታሪክ ላይ የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡
በተአምራቱ ላይ የሌሎች ቅዱሳን ገድላት ላይ ከድንግል ማርያም ጋር የተገናኙ ታሪኮች ፣ ከነገረ ማርያም የተውጣጡ ታሪኮች ፣ የቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ የደብረ ቁስቋም ድርሳን /Theophilus of Alexandria, Homily on mount Qusquam, Conti Rossni 1912/, ራእየ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ (መጽሐፈ ልደታ ለማርያም) ፣ የአፄ ዳዊት የስናር ዘመቻ ፣ የመጽሐፈ ሐዊ በፓትርያርክ ገብርኤል መተርጎም ፣ በቆጵሮስ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን የተደረገላቸው ተአምር ፣ በኢየሩሳሌም የትንሣኤ ቅዱስ እሳት መውረድ የተደረገለት ኢትዮጵያዊ ታሪክ በኋላ በተአምረ ማርያም የተካተቱ በሌሎች መጻሕፍት የነበሩ ታሪኮች ናቸው፡፡
ይህ ሁሉ ዝርዝር መረጃ የሚያሳየው ተአምረ ማርያም የድንግል ማርያምን ተአምራት ከመመስከር ባሻገር ምን ያህል ክፍለ ዘመናትን የተሻገረ የመንፈሳዊ ሥነ ጽሑፍ ሀብት እንደሆነና እንደዋዛ ሊታዩ የማይችሉ የኢትዮጵያና የዓለም ታሪክ መረጃዎች የተቀመጡበት እጅግ ውድ መጽሐፍ መሆኑን ነው፡፡
+ በተአምራት ላይ ምን ዓይነት ክፍተት ሊኖር ይችላል? +
ይህ እንዳለ ሆኖ የቅጂዎቹ መብዛት ፣ የተተረጎመበት ቋንቋ ሰንሰለት ርዝመት ፣ ታሪኮቹ የተፈጸሙበት ዘመን መራራቅ ፣ በእጅ ጽሑፍ እየተገለበጠ ከትውልድ ትውልድ የተሻገረ መሆኑ ፣ ሁሉም ቅጂዎች የሚይዙት ተአምራት ቁጥር ፣ ቅደም ተከተልና የታሪክ ይዘት መለያየቱ ተአምረ ማርያምን ሁሉም ወደተስማማበት አንድ ቅጂ ማምጣት ምን ያህል ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ሥራ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በዚህ መካከል ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲሸጋገር የሚፈጠር የሃሳብ መጥፋት (Loss in translation) ፣ ጸሐፊያኑ በራሳቸው የሥነ ጽሑፍ ስልት ታሪኮቹን ሲተርኩ የሚጨምሯቸው አገላለጾች ፣ በነገሥታት ቤት ያሉ ጸሐፍት ነገሥታቱን ደስ ለማሰኘት በትርጉም ሥራ ላይ የሚጨምሯቸው አንዳንድ አንቀጾች ፣ ሆን ተብሎ ቤተ ክርስቲያንን ለማዋረድና የተአምሩን ክብር ለማቃለል ለተንኮል የሚገቡ ለማጋጨት የሚገቡ ታሪኮች ፣ ከቤተ ክርስቲያንዋ መሠረተ እምነትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚላተሙ በመንደር ማተሚያ ቤት እየታተሙ የሚሰራጩ ታሪኮች በተአምረ ማርያም ላይ ለሚሠራው የሊቃውንት የአርትዖት ሥራ እጅግ ትልቁ እንቅፋት ሆኖ ቆይቶአል፡፡
በተአምራትና ገድላት ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል የታወቁትን በምሳሌነት ላንሣ፡፡ የመጀመሪያው የታሪክ ተፋልሶ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ አባት ኖረ የሚባልበት ዘመንና በታሪኩ ውስጥ የሚገኙ ክስተቶች ላይገጥሙ ይችላሉ፡፡ ወይንም አንድን አባት እገሌ ሾመው ተብሎ ይነገርና በሿሚና ተሿሚው መካከል የብዙ መቶ ዓመታት ልዩነት ሊገኝ ይችላል፡፡ ይህም ሆን ተብሎ የሚደረግ ነገር ሳይሆን መጽሐፉ በእጅ ጽሑፍ ከዘመን ዘመን ሲሸጋገር የሚፈጠር የነገረ ገድል /hagiography/ አጥኚዎች ሁሉ የሚስማሙበት የተለመደ እንከን /Common error/ ነው፡፡
ወዳጄ የዛሬ መቶና ሃምሳ ዓመታት በተፈጸሙ ታሪኮች ላይ መስማማት አቅቶን እርስ በእርስ እየተጋደልን ባለንበት ሁኔታ ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ በሆናቸው ታሪኮች ላይ ክፍተት ሲገኝ ‘ምን ሲደረግ?’ ብሎ መንገብገብ እንዴት ተገቢ ሊሆን ይችላል? በአንዳንድ ተአምራት ላይ ደግሞ ስለ አንድ አባት የልጅነት ታሪክ የሚተረከው ትርክት የሌላ አባት ሆኖ ሊገኝ ይችላል ፣ ወይንም ስለ አንድ አባት መጠሪያ ስም አሰያየም በእኛ ዘንድ ያለው ታሪክና ያ አባት በተወለደበት ሀገር የሚተረከው ታሪክ የተለያየ ገጽታ ሊኖረው ይችላል፡፡
ይህም እንደላይኛው ሆን ተብሎ የሚፈጠር ነገር አይደለም፡፡ ከሀገር ሀገር ከክፍለ ዘመን ወደ ሌላ መቶ ክፍለ ዘመን ይቅርና አሁን ባለንበት በዚህ 2015 ዓ.ም. ላይ ስላበቃው ጦርነት እንኳን በሀገራችን ከሰሜን እስከ ደቡብ የምንተርከው ትረካ /Side of the story/ ተመሳሳይ አይደለም፡፡
አባቶቻችን ትሑታን አንባቢዎች ስለነበሩ ያገኙትን መረጃ ጽፈው ለዚህ ትውልድ ሲያስተላልፉ ‘እኛ ዘንድ የደረሰው ይህ ብቻ ነው’ ከሚል ትሕትና ጋር ነው፡፡ ለምሳሌ የመጽሐፈ ቅዳሴ ትርጓሜ ስለ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ታሪክ ሲተርክ ‘ታሪኩ በእኛ ዘንድ የለም ፤ አቶ እገሌ ግን ሶርያ ወርደው ታሪኩን ይዘውልን መጥተዋል’ ብሎ እስከመጥቀስ የሚደርስ ትሕትና የሚታይበት አጻጻፍ እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ የሚገኙ የታሪክ ተፋልሶዎች ብዙ ከማንበብና ከማመሳከር የሚከሰቱ የቀለም ሠረገላ መደናቀፎች እንጂ የንዝህላልነት አይደሉም፡፡
በተአምራት ላይ ሆን ብለው የሚያፋጅ መልእክት ያለው ሃሳብ የሚጽፉ ቀሳጢዎችም አልጠፉም፡፡ በአንድ የተአምር ቅጂ ላይ ‘የተስፋይቱ ምድር አሜሪካ’ እንደሆነች ተደርጎ በቅንፍ ገብቶ ተጽፎ አንብቤ ነበር፡፡ ዓይኔን ለማመን ተቸግሬ ግእዙን ዞሬ ስመለከተው ግን ጨርሶ እንደዚያ የሚል ቃል የለበትም፡፡ ይህን የሚያደርገው ሰውዬ እንግዲህ የአሜሪካ ፍቅርና የቤተ ክርስቲያን ጥላቻ ያለበት ነው፡፡ ከዚህም የከፉ ለማንበብ የሚያስጸይፉ ጨርሶ ቤተ ክርስቲያን የማታውቃቸውና የማታምናቸው ታሪኮች በቤተ ክርስቲያኒቱ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ባልተማሩ ደፋር ጸሐፍት ተጽፈው በገድል ስም ታትመው ወጥተዋል፡፡

በራሳቸው በጀት የሚያሳፍሩ ታሪኮችን በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጠው እያተሙ እያወጡ ቤተ ክርስቲያንን ለማንጓጠጥ ያመቻቹ አጽራረ ቤተክርስቲያንም እንደነበሩና ሲነቃባቸው መጽሐፎቻቸውን መደበቃቸውም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ መቼም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ ዱላውን ያላሳረፈባት የለምና ከብዙ መቶ ክፍለ ዘመናት በፊት የተጻፉ ታሪኮችን አሁን ካለው የዘር ፖለቲካ ጋር እንዲጋጩ በሚያደርግ መንገድ እንዲቃኙና ቤተ ክርስቲያንን ለእሳት እንዲዳርጉ ሆነው የተተረጎሙ መጻሕፍትም ብዙ ናቸው፡፡ በ2009 የግንቦት ርክበ ካህናት ላይ የተነሣው ሌላ ጉዳይ ‘አራት ኪሎ ነዋሪ ስለሆኑ ሴት’ ‘ስለ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሳይቀር የሚያወሩ ፖለቲካ ቀመስተአምራት’ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅና ተጨምረው ምእመናንን ግራ ሲያጋቡ እንደነበር ተጠቅሶ ለሊቃውንት ጉባኤ መመሪያ ተሠጥቶአል፡፡
የሚደንቀው ይህ ሁሉ ሲሆን የአብዛኛዎቹን ተአምራትና ገድላት በዐረቢኛ ጽፋ ለኢትዮጵያ የሠጠችው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ስንክሳርዋን ፣ ተአምራትዋንና ገድላትዋን በታሪክና በነገረ መለኮት ሊቃውንትዋ በማስገምገምና አርሞ በማሳተም ትውልዱን ከቅዱሳን ገድላት ጋር ለማስተሳሰርና ገድላትን ወደ መንፈሳዊ ፊልም ሙሉ በሙሉ እስከመቀየርና በትውልዱ ልብ ውስጥ እስከመሳል ድረስ ስኬታማ መሆን ችላለች፡፡ ከእነርሱ ተቀብለን የተረጎምናቸው መጻሕፍትን እነርሱ ሲያርሟቸው በእኛ በኩል ግን ተመሳሳይ ሥራ አልተሠራም፡፡
ለምሳሌ በሚያዝያ 10 በሚነበበው ስንክሳር ላይ የተቀመጠው ‘“ወሰብአ ኢትዮጵያሰ ኢይሲሙ ሊቀ እማዕምራኒሆሙ’ /የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ/ የሚልን በ318ቱ ሊቃውንት የተነገረ አንቀጽ በመተላለፋቸውና በንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጵጵስናን በመጠየቃቸው ምክንያት ድርቅ መቅሠፍት ሆኖ ወረደባቸው’ የሚል የሐሰት ታሪክ አንዱ ነው፡፡ ይህንን የውሸት ታሪክ ግብፃውያኑ ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የጨመሩት አንቀጽ ቢሆንም የ318ቱ ሊቃውንትን ቃል የምታከብረዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ያለ ጥያቄ አምና ተቀብላው ኖራለች፡፡
የሚገርመው ግብፃውያኑ ይህንን የሐሰት ትርክት ሲጨምሩ ያበላሹት ሦስት መጻሕፍትን መሆኑ ነው፡፡ አንደኛው መጽሐፈ ስንክሳር ፣ ሁለተኛው ፍትሐ ነገሥት ሦስተኛው የኒቅያ ጉባኤ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህንን ሥራ በወቅቱ ከነበሩት ጳጳስ ጋር ተስማምቶ የሠራው የፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ Safey Ibn Al-Assal (13 Ad) ነበረ፡፡ ይህንን ስኅተት የግንቦት 2009 ዓ.ም. ርክበ ካህናት ላይ የብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማን ቀደምት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደማስረጃ በመጥቀስ ከስንክሳር እንዲወጣ ወስኖአል፡፡ በመጻሕፍት ላይ ‘በሊቃውንት ጉባኤ ታርሞና ተስተካክሎ የወጣ’ የሚል አንቀጽ በመጻሕፍት ላይ የምናገኘው ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ የኖረ አሠራር ስለሆነ ነው፡፡
የሚገርመው በእኛ ቤተ ክርስቲያን ይህ ውሳኔ ከመወሰኑና ከመታረሙ አስቀድሞ ግን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የፍትሐ ነገሥት አዲስ ቅጂ ላይ ‘ይህንን የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ’ የሚል አንቀጽ ስኅተት መሆኑን በመግለጽ አብራ እንደሚከተለው ከእርማት ጋር አሳትማዋለች :-
‘The Ethiopians are not to have a Patriarch from their scientists or by their own choice alone because their patriarch should be under the hand (authority) of the one on the chair of Alexandria’ [This again is wrong, because the council of Nicea did not have any knowledge of Ethiopia which did not have a bishop at the council and did not have a bishop until St. Athanasius ordained Fremenatous for them after the council of Nicea]
‘ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል በራሳቸው ምርጫ ብቻ ፓትርያርክን ሊሾሙ አይገባቸውም፡፡ ምክንያቱም ፓትርያርካቸው በእስክንድርያ መንበር ሥልጣን ሥር መሆን ይገባዋል’ [ይህም ዳግመኛ ስኅተት ነው ፤ ምክንያቱም የኒቅያ ጉባኤ በጉባኤው ወቅት ጳጳስ ስላልነበራት ኢትዮጵያ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያም ቅዱስ አትናቴዎስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ ፍሬምናጦስን እስከሾመላት ድረስ ጳጳስ አልነበራትም] (Al Magmou Al-Safawy Le Ibn Al Assal – The Collection of Church and Civil Laws, 13th Century A.D. page 6)
የግብፅ ቤተ ክርስቲያን አርአያ የምትሆነው የቀደሙ ገድሎችዋን በማረምና በማጥራት ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ አዳዲስ የቅዱሳንንና በየዘመኑ የሚሠዉ ሰማዕታትን ገድላት በመጻፍና ስንክሳር ውስጥ በማካተት ፣ አዳዲስ ተአምራትን በመመዝገብና በገለልተኛ አካል ምስክርነት በማሠጠት ፣ የሕክምና ማስረጃ ሳይቀር የተካተተበት ዘመናዊ የተአምረ ማርያም መጻሕፍት /Modern Miracles of Mary/ በማሳተም አገልግሎትዋን መቀጠልዋ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለ ጽኑዕ ሃይማኖት ፣ ባለ ብዙ ተጋድሎ ፣ ባለ ብዙ ታሪክ ብትሆንም በአስተዳደር ረገድ በሲኖዶሳዊ መንበር በሁለት እግርዋ ቆማ ራስዋን ማስተዳደር ከጀመረች ገና መቶ ዓመት እንኳን ያልሞላት በመሆንዋ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘርፍ ከሺህ ዓመታት በላይ የተላለፈ ሰንሰለት ካላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር እያነጻጸርን ልንወቅሳት አንችልም፡፡ በአዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከዛሬ በርካታ ሥራዎችን እንዳትሠራ ጋሬጣ የሆነባት የአስተዳደራዊ ቁርጠኝነት ማጣት ብቻ አልነበረም፡፡ ከአዋልድ መጻሕፍቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተጨማሪ ጨርሶ የድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነትዋንና ምልጃዋን የማያምኑ ነገር ግን ከሌሎች የተላኩ ሰዎች በተአምርዋና በገድል መጽሐፍዋ ላይ በስድብ መንፈስ በየዘመኑ እየተነሡ ብዙ ሥራ ሠርተዋል፡፡
ወደ አውሮጳ ጎራ ብለው ሲመጡ ወይንም ከሚስዮናውያን እግር ሥር ትንሽ ቁጭ ሲሉ የሀገራቸውን ነባር እውቀት የጠሉና ራሳቸውን በውጪ ሊቅ ሂሳብ የሚያዩ ፣ ዶ/ር እጓለ እንደሚሉት ያለ የእውቀት ተዋሕዶ በተአቅቦ ማድረግ የተሳናቸው ብዙዎችን አሳልፋለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን አስተምራቸው ፣ በብራናዎችዋ ተከብረው ሳለ እንደ ገለልተኛ አጥኚ እየተቹ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን ሰድቦ ለሰዳቢ የሠጡና ቆይተው የሚፈነዱ የውዝግብ ፈንጂዎችን ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ ቀብረው የሔዱ ምሁራንም ብዙ ናቸው፡፡

በቤተ ክህነት መዋቅር ውስጥ ሳይቀር ገብተው መጻሕፍቱን የበለጠ እስከመቆንጸል ድረስ ሥልጣን ይዘው የቆዩ ፣ ደመወዝ ከሌላ ቦታ የሚቀበሉ ብዙ ሐሰተኛ ወንድሞችም እንደነበሩና እስካሁንም ድረስ እንዳሉ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ የሚገኙ ክፍተቶችን ቤተ ክርስቲያንዋ ‘ሆነ ብላ (ምን እንደሚጠቅማት ባይታወቅም እነርሱ እንደሚሉት ክርስቶስን ለመሸፈን ብላ) ያደረገቻቸው ናቸው’ የሚል የሴራ ትንታኔ (conspiracy theory) እየሠጡ ራሳቸውን እውነት ቆፍሮ እንደሚያወጣ ጀግና ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ እንደ ቤተ ጣዖት እየሣሉ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የጻፏቸውና በነጻ ሳይቀር ሲያድሏቸው የኖሯቸው ንቀትን የተሞሉ መጻሕፍትና በየጓዳው አበል እየከፈሉ የሠጧቸው ሥልጠናዎች ቤተ ክርስቲያንን ቁም ስቅሏን ሲያሳያት መቆየቱ የማይዘነጋ ነው፡፡ ይህም መከረኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍትዋ ላይ በሰከነ መንገድ የአርትዖት ሥራዎችን በመሥራት ፈንታ ስሙ ማሕሌትዋ ፣ ቅዳሴዋ ፣ ንባብዋና ትርጓሜዋ ፣ ሥጋው ምግብዋና ደሙ መጠጥዋ የሆነውን ክርስቶስን ‘ጨርሶ አታውቂውም’ የሚሏትን ከሳሾችዋን በማስታገሥ ሥራላይ ተጠምዳ እንድትቆይ ግድ ሆኖባት ቆይቶአል፡፡ ‘ሰይጣን አዘገየኝ’ እንዳለ ሐዋርያው፡፡
ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሊቃውንትና በመጻሕፍት መምህራን በጥራት እየተሠሩ ያሉ የገድላትንና የድርሳናት ሥራዎች እጅግ ተስፋ ሠጪ ናቸው፡፡ ለዚህም የመጋቤ ምሥጢር ዶ/ር አባ ኅሩይ ኤርምያስን በከፍተኛ ጥራት እየተተረጎሙ ያሉ የገድላትና የድርሳናት ሥራዎችን እንደ ምሳሌ ልጠቅስ እወዳለሁ፡፡ የቅኔና የመጻሕፍት መምህር የሆኑት አባ ኅሩይ ኤርምያስ አስቀድሞ መዝገብ ታሪክ በሚል ስንክሳርን በአጭሩ የሚያስቀምጡ ተከታታይ መጻሕፍትን ያበረከቱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር ላይ ይገኛሉ፡፡
በጠቀስነው የገድላትና ተአምራት ሥራ ላይ ገድለ ታዴዎስን ፣ መጽሐፈ ምሥጢርን እጅግ በተደከመበት ጥራት ከምንጩ አመሳክረው ፣ አገባቡን አጥርተው ያሳተሙ ሲሆን ይህን ጽሑፍ በምጽፈበት ጊዜ ያየሁት ‘The Vita of St. Qawstos A Fourteenth-century Ethiopian Saint and Martyr (A New Critical Edition, Translation, and Commentary የተሰኘው በ2021 የታተመ ሥራቸው ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ የቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ የራእየ ማርያም Critical review ፣ የሙኃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የገድለ ተክለ ሃይማኖት ጥናታዊ ሥራ ወዘተ ምን ያህል ችግሮችን እንደፈቱ የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏትን የቅኔ ፣ የመጻሕፍት ፣ የሥነ ጽሑፍ ፣ የሥነ ድርሳናት ፣ የታሪክና የነገረ መለኮት ሊቃውንት አሰባስባ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ የማያዳግም በቁጥር የመወሰንና የአርትዖት ሥራ የሚሠራ አካል በሊቃውንት ጉባኤ ሥር ብታቋቁም ማንም ከፊትዋ ሊቆም የማይችል ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
እስከዚያ ድረስ በቅዱስ ጎርጎርዮስ አነጋገር ‘እንደ ዝንብ ሕር እያሉ ቁስልዋን እየፈለጉ’ የሚያደሟትና በእርስዋ ማዋረድ ለመክበርና እንጀራቸውን ለመጋገር የሚጥሩ ፣ ዘመኑን እያዩ አጋጣሚውን ለጥቃት ለመጠቀም የሚሞክሩ ፣ ከወንጌል አገልግሎትዋ ፣ ከማያቋርጥ ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ ፣ ከጾምና ጸሎትዋ የሚያናጥቧት መኖራቸው የግድ ነው፡፡ ‘ከሰደበኝ የደገመኝ’ የሚለውን ባለመረዳት ማንም ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተነሣ ባወራ ቁጥር እንዲህ ተባለ እያሉ የገዛ ልጆችዋ ማራገባቸውና ትልቅዋን ቤተ ክርስቲያን በታናናሽ ሚዛኖች ለማስመዘን መሞከራቸውም አንዱ የችግሩ ገጽታ ነው፡፡
ንጉሥ ዳዊት ሳሚ የተባለ ሰው ሲሰድበው ‘ከአብራኬ የወጣ ልጄ እየሰደበኝ እርሱ ቢሰድበኝ ምንም አይደል’ እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ካሳደገቻቸውና ከአፈር ካነሣቻቸው ሰዎችም ብዙ ስድብን ተቀብላለችና ባላሳደገቻቸው ብትሰደብ አይደንቃትም፡፡ የሌሎችን ትንኮሳ እየተከተልን የምናወራና የምንሠራ ከሆነ እንደ ቤተክርስቲያን ተቀባይ /reactors/ እንጂ አንሺዎች /actors/ መሆን አንችልም፡፡ ሆያ ሆዬ ላለ ሁሉ ሆ የምንል ከሆነ አጀንዳ ተቀባይ ሆነን የከበረች ቤተ ክርስቲያናችንን እናስንቃለን፡፡ እንደ ተቋም ሥራችንን መቀጠል ፣ እንደ ክርስቲያን የራሳችን እምነት ማጽናትና ቤተ ክርስቲያን የምትለንን ብቻ መስማት ከሁላችን ይጠበቃል፡፡
በሐዋርያቱ ቃል ልዝጋው ፦
‘ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም ፤ ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም። በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ’ ‘እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ’ 2ጴጥ. 2፡9 ፣ ይሁዳ 20-24
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 13 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

🛑ጾመ ገሀድ🛑
❇️በየኔታ ዘለዓለም ሐዲስ❇️
ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው። በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው። እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን። በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ። ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡
ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።
በሌላም በኩል ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው። ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡
ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን
ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡
ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው
በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ፡፡ በማለት ይገልጸዋል፡፡
ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን። ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ አበው ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው
በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ። ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡ ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጂ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም። ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡
በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ። እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው። ጾመ ነቢያት ስንት ነው? የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው። እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሃም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡ የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)
ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ እንዳዘጋጀው

+++የሕፃናት ጥምቀት+++
አዳምና ሔዋን ሕግ አፍርሰው ከተከለከሉት ዛፍ ፍሬ ከበሉባት ሰዓት ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔርን ተገፈው እርቃናቸውን ቀርተዋል፡፡ በወቅቱም የተሰማቸውን እንግዳ የሐፍረት ስሜት መቆጣጠር ስለተሳናቸው ዕርቃናቸውን የሚሸፍኑበትን ቅጠል በገነት ካሉት ዛፎች ቆርጠው በሰውነታቸው ላይ አገለደሙ፡፡ እግዚአብሔርም ከገነት ባስወጣቸው ጊዜ ያገለደሙት የቅጠል ስፌት የዚህን ዓለም ብርድ እንደማይቋቋምላቸው ስላወቀ ከእንስሳት ለምድ የተዘጋጀ የሚሞቅ የቁርበትን ልብስ አለበሳቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የሰው ልጅ ሁሉ ልብስ ያስፈልገው ጀመር፡፡ የዕድሜ ክልል ገደብ ሳይኖረው አረጋዊውም ፣ዛሬ የተወለደውም ሕፃን በጨርቅ የሚጠቀለል ሆነ፡፡
ማንኛውም ሕፃናት ልጆች ያሉት ጤናማ ወላጅ ልጆቹ የልብስን ጠቀሜታ ስላልተረዱ ‹አድገው እስኪረዱት ድረስ እርቃናቸውን ይቆዩ› በማለት እንደማይተዋቸው የታወቀ ነው፡፡ ምንም ክፉና ደጉን ባይለዩ፣ ራቁት የመሆን የሐፍረት ስሜት ባያሸንፋቸውም ፤ ከጤናቸው አንጻር በብርድ እንዳይታመሙበት ሲል ለልጆቹ በማሰብ ልብስ ያለብሷቸዋል፡፡
የሰው ልጅ ሥጋዊ ወይም ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ፍጥረት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለግዙፍ ሥጋው መጎናጸፊያ ልብስ እንደሚያስፈልገው ፤ ለረቂቅ ነፍሱም ልብስ ያስፈልጋታል፡፡ በልብስ ያልተሸፈነ ሰውነት ለብርድና ለተለያዩ በሽታ አምጪ ሕዋሳት እንደሚጋለጥ ፣እንዲሁ በልብስ ያልተሸፈነች ነፍስም በኃጢአት ከሚመርዟት አጋንንት ማምለጥ አትችልም፡፡ ታዲያ ይህ የነፍሳችን ልብስ ምንድር ነው? እንዴትስ ነው የምትለብሰው?
ድንኳን ሰፊ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነፍሳችን ስለምትለብሰው ረቂቅ በፍታና ስለምትለብስበትም መንገድ ምንነት ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ ‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል› ሲል ይናገራል (ገላ 3፡27)፡፡ ከዚህም የሐዋርያው ትምህርት በመነሣት የነፍስ ልብስ የተባለው ‹ክርስቶስ› ሲሆን ፤ እርሱን የምንለብስበት መንገድ ደግሞ ‹ጥምቀት› መሆኑን እንረዳለን፡፡
በዛሬ ጽሑፋችን ምሥጢራትን በመመገብ የእናትነት ድርሻዋን የምትወጣው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለምን በሕፃንነት ዕድሜያችን እንድንጠመቅ እንደምታደርገን በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ሲነሣ በተቃራኒ የትምህርት ጎራ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ከሚያቀርቧቸው የተቃውሞ አሳቦች መካከል ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ አንደኛው ‹ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ› የሚለውን የቅዱስ ጴጥሮስን የስብከት ቃል ይዘው ‹እነዚህ የምታጠምቋቸው ሕጻናት ምን ኃጢአት አለባቸው?› ሲሉ የሚጠይቁት ሲሆን ፣ሁለተኛው ደግሞ ‹ገና ሕጻናት ሲሆኑ ምን አውቀው ነው ያለ ፈቃዳቸው የምታጠምቋቸው?› የሚል ከማወቅ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ነው፡፡(ሐዋ 2፡38)
የመጀመሪያው ጥያቄ የጥምቀትን ጥቅሞች ካለመረዳት የመጣ ጥያቄ ይመስላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት ከሚፈጸምባቸው ምክንያቶች አንዱ ለኃጢአት ስርየት እንደሆነ ቢናገርም ‹ለኃጢአት ሥርየት ብቻ› ግን አይልም፡፡ ከሁሉም በላይ በጥምቀት የምናገኘው ትልቁ ጸጋ ‹ልጅነት›ን ነው፡፡ ስለዚህም ታላቅ ጸጋ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ አለቃ ለኒቆዲሞስ ‹ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ… › በማለት በጥምቀት ስለሚገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት አስተምሮታል፡፡(ዮሐ 3፡5) ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንደሚናገረው ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ኃጢአት ፣በደል አለባቸው ብላ ሳይሆን ፤ ከለጋነት ዕድሜያቸው ጀምረው ፍቅሩን እያጣጣሙ እንዲያድጉ የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ ልትሰጣቸው ነው፡፡
ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ስንመጣ በራሱ በጥያቄው መነሻ አሳብ ላይ የምንመለከተው እንደ ገደል የሰፋ ክፍተት አለ፡፡ ይህም ክፍተት ጥያቄውን የሚጠይቁ ሰዎች የተነሡበት ‹ሕፃናት አያውቁም› የሚለው ጭፍን መንደርደሪያ ነው፡፡ እነርሱ ‹ሕጻናት እንደማያውቁ በምን አወቁ? አንድ ሕፃን ስላልተናገረና አሳቡን በቃላት ስላልገለጸ ብቻ አያውቅም ሊባል ይችላል? ፡፡ እንዲህ ካሉ ደግሞ የጌታ እናት እመቤታችን ወደ እርሱ እንደቀረበች አውቆ በስግደት የደስታውን ስሜት ስለገለጸው የስድስት ወር ፅንስ ምን ይላሉ? ሳያውቅ ነው የዘለለው ሊሉን ይሆን? ቢቀበሉ ደግሞ ይህን የመሳሰሉ ድንቅ ማስረጃዎችን ከቅዱሳን አበው ገድላት እናቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እንኳን የአዋልዱን ይቅርና የአሥራው መጻሕፍቱንም ምስክር ለማመን ስለሚቸገሩ ማስረጃ አናባክንም፡፡
ታዲያ እነዚህን ጥያቄዎች ስንጠይቅ እኛ ደግሞ በተቃራኒው ሕጻናት ያውቃሉ ወደሚል ሌላ ጽንፍ እያመራን አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትን የምታጠምቀው ያውቃሉ ወይም አያውቁም ብላ አይደለም፡፡ የቤተሰቦቻቸውን እምነት ምስክር በማድረግ ነው እንጂ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልጅነታቸው ጥምቀተ ክርስትና የተፈጸመላቸው እንዳሉ የሚያሳዩ ልዩ ልዩ የንባብ ክፍሎች አሉ፡፡ ለአብነትም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በተመሳሳይ ምዕራፍ ላይ የምናገኛቸውን ሐር ሸጯ ልድያንና የወኅኒ ቤተ ጠባቂውን ማቅረብ እንችላለን፡፡ መጽሐፉ ሁለቱም ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተጠመቁ ይናገራል (ሐዋ 16፡15 ፣34)፡፡ ታዲያ ከቤተሰቦቻቸው መካከል ሕፃናት ሊኖሩ አይችሉምን?
ሌላው በበዓለ ሃምሳ ከተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ውስጥም ስለ ሕፃናት ጥምቀት የሚናገር ግልጽ ማብራሪያ እናገኛለን፡፡ ይኸውም ‹ኃጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ… የተስፋው ቃል (ተጠምቆ መንፈስ ቅዱስን መቀበል) ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ነውና› የሚለው ሲሆን በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ‹ለልጆቻችሁ› የሚለው ቃል ያለ ማብራሪያ ጥምቀት ለሕፃናት እንደሚፈጸም የሚያሳይ ነው፡፡(ሐዋ 2፡38-39) ጌታችንም በወንጌል ‹ሕፃናትን ተዉአቸው ፤ ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው› ሲል የተናገረውን ቃል እንዴት እንረዳዋለን? ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር እንዴት ይቀርባሉ? ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በምሥጢራት (Sacraments) ነው፡፡ ታዲያ ከምሥጢረ ጥምቀት የበለጠ ሕፃናት እና አምላክን በአባትና ልጅነት የሚያቀራርብ ምን አለ? ሕጻናት እንዳይጠመቁ ከመከልከል የበለጠስ እነርሱን ከፈጣሪ የማራቅ ሥራ ከየት ሊገኝ ይችላል?፡፡(ማቴ 19፡14)